Tuesday, October 9, 2012

የአቡነ ገብርኤል ማካሮፍ ሽጉጥ ጠፋ


  • ሰርቀሀል ተብሎ የተጠረጠረው ዲ/ን ፍጹም እንዳለ የተባለ አገልጋያቸው እንዲባረር ተደርጓል፡፡

በአቋማቸው ወላዋይነት እና ጠንካራ ነው ብሎ ያመኑበትን ክፍል በመጠጋት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚታወቁት አቡነ ገብርኤል በቤታቸው ደብቀውት የነበረው ማካሮፍ ሽጉጥ ጠፋ፡፡ አጣሪ ኮሚቴ አቋቁመው ነገሩን እንዲጣራ እያደረጉ ነው፡፡ የአጣሪ ኮሚቴው ሊቀመንበር ከሀገረ ስብከተ ስራ አስኪያጅነት ከተባረረ በኃላ አሁን አቡነ ጳውሎስ ካረፉ በኃላ በአባ ገብርኤል ወደ ቦታው የተመለሰው አለም እሸት ነው፡፡ አለም እሸት ከስልጣኑ የተነሳው ከ12 መኪና በላይ የሚሆን ህዝብ ከአዋሳ መጥቶ አቤቱታ ስላቀረበበት እንደሆነ አይዘነጋም፡፡ ከቅዱስነታቸው ዕረፍት በኃላ ግን አለምእሸትን አባ ገብርኤል በማን አለብኝነት መልሰውታል፡፡ 

የሽጉጡን መጥፋት በተመለከተም ምንም እንኳ አለም እሸት ማኅበረ ቅዱሳናዊ የምርመራ ዘዴውን ተጠቅሞ ለማውጣጣት ቢሞክርም ልጁ ግን ባልወሰደድኩት ንብረት እንዴት እጠየቃለሁ በማለቱ አባረውታል፡፡ እውነተኛውን ሌባ ፈልጎ አንደማውጣት ድሀን በመግፋት መፍትሔ ሰጠን የሚል አሰራር የእነ አባ ገብርኤልን እና አለምሸትን አምባገነንነት ያሳያል፡፡

ሽጉጥ በጓዳ አስቀምጠው የሀይማኖት አባት ነኝ ለማለት መሞከር በእጅግ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ ነገሩ አሳፋሪ ስለሆነም ለፖሊስ ለማመልከት አልደፈሩም፡፡ እስራኤልን የሚጠብቅ አያንቀላፋም የሚለውን ቃል ያላነበበቡት አባቶቻችን ራሳቸውን ለመጠበቅ የማያንቀላፋውን ጌታ ትተው ሽጉጥን ተስፋ ማድረጋቸው ይገርማል፡፡ እውነትን ጽድቅን እየሰሩ እግዚአብሔርን ተስፋ ከማድረግ ይልቅ ሁሉን እያደፈረሱ በሽጉጥ መታመን የማይጠቅም ነገር መሆኑን መዘንጋታቸው ገርሞናል፡፡

ብጹዕነታቸው በደርግ ጊዜ አድርገውት በነበረው ንግግር “ሰው ራሱን በሚያስፈልጉ ነገሮች መጠበቅ አለበት፡፡ እግዚአብሔርም እኮ የሚጠብቁት ጠባቂ መላዕክት አሉት” በማለት እግዚአብሔርን በማያውቅ ባህሪያቸው ስለ እግዚአብሔር የስህተት ትምህርትን አስተምረው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ በቅዳሴያችን “መላዕክትን የምትጠብቃቸው አንተ ነህ” የተባለውን ጌታ፤ አቡነ ገብርኤል ግን ብቻውን ምንም እንደማያደርግ አስበው መላዕክቱ ይጠብቁት ነበር ማለታቸው በወቅቱ ትዝብት ላይ ጥሎዋቸው እንደ ነበረ ይታወሳል፡፡ እኚሁ ጳጳስ ታድያ እግዚአብሔርም ይጠበቃል ብለው የሚያምኑ በመሆናቸው ለራሳቸው መጠበቂያ ሽጉጥ ቢይዙ የሚደንቅ አይሆንም፡፡ ብቻውን ሀያል እና አሸናፊ የሆነውን ጌታ በማንነቱ አለማወቅ እና ልጆቹን አክብሮ እንደሚዝ እና አንደሚጠብቅም አለማወቅ ከማካሮፍ ሽጉጥ ጋር ተቃቅፎ ለመተኛት እንደሚዳርግ እሙን ነው፡፡ የሀይማኖት አባቶች የሚጠበቁት በመንፈስ ቅዱሰ እንጂ በሽጉጥ አለመሆኑን ለአባቶቻችን እግረ መንገዳችንን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡

10 comments:

  1. gedel gibu, yesetan lijoch. Awiritachu motachuhal... Enante eyawerachu lelaw eyesera betam tilewachu hedewal. Weregna erkus pente

    ReplyDelete
    Replies
    1. anetew keabune geberail gare betegeba ayechalm? tawkachewaleh? engedaw kenemekebut yetsegur kelm ena nufakayachew ezerezerlehalew'

      Delete
  2. abune gabriel mis the only bishop has no aim

    ReplyDelete
  3. i hope it is nothing more than praivate matter.

