Monday, April 29, 2013

አባ አብርሃም እና ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ ያለውን የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ



(http://awdemihreet.blogspot.com/) በማኅበረ ቅዱሳን አይዞህ ባይነት የአሜሪካውን ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል አላስረክብም ብለው የነበሩት አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ፡፡ ይህ በቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ፊርማ የወጣው እና አድራሻውን ለአባ አብርሃም ያደረገው ደብዳቤ እንዳስታወቀው አባ አብርሃም ሀገረ ስብከቱን በዝውውር ለቀው ከወጡ በኃላ የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት አላስረክብም ማለታቸው ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡


አባ አብርሃም ቤተክርሰቲያን አንዲት መሆንዋን መረዳት ከብዷቸው እና እሳቸውን ለማዘዝ ሙሉ ስልጣን ያለውን ቅዱስ ሲኖዶስ ተጋፍተው ላለፉት ሁለት አመታት የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት አላስረክብም በማለት በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሽፍታ ሠራዊት ማስፈራቸው አስገራሚ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ እኚህ ጉድ አያል     ቅበት የሆኑት ጳጳስ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሳካው እሺ ብሎ በመታዘዝ መሆኑ ከዲቁና እስከ ጵጵስና ድረስ አለመረዳታቸው በብዙዎች ዘንድ የሚያስተዛዝብ ሆኗል፡፡ 

Thursday, April 25, 2013

የቤተ ክህነቱ የሰሞኑ ሁኔታ እና የማኅበረ ቅዱሳን ጫጫታ



 http://awdemihreet.blogspot.com/
ከጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ወዲህ በአሉበት ሁኔታ መቆየት አለመቆየታቸው እያሰጋቸው የመጣው አቶ ተስፋዬ ውብሸት እና አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ ከሥራ ከመሰናበታቸው በፊት ጠቀም ያለ ገንዘብ ለማግኘት እያደረጉ ያለው እንቅስቃሴ ሁሉ እየከሸፈባቻ ሲቸገሩ ያላቸውን ቀሪ የገንዘብ ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚያስደስት እቅድ ይነድፋሉ፡፡ እሱም ለቅዱስ ፓትርያርኩ የውጭ ግንኙነት ኃላፊን ከማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች መካከል መንግስት ሾመልዎ በማለት ማስቀመጥ ነው፡፡
ይህንን እቅዳቸውን ከማኅበሩ አመራር ጋር ከተነጋገሩበት በኋላ በአዲስ አበባ መስተዳድር የሚሰራውን አቶ ታምሩ አበራ የተባለውን ግለሰብ ያጫሉ፡፡ ይህን ግለሰብ ለፓትርያርኩ መንግስት መደበልዎ ብሎ ማቅረብ እና ከዚያም በመንግስት ስም ተከልሎ የማኅበረ ቅዱሳንን ፍላጎት በመንግስት ስም ለማስፈጸም  አስፈላጊውን ሁሉ አድርገው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ያቀርባሉ፡፡ ይህ አካሄድ እውነት እንዳልሆነ የተረዱት የቤተክርስቲያን ልጆችም ሁኔታውን በትኩረት በመከታተል ሀሳቡን የሚያከሽፍ እንቅስቃሴ ይጀምራሉ፡፡ እንቅስቃሴው ውጤት አግኝቶም መንግስት የመደበውም ሆነ የሚመድበው ሰው እንደሌለ ለቅዱስ ፓትርያርኩ በአቶ አባይ ጸሀዬ በኩል ያስታውቃል፡፡ 

በዚህ የተናደዱት እነ ተስፋዬ እና እስክንድር ከማኅበረ ቅዱሳን አንጃ ብሎግ ከሆነችው ሐራ ተዋህዶ ጋር በመቀናጀት የስም ማጥፋት ሥራውን ጀመሩ፡፡
ሀራ ተዋህዶ ሲቆጫት ሲያንገበግባት፣ የሚያደርጋትን ሲያሳጣትና ማኅበረ ቅዱሳን የፈለገው ነገር አልሳካ ሲላት ያረረውንም የመረረውንም፣ ያልተባለውንም ነገር ሁሉ “ሰበር” ደንገር እያለች እንደ ታላላቅ ወንድሞችዋ እነ ደጀ ሰላም መዘባረቅ ጀምራለች፡፡

ለአንባቢዎቻችን



ብሎጋችን ለተወሰነ ጊዜ ዝምታን መርጣ ቆይታ ነበር፡፡ በዝምታው  ወቅት በርካታ አንባቢዎች በኢሜልና በአስተያየት ለሰጣችሁን ምክርና ማበረታቻ እያመሰገንን አሁን ግን እንደገና በቤተክህነት አካባቢ ያሉ ዘገባዎችን የምንቀጥል መሆኑን እንገልጣለን፡፡