Sunday, June 17, 2012

ጉባኤ ከለባት!

click here to read in PDF
     ከ ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

(ወደ ዋና ርዕሴ ከመዝለቄ በፊት በተለምዶ እንዲሁም በስማ በለው ስለሚተረጎሙ ቃላትና ስለሚነገሩ የቃላት ፍቺዎች ከዚህም አልፎ ቃላቶቹ ታሪካዊና ስነ መለኮታዊ መሰረተ ሃሳባቸው ለቀው ሌላ ትርጓሜና አንድምታ ይዘው ስለሚገኙ አንዳንድ የቤተ-ክርስቲያን ቋንቋዎች በጥቂቱ እንመለከታለን። በተጨማሪም በቤተ-ክርስቲያናችን ታሪክ ጉባኤ ከለባት (የውሾች ጉባኤ) በመባል ስለሚታወቀው የመለካውያን ጉባኤ የርዕሳችን ሰፊው ክፍል የሚይዝ ይሆናል። በስተመጨረሻም አጫጭርና ጠንካራ ማሳሰቢያዎችን ተካተዋል። መልካም ንባብ!)
ወቅቱ ከምን ጊዜ በላይ የሃይማኖት መሪዎች በመንፈሳዊ ስልጣን ስም ያሻቸውን ሲያደርጉና ሲፈጽሙ እንዲሁም ኢ-ክርስቲያናዊ በሆነ የስነ- ምግባር ጉድለት ተዘፍቀው ድሃውን ሲበድሉና ጻዲቁን ሲያጎሳቁሉ ማየቱ የዕለተ ዕለት ተግባራቸው ከሆነ ረጅም ዘመን አስቆጥሯል። ስለሆነም ጸሐፊው እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ስርዓትና አስተምህሮ መሰረት መንፈሳዊ ስልጣን በተመለከተ የአንዳንድ ቃላቶች ፍቺ በማብራራት ለመንደርደር ተገዷል። ይኸውም ሲኖዶስ ማለት ስርወ ቃሉ ከግሪክ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም “ጉባኤ” ማለት ነው። 1 እዚህ ላይ በዋናነት የቃሉ ትርጓሜ ማስፈር ያስፈለገበት ምክንያትም ብዙሐኑ የቤተ-ክርስቲያናችን ተከታዮች ምእመናን ከየዋህነት የተነሳ ስለ ቃሉ ያላቸው የተሳሳተ ትርጓሜ ለማስተካከልና ትክክለኛ የቃሉ ፍቺና መንፈሱም ለማስጨበጥ ታስቦ ነው።
 ü ሲኖዶስ ማለት የማይሳሳት፣ የማይከሰስ፣ የማይጨበጥና የማይዳሰስ፣ ስህተት የማያውቃቸው የልዩ ፍጥረታት ስብስብ ማለት አይደለም። ምንም እንኳን በሐዋሪያት ዘመን ሲኖዶስ ማለት ፈቃዳቸው/ሁለ መናቸው ለመንፈስ ቅዱስ ያስገዙ ቅዱሳን ስብስብ ማለት ቢሆንም በውሳኔዎቻቸውም ፍፁማን ቢሆኑ በቤተ-ክርስቲያን ታሪክ ግን ይህን ሐቅ የሚያደበዝዙ ክስተቶች ቆጥረን ለመዝለቅም አይቻለንም።
ü ሲኖዶስ ማለት ክንፍ ያላቸው የሰው ወፎች ስብስብ ማለትም አይደለም። ሲኖዶስ በመጽሐፍ የሰፈረው አምላካዊ ቃል የሚጠብቅና የሚያስጠብቅ ክፍል ነው።
ü ሲኖዶስ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሽሮ በምትኩ ሌላ የሚያበጃጅ የተለየ ስልጣን ያለው አካልም አይደለም። ሲኖዶስ ማለት ከሁሉም በላይ ከሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ በታች ነው።
ü እውነተኛ ሲኖዶስ መሰረቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጣለ ነው። ተሰብሳቢዎቹም በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ጉባኤቸውን ያካሂዳሉ ሲባል አንድ ልብና አንድ ሃሳብ ሆነው በአንድ ቃል የሚያጸድቁትም ሆነ የሚሽሩትን ለእግዚአብሔር ክብር መጽሐፍ ቅዱስን ያማከለ ሲሆን ብቻ ነው!!
