Wednesday, October 31, 2012

የሲኖዶሱ የስምንተኛ ቀን ውሎ

READ PDF: sinodos 8
  • ·        ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ በቦታው ይቆያል
  • ·        አዲስ አበባ ለአቡነ ህዝቅኤል እና ለአቡነ ዳንኤል ተሰጥቷል
  • ·        የአክሱሙ ንቡረዕድ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተወስኗል

የእነ አባ መሸ በከንቱ ስብስብ የሆነው የጉድ ሙዳዮቹ ሸንጎ የሚተዳደሩበትን ሕግ እና ያላቸውን የስልጣን ደረጃ በማያውቁ እና ወይ ከእውቀት ወይ ከምግባር በሌሉበት ጨዋዎች በመወረሩ የማይመለከተውን ነገር እያየ በጊዜው ሲቀልድ ውሏል፡፡
ደንብ የማያነቡ ሕግ የማይገዛቸው ጮሆ ማውገዝ ጮሆ መወሰን እንጂ በምክንያት እና በእውነት ተገዝቶ ለመኖር በማይፈልጉ እና በማይችሉበትም ጳጳሳት ስለተሞላ የአንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምርጫ  የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስን ብቻ የሚመለከት መሆኑን እየዘነጉ ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስን ከስራ አስኪያጅነት ለማውረድ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡

Tuesday, October 30, 2012

ሲኖዶሱ በሰባተኛ ቀን ውሎው ቃለ ጉባኤ ላይ ሲጨቃጨቅ ዋለ

Click here to read in PDF:sinodos 7
ሲኖዶሱ በትናንትናው ዕለት በነበረው ስብሰባ ቃለጉባኤ ሲያስነብብ እና ሲጨቃጨቅበት ውሏል፡፡ አቃቤ መንበሩ አቡነ ናትናኤል የባንዲራ ቀን ለማክበር ሄደው ስለነበር ስብሰባው የተካሄደው እሳቸው በሌሉበት ነበር፡፡ ቃለጉባኤው ሲነበብ ካነጋገሩት ነገሮች መካከል ዋነኛው የአሜሪካው ጉዳይ ነበር፡፡ ያጸደቁትን እና የሚተዳደሩበትን ህግ የማያውቁ የሲኖዶሱ አባላት የአርባ ምንጩ አቡነ ኤልያስ መሪነት እኛ የወሰንነው ሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ ይነሳ ብለን ነው ለምንድን ነው የማይነሳው? ብለው ህገ ደንቡ በማይፈቅድላቸው ጉዳይ ሙግት ጀመሩ፡፡
ነገሩ ወደ ጭቅጭቅ በማምራቱም አቡነ ናትናኤል ባሉበት በዛሬው ዕለት እንደገና እንዲታይ ተወስኗል፡፡ እንደገና ይታይ ሲባልም በክብረ መንገስት ሕዝብ ተዋርደው እና አንገታቸውን ደፍተው የወጡት አቡነ ዮሴፍ ጉዳዩን ደግመን የምናየው ከሆነ የምናየው አቡነ ፋኑኤል በሌሉበት መሆን ነው ያለበት ቢሉም አቡነ ፋኑኤል ግን እስከ አሁን ድረስ የማንም ሀገረ ስብከት ጉዳይ በሲኖዶስ ሲታይ ሊቀ ጳጳሱ ባለበት ነው የኔ ጊዜ ለምንድን ነው የምወጣው? የአቡነ ገብርኤል ጉዳይ የታየው እሳቸው ባሉበት ነው ስለዚህ እኔ ባለሁት ነው የሚታየው በማለት መልሰዋል፡፡