    ReplyDelete
  4. i hope it is nothing more than praivate matter.

    ReplyDelete
  5. ma negerachehu,papapapa tegeremalachuhe kebade eko nachehu????

    ReplyDelete
  6. ሰላም አወደ ምህረት እስከ አሁን ካነበብኩትከብዙ በጥቂቱ ስለ ድሮው አባ ቃለ ጽድቅ(ቃለ ሃጥዕ)በአሁን ሰአት ያለ አቅማቸው አባ አብረሃም ስለተባሉት የጻፋችሁትን አንብቤላችኋለው እውነት ነው። የኔን ያህል ግን ማንም አያውቃችውም እኔ የማውቃችው አሰብ ካምፕ ጠባቂ ከነበሩበት ጀምሮ እና በአሁን ሰዓት ፓትርያክ ለመሆን ላይ ታች እስከሚሉበት ድረስ መናገር እችላለሁ ፤አቡነ አብርሃም አ/አ አውራጃ ምን ወንጀል ሲሰሩ ነበር ? መርካቶ ደ/ኅ/ቅ/ራጉኤል ቤ/ንስ ለአመታት እንዴት ሲመዘብሩ ቆዩ? ከወ/ት ሰብለ ወንጌል ጋርስ በምን ተጣሉ ምስጢሩስ ምንድ ነው? ሲ ኤም ሲ የተገነባው ባለ ሁለት ፎቅ መኖሪያ ቤታቸው በማን ገንዘብ ተሰራ?መሃንዲሱስ ማን ነበር ? በአንድ ወቅት እንደለመዱት ስር ለመበጠስ ደ/ማርቆስ ሲጓዙ ከባድ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ነበር ለምን የሆን ?ለማንወም የዚህን አውሬ ሰው ማንነት ለማወቅ ከፈለጋችሁ ይህ ጽሁፍ እንደደረሳችሁ ማወቅ እፈልጋለው P0ST ሆኖ ካየሁት እኩይ ተገባሩን ለመዘርዘር ዝግጁ ነኝ።

    ReplyDelete
  7. ወይ መሰግሉ አባ አብርሃም አሜሪካ ሀገር ልሂድ ብለው እንደለመዱት በየጳጳሳት ቤት የዘረፉትን ገንዘብ እየረጩ ነው አሉ እወነት የእግዚአብሄርን መሃሪነት በእርሶ አየሁ

    ReplyDelete
  8. ወይ መሰግሉ አቡነ አብርሃም(THE SEBLE WENGAL)ጵጵስና ይመረጡ ሲባል የለም እንዳራቸው እንዳልተባለ ዛሬ አሜሪካ ካልሄድኩ ብሎ ልመና ይባሱኑ ፓትርያርክ ለመሆን ገንዘብ መርጨት ማሳደም አቤት የእግዚአብሄር ምህረት በእርሶ አየሁት ይቀጥላል

    ReplyDelete
  9. ሰላም አ/ት ጥሩ ነው ለመሆኑ በታቦት ገንዘብ ጵጵስና የተሾመው አቡነ አብርሃም ተብዬው መሾሙ ሲገርም የህይወት ታሪካቸውን በጋዜጣ ሲያጽፉ ከአባታቸው ከደጓ መምህሩ መምህር እውነቴ ያስባሉት ሲያስቀኝ ይኖራል ይባስ አባ ተከስተ(አቡነ ሳሙኤል)ተካ አሉና አትላንታ የፓርኪንግ ገንዘብ ዝርፊያቸውን ረስተውት በአሜሪካ ሃገር ከትምህርት ቆይታቸው _____ተብሎ የተደሰኮረው ጉድ ይብሳል ታየ እኮ ትምህርታቸው ፓትርያርኩ የጥምቀት በአል ለማክበር ጎንደር በሄዱበት ጊዜ ደፋሩ ሳሙዔል በጃን ሜዳ ፓትርያርኩን ወክሎ ሄዶ ያ ሁሉ የቅዱስነታቸውን አንደበት ሲሰማ የኖረውን ጆሮአቸውን በማሸማቀቅ ምሁርንታቸውን ይፋ አድርገውታል ለመሆኑ ሰዶማዊነታቸውን ለመቨፈን ያወጡት መጻፍ ምን ላይ ደረሰ____? ይቆየን==================ጥያቄ አለን የጉድ ሙዳይ ወጣ ወይስ በገንዘባቸው አሳፈኑት _?በሚቀጥለው አስመሳዩ አቡነ አብረሃም በቅዱስነታቸው ሞት ምን ተሰማው;ደስታ ወይስ ሃዘን? ይደርልን____

    ReplyDelete