Monday, April 30, 2012

ኤፍሬም እሸቴ: ብትስማማ ነው እንጅ የሚያስደምመው ባለመስማማትህ ምን ይደንቃል? ክፍል 2

click here to read in PDF
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
 በጽሑፉ ክፍል አንድ ንባብ ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ምእመናን "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት: አንዲት ጥምቀት" ሲል በጻፈላቸው መልእክት በማንሳት አቶ ኤፍሬም ከግንዛቤ ማነስ እንዲሁም ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት እጥረት የተነሳ በደመነፍስ ያኮላሸውን የክርስትና አስተምህሮ የዓውዱን ታሪካዊ ስዋስዋዊና ስነ ጽሑፋዊ መልኩ ጠብቆ የመልእክቱን መንፈስ መጨበጣችንና ማግኘታችን የሚታወስ ነው::

ወደ ዋና ርእሰ ጉዳዬ ከማለፌ በፊት ግን በአንዳንዶች ዘንድ የተፈጠረውን የተሳሳተ ግምት ለማጥራት ያክል አንዳንድ ነጥቦች ለማለት እወዳለሁ። በተለይ ኤፍሬም እሸቴ "አቶ" በማለቴ ለተበሳጩ አንባቢዎቼና ለኤፍሬም የኤፍሬምን “የድቁና/ቅስና” ማዕረገ ክህነት በተመለከተ ትንሽ ልበል:: በመሰረቱ እኔ ኤፍሬም በዲቁናም ሆነ በቅስና ማዕረግ ስትጠራ ሰምቼ አላውቅም:: አባሪ ተደርጎ የተላከልኝና ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኘሁት "አደባባይ" የሚል ስያሜ ያለው ድረ ገጽም "ኤፍሬም እሸቴ" እንጂ ሌላ ተጨማሪም ሆነ ተደራቢ ቀሚስ አላየሁም አላነበኩምም:: በጻፍከው ጽሑፍም የተቀመጠው ስምህ ነው ስለዚህ "አቶ" ብዬ መጥራቴ የሀገሬን ባህልና ወግ መጠበቄ እንጂ በሌላ መልኩ መወሰድ የለበትም ስል በትህትና እጠይቃለሁ::

ላያገለግሉበት ብቻ ሳይሆን ከየት እንዳገኙት በግልጽ የማይታወቅ የቅስናም ሆነ የድቁና ማዕረግ ይዘው በቅስና፣ በድቁናና በሌሎች የቤ/ያን መጠሪያ ቀሚሶች ስር ተሸሽገው የሚኖሩ እንደ'ነ ስንታየሁ አባተ፣ዳንኤል ክብረት፣ ብርሃኑ ጎበና፣ ዶ/ር መስፍን ተገኝ፣ ሙሉጌታ ሃይለማርያም፣ ግርማ መታፈሪያ፣ ባያብል ሙላቱ፣ ሳምሶንና ሌሎች የማህበረ ቅዱሳን አባላት በቤ/ያን የክህነት ማዕረግ የሚጠሩ ዕጣን ሲሸተን ያፍነናል፤ አስሜ ትነሳብኛለች፤የዕጣን አላርጅክ ነኝ፤ የአጥንት ካንሰር አለብኝ፤ በማለት ሳይቀድሱ ሳያስቀድሱ የሚንቀሳቀሱ “ዲቁናቸውን” እና “ቅስናቸውን” በጋዜጣ ብቻ የምናነበው ግለሰቦች ግን “ማዕረጋቸው” እንደተጠበቀ ነው::

