Wednesday, October 31, 2012

የሲኖዶሱ የስምንተኛ ቀን ውሎ

READ PDF: sinodos 8
  • ·        ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ በቦታው ይቆያል
  • ·        አዲስ አበባ ለአቡነ ህዝቅኤል እና ለአቡነ ዳንኤል ተሰጥቷል
  • ·        የአክሱሙ ንቡረዕድ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተወስኗል

የእነ አባ መሸ በከንቱ ስብስብ የሆነው የጉድ ሙዳዮቹ ሸንጎ የሚተዳደሩበትን ሕግ እና ያላቸውን የስልጣን ደረጃ በማያውቁ እና ወይ ከእውቀት ወይ ከምግባር በሌሉበት ጨዋዎች በመወረሩ የማይመለከተውን ነገር እያየ በጊዜው ሲቀልድ ውሏል፡፡
ደንብ የማያነቡ ሕግ የማይገዛቸው ጮሆ ማውገዝ ጮሆ መወሰን እንጂ በምክንያት እና በእውነት ተገዝቶ ለመኖር በማይፈልጉ እና በማይችሉበትም ጳጳሳት ስለተሞላ የአንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምርጫ  የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስን ብቻ የሚመለከት መሆኑን እየዘነጉ ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስን ከስራ አስኪያጅነት ለማውረድ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡


