click here to read in PDF
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
በጽሑፉ ክፍል አንድ ንባብ ብርሃናተ
ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ምእመናን "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት: አንዲት ጥምቀት" ሲል በጻፈላቸው መልእክት
በማንሳት አቶ ኤፍሬም ከግንዛቤ ማነስ እንዲሁም ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት እጥረት የተነሳ በደመነፍስ ያኮላሸውን የክርስትና አስተምህሮ
የዓውዱን ታሪካዊ ስዋስዋዊና ስነ ጽሑፋዊ መልኩ ጠብቆ የመልእክቱን መንፈስ መጨበጣችንና ማግኘታችን የሚታወስ ነው::
ወደ ዋና ርእሰ ጉዳዬ ከማለፌ በፊት ግን በአንዳንዶች ዘንድ የተፈጠረውን የተሳሳተ ግምት ለማጥራት
ያክል አንዳንድ ነጥቦች ለማለት እወዳለሁ። በተለይ ኤፍሬም እሸቴ "አቶ" በማለቴ ለተበሳጩ አንባቢዎቼና ለኤፍሬም
የኤፍሬምን “የድቁና/ቅስና” ማዕረገ ክህነት በተመለከተ ትንሽ ልበል:: በመሰረቱ እኔ ኤፍሬም በዲቁናም ሆነ በቅስና ማዕረግ ስትጠራ
ሰምቼ አላውቅም:: አባሪ ተደርጎ የተላከልኝና ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኘሁት "አደባባይ" የሚል ስያሜ ያለው ድረ ገጽም
"ኤፍሬም እሸቴ" እንጂ ሌላ ተጨማሪም ሆነ ተደራቢ ቀሚስ አላየሁም አላነበኩምም:: በጻፍከው ጽሑፍም የተቀመጠው
ስምህ ነው ስለዚህ "አቶ" ብዬ መጥራቴ የሀገሬን ባህልና ወግ መጠበቄ እንጂ በሌላ መልኩ መወሰድ የለበትም ስል
በትህትና እጠይቃለሁ::
ላያገለግሉበት ብቻ ሳይሆን ከየት እንዳገኙት በግልጽ የማይታወቅ የቅስናም ሆነ የድቁና ማዕረግ ይዘው
በቅስና፣ በድቁናና በሌሎች የቤ/ያን መጠሪያ ቀሚሶች ስር ተሸሽገው የሚኖሩ እንደ'ነ ስንታየሁ አባተ፣ዳንኤል ክብረት፣ ብርሃኑ ጎበና፣
ዶ/ር መስፍን ተገኝ፣ ሙሉጌታ ሃይለማርያም፣ ግርማ መታፈሪያ፣ ባያብል ሙላቱ፣ ሳምሶንና ሌሎች የማህበረ ቅዱሳን አባላት በቤ/ያን
የክህነት ማዕረግ የሚጠሩ ዕጣን ሲሸተን ያፍነናል፤ አስሜ ትነሳብኛለች፤የዕጣን አላርጅክ ነኝ፤ የአጥንት ካንሰር አለብኝ፤ በማለት
ሳይቀድሱ ሳያስቀድሱ የሚንቀሳቀሱ “ዲቁናቸውን” እና “ቅስናቸውን” በጋዜጣ ብቻ የምናነበው ግለሰቦች ግን “ማዕረጋቸው” እንደተጠበቀ
ነው::