Tuesday, May 15, 2012

በዛሬው ጠዋት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ይቀርባሉ የተባሉት የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ አዘጋጆች ሳይቀርቡ ቀሩ

Click here to read in PDF
  • ስብሰባው አሁንም በቅዱስነታቸው እየተመራ ይገኛል
  • አቡነ ሳሙኤልና አቡነ አብርሃም የጋዜጣው አዘጋጆች ይወገዙልን እያሉ ነው።
ሲኖዶሱ በትናንትናው ዕለት ቀኑን ሙሉ በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ በወጣው ጽሁፍ ላይ ሲወያይ የዋለ ሲሆን ወደማምሻው ላይ ፈራ ተባ እያለ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅና ምክትል ዋና አዘጋጅ እንዲጠሩ የወሰነ መሆኑ ታውቋል። ጋዜጣው ላይ ከተጻፈው ሁሉ አብዛኛዎቹን ያበሳጨው ሀብታሞች ናቸው ተብሎ የተጻፈው ሲሆን ነገ ብንለምን ማን ያምነናል በማለት ቁጣቸውን ገልጸዋል። 
ማሕበረ ቅዱሳንን ደግሞ ያቃጠለውና በአባቶች በኩል ሾልኮ ሊገባ የፈለገው በጋዜጣው መንግስት በአሸባሪነት እንደፈረጃቸው መጻፉና ዶ/ር መስፍን መወገዙ መዘገቡ ነው። የማህበሩ አመራሮች በጋዜጣው ክፉኛ የተበሳጩ ሲሆን ወዳጅ ፍለጋና ህዝብ ማሳሳቻ የጋዜጣው አዘጋጅ የማያውቁትና ከውጭ የተዘጋጀ ነው በማለት አለቃቅሰዋል። የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ግን በጻፉት ጽሁፍ እንደሚኮሩና በእውነተኛነቱም እንደማይጠራጠሩ እየገለጹ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለት በነበረው የሲኖዶስ ስብሰባም ተጠርተው ይቅረቡ የተባሉት የጋዜጣው አዘጋጆች ወደ ስብሰባው ለመግባት ደጅ እየጠኑ የነበረ ቢሆንም በትናንትናው እለት ተጠርተው ይቅረቡ ያሉት አባቶች ዛሬ ደግሞ ይግቡ አይግቡ በሚለው ስለተወዛገቡ ሳይገቡ ቀርተዋል። ዋና አዘጋጁ ንስሐ ግቡ ብለን መጠቆማችን ስህተት ከመሰላቸውማ ጉዱን ሁሉ እንዘረዝርላቸዋለን እያሉ የነበረ ቢሆንም ደፍሮ ይግቡ የሚል ጠፍቶ የጠዋቱ ስብሰባ ተብትኗል። 