Sunday, October 28, 2012

ለቅዱስ ፓትሪያሪክ መርቆሪዎስ


በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
በለሱንየጠበቀፍሬዋንይበላል፥ጌታውንምየሚጠብቅይከብራል!
ቅድመ ሐተታ
በይድረስ የተጻፈውን ደብዳቤ ከመልዕክቱ ተቀባይ ከቅዱስ ፓትሪያሪኩ አልፎ ለአንባቢያን በግላጭ ማቅረብ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ቅዱስነታቸው ፊት ለፊት አፍጥጦ የሚጠብቃቸው በሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ቅራኔ ከዚህም አልፎ የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን  "ልክ ለሌለው" የመከፋፈልና የመለያየት፤ ማንም እንዳሻው እየተነሳ በራሱ አለቃ የሚሆንበት ሥርዓት አልበኝነት/ጋጠወጥነት ያነገሰ አሳፋሪ ገጽታ ለማስቆምም ሆነ አሁን ካለበት ሁኔታ ተባብሶ እንዲቀጥል ለማድረግ ሁለቱም አካላት የሚያሳዩት/የሚያንጸባርቁት አቋም በሌላ አገላለጽ በሚያስተላልፉት ውሳኔና በሚወስዱት እርምጃ በቀጥታ ቀዳሚ ተጠቃሚም ሆነ ተጎጂ የሆነውን የቤተ እምነቱ ተከታይ (ምእመናን) በመሆናቸው በዚህ ጉዳይ ማለትም እርቀ ሰላሙን በማውረድ ረገድ ማን ምን እያደረገ እንዳለ መጠነኛ ግንዛቤ ይኖረውና ያውቅም ዘንድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው።

ሲኖዶሱ በስድስተኛ ቀኑ ውሎው

Click here to read in PDF:Sinodos Day 6
  • የአሜሪካው አህጉረ ስብከት ጉዳይ አነጋግሯል
  • የካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር ብጹአን እነ ማን ናቸው? የሚለው መጽሐፍ ሰበር አጀንዳ መሆኑ አስገርሟል፡፡
  • ሊቀ ኤጲስ ቆጶስ ወይስ ሊቀ ጳጳስ?

በሲኖዶሱ የስድስተኛ ቀን ውሎ የአሜሪካው አኅጉረ ስብከት ጉዳይ ተነስቶ ያነጋገረ ሲሆን የአህጉረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ የሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ መልዕክት በንባብ ተሰምቷል፡፡ አንዲሁም የክህነት እገዳው ጉዳይ ይታይልኝ ያለው የማኅበረ ቅዱሳኑ ኦሪታዊው “ካህን” አቶ መስፍን ደብዳቤም በንባብ ተሰምቷል፡፡ አቡነ ፋኑኤል አለ የተባለውን ነገር ሁሉ በጥሩ ሁኔታ አብራርተዋል፡፡ ከአሜሪካ መነሳታቸው ሁሌም የሚያንገበግባቸው የጉድ ሙዳዩ አቡነ አብርሐም በሰሞኑ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የነበራቸው ዝምታ ተሰብሮ ካልመለሳችሁኝ የሚል አይነት ጩኸት ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ አቡነ ማቲያስም እኔም እኮ በአሜሪካ ስንት ስራ ሰርቻለሁ አትርሱት እንጂ እዛ የነበርኩ መሆኔን አይነት መልዕክት ሲስተላልፉ አቡነ ማርቆስ ደግሞ አቡነ ማቲያስን ለመገሰጽ ሞክረዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤልም አቡነ አብርሃምን ደግፈው ለመናገር ሞክረዋል፡፡ ምነው ቢሉ የሁለቱም ማዘዣ ጣቢያ አንድ ነዋ የሚል ምላሽ ያገኛሉ፡፡

Friday, October 26, 2012

የሲኖዶሱ ስብሰባ አምስተኛ ቀን ውሎ

click here to read in PDf: sinodosday five
  • ሲኖዶሱ የትናንትናው ውሳኔውን ሽሮ ተስፋዬ በቦታው በምክትል ስራ አስኪጅነቱ እንዲቀጥል ወስኗል
  • ለአክሱም ሚዚየም 13 ሚሊየን ብር ፈቅዷል
  • የአቡነ ጳውሎስ ንብረት እንዲቆጠር እና ወደ ሙዚየም እንዲገባ ወስኗል
  • ለአብነት ትምህርት ቤቶች በጀት መድቧል
  • የፓትርያርክ ምርጫ ደንብ እስከ ህዳር 30 ድረስ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተዋቅሯል ከኮሚቴው አባለት አንዱ አዲሱ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ እና በተማሪዎቹ ዘንድ ችኮው ተብሎ የሚጠራው ዶ/ር ሰሙ ይገኝበታል

