Esat andKnowledge:Click here to read in PDF
(ከጸሐፊው ግላዊ ገጸ መጽሐፍ(face
book) የተገኘ)
በሙሉጌታ ወ/ገብርኤል
(ሐምሌ 23
2004 ዓ.ም.፣ ዐውደ ምሕረት/www.awdemihret.blogspot.com) (ባለፈው ሳምንት “ኢሳት: በማቅ የአፍዝ አደንግዝ ፖለቲካ የተለከፈ የጽንፈኞች መናገሻ?” በሚል ርዕስ መቀመጫውን
አምስተርዳም ያደረገ የዜና ማሰራጫ ማዕከል የሕዝብ ዓይንና ጆሮ፣ ሃብትና ንብረት መሆኑ እየቀረ ሕዝብንና ሀገርን ለመበታተን እንዲሁም ለማውደም ቆርጠው ከተነሱ የበግ ለምድ የለበሱ አደጋ ጣዮች ሥመ መንፈሳውያን በማበርና ድምጽ በመሆን በሰሚ ጆሮ ላይ እየፈጠርው ያለውን ሃላፊነት የጎደለበት ልቅ ውዥንብርና ብዥታ በመታቀብ ተቋሙ በዋናነት ለተቋቋመበትና ለተሰለፈበት ዓላማ ራሱን ያስገዛ ዘንድ በጥቂቱ ለማሳሰብ ያክል ተወያይተን ነበር በይደር የተለያየነው። ለዛሬ ታሪካዊ ስህተቶችን ብቻ በማተኮር ተፋለሶቹን አንድ በአንድ ነቅሰን አንጥረንና አበጥረን በሰፊው እንመለከታለን።
ጽሑፉ ምንም እንኳን "የዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ታጋዮች" የሆኑ ድረ ገጾች በመላ የተላከ
ቢሆንም ድረ ገጾቹ በተላከላቸው
ጽሑፍ ይዘት ምንም ዓይነት ተቃውሞ እንደሌላቸውና በጽሑፉ እውነትነት ቢስማሙም በይፋ ለማስነበብ ግን ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። በቋሚነት ሀገራዊ፣ ሃይማኖታዊና ማህበረሰባዊ አመለካከቴንና አስተሳሰቤን ከማካፍልበት ግዙፍ ኢትዮጵያዊ ድረ ገጽ ሕዝብ እንዳያነበውና እንዳያየውም ተቋሙ በፈጠረው ጫና 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከስፍራው እንዲነቀል ተደርገዋል። ድርጊቱም ኢ- ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ
ሐዘን ተሰምቶኛል። በዚህ አጋጣሚ የዳያስፖራ "ነፃ
ፕሬስ/ሚድያ" ነጻ
ይውጣ! እያልኩ ለጊዜው ሥራዎቼን በመጽሐፈ ገጽ (face book) በኩል ለማስነበብ ተገድጃለሁ። ይህም እስኪታፈን ድረስ መሆኑ ነው እንግዲህ።
የጽሑፉ መልክ - ተንጋዶ የተጻፈውን ወይንም ደግሞ በኢታሊክ የሰፈረውን ከተናጋሪው ጋዜጠኛ ቃል
በቃል የሰፈረ ሲሆን መስመር የተሰመረባቸው
ቃላት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቃላት ለመሆናቸው ለማስታወስ ነው።መልካም ንባብ!)
የጋዜጠኛው
ሃይማኖታዊና
ታሪካዊ
ስህተት÷
"ፋይናሊ
ሊያሸንፉዋቸው ስላልቻሉ
ምን ብለው
ገቡ ክርስቲያኖቹን
እኛም አመንን
ብለው በቤተ-ክርስቲያን
ውስጥ ገቡ።
በሃይል ማሸነፍ ሲያቅታቸው
ምን ውስጥ
ገቡ ክርስቲያኖች
ነን ብለው፤
ሳይሆኑ ክርስቲያን
ነን ብለው
ሃይማኖት ተቋምን
መቆጣጠር ያዙ
ከዛን ጊዜ ጀምሮ
ነው የእምነት
ተቋማት ቤተ-ክርስቲያን
በገዢዎች ስር
መዳፍ ስር
እየወደቀችው ያለችው”
ኢህአዴግ እያደረገው
ያለው ከቄሳሮች የተለየ
ነገር አይደለም
በመስጊድም በቤተ-ክርስቲያን
በኩልም ሁሉ
ሊያደርግ የሚፈልገው
እነዚህን ተቋማት
ለእምነቱ ለእሱ
ለአገዛዙ እንዲመቹት የማድረግ
ነው:: ገብቶባቸዋል።
በህገ መንግስቱ
ላይ የነፃነቶች
አለ ተብለዋል
ኢህአዴግ ግን
እንደፈለገ ገብቶ
የራሱ አመራር አስቀምጠዋል”
የኢሳት ጋዜጠኛ ደረጀ ሀብተ ወልድ