በስብሰባው ዕለት አቡነ አብርሃምና አቡነ ሳሙኤል ይወገዙልን እያሉ የነበረ ቢሆንም አንዳንድ አባቶች ግን እንዴት ነው ነገሩ እኛው ከሳሽ እኛው ዳኛ ሆነን ነገሩን ማየት እንችላለን ወይ? ጹሁፉን በመጻፋቸው ብናዝንም ከሰን ፈራጅ መሆናችን ግን አያስኬድም በማለት ሀሳቡን ተቃውመዋል። ሌሎቹም አስገብተን ደግሞ ስድባችንን እንስማ እንዴ? እንዲሁ የምንለውን ብለን እንወስን እንጂ በማለት ተናግረዋል።
አቡነ ፋኑኤል እኔ ቤት ሰርቻለሁ። አለኝ። ስሞት ግን ለቤተክርስቲያን ነው የማወርሰው። ቤት ያለን አሁን ለቤተክርስቲያን እንናዘዝ እንጂ ሰዎቹን ምን ብለን ነው የምናወግዘው? ብለው መናገራቸው የተሰማ ሲሆን ይሕም ንግግር አብዛኛዎቹን ጳጳሳት ያረገበ መሆኑ ተነግሯል። ካልተወገዙ እያሉ ሲወራጩ የነበሩት አባ አብርሃምና አባ ሳሙኤል ለአቡነ ፋኑኤል ንግግር ምላሽ ያልሰጡ ሲሆን ያላቸውንን የተንጣለለ ቪላም ለቤተክርስቲያን እናወርሳለን ለማለት አልደፈሩም። ምናልባትም እንዲያወርሱት ሕግ የሚያስገድዳቸው አካል ስላላም ለቤተክርስቲያን አወርሳለሁ ለማለት እንዳልደፈሩ ታውቋል።
የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ማርቆስ ቅዳሜ ዕለት እኔ ሳላውቅ እንዴት ይጻፋል በማለት የተናደዱ ሲሆን በእሳቸው ስልጣን ደረጃ የሚጻፈውን ሁሉ አንብቦ ማጣራት እንደሚከብድ ስለተረዱ ግን በሰኞው ዕለት እና በዛሬው ስብሰባ ረገብ ብለው መዋላቸው ታውቋል። እንዲያውም ጉዳዩ መታየት የነበረበት በሲኖዶስ በኩል ሳይሆን በስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ ተልዕኮ በኩል ጉዳዩ ታይቶ ብጹዕነታቸው አቡነ ማርቆስ የፈለጉትን አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንዲወስዱ መተው ነበረበት ሲሉ ይገልጻሉ::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስነታቸው አቡነ ጳውሎስ የሲኖዶስን ስብሰባ እየመሩ የሚገኙ ሲሆን ህልሙን እያስወራ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳንም ሊፈጥረው የፈለገው ውዥንብር ስላልሰራለት ነገሬን በምን ልዋጠው እያለ በመጨነቅ ላይ መሆኑ ታውቋል። እንዲያውም አንዳንዶች ሲኖዶሱ ላይ ባለው የይወገዙልን አረ ይቅር ጭቅጭቅ ቅዱስነታቸው ያልከፈሉትን ቲያትር በነፃ እየተመለከቱ ይገኛሉ በማለት ይገልፃሉ።
በተለይም እነ አቡነ ሳሙኤል የጋዜጣው አዘጋጆቹ ይወገዙልን ማለታቸው የሚያሳፍር ሲሆን እነዚህ ጳጳሳት በየትኛው የሃይማኖት ዕውቀታቸው ጳጳሳት እንደሆኑ እያነጋገረ ነው። ምክንያቱም ውግዘት የስነ መለኮት ትምህርት ስህተት ውጤት ነው እንጂ ተዘለፍኩኝ በማለት የሚፈጸም አለመሆኑን ማወቅ እንዴት ያቅታቸዋል? አንዲህ ያለው ሀሳብ የሚመነጨው ከትምህርት ማነስ እንጂ ከሌላ ሊሆን አይችልም እያሉ ይገኛሉ። መካሪዎቻቸው ማኅበረ ቅዱሳኖች የመንፈሳዊ ዕውቀት ድሃ በመሆናቸው እንደአባቶቻቸው እነ አቡነ አብርሃምና አቡነ ሳሙኤል ባለፈው ጥቅምት ሲኖዶስ አነበቡ፣ አስነበቡ፣ ጨበጡ፣ ሀሳብ ሰጡ በማለት አገሩን ሁሉ ይወገዙልን ማለታቸው ይታወሳል።

2 comments:

  1. Keberart wulude deborah

    ReplyDelete
  2. ቅዱስ ሲኖዶስ በሃይማኖትና በቀኖና ጉዳዮች አይሳሳትም፣ በአስተዳደር ጉዳዩች ግን ስሕተቶችን ያርማል፣ መተዳደሪያዎችን ያሻሽላል፡፡

    የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ያለ አግባብ የጸደቀ አባቶች በየዋሐት በደርግ ዘመን በየዩኒቨርስቲው በፖለቲካና በጥላቻ የተወሰዱ ወጣቶችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ለማምጣት ብለው የሠሩት አስተዳደራዊ ውሳኔ ሲሆን አሁን ሊታረምና በሰንበት ትምህርት ቤቶች መተዳደሪያ ሊተካ ይገባዋል፡፡