ሲኖዶሱ በአምስተኛ ቀን ስብሰባው በአቡነ ፊሊጶስ አማካኝነት  በተነሳው የተስፋዬ ይመለስልኝ ጥያቄ ግማሽ ቀኑን አቃጥሏል፡፡ በትናንትናው እለት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተስፋዬ እንዲነሳ ሲወሰን አጨብጭበው ተቀብለው የነበሩት አቡነ ፊሊጶስ ከማኅበረ ቅዱሳን በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በዛሬው እለት ተስፋዬ ይመለስልኝ በማለት በመጠየቃቸው አብዛኛውን ጳጳሳት ያስቆጣ ቢሆንም በተለይም የአቡነ ቄርሎስ የአቡነ እስጢፋኖስ የአቡነ ማርቆስ እና የአቡነ ሳዊሮስ ተቃውሞ ከፍተኛ ነበር፡፡
አቡነ ፊሊጶስ ትናንት ከስልጣኑ ይነሳ ሲባል ተስማምተው ሲያበቁ ዛሬ እንዴት ይመለስ ይላሉ ሲባሉ መልስ ለመስጠት ባይችሉም እንዲሁ በድርቅና ብቻ ያለተስፋዬ ስራ መስራት አልችልም በማለት ጸንተዋል፡፡

አራተኛው ቀን የሲኖዶሱ ስብሰባ

Click here to read in PDf: sinodos day 4
  • ·       ተስፋዬ ከምክትል ስራ አስኪያጅነቱ እንዲነሳ ተወስኗል
  • ·       ሰለሞን ቶልቻ ከገዳማት አስተዳደር ይነሳ ተብሏል
  • ·       እስክንድር ከህዝብ ግንኙነት ይነሳል
  • ·       ለግብጽ ቤተክርስቲያን የፓትርያርክ ምርጫ አምስት ጳጳሳት እንዲሄዱ ተወስኗል
  • ·       አቡነ ሰላማ የአክሱም ህዝብን የደረሰባቸውን ተቃውሞ ለማስተባበል ጉዳዬ ይታልኝ ቢሉም ሰሚ አላገኙም

በዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ በርካታ ጉዳዮች የታዩ ሲሆን የጠቅላይ ቤተክህነቱ ምክትል ስራ እስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ሁለት ስልጣን ደራርቦ መያዙ አግባብነት ስለሌለው በአንዱ ስልጣን በቤቶች አስተዳደር ብቻ ተወስኖ እንዲቀመጥ እና ከጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅነቱ እንዲነሳ ተወስኗል፡፡
ተስፋዬ ከቦታው እንዲነሳ የተወሰነበት ተጨማሪ ምክንያት ደግሞ ጠቅላይ ቤተክህነቱ በአቶ መመራት የለበትም የሚል ተጨማሪ ምክንያት በመቅረቡ ነው፡፡ አቶ ተስፋዬ የቤተክነቱ ትምህርት ስለሌለው እና የቤተክነትን ቋንቋ በብቃት ስለማያውቅ አንዳንድ ጉዳዮችን በአቶ ደንብ ማስተናገዱ ቅር  እንዳሰኛቸው ያልደበቁ ጳጳሳት ነበሩ፡፡