በሐዋሪያት ዘመን ሲኖዶስ የእግዚአብሔርን ክብር ልባቸውና መንፈሳቸው ለተሰበረ ሕዝብ ሲገልጥ እንዲሁም ምእመናን ከስህተት ትምህርት ሲጠብቅና ቤተ-ክርስቲያንን ለመልካም ነገር ሲያንጽ፣ ሲያዘጋጅ በአንጻሩ ደግሞ በበተያዩ ዘመናት የተነሱ ሃያላን ነገስታት ጥም ለማርካትና ፓለቲካዊ አጀንዳ አስፈጻሚዎች በመሆንም “ሲኖዶስ” ሲያጠፋ፣ ሲቆርጥ፣ ሲፈልጥ፣ ሲያሳድድ፣ ሲፈጅ፣ ሲያርድና ቅዱሳንን በወጡበት ሲያስቀር የመጣና ያለ ፈሪሃ እግዚአብሔር የማያውቃቸው መንፈሳዊ ካባ ያጠለቁ የስመ መንፈሳዊያን
ስብስብም እንደሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል። እርግጥ ይህን ዓይነቱ እውነት ከሰንበተ ክርስቲያን (የእሁድ ተሳላሚ) ልብ አይገኝም ታሪክን ለማወቅ ከሰባኪ ሳይሆን ከጉባኤ ነውና።
በመግቢያዬ እንደገለጽኩት አሁን ደግሞ ስለ ጉባኤ ከለባት ጥንተ ነገር በግርድፉ ልተርክላችሁ። “ጉባኤ ከለባት” የሚለው ሃይለ ቃል ከግእዝ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን በቁሙ ሲተረጎም “የውሾች ጉባኤ” ማለት ነው። ልብ ይበሉ! የሃይለ ቃሉ ተናጋሪዎች ሊቃነ ጳጳሳት ሲሆኑ ተቀባዮችም እንዲሁ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ዘመኑ 451 እ.ኤ.አ. ሲሆን በወቅቱ መርቅያን የተባለ ንጉስ ሮምን ይገዛበት የነበረ ዘመን ነው። ታድያ በዚህ ዘመን ልዩ/እንግዳ ነገር የተከሰተበት ዘመን አልነበረም። ልክ እንደ ቀድሞ ዘመናት አለመግባባትን እንዲሁ በተመሳሳይ ተስተናግዷል። የተለየ/እንግዳ ነገር ተከሰተ ቢባል እንኳ ንትርኩና ሽኩቻው ሳይሆን ንትርኩ ያስከተለው ጦስ ቀድሞ ከተካሄዱ ጉባኤያት ለየት ያደርገዋል። በዚህ ጉባኤ 650 ኤጲስ ቆጶሳት የተገኙ ሲሆን ጉባኤውም የተሰየመው ኬልቄዶን በተባለች ከተማ ነበር።
1 የካርዲናሎች ጉባኤም ሆነ ፖፑ አይሳሳትም፣ አይከሰስም ከመጽሐፍ ቅዱስም ይልቅ ፖፑ የበላይ ባለ ስልጣን ነው የሚለው ትምህርት የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ትምህርት ሳይሆን የሮማ ካቶሊክ ፕሮፖጋንዳ ነው። በዚህ ጉባኤ ምንም እንኳን ቀድሞ ሲብላላ የነበረው የአውጣኪ ትምህርት ያወገዘ ቢሆንም በዋናነት ጉባኤው ጎልቶ የሚታወቅበት ግን ኢየሱስን በማስመልከት ከወደ ሮም አከባቢ ቀዳማዊ ልዮን የተባለው የሮማ ሊቀ ጳጳሳት በመልዕክተኞች በኩል የተላከው ዱብዳ ደብዳቤ ነው። ደብዳቤው ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ጉባኤ ተዘርግቶበት የማይውቅ ርዕሰ ጉዳይ ያዘለ ከመሆኑ በተጨማሪ በደብዳቤ ውስጥ የተገለጸውን ትምህርት ጉባኤው ያለ አንዳች ማቅማማት አሜን ብሎ እንዲቀበል የሚያስገድድም ነበር።