ቀድሞውኑም ቢሆን ህገ ደንብ ማለት እናንተ ናችሁ ባስፈላጋችሁት ጊዜ ብቻ መጠቀም ትችላላችሁ ስለዚህ ኃይለ ጊዩርጊስን ከስልጣን አውርዱ ብላ ያዘዘቻቸውን የማቅን ፍላጉት ማስፈጸም እንጂ ለመንጋው እረኛ አድርጎ የሾማቸውን መንፈስቅዱስን መታዘዝ የማያውቁበት ጳጳሳት ሊቀ ስዩማኑን ከስልጣን ለማውረድ ቢፍጨረጨሩም አልሆነላቸውም፡፡ ስራውን በትጋት እየሰራ ያለው እና የማቅን ሰንካላ ጉዞ በተሳካ ሁኔታ እያፈረሰ ያለውን ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስን ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ማቅን በሚጠቅም መንገድ ማሳካት ሳይቻል ቀርቷል፡፡
እንደምን አደርክ ሲባሉ እንኳ መናፍቅ ማለት የሚቀናቸው አቡነ ኤልያስ ኃይለጊዮርጊስ ለምን ይነሳል? ብለው አቡነ ፋኑኤል ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ “መናፍቅ ስለሆነ ይነሳልኝ” ብለው ቢጮሁም ለመናፍቅነቱ ማስረጃ ሲጠየቁ ግን “መናፍቅ ነው መናፍቅ ነው” የሚል የድርቅና መልስ ሰጥተዋል፡፡ “እንኳን እኔ መኪናዬም ማኅበረ ቅዱሳን ነች” ሲሉ የነበሩት አቡነ አልያስ የአርባ ምንጭ ህዝብ በተነሳባቸው ጊዜ ግን መኪናቸው ከድታቸው በቀይ መስቀል መኪና ተደብቀው መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡ አቡነ ሉቃስም “ለመናፍቅነቱ እኔ ምስክር ነኝ” በማለት የተሰጣቸውን ማኅበረ ቅዱሳናዊ ግዴታ ለመወጣት ከአቡነ ኤልያስ ጎን ቆመዋል፡፡ በዚህ ጊዜ እንዲህ ያለውን የሞኝ ዘፈን መስማት የሰለቻቸው የወንጌል አርበኛው አቡነ ማርቆስ ብድግ ብለው “አልበዛም ወይ ያንንም ያንንም እየተነሳችሁ መናፍቅ ነው የምትሉት፡፡ የምንናገረውን እንወቅ እንጂ የተሰጠንን ኃላፊነት መዘንጋትም አግባብ አይደለም፡፡ ለመሆኑ አታፍሩም ወይ? አያሳፍረንም ወይ? ለኅሊናችንስ አይከብደንም ወይ? እየተነሳን በሀሰት ስም እየለጠፍን ተሀድሶ ምናምን እያልን ልጆቻችንን የምናበረው እስከ መቼ ነው? አያሳዝናችሁም ወይ እንዲህ ያለው ስራ? እንዴት ያልሆነ ነገር ይወራል፡፡ እኛ እኮ አባቶች ነን እንጂ የሰው ጩኸት አድማቂዎች አይደለንም፡፡” በማለት ጩኸት አድማቂዎቹን ጳጳሳት ተችተዋል፡፡
በሲኖዱሱ ስብሰባ ወቅት ድምጻቸው ፈጽሞ ያልተሰማው አቡነ ገሪማ ይናገሩ እንጂ ለምን ዝም ይላሉ? ተብለው ተጠይቀው በሰጡት መልስ “እኔ እንኳ ልናገር አልፈልግም ተናገር ካላችሁኝ እናገራለሁ፡፡ በጣም የምታሳዝኑ ጉዶች ናችሁ፡፡ እየተቀባበላችሁ እገሌ መናፍቅ ነው እገሌ እንደዚህ ነው ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ኃይለ ጊዮርጊስ ልጃችን ነው፡፡ አረ ለመሆኑ ከመቼ ወዲህ ነው ሥራ አስኪያጅን እናንተ የምታነሱት እና የምታስቀምጡት? ስራ አስኪያጅ መሾምም ሆነ መሻር የሊቀ ጳጳሱ መብት ነው፡፡ ስራ አስኪያጅን ለመሾም ሊቀ ጳጳሱ እና ፓትርያርኩ እየተማከሩ የሚያደርጉት እንጂ ከመቼ ወዲህ ነው በሲኖዶስ የሚታየው? ይህ አካሄድ ትክክልም ተገቢም ያልሆነ አካሄድ ነው፡፡ ይሄ የሊቀ ጳጳሱ ጉዳይ ነው እኛን አይመለከተንም፡፡ አይነሳም የሚነሳበትም ምክንያትም የለም፡፡ በቀደም ዝም ብዬ አይቻችኋለሁ የኔን ስራ አስኪያጅ ተሀድሶ ነው መናፍቅ ነው አላችሁ፡፡ እየተነሳችሁ ተኃድሶ እየተነሳችሁ መናፍቅ ለመሆኑ የምትሰሩትን ስራ ታውቁታላችሁ ወይ? የምትሰሩት ስራ ሁሉ የቡድን ስራ ነው? አንድ የሁሉ አባት ሊሆን የተቀባ ጳጳስ ይህን ማድረግ አለበት ወይ? እንዲህ ያለው ቡድንተኝነት በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ መስተካከሉ ይበጃል፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡ የአቡነ ገሪማ ንግግር ሁሉንም ያስደነገጠ ሲሆን እሳቸውን ለመቃወም የደፈረ ማንም አልነበረም፡፡ ከዛ በኃላም እንደ ህገ ደንቡ ስራ አስኪያጅን መሾም እና መሻር የሊቀ ጳጳሱ መብት ነው በሚል ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ እንዳይነሳ ተወስኗል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ የታየው በመጠንዋ ከሁሉ ሀገረ ስብከቶች ትንሽ የሆነችው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንደ ገና እንደ ግምባር ስጋ ለአራት እንድትከፋፈል በመወሰኑ በአራቱ ኩርማን ሀገረ ስብከቶች ማን ይሾም? የሚለው ጉዳይ ነበር፡፡ ወትሮውንም አዲስ አበባ ለአራት እንድትከፈል የፈለጉት ጳጳሳት ከምቾቱ እና ከሌላ ሌላ ነገርዋ ጋር አዲስ አበባ ለኔ ትሁን በሚል ስሜት ቢቁለጨለጩም እጣ እንዲጣል ተወስኖ እስከ ግንቦት ድረስ አቡነ ህዝቅኤል እና አቡነ ዳንኤል ሁለት ሁለት ሀገረ ስብከት ተከፋፍለው እንዲመርዋት ተወስኗል፡፡ አቡነ ህዝቅኤል እዚህ አዲስ አበባ ሁለት ሀገረ ስብከት ከያዙ የቦንጋውን ይልቀቁ ቢባሉም ሁሉንም እይዛለሁ እንጂ አልለቅም ብለዋል፡፡
የአክሱም ጉዳይ በተመለከተ ሲኖዶሱ የአክሱሙን ንቡረዕዱ ይነሱ ብሎ ወስኗል፡፡ ይህ ውሳኔ ችግሩን እያባባሰው እንዳይሄድ ያሰጋል፡፡
ሲኖዱሱ በነገው ዕለት ስብሰባውን ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

