Click here to read in PDF
ምንጭ፡-http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com
"ማኅበረ ቅዱሳን"፣ "እውን የማኅበረ ቅዱሳንና ኦርቶዶክስ 'ተሐድሶ' ፍልሚያ ወይስ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሕልውና ጉዳይ"? በሚል ርዕስ ደጀ ሠላም (deje selam) በተባለው ትዊተር ገጹ ላወጣው የማደናገሪያ ጽሑፍ የተሰጠ መልስ
ድሮ ልጆች ከሚያውቁት ሠፈር
ርቀው እንዳይሄዱና እንዳይጠፉ ጭራቅ ይበላሃል፤ ጭራቅ ይበላሻል እየተባሉ በዐዋቂዎች ማስፈራሪያ ይደረግባቸው ነበር፡፡ ይህ ጭራቅ በሕይወት የሌለና በምናብ የተፈጠረ ሲሆን፣ ጥርሶቹ ሾል ሾል ያሉ፣ ሁለት ትልልቅ ዓይኖች ከፊት፣ ሁለት ትልልቅ ዐይኖች ደግሞ ከማጅራቱ /ጭንቅላቱ/ በኩል በድምሩ አራት
ዐይኖች ያሉት
ሲሆን አንገቱን ዞር ዞር ማድረግ ሳያስፈልገው በሁሉም አቅጣጫ ስለሚመለከት ማንም
ሊያመልጠው አይችልም፡፡
ጭራቅ በቁመናው ሰው
እየመሰለ ከሰው
መካከል በተለይ ልጆችን እየመረጠ፣ ወስዶ
በትልቅ ጋን
ውስጥ እንዳለ በመክተት ከቀቀለ በኋላ
ያለ ቢላዋ
ሥጋቸውን የሚነጭ አውሬ ነው ይባል ነበር፡፡ ምንም
እንኳን ጭራቅ
በግዑዙ ዓለም
የሌለና የፈጠራ መሆኑን ብናውቅም በአባቶችና በእናቶች በተደረገብን ጫና
ሳቢያ ዛሬም
ያለ የሚመስለን ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡
አባቶችና እናቶች ልጆችን እንዲታዘዙ የሚያደርጉት በጭራቅ በማስፈራራት ነበር፡፡ እኛም
ልጆች በጊዜው ጭራቅ መጥቶ እንዳይበላን የተሰጠንን ሥራ
ባንወደውም ሠርተናል፡፡ ጀንበር ሳይጠልቅ ወደ
ቤት ስብስብ ብለን እግራችንን ታጥበን፣ እራት በልተን ተኝተናል፡፡ አፋችን ክፉ ቃል እንዳያወጣ ገደብ
ተደርጎበታል፡፡ ጭራቅ
እንዳይበላን አባትና እናታችን ጉያ ውስጥ ውሽቅ ብለን፣ ፍርሃት እንደናጠን አድገናል፤ ኖረናል፡፡