ከዚህም የተነሳ ጉባኤው ከፍተኛ የሆነ ግጭትና ብጥብጥ ከማስነሳቱ በተጨማሪ ቀደም ብሎ ለሦስት ጊዜት ጉባኤ ዘርግተው አንድ ልብና አንድ ቃልም ሆነው ሌላው ሲያወግዙ፣ ሲለዩና በግዞት ሲያኖሩ የመጡ ሊቃነ ጳጳሳት እርስ በርሳቸው ተወጋግዘውና ተፋጅተው ያለ ፍሬ መለያየታቸው ጉባኤው በቤተ-ክርስቲያን ታሪክ የተለየ ያደርገዋል።
2 ይህ የኬልቄዶን ጉባኤ በመባል የሚታወቀው 4ኛ ጉባኤ በቤተ-ክርስቲያናችን (በኦርቶዶክ አብያተ ክርስቲያናት) ዘንድ ተቀባይነት የሌለውና የማይቆጠርም ሲሆን ጉባኤ ከለባት የሚለውን ስያሜ ሊያገኝ የቻለውም ከዚህ የተነሳ ነው።
ውግዘት በቤተ-ክርስቲያን ታሪክና በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ:
ማውገዝ ከህብረት መለየት ማግለል ማስናበት ማለት ሲሆን ቃሉ ራሱ ከፍተኛ ስነ መለኮታዊ እሴት ያለው ነው። ቀደም ስንል እንደተመለከትነው የቤተ-ክርስቲያን መሪዎች ከመላ ጎደል ሐዋሪያዊ አስተምህሮዋን ለመጠበቅ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያፈነገጡ ትምህርቶችን አሁንም በከፊል መጽሐፍ ቅዱስ ማዕከል ያደረገ እርምጃዎች እየወሰዱ መጥተዋል። ይህ የአባቶቻችን መጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ያደረገ አካሄድ መካከል አንዱና አንኳር ነጥብ የተመለከትን እንደሆነ በተለይ ቀድመው የተካሄዱትን ሦስቱ ጉባኤት ያሳይዋቸው
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስነ ምግባር ተጠቃሽ ነው። በእነዚህ ጉባኤት የተላለፉ ውግዘቶች ራሱን የቻለ የጎላ ስነ መለኮታዊ ስህተቶች ቢኖሩትም የአንድም ተከራካሪ ግለሰብ መጽሐፍ ቅዱሳዊና መሰረታዊ መብቱ ግን አልከለከሉም (አልገደቡም ማለት ግን አይደለም)።
እነዚህ የኒቅያ፣ የቁስጥንጥንያና የኤፌሶን ጉባኤ በመባል የሚታወቁ ጉባኤት (ጉባኤዎቹ በመዘርጋት ረገድ ራሱ የቻለ ፖለቲካዊ አንድምታ ቢኖረውም) ከየቅጣጫው የተገኙ የቤተ-ክርስቲያን መሪዎች በተገኙበት ተወጋዦቹ ምንም መጨረሻቸው ውግዘት ቢሆንም “መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ይህንኑ ነው ሲሉ” በጉባኤ ፊት ቀርበው እንደ መረዳታቸው ስፋትና ጥልቀት ከቅድሳት መፃህፍትን እያጣቀሱ ሽንጣቸውን