Monday, August 5, 2013

በእጅ አዙር የቤተክርስቲያኒቱን መዋቅር መቆጣጠር የሚፈልገዉ የጸሐፍት ፈሪሳዊያን ጥርቅሙ ማህበረ ቅዱሳን በአሰበ ተፈሪ ድብቅ ሴራዉ ተጋለጠ

Read In PDF: Asebeteferi
 ከመሪጌታ የሻውወርቅ
ሐራ ዘተዋህዶ በተባለዉ የማህበረ ቅዱሳን መርዝ መርጫ ድረ ገጽ ላይ በምእራብ ሐረርጌ በአሰበ ተፈሪ ቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ዉስጥ ከእሁድ ሰንበት ቅዳሴ በኋላ ምእመኑና ማህበረ ካህናቱ የሰበካ ጉባኤ አባላት ምርጫን ለማከናወን በሐገረ ስብከቱ ተይዞ የነበረዉን ፕሮግራም ሰንበት ት/ቤት አባላት ነን ከሚሉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የማህበረ ቅዱሳን አመራሮችና በጣት በሚቆጠሩ ግለሰቦች የተፈጠረዉን ከኦርቶዶክሳዊ አማኝ ስነምግባር ዉጪ የሆነዉን ሁከት እንደለመደዉ ማህበሩ በአንድ የማህበረ ናታኒም የተሰራ ተንኮል እንደሆነና ከዚሁም ጋር የሐገረ ስብከቱን ስራ አስኪያጅና ጸሀፊ ለመወንጀል የታሰበበት ጽሁፍ አስነበበን፡፡

ያሳዝናል እድሜ ልኩን እንደ ግብር አባቶቹ ጸሐፍት ፈሪሳዊያን/ቤተ አይሁድ/ ለጥፋት የተቋቋመ ማህበር፡፡ መቼ ይሁን እዉነቱን እዉነት ሐሰቱን ሐሰት የሚለዉ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሐፍት ፈሪሳዊያን ተይዞ ሊቀ ካህን ሐና ጋር በቀረበበት ግዜ አንድ ክስተት ተከሰተ ይሄዉም ሊቀ ካህኑ ሐና ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀዉ፡፡ አምላካዊ መልሱ በግልጥ ለአለም ተናገርኩ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት  በቤተ መቅደስና በምኩራቦች በግልጽ አስተማርኩኝ በስዉርም ምንም አልተናገርኩም፡፡ ስለምን ትጠይቀኛለህ; የሰሙትን ጠይቅ እነርሱ እኔ የተናገርኩትን ያዉቃሉ አለዉ፡፡ በዚህ ግዜ ግን አንድ አሳዛኝ ክስተት ተከሰተ የሊቀ ካህኑ ሎሌ የነበረ አገልጋይ ኢየሱስ ክርስቶስን ለምን እንዲህ አይነቱን መልስ ለሊቀ ካህኑ ትመልሳለህ ብሎ ጌታን በጥፊ መታዉ፡፡ እጅግ የሚገርመዉ አምላካዊ መልሱ ነዉ፡፡ ኢየሱስም መልሶ #ክፉ ተናግሬ እንደሆንሁ ስለ ክፉ መስክር መልካም ተናግሬ ከሆነ ግን ስለምን ትመታኛለህ አለዉ፡፡$ የዮሀንስ መንጌል ምእራፍ 18፤19-23  ይህንን ጥቅስ የወሰድኩበት አንድ ምክንያት አለኝ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን እንደ ምሰሶ ደግፎ ይዞ እንደቆመ ራሱን ይቆጥራል' እርሱ እንጂ ሌላ መንፈሳዊ ማህበር ለቤተክርስቲያኒቱ እንደማያስፈልግ ያዉጃል፡፡ 

