Thursday, February 21, 2013

ኢሳት ይጠየቅልኝ!

ዝርዝር ጥልቀት ያለው ሐተታ ቀርቶ የውጣ ቃልም ብትሆን ስለ ኢሳት አንጻራዊ አመለካከት ማንጸባረቅ፡ ተቋሙ እየተከተለው ያለውን አሰራርና እየሄደበት ያለው ማንንም የማይጠቅም መንገድ እንደ ዜጋ በግልጽ መናገር: ትንፍሽ ማለት በተለይ "ይውደም!" ከተባለ "ይውደም!"- "ይቅደም!" ከተባለም እንዲሁ በተመሳሳይ ድምጽ "እንዴትና? ለምን?" በሌለበት ሁኔታ "ይውደም!" በማለት ድምጹን በማስተጋባት በሚታወቀው ማህበረሰብ አካባቢ ዘንዳ ምን ዓይነት ስም ሊያሰጥ እንደሚችል በሚገባ ጠንቅቄ አውቃለሁ። የደርግ ወታደራዊ መንግስት ቀን ጨለማ ሳይል የንጹሐን ዜጎች ደም ደመ ከልብ ሲያደርግና በገዛ ሕዝቡ በአደባባይ በጥይት ሲደበድብ/ሲረሽን አገኘሁበት የሚለው ክስ አንዱ "ጸረ አብዮት ነው!በማለት ነበር ሲሉ ከሞት ያመለጡ ምስክሮች እንደሚናገሩት ማለት ነው። ያም ሆነ ይህ መስመሩ ስለ ለቀቀና አቅጣጫው ክፉኛ ስቶ ስለሚገኘው: ታማኝነት የጎደለበት፡ ከምንም በላይ ደግሞ የሞያው ስነ ምግባር በሚጣረስ መልኩ ሆነ ተብሎ እየተደረገ ያለው የኢሳት አሰራር ጭብጥ ላይ የተመረኮዘ ተጨባጭ ሃሳብ ይዤ መመጎቴ ተከትሎ በጸሐፊው /ለሚለጠፉ ታቤላዎች አግባብነት የለውም ችግሩም ይቀርፈዋል የሚል እምነት የለኝም።
የኢ////ያን በተመልከተ በተለይ ከወቅቱ ጋር በተያያዘ የሃይማኖት መሪዎች የእርስ በርስ የመተረማመሱ ነገር እንዲሁም
በሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች በኩል ከመንፈሳዊነት ይልቅ እልከኝነት የተሞለበት ስብእናቸው አይሎ ከመውጣቱ የተነሳ የከሸፈውን እርቀ ሰላም በኢሳት በኩል ያለ አንዳች ተጨባጭና ደረቅ ማስረጃ የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ ለማድረግ የተሰሩ "ዜናዎችና ሐተታዎች" ብዛቱ ስፍር ቁጥር የለውም። ይህ የምለው ደግሞ እንደ ወንጌል አገልጋይነቴ እውነቱ እውነት ለማለት እንጅ ለመንግስት ጥብቅና ለመቆም ቃጥቶችም አይደለም። ቀደም ሲል በእኔ በኩልም ሆነ በሌሎች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆችና መምህራን አማካኝነት ከዚህ ሁሉ የሃይማኖት መሪዎች ትርምስ ጀርባ ለመልካም ነገር የሚያበቃ አቅም ባይኖረውም ለሁከትና ለረብሻ ግን የሚስተካከለው የሌለው "ማህበረ ቅዱሳን" በማለት ራሱን የሚጠራ ስመ መንፈሳዊ አጽራረ ጽድቅ ድርጅት የኢ////ያን የማፈራረስ ዓላማ አንዱ ስትራቴጂ መሆኑ በተጨባጭ ሲነገር መክረሙን የምንዘናጋው እውነት አይደለም።

Saturday, February 2, 2013

አይቴ እረክቦ ለጋኔን ከመ እብሎ እንብየ ለጋኔን?

REad in PDF: Ayte Arekebo
መሪ ጥቅስ:
"በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል። ወይስ መጽሐፍ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን? ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል። (7) እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙከእናንተም ይሸሻል፤ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ። ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ። በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።" ያዕቆብ 4፣ 1- 8
የጽሑፉ ዓላማ: ለሸቀጥ፣ የዋኁን ሕዝብ ለማታለልና ብሎም ለማደናገር ሲባል ብቻ በቆርጠህ ቀጥል ሥጋዊ መርህ እንዲሁም ፈሪሐ እግዚአብሔር በሌለበትና በማን አለብኝነት መንፈስ በድፍረት ተጀምሮ በቁንጽል የተተወ ቃለ-እግዚአብሔር ለመሙላት ተፃፈ። ከዚህ ያለፈ ጸሐፊው ሆኑ ጽሑፉ አንዱን በመደገፍ ሌላውን የማጥቃት ዓላማ የላቸውም። አሁንም ከታሰበበት ተዘግቶ የሚዘጋ በር የለምና ሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች ወደ ልባቸው ተመለሰው ከመከሩ ሰላም የማያወርዱበትና ዕርቅ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም ብለው ያምናሉ። ስድስተኛ ፓትሪያሪክ ለመምረጥና ለመሾም እየተጣደፈ የሚገኘው ሥርዓት አልባው የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ በተመለከተ በሚቀጥለው ጽሑፌ በስፋት የምንዳስሰው ይሆናል።