Monday, August 5, 2013

በእጅ አዙር የቤተክርስቲያኒቱን መዋቅር መቆጣጠር የሚፈልገዉ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ጥርቅሙ ማህበረ ቅዱሳን በአሰበ ተፈሪ ድብቅ ሴራዉ ተጋለጠ

Read In PDF: Asebeteferi
 ከመሪጌታ የሻውወርቅ
ሐራ ዘተዋህዶ በተባለዉ የማህበረ ቅዱሳን መርዝ መርጫ ድረ ገጽ ላይ በምእራብ ሐረርጌ በአሰበ ተፈሪ ቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ዉስጥ ከእሁድ ሰንበት ቅዳሴ በኋላ ምእመኑና ማህበረ ካህናቱ የሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫን ለማከናወን በሐገረ ስብከቱ ተይዞ የነበረዉን ፕሮግራም ሰንበት ት/ቤት አባላት ነን ከሚሉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የማህበረ ቅዱሳን አመራሮችና በጣት በሚቆጠሩ ግለሰቦች የተፈጠረዉን ከኦርቶዶክሳዊ አማኝ ስነምግባር ዉጪ የሆነዉን ሁከት እንደለመደዉ ማህበሩ በአንድ የማህበረ ናታኒም የተሰራ ተንኮል እንደሆነና ከዚሁም ጋር የሐገረ ስብከቱን ስራ አስኪያጅና ጸሀፊ ለመወንጀል የታሰበበት ጽሁፍ አስነበበን፡፡

ያሳዝናል እድሜ ልኩን እንደ ግብር አባቶቹ ጸሐፍት ፈሪሳዊያን/ቤተ አይሁድ/ ለጥፋት የተቋቋመ ማህበር፡፡ መቼ ይሁን እዉነቱን እዉነት ሐሰቱን ሐሰት የሚለዉ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሐፍት ፈሪሳዊያን ተይዞ ሊቀ ካህን ሐና ጋር በቀረበበት ግዜ አንድ ክስተት ተከሰተ ይሄዉም ሊቀ ካህኑ ሐና ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀዉ፡፡ አምላካዊ መልሱ በግልጥ ለአለም ተናገርኩ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት  በቤተ መቅደስና በምኩራቦች በግልጽ አስተማርኩኝ በስዉርም ምንም አልተናገርኩም፡፡ ስለምን ትጠይቀኛለህ; የሰሙትን ጠይቅ እነርሱ እኔ የተናገርኩትን ያዉቃሉ አለዉ፡፡ በዚህ ግዜ ግን አንድ አሳዛኝ ክስተት ተከሰተ የሊቀ ካህኑ ሎሌ የነበረ አገልጋይ ኢየሱስ ክርስቶስን ለምን እንዲህ አይነቱን መልስ ለሊቀ ካህኑ ትመልሳለህ ብሎ ጌታን በጥፊ መታዉ፡፡ እጅግ የሚገርመዉ አምላካዊ መልሱ ነዉ፡፡ ኢየሱስም መልሶ #ክፉ ተናግሬ እንደሆንሁ ስለ ክፉ መስክር መልካም ተናግሬ ከሆነ ግን ስለምን ትመታኛለህ አለዉ፡፡$ የዮሀንስ መንጌል ምእራፍ 18፤19-23  ይህንን ጥቅስ የወሰድኩበት አንድ ምክንያት አለኝ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን እንደ ምሰሶ ደግፎ ይዞ እንደቆመ ራሱን ይቆጥራል' እርሱ እንጂ ሌላ መንፈሳዊ ማህበር ለቤተክርስቲያኒቱ እንደማያስፈልግ ያዉጃል፡፡