የቤተክርስቲያኒቱን መዋቅር በሙሉ የእርሱ ሐሳብ አራማጆች በሆኑ አባላቱ ብቻ መቆጣጠር ለእርሱ ህልዉና አማራጭ የሌለዉ መፍትሄ እንደሆነ ከወሰነም ቆይቶአል፡፡ እርሱ ከሌለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ እንደምትጠፋ ከወሰነም ሰንብቶአል፡፡ ስለዚህ በዚህ ሰይጣናዊ ምክር የተተበተበ ማህበር በመሆኑ ጌታን በጥፊ እንደመታዉ ሎሌ አንድም ቀን ክፉዉን ክፉ መልካሙን መልካም ብሎ ሳይመሰክር እድሜ ልኩን የአለቃዉ የዲያብሎስ ሎሌ ሆኖ የቤተክርስቲያን ልጆችን ሲከስ  ዘመን እያለፈበት መጣ፡፡ ያሳዝናል እንዲህ ሆኖ ለፍርድ መቀመጥ! እግዚአብሔር ከዚህ እርግማን ይሰዉረን፡፡ አሜን!!!

በአሰበ ተፈሪ ቅድስት ልደታ ቤ/ክ የተፈጠረዉን እዉነት ግን  ይሄ ነዉ፡፡
1.      የሁለቱ ደብር ሰበካ ጉባኤ ማለትም የቅድስት ልደታ ለማርያምና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ/ክ ሰበካ ጉባኤ አባላት የአገልግሎት ግዜዉ ያበቃ በመሆኑ አዲስ የሰበካ ጉባኤ አመራር ቃለ አዋዲዉ በሚያዘዉ መሰረት ማስመረጥ የሚገባ በመሆኑ ሰበካዉ አጠቃላይ ሪፖርቱን እንዲያቀርብና ማህበረ ምእመናኑ አስመራጭ ኮሚቴ እንዲመርጡ በሀገረ ስብከቱ ተደረገ፡፡ በዚህ ሰአት ማህበረ ምእመኑ ከዚህ በፊት ለቤተክርስቲያኒቱ ልማትና ወንጌል አገልግሎት እጅግ የሚፋጠኑና የሚተጉ ተወካዮቻቸዉን በአስመራጭ ኮሚቴነት መረጡ፡፡ በዚህ ያልተደሰተዉና ከዚህ በፊት ለረጅም አመታት የራሱን አባላት የሰበካ ጉባኤና ሰንበት ትምህርት ቤት አመራር አድርጎ የቆየዉ ማህበረ ቅዱሳን አንዳንድ አባላቶቹ በእለቱ ተቃዉሞ ሊያነሱ የሞከሩ ቢሆንም የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች' ካህናቱና ማህበረ ምእመኑ በያዙት ጽኑ አቋም ምርጫዉ በሰላም ተጠናቀቀ፡፡ ይሁን እንጂ እድሜ ልኩን በክስ የኖረዉ ማህበረ ቅዱሳን የሐሰት ክሱን ይዞ ሀገረ ስብከትም  የሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንባቆም ጋር ቢሄድ ተቀባይነት በማጣቱ የሰበካ ጉባኤዉ ምርጫ ሂደት  አዲስ ከተሰራችዉ ቤተክርስቲያኒቱ ምረቃ በኋላ እንዲከናወን ተወስኖ አበቃ፡፡
2.     ይሁን እንጂ እስከ ሊቀ ጳጳሱ ቅሬታዉን አቅርቦ የሐሰት ክሱ ተሰሚነት ያጣዉ ይሄዉ የጸሀፍት ፈሪሳዊያን ስብስብ እንደ ግብር አባቶቹ የምርጫዉን እለት ጠብቆ ሁከት መፍጠርና ቤተክርስቲያኒቱን ማወክ እንደ መፍትሄ ሐሳብ ይዞ በ21/11/2005 እሁድ ከቅዳሴ በሁዋላ የራሱ አባላት የሆኑትንና የእርሱ ደጋፊ የሆኑ ነገር ግን የሰንበት ትምርት ቤት አባላት ያልሆኑትን የመዝሙር ዩኒፎርም በማስለበስና ከበሮ በማስመታት የምርጫ ሂደቱ ሊከናወን ሲል ረብሻ አስነሱ፡፡ የህግ አካልም 'ህዝበ ክርስቲያኑም' ማህበረ ካህናቱም ቢለምናቸዉ እንቢ በማለት ሁካታ በመፍጠር የምርጫ ሂደቱ በእለቱ እንዳይከናወን መሰናክል ከመፍጠርም አልፈዉ የሐገረ ስብከት ሰራተኛ የሆኑ አንድ አባት ላይ የድብደባ ወንጀልም ፈጽመዋል፡፡ በጣም የሚያሳዝነዉ እንደ እንሰሳዋ ተረት እኔ ካልሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ያለዉ ማህበረ ቅዱሳን እንኳን ታላላቆች የቤተክርስቲያን አባቶችን ለጸጥታ የመጡ የፖሊስ አካላትንም ሊያከብር አልቻለም፡፡ ራሱን ከቤተክርስቲያንም ከመንግስት ህግም በላይ አድርጎ ስለሚቆጥር፡፡
