Read in PDF: kahematocacehun
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
መግቢያ:
የተራበ እንጅ የጠገበ ሰው ባያሳዝንም የሀገሬ ሰው "ከተራበ ይልቅ የጠገበ
…" እንዲል ሰው ሲባል ሆዱ ሞልቶ/በልቶ ካደረ መጀመሪያ ጸብ የሚጀምረው ከፈጠሪው ጋር ለመሆኑ ስለሚበላና ስለሚጠጣ ጨርሶ
ሃሳብ ለሌለው/የማይገባው ሰው ነገሩን ማውሳት በራሱ ቀባሪን የማርዳት ያክል ነው የሚሆነው። አንድ ሰው ስለሚላው፣ ስለሚጠጣውና
ስለሚያርፍበት መጠሊያ ስፍራም የሚያሳስበው ነገር ከሌለ ባለቤት ከሌለው ከሜዳ አህያ የሚለየው በተፈጥሮ ብቻ ይሆናል። አንድ እውነት
አለ ይኸውም: አንድ ከድህነት ወለል በታች ይኖር የነበረ ሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀድሞ በነበረው ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ይኖር ሳለ
ያላየውን ሀብትና ንብረት ማፍራት ሲጀምር የቀድሞ ህይወቱን የዘነጋ እንደሆነ በቀላሉ የነበረውን ታላቅህን የማክበር ባህሪ፣ በሰዎች
መካከል የነበረውን ፍቅርንና ይታይበት የነበረውን ትህትና በአጠቃላይ ፈሪሐ እግዚአብሔርን አጥቶ ሣር ቅጠሉ ሁላ "ምን
አልክ አንተ? ..." እያለ ግዑዙን አካል ሳይቀር እያገላመጠ ከራሱ ጥላ እስከመጣላት ድረስ መሄዱ የማይቀር ነው።
ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ ዘንዳ በዛሬው ዕለት ላካፍላችሁ ወደ ወደድኩት ወደ ቅድመ
ፍሬ ነገሬ/መልዕክት ሳልፍ ለጽሑፌ መነሻ የሆነኝን ነጥብ እንደሚከተለው በአጭሩ ላስቀምጥ። በዕረፍት እንዲሁም በአንዳንድ ጉዳዮች
ምክንያት በአሜሪካ ጥቂት የማይባሉ ክፍለ ግዛቶች ለመዘዋወር ዕድሉ ገጥሞኝ በማደርጋቸው ጉብኝቶች ሁሉ በሄድኩበት ክፍለ ግዛት እናት
ቤተ ክርስቲያኔን ጎራ ሳልል የተመለስኩበት ዕለት የለም። በጉብኝቴ ወቅትም በርካታ መጠሪያ ያላቸው አብያተ ክርስትያናት አስተዳዳሪዎች፣
ካህናት አገልጋዮችና ደቀ መዛሙርት እንዲሁም የምእመናን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ችያለሁ። ታድያ በእነዚህ ሁሉ ቀናት ለመታዘብ እንደቻልኩ
በሀገር ቤት የምትገኘውን "ቤተ ክርስትያን" የራሱ መልክና ገጽታ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተዘፍቃ እንደምትገኝ
ሁሉ በውጭው ዓለም በተለይ በሰሜን አሜሪካ የምትገኘው "ጉባኤም" እንዲሁ ራሱ በቻለ ሌላ ገጽታ ያለው በቀላሉ የማይታለፍና
ምናልባትም አሉ በማለት ልንዘረዝራቸው የምንችላቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮች ሁሉ እንደ ምንጭ ሊወሰድ የሚችል ትርጉሙ የጠፋበት
"የቤተ ክርስቲያን" ምስረታ፣ በአገልጋዮች ካህናትና በምእመናን መካከል ያለውን መራራ ግኑኝነት፤
እንደው ካህን እንደ ምጻተኛ፣ የእድር ዕቃ ያክልም ክብር የሌለውና በአንጻሩ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ያላቸው ባለሀብቶች በገንዘባቸው
ብዛት፣ በቀድሞ መንግሥት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በቀድሞ መጠሪያቸውና ማዕረጋቸው፣ በአስኳላው ሚዛን የሚደፉ ግለሰቦችም እንዲሁ ነን/አለን በሚሉት ሁሉ ፍጥጥ ባለ መልኩ እንደፈለጉ የሚሆኑበትን አሳዛኝ
የአብያተ ክርስቲያናት ሁኔታ አንስተን በአጭሩ እንወያያለን።