Wednesday, September 26, 2012

‹‹አንድ አድርገን›› እውነት ተናገረ


በዲያቆን ፈታሂ በጽድቅ
በኦገስት 23, 2012 በአንድ አድርገን ብሎግ ላይ ፖስት የተደረገውን ‹‹የአቡነ ጳውሎስ ሽኝት በፎቶ›› የሚለውን የፎቶግራፍ ስብስብ አይተው ሲጨርሱመጨረሻቸው መጨረሻችን የሚል ቃል በትምህርተ ጥቅስ ተቀምጦ ያነባሉ፡፡ ይህን ቃል ሳነብ ነው ‹‹አንድ አድርገን›› እውነት ተናገረች የሚለውን ለማስፈር የተነሳሳሁት፤ ምክንያቴንም እነሆ፡-
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ በክብር የትንሳኤው ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከአዳም የወረሱት ነውና ስጋዊውን ሞት ሊያስተናግዱ ግድ ነው፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ በማመናቸው ሁለተኛው ሞት እነርሱ ላይ ስለማይሰለጥን በትንሳኤ ሞት ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ ሲሉ ይሳለቁበታል፡፡ ትንሳኤው ለማግኘት ግን በክርስቶስ ብቻ ማመን የመጀመሪያውም የመጨረሻውም መንገድ ነው፡፡
‹‹አንድ አድርገን›› ላይ አመጽንና ጸረ ወንጌልነትን የሚሰብኩን ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ የማያምኑ ሰዎች መሆናቸውን ጽሑፎቻቸው የሚናገረ በመሆኑ ለትንሳኤ መብቃታቸውን ብጠራጠር ለምን ብሎ የሚሞግተኝ ሰው ይኖራል ብዬ አልጠብቀም፡፡ ይህን ጥርጣራዬን ደግሞ ራሳቸው ቀደም ሲል ባሰፈርኩት ቃል አረጋግጠውልኛል፡፡
መጨረሻቸው መጨረሻችን” የሚለውን ያሰፈሩት የአቡነ ጳውሎስ በድን ያረፈበትን ባዶ ጉድጓድ ካሳዩ በኋላ ሲሆን የአቡነ ጳውሎስ መጨረሻ የሆነው ይህ ጉድጓድ የእኛም መጨረሻ ነው ማለታቸው እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የአቡን ጳውሎስ መጨረሻ ያቺ አርባ ክንድ ጉድጓድ እንዳልሆነች እርግጠኛ ብሆንም  የእነርሱን መጨረሻ ግን ራሳቸው መጨረሻችን” ብለው ያሰፈሩትን እንድቀበል እገደዳለሁ ‹‹ከባለቤቱ ያወቀ…›› ይባል የለ?

Monday, September 24, 2012

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን መሪዎች ሊቃነ ጳጳሳት ህይወት አደጋ ላይ ወድቀዋል


                                            በዲ/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
(ዐውደ ምሕረት፣ ሠኞ፣ መስከረም 14 2004 ዓ.ም. awdemihret.blogspot.com//awdemihret.wordpress.com)(ቀጣዩ ጽኁፍ ኢትዮጵን ሪቪው በተባለ ዌብሳይት ላይ ከወጣ በኃላ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማህበረ ቅዱሳን ኢሳት በመባል ከሚታወቀው ያለ ነውርና ጠማማነት በጎነትና ቅንነት የማይወጣበት የህውከተኛችና የነውጠኞች የፕሮፖጋንዳ ማእከል ለጥፋትና ለመዓት ከማህበሩ ጎን ተሰልፎ የሚሰራቸው ስራዎች በመንቀፉ እንዲወገድ የተደረገ ጽኁፍ ነው፡፡ 
ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በበሬ ወለደ ውሸት ተቃቅፎ እያሸረገደ የሚገኘው ይህ "የቴሌቭዥን ጣቢያ" በሚፈጥረው ተጽእኖ ድህረ ገጹም በበኩሉ ኢሳትን አትንኩብኝ ከእሱ ጋር ያለኝ የአላማ አንድነት ጽኁፎቻችሁን በነፃነት ለማስተናገድ አይፈቅድልኝም ሲል የዲያቆን ሙሉጌታ ወልደገብርኤልን ጽኁፍ ከድረ ገጹ አስወግዷል፡፡”
ስለዲሞክራሲያዊ መብት እታገላለሁ እያለ ባለው ትንሽ እድሉ ዲሞክራሲያዊ መብትን የሚያፍን ስብስብ ከዚህ አስተሳሰባችሁ ጋር ስልጣን ብትይዙ ምን አይነት አምባገነን እንደምትሆኑ ስናስብ ይዘገንነናል፡፡ ኢትዩጵን ሪቪዎች ሕሊናችሁ ስለማያምንበት ዲሞክራሲ ማውራት ብታቆሙ ጥሩ ነው፡፡ ሙሉጌታንም አይዞህ በርታ ለእውነት መታገልህን ቀጥል ልንለው እንወዳለን፡፡ መልካም ንባብ ይሁንላችሁ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ሆነ በነባራዊው ዓለም እንደ እስራኤል ያለ ለሰውም ለፈጣሪም የማይመለስ እልከኛ፣ ፈታኝ፣ አመፀኛና አብግን ዜጋ ሌላ ይኖራል ብዬ አላስብም። እስራኤል ከተፈጠረበት ጊዜ ጀመሮ አሁን እስካለበት ጊዜ ድረስ ያለውን ገጽታና መታወቂያ ከወንጭፍና ሰይፍ ወደ መከናይዝድ ተሸጋገረ እንጅ አንዲትም ዘመን ብትሆን እየጎነተለም ሆነ እየተጎነተለ በሰላም የተኛበት ዕለት የለም። ወደ ጥንተ ነገሩ በመመለስ የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ፣ ባህልና ወግ ምን ይመስል እንደነበረ/እንደሚመስል ለማወቅና ለመመርመር የተፈለገ እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ታሪክ ሳያዛንፍ ሊተርክልን የሚችል ሌላ መጽሐፍ አይኖርምና መጽሐፉን በሽፍኑ ከመሳለም ባለፈ ገልጠን ማንበቡ የላቀ ጥቅም ሊኖረው እንደሚችል በዚህ አጋጣሚ ለመጠቆም እወዳለሁ።