3.     የማህበሩ ሁካታ በዚሁ ሁኔታ የተጠናቀቀ ቢሆንም ሐገረ ስብከቱ ከመጀመሪያ ጀምሮ እልህ አስጨራሽና ለትእግሰቱ የመጨረሻ የሆነዉን ምክርና ዉይይት ከዚህ ማህበር አባላት ነን ከሚሉ ጋር ያደረገ ቢሆንም ከዚህ በላይ ማህበሩና የሰንበት ትምህርት ቤቱ አመራር ነን የሚሉ ማህበረ ቅዱሳኖች ቤተክርስቲያኒቱን እያወከ መቀጠል የለበትም በማለት ድሬደዋ ከተማ ከሚገኙት ከሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንባቆም 'ከህግ አካላት' ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመመካከር አስፈላጊዉን እርምጃ እንዲወሰድ አድርጎአል፡፡ ይህ እርምጃ ማህበረ ካህናቱን ምእመናኑን እጅግ ያስደሰተ እርምጃም ሆኖ ተገኝቶአል፡፡ በዚሁ መሰረትም ደግሞ ይህ እርምጃ ትክክለኛ አካሄድ እንጂ እነርሱ እንደሚሉት ሐገረ ስብከቱ ከማህበረ ናታኒም ጋር ተቀናጅቶ ያደረገዉ አይደለም፡፡
4.    የሐይማኖት አበዉ ርዝራዥ አባላት የተጠራቀሙበት ነዉ ያሉት ማህበረ ናታኒም ያሉት ማህበር የተቋቋመዉ በ2003ዓ/ም ብጹእ አቡነ ማቴዎስ አሁን የጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ ሆነዉ እያገለገሉ ያሉት አባት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ  በነበሩበት ወቅት የቅድሰት ልደታ ለማርያም ቤ/ክ ከ19 አመት በላይ ሳትሰራ ስትጓተት ቆይታ በእነዚህ ወጣቶች ተነሳሽነት በአንድ የወንጌል አገልግሎት ጉባኤ በማዘጋጀት ከ600000.00(ስድስት መቶ ሺህ ብር) በመሰብሰብና ከዚያም በሁዋላ በተደረጉ ከፍተኛ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ከ2500000.00(ከሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) በማሰባሰብ ህንጻ ቤ/ክ 19 አመት የማህበረ ቅዱሳን ደጋፊ የሆነዉ ህንጻ አሰሪ ጥቂት አመራር በከፍተኛ ምዝበራና ብክነት ሲያጓትት የቆየዉን ህንጻ ቤ/ክ ስራ  በሁለት አመት ዉስጥ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ያደረገ ማህበር በመሆኑና   በአቡነ ማቴዎስ በጎ ፍቃድ የተቋቋመ ማህበር እንጂ ማ/ቅ እንደሚለዉ የመናፍቃን ጥርቅም አይደለም፡፡ አሁን ግዜ ያጥራል እንጂ ማህበረ ናታኒምና ማህበረ ጽዮን በቅንጅት በገጠር አብያተ ክርስቲያናት ላይ እየሰሩ ያሉትን መንፈሳዊ አገልግሎት መዘርዘር የሚቻል ነበር፡፡ ነገር ግን ዉዳሴ ከንቱ ስለሚሆን አልፈነዋል፡፡
5.     አቶ ታረቀኝ በቀለ ለቤ/ክ የቁርጥ ቀን ፈጥኖ ደራሽ ልጅ እንጂ እንደ እነርሱ/ማህበረ ቅዱሳን/ ለአባቶች የማይታዘዝ' ወላጆቹ የሚሉትን የማይሰማ' ህግን የማከብር  አይደለም፡፡ የሐገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ሊቀ ብርሀናት ከሀሊ በቃሉ  እና የሐገረ ስብከቱ ጸሐፊ ሊቀ ህሩያን ደረጀ ብርሀኑ በማህበረ ካህናቱ በማህበረ ምእመኑ እጅግ የተወደዱ ለቤ/ክ ጥቅም የቆሙ ለሰዉ ልጅ መዳን የሚጨነቁ የቤ/ክ ዶግማና ቀኖና እንዳይደፈር የሚሰሩ አባቶች እንጂ በማህበር ወይም በሰዉ ሐሳብ የሚመሩ አባቶች አይደሉም፡፡ ነገር ግን ማህበሩ ለእርሱ ዉሸት ያልተባበሩትን እድሜ ልኩን የሀሰት ታፔላ ሲለጥፍ የኖረ በመሆኑ ነገሩ ከዝንብ ማር አይጠበቅም ነዉ፡፡