Thursday, October 25, 2012

የሲኖዶሱ ስብሰባ በሶስተኛ ቀን ውሎው


  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለአራት እንዲከፈል ተወስኗል

የዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ የእርቁን ጉዳይ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ ነው፡፡ እርቁን አሁንም አላላቅ ያለ አጀንዳ ሲሆን በማንያዘዋል አማካኝነት ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋር የተነጋገሩት አቃቤ መንበሩ አቡነ ናትናኤል ዛሬም በድጋሚ ሄዶ የመነጋገር ፍላጎቱን ቢያሳዩም ሲኖዶሱ በሲኖዶስ ተወክለው  እርቁን የጀመሩት እነ አቡነ ገሪማ እርቁን ይጨርሱ ሲሉ በድጋሚ ወስኗል፡፡
እርቁን በሚለመከት በተደረገው ውይይት ከሁለተኛው ቀን የከረረ ክርክር በሶስተኛው ቀን የተደረገ ሲሆን አንዳንዶቹ ሀሳቦች በቀጥጣ እርቁ ላይ እንቅፋት የሚፈጥሩ ጉዳዮችን በግልጽ አንስተው የተነጋገሩባቸው ነበሩ፡፡ እርቁ ቢሳካ ለቤተክርስቲያን ሰላም እና አንድነት እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ እርቁን ተግባራዊ ለማድረግ ግን ከሁለቱም ወገኖች ሙሉ ፈቃድ እና አላስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ከማቅረብ መታቀብ ወሳኝ ነው፡፡

Wednesday, October 24, 2012

ሲኖዶሱና ሁለተኛ ቀኑ

Read in PDf:day 2
በዛሬው እለት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ የተነሱት ሁለት አጀንዳዎች ብቻ ሲሆኑ እነርሱም የቤቶች አስተዳደር ጉዳይ እና የእርቁ ጉዳይ ነው፡፡ እርቁን በተመለከተ አቡነ መርቆሬዎስ የላኩት ደብዳቤ የተነበበ ሲሆን ቅዱስነታቸው በደብዳቤው መጥታችሁ ፊት ለፊት እንነጋገር የሚል መልእክት ያለው ነው፡፡ አስታራቂ ኮሚቴዎቹ ቀርበው ስለእርቁ ሁኔታ ያስረዱ ሲሆን መጥታችሁ እንነጋገር የሚለውን የአቡነ መርቆሬዎስ መልእክት ተመርኩዘው አቡነ ናትናኤል የመሄድ ፍላጉት ቢሳያዩም ሲኖዶሱ ግን እርስዋ አይሄዱም ከዚህ በፊት የጀመሩት እነ አቡነ ገሪማ ናቸው መሄድ ያለባቸው ሲል ወስኗል፡፡
እርቁን በተመለከተ የተንሸራሸሩ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ለዕርቁ ሲኬት ሲባል እናልፈዋለን፡፡ የቤቶች አስተዳዳርን በተመለከተም የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪጁ አቶ ተስፋዬ ስለአጠቃላይ ሁኔታ ቀርቦ አስረድቷል፡፡

Monday, October 22, 2012

የሲኖዶሱ የዛሬ ቀን ውሎ

Read in PDf:Day 0ne
  • 21 አጀንዳዎችን መርጧል በ5 ተወያየቶ ጨርሷል
ሲኖዶሱ በዛሬው ዕለት ስብሰባውን የጀመረ ሲሆን  በዛሬው እለት ስብሰባውን በአጀንዳ ቀረፃ እና በተቀረጹት አጀንዳዎች ላይ በመወያያት አሳልፎዋል፡፡
በስብሰባው ላይ ከተነሱት አጀንዳዎች መካከል
·        የቤተክርስቲያኒን ህግጋት ማሻሻል
·        የፓትርያርክ ምርጫን ኅግ ማውጣት
·        ለአቃቤ መንበሩ ህግ ማውጣት
·        የቁልቢ ገብርኤል ጉዳይ
·        የእርቁ ጉዳይ
·        የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይ
·        የቤቶች አስተዳደር
·        የወደፊት እቅድ

