REadin PDF:
በየሆቴሉ በድብቅ ይሰበሰባሉ ሲባሉ የቆዩት
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አለቆች በገሀድ በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ተሰብስበው ፓትርያርኩንና አንዳንድ የማኅበሩን ደጋፊ
ሊቃነ ጳጳሳት አስጠነቀቁ፡፡ ጥያቄዎቻችን ምላሽ የማያገኙ ከሆነ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር በጥቁር ራስ (መነኮሳት ባልሆኑ) ሰዎች
እንዲካሄድ በሕጋዊ መልኩ እንደሚጠይቁ አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ሰራተኞች ቤተክርስቲያኒቱ የአሰራር ለውጥ እንደሚያስፈልጋት
አምነው ለውጡ ሁለንተናዊና መላውን የቤተክህነቱ ክፍል ሊያቅፍ እንደሚገባ ሕጉም ከዋናው ከሕገ ቤተክርስቲያን መጀመር እንዳለበትና
በየደረጃው ደንቦችና መመሪያዎች ሊወጡ እንደሚገባው አስረድተው ይህንን የሚሰራው አካልም ከቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከሊቃውንት ጉባዔ፣ በየደረጃው
ከሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ሰራተኞች ፣ ከገለልተኛ ባለሙያዎች ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተወጣጣ ኮሚቴ መሰራት
እንደሚገባው አስምረውበታል፡፡
ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጥያቄያችሁ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ትኩረት
ይፈልጋል በማለት ኮሚቴ እንዲቋቋም ፈቅደዋል በቤተክህነቱ አዳራሽ
መሰብሰብ እንደሚችሉ አረጋግጠውላቸዋል፡፡
ስብሰባው ያበሳጫቸው አቡነ እስጢፋኖስ ግለቱ ከብዷቸው ወደ አሜሪካ እንደሚሄዱ
ተናግረዋል፡፡