Thursday, May 9, 2013

አድብቶ ነዳፊው ዳንኤል ክብረት የአውስትራሊያ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለመሆን እየሞከረ ነው


(http://awdemihreet.blogspot.com/)ባለሁለት ሚስቱ እና ፈቱ ዳንኤል ክብረት ያፈረሰ ሰው የሚገባውን ማርገጃ አድማቂነት እምቢኝ ብሎ ባልተማረው ትምህርትና በማይመልሰው ተሰጥኦ “ዲያቆን” ተብሎ ለእርሱ ብጤ ጨዋ ማኅበርተኞቹ “ሊቅ” ሆኖ እና “ሊቅ” ተሰኝቶ ከእውነተኛ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትና አባቶች ሸሽቶ እንደ እርሱ በሁለት ሀሳብ በገንዘብ እና በዝሙት ከሚያነክሱ አባ አብርሃም እና አባ ኤዎስጣጢዎስን ከመሰሉ ግለሰቦች ተጠግቶ በአድርባይ ብዕሩ እነዚህን የጉድ ሙዳዮች እየሸላለመ የነበረበት ሁኔታ አልበቃ ብሎት አሁን ደግሞ የአውስትራሊያ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ለመሆን ደፋ ቀና እያለ ነው፡፡
ማህበርዋን በዋና ጸሐፊነት በመራባቸው ረጅም አመታት ከየዋኃን አባላት ከሚሰበሰበው ገንዘብ እና ከቤተክርስቲያን የድርሻውን ወስዶ በሲኤምሲ ሁለት ቤቶችን የሰራው እና እና ከጊፍት ሪል እስቴት አንድ ቤት በመግዛት የሦስት ቤቶች ባለቤት የሆነው ዳንኤል ክብረት አሁን ደግሞ ሌላ ሦስት ቤት የሚሰራበትን ገንዘብ ከቤተክርስቲያን ለመዝረፍ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህንን ለማሳካት በሲአይኤ ወኪልነት በሚታወቀው እና እንደ እባብ ልስልስ ገላውን እያሳየ የተንኮል ድሩን በሚያደራው እና በቅርቡ የማኅበሩን አንጃ በሀሳብ የተቀላቀለው  በአቶ ባያብል አማላጅነት ጉዳዩ መስመር የያዘለት የመሰለው ዳንኤል ለቅርብ ወዳጆቹ የአውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የመሆኑ ጉዳይ ያለቀለት መሆኑን ሲናገር ተሰምቷል፡፡ በዚህም ተቋርጦ የነበረው የዳንኤል እና የባያብል ፍቅር የታደሰ መስሏል፡፡

Thursday, May 2, 2013

‹‹ጎልጎታ››፡- ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር . . .!!!


በፍቅር ለይኩን፡፡

ለዚህ መጣጥፌ የመረጥኩት የእውቁ ሠዓሊና ባለ ቅኔ የገብረ ክርስቶስ ደስታን ‹‹ጎልጎታ››በሚል ርዕስ የተጠበበትን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የሥነ ስቅለት አስደናቂና ዘመን አይሽሬ (classical) ሥራውን ነው፡፡ የዚህን ገጣሚና ሰዓሊ፣ እጅግ ተወዳጅና ተደናቂው የሆነውን ‹‹የጎልጎታን››ስነ ስቅለት፣ ፍቅርን ተጠበበትን ድንቅ ሥራውን ፅንሰትና ውልደት ታሪክ በአጭሩ ላውጋችኹ፡፡

ገጣሚና ሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ ስሙ ጎልቶ ከሚጠቀሱ የስነ ጥበብ ሰዎች ዘንድ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ እውቅና ታላቅ ሰው ነው፡፡ ገ/ክርስቶስ ዘመናዊ የስዕል ሙያን በአገር ውስጥና በአውሮፓ ከተማረ በኋላ በአገሩ እምብዛም አልቆየም ነበር፡፡ በአገራችን በተከሰተው የ1966 አብዮትናከነደደው የነውጥና የለውጥ እሳት የተነሣ እንደ ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ወገኖቹ የእርሱም ዕጣ ፈንታ ስደት ሆኖ ነበር፡፡
ገ/ክርስቶስ በትምህርትና በስደት ሕይወት ለረጅም ዓመታት በባሕረ ማዶ በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ አውሮፓውያኑ ወይም በአጠቃላይ ነጮች ለአፍሪካውያንና ለጥቁር ሕዝቦች ያላቸው ዘረኝነት፣ ንቀትና ጥላቻ በእጅጉ ያብሰለስለውና እረፍት ይነሳው ነበር፡፡

ከምንም በላይ ደግሞ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምድር ተምሳሌት፣ በዓለማችን ታሪክ ታይቶና፣ ተሰምቶ በማይታወቅ ጀግንነትና ወኔ ኢትዮጵያውያን፣ አባቶቹ ወራሪውን የኢጣሊያንን ቅኝ ገዢ ኃይል በዓድዋ ጦር ግንባር በአኩሪ ጀግንነት አሳፍረው የመለሱ ኃያላን መሆናቸውን አሳምሮ ለሚያውቀው ገ/ክርስቶስ ይህ የአውሮፓውኑ ትምክህትና ንቀት ከመገረምም በላይ ሆኖበት ነበር፡፡