    1. ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ቃለ ዓዋዲንና ለወጣቶች ሰንበት ትምህርት ቤትና የማኅበራት መተዳደሪያን ደንብን መስጠቱ ሊስተካከል ይገባል፡፡ ወጣቱ በማንኛው ይካተት (ከቤ/ክ ውጭ በማኅበር ወይስ ቤ/ክ ውስጥ በሰንበት ት/ቤት)ስለዚህ ሁሉም ምእመናን በቃለ ዓዋዲ የሚተዳደሩ ሲሆን ወጣቶች በሰንበት ትምህርት ቤት ብቻ ይታቀፋሉ፡፡ መተዳደሪያቸው የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት መተዳደሪያ ይሆናል፡፡
    2. የማኅበራት አደረጃጀት በኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ፈጽሞ የለም በሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ያልተለመደ ሕገ ወጥ አሠራር ነው፡፡
    3. ማቅ የራሱን አባላት ለማበራከት ከቤተ ክርስቲያን አባላት አባላትን ይመርጣል፣ ጉዳዩ ምንድን ነው ሌላ ቤተ ክርስቲያን ለመመሥረት ነው
    4. የማቅ ንብረቶች አዛዥ የላቸውም፣ ሂሳቡ ተቆጣጣሪ የለውም፣
    5. የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ሲመረቱ መሥፈርቱን ቅዱስ ሲኖዶስ አያውቀውም
    6. ቅዱስ ሲኖዶስ ደንቡን አጸደቀ እንጅ የአባልነት ፎርም አላጸደቀም
    7. አባላት በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ለስንት ጊዜ አባል እንደሚሆን ድንጋጌ የለም
    8. ማኅበረ ቅዱሳን ከሰበካ ጉባኤ፣ ከወረዳ፣ ከሀገረ ስብከት እና ከጠቅላይ ቤ/ክ በላይ ገንዘብ ይሰበስባል
    9. የማኅበረ ቅዱሳን አመራር አባላት ከሰባ በመቶ በላይ ፖለቲከኛዎች ናቸው
    10. ማኅበረ ቅዱሳን ከሙስሊም አሸባሪዎች ጋር ከፍኛ ተመሳሳይነት አለው
    11. ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክህነትና ለሊቃውንት ከፍተኛ ጥላቻ አለበት
    12. ማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ከቃለ ዐዋዲ ይበልጣል
    13. ማኅበረ ቅዱሳን ለበርካታ ሰንበት ትምህረት ወጣቶች መዳከም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው
    14. የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ከቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አደረጃጀት ጋር ከፍተኛ ተቃርኖ አለው
    15. ማኅበረ ቅዱሳን የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን እየመረጠ የራሱ አባል ያደርጋል
    16. ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ (ከያሬዳዊ መዘምራን መሪጌቶች፣ ለሰንበት ትምህርት ቤት) ለመጀመሪያ ጊዜ የመዘምራን ኳየር ያዋቀረ ሕገ ወጥ የፕሮቴስታንት ተምሳሌት
    17. ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ጸሎት ይልቅ ለራሱ የቡድን ጸሎት ቅድሚያ ይሰጣል
    18. የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሳይምሩና ሳይመረመሩ ሹመትን ይቀበላሉ
    19. ማኅበረ ቅዱሳን ሳይፈቀድለት በበጎ ፈቃድ ማገልገል ሲገባው እጅግ ከፍኛ ደመወዝ እየከፈለ ሰዎችን ያሠራል
    20. ማኅበረ ቅዱሳን ሳይፈቀድለት ከሦስተኛ ወገን ጋር ውል ይገባል በቅርቡ የዐራት ሚሊያን ብር የኮንስትራክሽን ውል ገብቷል፣ ጉዳዩን ጠቅላይ ቤጸ ክህነት አያውቀውም
    21. ማኅበረ ቅዱሳን በርካታ ትናንሽ ማኅበራትን አጥፍቷል፣ ጠቅልሏል፣ ሥራቸውን ወርሷል
    22. ማኅበረ ቅዱሳን ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውጭ በርካታ ነጋዴዎችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ አባላቱ እንዲያደርግ ማን ፈቀደለት (ዕውነተኛ ከሆነ ለምን ከማኅበር ይልቅ ለቤ/ክ አገልጋይ አያደርጋቸውም)
    23. የማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ ባለቤት ማነው
    24. ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ደረጃ የግለሰቦችን መረጃ ይሰበስባል፣ ትውልዳቸውን ያጠናል…. ለምን
    25. የማኅበረ ቅዱሳን የመረጃ መረቦች ግልጽነት የሌላቸው እና የዋናው አንጃ ውክልና ያላቸው የማኅበረ ቅዱሳን የፖለቲካና ዓለማዊ ጥላቻ ማስተላለፊያ ድረ ገጾቹ የማኅበረ ቅዱሳን ትክክለኛ መልክ ሲያሳዩ ይፋዊ ሆነው የእኔ የሚላቸው ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳንን በጭምብል ያሳያሉ
    26. ማኅበረ ቅዱሳን እጅግ ዘርፈ ብዙ በሆነና በጣም በተስፋፋ የንግድና የልመና፣ የፕሮጀክት መረብ ለምን ኖረው
    27. ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ በጀት መድቦ፣ መምህራን ቀጥሮ በሚያቋቁማቸው ገዳማትና፣ አብነት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጨማሪና መጠነኛ ድጎማ እየሰጠ መምህራኑንና ተማሪዎቹን አባላት ወይም ደጋፊ ያደርጋል፡፡ ይህም ማለት በሰው ቤት ውስጥ ለሠራተኛዎ ተጨማሪ ብር ባለ ድርብ ተልዕኮ ማድረግ ነው
    28. ማኅበረ ቅዱሳን በርካታ ማኀበራትን በአርአያው ፈጥሯል ለምሳሌ (ደጆችሽ አይዘጉ፣ የቴዎሎጅ ምሩቃን ማኅበር፣ የአቡነ ሐራ ማኅበር፣ ማኅበረ ሰላም፣ … )
    29. ማኅበረ ቅዱሳን ለብዙ አባላቱ ከፍተኛ የኑሮ ድጎማን በቤ/ክ ስም ሰጥቷ፣ መኪና ገዝተዋል፣ ቤት ሠርተዋል…
    30. ማኅበረ ቅዱሳን ሁለት የመንደር ቡድኖች አሉ የጎንደሮች ቡድን አቡነ መርቆሬዮስን ፓትርያርክ ለማድረግ የሚንቀሳቀስ፣ እና የሸዋ ቡድን የሸዋ ፓትርያርክ ለመሾም የሚንቀሳቀስ ሌላው አጫፋሪ ነው፡፡

    ተጨማሪ ሠላሣ ጉዳዩችን በቀጣይ ይጠብቁ

    ReplyDelete