ገትረው ሞግተው ተሟግተው እምነታቸው በይፋ በመግለጽ ነበር። በእነዚህ ጉባኤት ታሪክ አንድም የቤተ-ክርስቲያን ሊቅ በሌለበት እንዲህ ታስተምራለህ ተብሎ በስሚ ስሚ ወይንም ደግሞ ባላንጣዎችሁ በሚቀርቡት ክስ የተነሳ የተወገዘ የለም። በኢትዮጵያ መዲና በአዲስ አበባ ከተማ መቀመጫው ያደረገ ሲኖዶስ ታሪካዊ ስህተት እየፈጸመ ነው ሲባልም ይህን እውነት መሰረት ያደረገ ነው።
ሌላው ውግዘትን በተመለክተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ማለታችን አይቀርም። መጽሐፍ ቅዱስ መሰረት የሌለው ክርስቲያናዊ ትምህርት የለምና ጥያቄው መነሳቱ ተገቢ ነው። አሁንም መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ሰው ከሕብረት/ከጉባኤ ስለ መለየት በተመለከተ ግልጽ የሆነ ትምህርት ነው ያለው። ከጌታ ትምህርቶች መካከል የተነሳን እንደሆነም “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም። ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።” (ማቴ. 18÷ 15) ልብ ይበሉ! የተዘረጉ ጉባኤት (በተለይ ቀደምቶቹ) ጉባኤዎቹ በከፍተኛ ወጪ ከመዘርጋቸው በፊት የተለየ ትምህርት እያሰራጩ ነው ተብለው ስማቸው የተሰማ የቤተ-ክርስቲያን መሪዎችና መምህራን ሊቃውንት አስቀድሞ በወዳጆቻቸውና በቅርበት በሚያውቋቸው ግለሰቦች አማካኝነት በኩል “ተው! እንዲህማ አይደለም እየሳትክ ነው” ተብለው ሲያበቁ “የለም! ትክክል ነኝ!” ሲሉ ትምህርታቸውን እየገፉበት በመምጣታቸው ነበር ጉባኤ ራሱ መዘርጋት ያስፈለገበት ምክንያት። ውግዘቶቹም የተላለፉት ተወጋዦቹ “ብዙሐኑ በተስማሙበትና በሚስማሙበት ትምህርት ሳይሆን ከዚህ ቀደም ባልኩትና አሁንም ደግሜ በዚህ ጉባኤ ፊት ባረጋገጥኩት ቃሌ ጸንቻለሁ! የምለውጠው ቃልም ሆነ የምቀይረው ሃሳብ የለኝም ” በማለታቸው ነበር። ታድያ ለመጽሐፍ ቅዱስ ቃል (ማቴ. 18÷ 15) ጆሮ ያልሰጠና ጆሮም የሌለው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ የሰዎች ሰብዓዊ መብት ቢጥስ ምን ይደንቃል? አበው የኬልቀዶን ጉባኤን ጉባኤ ከለባት/የውሾች ስብሰባ ሲሉ የሰየሙትን ዱብዳ እንግዲህ ይህን ይመስላል። በተመሳሳይ አሁንም ቢሆን የበልዓምን የስህተት መንገድ ተከትሎ የሚደረገውን ማንኛውም ዓይነት ትልቅም ትንሽም ሕገ ወጥ ጉባኤ ጉባኤ ከለባት/የውሾች ጉባኤ ይባላል። ፈጽሞም ተሰሚነት/ተቀባይነት የለውም ለወደፊቱም ተቀባይነት አይኖረውምም!!