Sunday, October 21, 2012

የአባ ናትናኤል ጉዳይ

  • ከእስር ከተፈቱ ሳምንት ሆኗቸዋል
  • ለእስር ያበቃቸው ዋነኛው ምክንያት ማኅበረ ቅዱሳን በደብሩ የሚካሄደውን ግልጽ ጨረታ አጭበርብሮ ለማሸነፍ በመፈለጉ ነው፡፡
የአየር ጤና ኪዳነ ምህረት / አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ናትናኤል መላኩ ባለፈው ጥቅምት 2 2005 ዓ.ም. በአዋሳ ፖሊሶች አማካኝነት ታስረው የተወሰዱ ቢሆንም ባለፈው ሳምነት እሁድ እሳቸውን ለማሳሰር የሚያበቃ ምንም ምክንያት እንደሌለ ስለታመነበት ከእስር እንዲፈቱ ተደርገዋል፡፡ ከአዋሳ ሀብታሞች እና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ተሻርከው እንዲታሰሩ ያደረጉት ፖሊሶችም በድረጊታቸው በክልል መንግስት ተገምግመው በከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ታልፈዋል፡፡ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ የተባለው ፖሊስ ቁርጥራጭ ሳንቲም ተቀብሎ ንጹህ ሰው ለማሰር በመሞከሩ በራሱ ላይ ግለ ሂስ እንዲያደርግ የታዘዘ ሲሆን ከስራው መታገድም ያሳጋዋል፡፡
አባ ናትናኤል ለምን ታሰሩ?

Monday, October 15, 2012

በጉጂቦረና ሀ/ስብከትሥር የምትገኛው የሻኪሶ ምስራቀ ፀሐይ ቤ/ክ ያለችበት ሁኔታ

gugi borena church
ከፍርዱ ወልደነጎድጓድ
      ይህቺ ቤ/ክ ከተቆረቆረች 70 አመትአስቆጥራለች ታድያ በነዚህ አመታት ውስጥ በእሾህ አጠገብ እንደበቀለች ቁልቋል እየደማች  የከረመች ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ሰሞኑን የአውደ ምህረት ብሎግ በጉጂ ቦረና ሀ/ስብከት ያለበት ሁኔታ በሰፊው ዘግባለች ነገር ግን ያገረ ስብከቱ ችግር መነሻ የሻኪሶ ቅ/ማርያም ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው የሻኪሶ ቅ/ማርያም ሰበካጉባኤ የተመረጠው በ1984ዓ/ም ነው በወቅቱ ሀገረ ስብከቱ የነበረው በሐዋሳ ነው፡፡ ሊቀ ጳጳሱም አቡነ በርተሎሚዮስ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ የሻኪሶ ቅ/ማርያም አስተዳዳሪ የነበሩት አባ ብርሃነ ስላሴ የአሁኑ አቡነ ዲዮስቆሮስ ናቸው እኚህ አባት ከዘዋይ እንደመጡ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ፍቅር ነበራቸው፡፡ ብዙዎችን ከባዕድ አምልኮ መልሰዋል፡፡ በ2004 በየካቲት 4 የተመረቀው ህንፃ ቤተክርስቲያንን መሰረት ያስጀመሩት እሳቸው ነበሩ፡፡ በኃላ ግን እጅግ የሆነ ፈተና ተነሳባቸው፡፡ በማ የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም? በአቡነ በርተሎሚዮስ ተቀምጦ ከአንድም ሶስት ጳጳሳት በሀገረ ስብከቱ ላይ ሲቀያየሩ በኃላም ሀገረ ስብከቱ በሁለት ስራ አስኪያጅ ሲመራም በመጨረሻ በአቡነ ሳዊሮስ የወረደው ሰበካ ጉባኤ ነው ይህ ሰበካ ማን ነው? ማህበረ ቅዱሳን በ1983 በብላቴ ጦር ማሰልጠኛ ተመስርቶ ወደ ተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ላይ መርዙን ሲረጭ ወዲያውኑ ነው የማቅ ህዋስ በሻኪሾ የተገኘው ምክንያቱም የደርግ መንግስት የአሁኑ ሜድሮክ ጎልድ የቀድሞ ለገደንቢ ወርቅ ልማት ድርጅትን ሲከፍት በተለያዩ ፊልድ ቀጥሮ ያመጣቸው ሰራተኞች የማኅበሩ አባል በመሆናቸው ነው፡፡

