Saturday, May 10, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን የማተራመስ ሥራውን በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረስብከትም ቀጥሏል።

ላለፉት 20 ዓመታት ቤተክርሰቲያንን እያተራመሰ እያመሰ እየበጠበጠ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ለማኅበሩ የማያሸረግዱ ብጹአን አባቶችን መቃወሙን እና ወጣቶችን ደግሞ ማሳደዱን አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። በተለይም በሄዱበት ሀገረ ስብከት ሁሉ ለማኅበረ ቅዱሳን ባለማንበርከክና ቤተክርስቲያንን በዱርዬ መንጋ እንዳትወረር ነቅተው በመጠበቅ የሚታወቁትን ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስንም አላማቸው ገንዘብ በሆኑ አባላቱና ደጋፊዎቹ አማካኝነት መቃወሙን ቀጥሏል። ከአባላቱ መካከልም በተለይም  ሳሙኤል ደሪባ እና ጌታሁን አማረ የተባሉና ገንዘብ በማጭበርበርና ሙዳይ ምጽዋት በመገልበጥ የታወቁ ሁለት ግለሰቦች የሚያደርጉት የማበጣበጥ ሥራ ብዙ ቢሆንም የተፈለገውን ውጤት ግን ላስገኝላቸው አልቻለም።
ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ ከቅዱስ ፓትራርኩ ጋር
 ሳሙኤል ድሪባ ባካ ቅድስት ማርያም በምትባለው እና በወሊሶ ወረዳ ከምትገኘው ቤተክርስቲያን በሀገረ ስብከትም ሆነ በወረዳው ቤተክህነት ሳይታዘዝ ራሱ ሂሳብ ሹም መርጦ ገንዘብ ያዥ አስቀምጦ እና ቁጥጥር አድርጎ በሊቀ ጳጳሱ ከተፈቀደላቸው ኮሚቴዎች ውጭ በራሱ የሚታዘዝ ኮሚቴ በማን አለበኝነት በመፍጠር ከዘጠና ስምንት ሺህ ብር በላይ አጉድሏል። ይህም በኦዲተር ማስረጃ የተረጋገጠ ነው።