2 እስከዚህ ዘመን ድረስ አንዲት ሃይማኖት አንዲት ቤተ-ክርስቲያን እንደነበረች ሲሆን ስምዋም ሐዋሪያዊት ቤተ-ክርስቲያን በመባል ትታወቅ እንደነበረች የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።
3 ከፊል የተላለፉ ውግዘቶች ተወጋዦቹ (አንዳንዶቹ) ከነበራቸው ምጡቅና ረቂቅ እውቀት፣ የክህነትና የቤተ-ክርስቲያን ስልጣን፣ ከአንደበተ ርቱዑነታቸውና ከመንፈሳዊ ብስለታቸውም የተነሳ ቀደም ብለው ካፈራቻቸው ተከታዮች/ደጋፊዎች፣ በእኩያዋቻቸውም ከነበራቸው አክብሮት ተዳምሮ ገና በቀላሉ ሊፈቱ ይችሉ የነበሩ ችግሮች ገና ለገና ባይስማሙስ ተብሎ በፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት የተፈጸሙም አሉ ተብሎ ስለሚታመን ነው።
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የእምነት ተከታዮች በሙሉ:
“አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል” (1ኛ ጢሞ. 6፣ 11) ለምን? ቢሉ የሀገሬ ሰው የዝንጀሮ መንጋ ቢከተሉት ገደል ያለው እንዳይደርስብህ እንለዋለን።
ለመገናኛ ብዙሐን:
ጉዳዩ አባ ጳውሎስን የሚያንኮታኩትና የሚያዳክም ፍሬ ነገር ቢኖረው ኖሮ ይሄኔ ስንሻው ተገኘ እየተባለ በተገኘችው ትንሽ ቀዳዳ እያሰፋና እንደ ላስኪትም እየወጠረ የማያፏጭ ፍጥረት አይኖርም ነበር። ለመሆኑ “ፍትሕ ተጓደለ ድሃ ተበደለ! ፍትሕ እንሻለን! ፍትሕ! ፍትሕ! ዳኝነት!” እየተባለ ብዙ የሚጮክለት ምን ዓይነቱ ፍትሕ ይሆን? ሰው ሳይደመጥ፣ ቀርቦም የእምነትም ሆነ የክህደት ቃሉን ሳይሰጥ፣ ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን ተጥሶ የአንድ ወገን ድምጽ ብቻ ተሰምቶ ለዛውም የከሳሽ አቤቱታ ሰው ባልዋለበት ጥፋተኛ ነህ
ተብሎ ሲገፋ ለአላስፈላጊ የህይወት ውጣ ውረድም ሲዳረግ እንዴት አስቻላችሁ? እንግዲህ ወደድንም ጠላንም እነዚህ ወገኖችም እኩል እንደሌላው የፍትህ ያለህ! ጭኸት የሚሻቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው። ስለ ሌላው እምነት የፍትህ ጉዳይ ሲጮክ ስለ እነዚህም ሽፋን ተሰጥቶት “የፍትህ ያለህ! የዳኛ ያለህ!” ተብሎ መጮክ በተገባ ነበር ዳሩ ግን ፖለቲካዊ ትርፉ ሲሰላ ሚዛን የማይደፋ ሆኖ በመገኘቱ ይቅር ርዕሰ ዓንቀጽ ተሰርቶ ሊጮክላቸው ቀርቶ ጽሑፎቻችን እንኳን ላለማስተናገድ ያለምንም ምክንያት በሮቻችሁ ዘግታችኋል።
ጠቢቡ “አባቱን የሚረግም እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ” ሲል እንዲህ ያለ ነገር ገጥሞት ይሆን?
ራሱን ስደተኛ ሲል ለሚጠራ ሲኖዶስ:
 እናንተ የስደታችን ምክንያት “ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን ተጣሰ፣ ፈረሰ!” ነው ባዮችስ ወዴት ናችሁ? ምን አላችሁ? ምን ነው? ባልገባችሁ፣ በማይገባችሁ፣ በማያገባችሁና በማይመለከታችሁ ጉዳይ ከበሮ ስትደልቁና ስታሳብቁ በየአደባባዩም ተጽፎ የተሰጣችሁን ስታነበንቡና ይህን ይበሉልን ተብላችሁ አፋችሁ እንደ ተከፈተ መቃብር ስትከፍቱ፣ መስቀል ተሸክማችሁ ጥላም ዘርግታችሁ አላህ ወአክበር ስትሉና ስታስብሉ ያላሳፈራችሁ በእምነት የሚመስሏችሁ፣ በገዛ ልጆቻችሁና ወንድሞቻችሁ በጠራራ ጸሐይ በአደባባይ ፍትህ ሲጓደልባቸው ሲበደሉና አለ አገባብ ሲገፉ ዝም ያላችሁ? ወይስ መጽሐፍ “መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና” (ማቴ 6፥21) እንዲል ልባችሁ በሰዎች እጅ ሆነችና አይታችሁ እንዳላያችሁ ሰምታችሁም እንዳልሰማችሁ በመሆን የድሃውን ጭኸት እንዳትጮኹ ቆልፈው አስቀመጧችሁ?