6.    ስለዚህም ማህበረ ቅዱሳን እስከ መቼ እንደ ቀበሮዋ የበግ ለምድ ለብሰህ ትኖራለህ፡፡ አንተ ከተቋቋምክ ጀምሮ ከ7000000(ሰባት ሚሊዮን) ኦርቶዶክስ አማኞች በአንተ ክስና ተንኮል በመናፍቃን እንደተበሉ አልሰማህም፡፡ አሁን ወጣቱ ወደ ቤተክርስቲያኑ ተመልሶ ስታይ አይንህ ለምን ደም ይለብሳል፡፡ በአንድ ሐጥእ መመለስ በሰማይ መላእክት ዘንድ ደስታ ከሆነ በወጣቶች ወደ ቤተክርስቲያን መመለስ ከተናደድክ ግብርህ እንደ ስምህ ከቅዱሳን ጋር ሳይሆን የሰዉን ልጅ መጥፋት ከሚመኘዉ ከዲያብሎስ ጋር ነዉ፡፡  ስለዚህ ያ የአንተ ክፉ ዘመን አብቅቶአል፡፡ ፤ቤተክርስቲያናችን ብሩህ ዘመን በእዉነተኛዉ እረኛ በክርስቶስ የተበሰረላትን እየጠበቀች በመሆኑ አንተ ከዚህ በሁዋላ በቤ/ክ ስፍራ የለህም፡፡ ስፍራህ አሁን እየኖርከዉ እየተለማመድከዉ ባለዉ ድቅድቅ ጨለማ ነዉ፡፡ ግን ግዜ አለህ ንስሀ ለመግባት ምክንያቱም የክርስትና ማእከሉ ሰዉ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር የሚያድነዉ ሰዉን ነዉ እናንተ የጠላችሁት ደግሞ ሰዉን፡፡ ስለዚህ #የጠቢብ አይኑ በራሱ ነዉ$ ስለሚል ጠቢቡ ሰለሞን ወደራሳችሁ ተመልሳችሁ እራሳችሁን እዩ  ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡ አሜን!!!

2 comments:

  1. የማህበረ ቅዱሳን/ይህ ስም እንኳን/ ለእርሱ ግብር መገለጫ ባይሆንም ግን ለግዜዉ ይጠራበትና ገና ገና በምስራቅ ኢትዮጵያ የሰራዉ ግፍ ገና ይጻፋል አምላክ ቢፈቅድ፡፡

    ReplyDelete
  2. are sure des yilal

    ReplyDelete