(http://awdemihreet.blogspot.com/) በማኅበረ ቅዱሳን አይዞህ ባይነት
የአሜሪካውን ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት ለብጹዕ
አቡነ ፋኑኤል አላስረክብም ብለው የነበሩት አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ፡፡ ይህ በቅዱስ
ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ፊርማ የወጣው እና አድራሻውን ለአባ አብርሃም ያደረገው ደብዳቤ እንዳስታወቀው አባ አብርሃም ሀገረ ስብከቱን
በዝውውር ለቀው ከወጡ በኃላ የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት አላስረክብም ማለታቸው ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡
አባ አብርሃም ቤተክርሰቲያን አንዲት መሆንዋን መረዳት ከብዷቸው እና
እሳቸውን ለማዘዝ ሙሉ ስልጣን ያለውን ቅዱስ ሲኖዶስ ተጋፍተው ላለፉት ሁለት አመታት የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት አላስረክብም በማለት
በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሽፍታ ሠራዊት ማስፈራቸው አስገራሚ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ እኚህ ጉድ አያል ቅበት የሆኑት ጳጳስ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሳካው እሺ ብሎ በመታዘዝ
መሆኑ ከዲቁና እስከ ጵጵስና ድረስ አለመረዳታቸው በብዙዎች ዘንድ የሚያስተዛዝብ ሆኗል፡፡