ለማንኛውም መልሰን እስክንገናኝ ድረስ በዚች አጭር ግጥም ልለያችሁ።
ኧረ ምን ዓይነት ነው የሃይማኖት ዱብዳ:
የባሪያቱን አስወድዶ የጭዋይቱን ልጅ ሚያስከዳ።
ኧረ ምን ይሻላል ጳጳሳቱ አበዱ:
መስቀል አንጠልጥለው ሲያበቁ ክርስቶስን ከነ ወንጌሉ የካዱ።
ኧረ ሰዎቹ (ሊቃነ ጳጳሳቱ) ሞኞች ናቸው:
እንዳባዘኑ በጎች ጋጣ እንደ ጠፋባቸው:
በአባቱ ቀኝ የተቀመጠውን ሊቀ ካህን ማጣታቸው።
የዝንጀሮ መንጋ ቢከተሉት ገደል
 እስቲ ጨምሩበት በበደል ላይ በደል!
ከዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
yetdgnayalehe@gmail.com
Unated States of__america

8 comments:

  1. ሙሌ ጹሁፍህ ሁሌም ይነፍቀኛል። እይታህ ያስቀናል። በርታልን። ያንተን ጽሁፎች ማንበብ የምንናፍቅ ወገኖች እንዳለን ሁሌ ሁሌም ስምህን ሲሰሙ አጋንንት እንዳለበት የሚጮሁና የሚሳደቡ እንዳሉ አትዘንጋ። ሰይጣን ሁሌም ባህሪውን አይቀይርምና በእመነት በርትተህ ከመዋጋት ወደ ኋላ አትበል። እንወድሃለን በጣም።

    ReplyDelete
    Replies
    1. mulu are u sure that u are full? why u leave ur country? maferiya

      Delete
  2. ዲያቆን ሙሉጌታ የምትጽፋቸው ነገሮች እውነትነት አላቸው ግን የቃላት አመራረጥ ላይ ብትጠነቀቅ ምን ይመስልሃል?ስድብ የሚመስሉ ማዋረጃ የሚመስሉ ቃላትን ለምን ትጠቀማለህ?የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስን አባባል እባክህ ብታጤነው ምን ይመስልሃል?
    እባክህ ከላይ የጻፍኳቸው ያወጣኋቸው ዓረፍተ ነገሮች ይከብዳሉለሚለው ካቶሊኮችን ሊያስቆጣ ይችላል ሰው ሁሉ እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲመጣ ነው እንጂ ያንጊዜ ፕሮፖጋንዳ ከሆነ የአሁኖቹ ካቶሊኮች ይህንን ባይቀበሉት ሲያነቡት ያዝናሉ ኦርቶዶክስ ማወደስ ብቻ ይመስልብሃል::ሌላው በውጭ ላሉ አባቶች የሲኖዶስ ክፍሎች የጻፍከውም ይከብዳል ስለዚህ በአክብሮት ቃላትና በፍቅር ብትጽፋቸው ምን ይመስልሃል::እነርሱ እንዲህ ካልሆነ ካላልክ በቀር በደረስብህ ነገር ሳይሆን መጻፍ ያለብህ ሰዎችን አስተምረህ ለመመለስና ለእውነት እንዲቆሙ ማድረግ ቢሆንስ?