Tuesday, October 9, 2012

የአቡነ ገብርኤል ማካሮፍ ሽጉጥ ጠፋ


  • ሰርቀሀል ተብሎ የተጠረጠረው ዲ/ን ፍጹም እንዳለ የተባለ አገልጋያቸው እንዲባረር ተደርጓል፡፡

በአቋማቸው ወላዋይነት እና ጠንካራ ነው ብሎ ያመኑበትን ክፍል በመጠጋት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚታወቁት አቡነ ገብርኤል በቤታቸው ደብቀውት የነበረው ማካሮፍ ሽጉጥ ጠፋ፡፡ አጣሪ ኮሚቴ አቋቁመው ነገሩን እንዲጣራ እያደረጉ ነው፡፡ የአጣሪ ኮሚቴው ሊቀመንበር ከሀገረ ስብከተ ስራ አስኪያጅነት ከተባረረ በኃላ አሁን አቡነ ጳውሎስ ካረፉ በኃላ በአባ ገብርኤል ወደ ቦታው የተመለሰው አለም እሸት ነው፡፡ አለም እሸት ከስልጣኑ የተነሳው ከ12 መኪና በላይ የሚሆን ህዝብ ከአዋሳ መጥቶ አቤቱታ ስላቀረበበት እንደሆነ አይዘነጋም፡፡ ከቅዱስነታቸው ዕረፍት በኃላ ግን አለምእሸትን አባ ገብርኤል በማን አለብኝነት መልሰውታል፡፡ 

የሽጉጡን መጥፋት በተመለከተም ምንም እንኳ አለም እሸት ማኅበረ ቅዱሳናዊ የምርመራ ዘዴውን ተጠቅሞ ለማውጣጣት ቢሞክርም ልጁ ግን ባልወሰደድኩት ንብረት እንዴት እጠየቃለሁ በማለቱ አባረውታል፡፡ እውነተኛውን ሌባ ፈልጎ አንደማውጣት ድሀን በመግፋት መፍትሔ ሰጠን የሚል አሰራር የእነ አባ ገብርኤልን እና አለምሸትን አምባገነንነት ያሳያል፡፡

Monday, October 8, 2012

የጉጂ ቦረና ሀረገ ስብከትን ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ሆኖ የሚበጠብጡት ሊቀ ስዩማን ልሳነ ወርቅ ሁንዴ ታሰሩ

lesanework
ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ሆነው ጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከትን በመበጥበጥ የሚታወቁት እና በሁከተኝነታቸው እና በስልጣን ብልግና በህዝቡ ጥያቄ ከስልጣናቸው ቢነሱም በማኅበሩ የልብ ልብ ሰጪነት እንደ እነ ሲያምር ተክለማርያም ማኅተም አላስረክብም ያሉት ሊቀስዩማን ልሳነ ወርቅ ሁንዴ በስም ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥረው ታሰሩ፡፡

መመሪያ በመተላለፍ፣ ህገ ወጥ ስብሰባዎችን በመፍቀድ፣ ለበላይ አካል አልታዘዝም በማለት ከስራ ታግደው የነበሩት እኚሁ ግለሰብ በቅርቡም በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዕረፍት ምክንያት ሀገሪቱ አውጃው የነበረውን ብሔራዊ ሀዘን በመተላለፍ ባንዲራ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረጋቸው አቤቱታ ቀርቦባቸው ከመንግስት አካላት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶዋቸው የነበሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እኚሁ ግለሰብ ከዚህ በፊትም በሰሩት ወንጀል ተከሰው ጥፋተኛ መሆኑ ታምኖበት በሁለት አመት ገደብ ተፈትተው የነበረ ቢሆንም ትዕቢት የተሞላ ልብ የሚያደርገውን አያውቅም እና አሁንም ወንጀል ከመስራት ባለመመለሳቸው በስም ማጥፋት ወንጀል ተከሰው ታስረዋል፡፡