3 comments:

  1. እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ባይጠብቅ ኖሮ ምንኛ በተኩራራችሁ ነበር፡፡ ለአውሬው የስድብ መንፈስ ተሰጥቶታልና ተሳደቡ፡፡ ከልባችሁ የተረፈው ክፉ ቃል በአንደበታችሁ ይወጣል፡፡ ወሬ ንፋስ ነው፤ቤተክርስቲያን እናንተን በገንዘብ አስታጥቀው እንደላኩ የመናፍቃን ድርጅቶች በአሸዋ ላይ አልተመሰረተችምና በእናንተ ክፉ ስራ ፈፅሞ አትጎዳም፡፡
    አባቶችን ለምን እንደምትሳደቡ እናውቃለን፤ትውልዱ አባቶቹን መናቅ እና መሳደብ ከጀመረ ቤተክርስቲያንን፣ ቅዱሳንን፣ ብሎም እመቤታችንን መስደብ ይጀምራል ብላችሁ ነው፡፡ በግ የአባቱን ድምፅ ያውቃል፤ ይሰማልም፡፡ የእናንተን የተኩላዎቹን ድምፅም ያውቃል፤ይሸሻልም፡፡ ግን ምናል እዛው ሄዳችሁ ብትቀሩ፤ ምናል ባትበጠብጡን፡፡ የመውጊያውን ብረት መቃወም አይጠቅምም፤ ይጎዳል አንጂ፡፡

    ReplyDelete
  2. ግሩም ነው ይበል ብጹዕ አቡነ ገሪማ!መንፈሳዊ መሰል የተንኰል ማዕበል ለሆነው
    ቡድን ቃል አቀባይ ሆነው የተነሳሱ ያርጋጅ አናጓጅ አንድ �5 አናጓጅ አንድ ሁለት ጳጳሳትን በይፋ መገሠጽዎ መንፈስ ቅዱስ ነው ያነሳሳዎ ምክንያቱም(ገሥጾሙ በቅድመ ኵሉ)ጋጠ ወጦችን
    ጋጠ ወጥነታቸውን በሁሉ ፊት አስታውቅባቸው ይላልና ነው።

    ReplyDelete
  3. ግሩም ነው ይበል ብጹዕ አቡነ ገሪማ!መንፈሳዊ መሰል የተንኰል ማዕበል ለሆነው
    ቡድን ቃል አቀባይ ሆነው የተነሳሱ ያርጋጅ አናጓጅ አንድ ሁለት ጳጳሳትን በይፋ መገሠጽዎ መንፈስ ቅዱስ ነው ያነሳሳዎ ምክንያቱም(ገሥጾሙ በቅድመ ኵሉ)ጋጠ ወጦችን
    ጋጠ ወጥነታቸውን በሁሉ ፊት አስታውቅባቸው ይላልና ነው።

    ReplyDelete