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete
  3. ወንድማችን እግዚአብሔር አምላክ አሁንም ጥበቡን ይግልጥልህ። እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የራሱ የሆኑት ሰዎች አሉት። ሰው ግን አያውቃቸውም እርሱ ራሱ ያውቃቸዋልና።ጌታ አምላካችም በዚህ ምድር በነበረበት ዘመን በእርሱ ማመንና መከተል ያቃታቸው ሊቀ ካህናትና ካህናት ነበሩ። ለሞትም አሳልፈው የሰጡትም እነዚሁ ሰዎች ናቸው። ዛሬም በዘመናችን ለቤተ ክርስቲያን ችግር እየፈጠሩ ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት ካህናቶች ናቸው። ታርክ እራሱን በዘመናት እየደገመ ነው። ለቤተ ክርስቲያን ልጆች መከፋፈል የእነዚሁ አባቶች ችግር ነው። ለራስ ምኞትና ፍላጎት የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ በመፈለጋቸው ነው።ለመሆኑ ከውግዘት ምን ይገኛል? ምንም ሰውን ከጥፋቱ መክሮ አስተምሮ መመለስ ግን በሰማያት ዋጋ ያሰጣል እንጅ። ዳሩ ግን ልብ እንደ ፈርዖን ከደነደነ ምን ይደረጋል። እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው ከማለት የበለጠ ነገር የለም።እውነት ከመናግር ዝም አለማለት ነው።ሃይማኖታችንንና ሀገራችን እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቃት።

    ReplyDelete
  4. በአግባቡ ለተወገዙ ሰዎች ያለአግባብ መቆርቆር የአጋንንት ወዳጅ ከመኾን አይዘልም፤ በእግዚአብሔር ሥራ የማይደሰቱ፣ ሰይጣንና ግብረ አበሮቹን የማያወግዙ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ያመፁ ናቸውና፡፡ በሃይማኖትና በምግባር ከተወገዙ ሰዎች መራቅ ይገባል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ወንድሞች ሆይ፣ ከእኛ እንደተቀበለው ወግ ሳይኾን ያለሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን” በማለት በግልጽ ተናግሯል፡፡ (2ተሰ.3÷6)፡፡ ይህ ቃል ቁርጥ ትእዛዝ እንጂ ምክር አይደለም፤ “እናዛችኋለን” ይላልና፡፡ ከትእዛዝም ጥብቅ ትእዛዝ መኾኑን ደግሞ “በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም” የሚለው ሐረግ ምስክር ነው፡፡ ይህ የሐዋርያው የብቻው ትእዛዝ ሳይኾን በዘመኑና ከእርሱ በኋላ የሚነሡ ቅዱሳን አበው ሁሉ ትእዛዝ ነው፡፡ “እናዛችኋለን” ይላል እንጂ “አዛችኋለኹ” አይልምና፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. በአግባቡ ማለት ምን ማለት ነው? ለመሆኑ የተከሰስኩበትን ክስ አላውቀውም ጠርቶ ያናገረኝም ሰው የለም። አባቶቼ እናንተ አድል ስጡኝና አናግሩኝ ሲባሉ ዝምበል በለው አናናግረውም ማህበረ ቅዱሳን ያጠናውን አምኖ ማውገዝ ነው ማለት ነው አግባብ። ህሊና ካለህ ነገሩን በቅጡ መርምር አሊያ ግን ዝምብሎ የራስን ስሜት ኣዳመጡ የፈለጉትን ማውራት ተገቢ እመስለኝም። ያ ወንድም ያ ሥርዓት መሄዱን በምን አወክ ከሳቾቹ ስላሉ? ወይስ በምን? ብቸኛው ማወቂያ ዘዴ ጠርቶ መመርመር ነው። ያን ደግሞ አባቶችን አላደረጉም። ስለዚህ ከነሱ ሀሳብ ጋር መንፈስቅዱስ ፈጽሞ ሊስማማ አይችልም። ፈጽሞ እነርሱ ግን ስራቸውን በአግባቡ ስላልሰሩ ደም እንደሚፈለግባቸው አትዘንጋ።

      Delete