Sunday, April 29, 2012

አማኝ እንጂ አክራሪ አትሁን።


 Click here to read in PDF                                                      
                                                  ከብርሃን ጸጋዬ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ
አማኝ እንጂ አክራሪ አትሁን። አማኝ ያመነውን የሚኖር በፍቅርም የሚማርክ ጀግና ነው። አክራሪ ግን ጥቂት እውቀቱን ከዱላ ጋር ለማስከበር የሚሞክር ነው። የከረረ ነገር መበጠሱ አይቀርም። የከረረ ነገር ሲከርም ሲበጠስም ስጋት ነው። አክራሪነት የአለሙ ልከኛ ሰው እኔ ነኝ። ከኔ በቀር በአለም ላይ ማንም መኖር የለበትም። ከምስራቅ ስገላበጥ ምእራብ እደርሳለሁ። ከሰሜን ስራመድ ባንድ ስንዝር ደቡብን እረግጣለሁ። ስለዚህ ከኔ ውጪ ማንም መኖር የለበትም ብሎ እንደማሰብ ነው። የአክራሪነት ምንጩ አለማወቅ ነው። አክራሪ ሰው በከሳሽነት መንፈስ የተያዘ እንጂ የሚያሳየው ማራኪ ስራ የሌለው ነው። ጥቂት እውቀቱ ከሰፋች የካደ ስለሚመስለው ላለማወቅ ተጠንቅቆ የሚጓዝ ነው። እርሱ ካለበት ገድጓድ ውጪ አለም ያለ የማይመስለው የለመድኩት ሰይጣን ይሻላል ብሎ ከመቃብር ጋር በኪዳን የሚኖር ተስፋ የሌለው ሳይሞት መኖር ያቆመ ሳይቀበር እውቀቱን የጨረሰ ሰው ነው። የአክራሪነት ወንድሙ አለማወቅ ነው። እኔ ያወቁት ብቻ ትክክል እኔ ከሰማሁት ውጪ ያለው ያተነገረ ነው አለም በኔ ጓዳ በኩል ነው የምታልፈው እኔ ያልገባኝ ነገር እንዴት ልክ ይሆናል? ብሎ የሚያስብ ነው። መሀይም ማለት ያልተማረ ሳይሆን መማር የማይፈልግ ነው። የሰይጣን ትልቁ ግዛቱ ድንቁርና ነው። ሰዎች የህሊናን አይናቸውን ካላሳወረ በቀር አያመልኩትምእና ህሊናቸውን ያጨልማል ማወቅ እንደጨረሰ ሰው የምትኖር ከሆነ መኖርህ ምክንያት አልባ መሆኑን አስብ። ባለህበት ጉድጓድ መጠን ሁሉንም ነገር ካየሀው ሁሉም ነገር ይጠብብሀል። ትንሽ እውቀትም የስጋን ሀይልን ይሻልና እውቀትህን አሟላው

Saturday, April 28, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችና አባላት ጭፍን እይታ

Click here to read in PDF

መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ ሲል መንፈሳዊ እይታችን ሚዛናዊ በሆነና እውነት ባለው ነገር ላይ እንዲመሠረት ይመክረናል (1ተሰ. 5፡20-21)። ይህን ሐዋርያዊ ቃል መመሪያው ያላደረገ ሰው ግን የሚያምነውና የሚኖረው በጭፍን ነው። በማኅበረ ቅዱሳን ዘንድ ወንጌል ስሙ ብቻ እንጂ ግብሩ ፈጽሞ የማይታወቅ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን ማለት ደግሞ የእነርሱ ማኅበር ይመስላቸዋል። እነርሱ በጥላቻ ተሞልተው “መናፍቅ” የሚሉት ማንኛውንም የማኅበሩ አባል ያልሆነውን ሰው ነው። “እገሌ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነው። እንዴት መናፍቅ ትሉታላችሁ” ተብለው ሲጠየቁ “ማኅበራችን አያውቀውም ስለዚህ መናፍቅ ነው” የሚል ነው መልሳቸው።

ለእነርሱ የምንፍቅና መመዘኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማ አይደለም፤ የማኅበራቸው አባል መሆን አለመሆን ነው። መናፍቅ የሚለው ስም ትርጉሙ ቢገባቸው፣ በሀሳቡ መንፈስ ቅዱስ ከተስማማ ሰውዬውን ከመንግስተ ሰማያት የሚያስወጣ ቃል ነው። ስለዚህ ይህን የማለት ስልጣን ያለው አንድ የፅዋ ማህበር ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን ናት። ቤተክርስቲያንም ሸክሙ ስለሚሰማት ዝም ብላ መናፍቅ አትልም። የነገሩን መነሻና መድረሻ መዝና፣ ባለጉዳዩን አናግራ፣ አስተምራ፣ ጥፋት ቢገኝበት ንስሀ እንዲገባ ነግራ፣ አልመለስ ካለና በሀሳቡ ከጸና ብቻ ነው መናፍቅ የምትለው። ምክንያቱም የአንድ ሰው ነፍስ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ጠንቅቃ ታውቃለች እና ነው። ማህበረ ቅዱሳን ግን በሆነ ባልሆነው፣ መሽቶ እስኪነጋ ሰውን መናፍቅ ለማለት ብቻ የሚደክም፣ ሰውየው ቢመለስ እንኳ መመለሱን የማይፈልግ፣ በጭፍን ጥላቻ የተሞሉና ጥላቻቸውን የሃይማኖት ካባ የሚያለብሱ ተራ አስተሳሰብ የዋጣቸው አመራሮችና እነርሱን በጭፍንንነትና በቅንንነት አምነው የሚከተሉ አባለት ያሉት ማኅበር ነው።

Friday, April 27, 2012

ኤፍሬም እሸቴ: ብትስማማ ነው እንጂ የሚያስደምመው ባለመስማማትህ ምን ይደንቃል?

Click here to read in PDF
 በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

ጥብቅ ማሳሰቢያ: ጽሑፉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመደገፍ የተጻፈ ጽሑፍ አይደለም:: ጽሑፉ ኤፍሬም እሽቴ የተባለው አንድ "የማህበረ ቅዱሳን" የስራ አመራር አባል ግለሰብ “ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም” ሲል ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ በጻፈው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምህሮ የማይወክል ዝርው ይዘት ያለው ጥሬ ጽሑፍ አስቸኳይ እርምት እንዲደረግበትና በክርስትና ስም በአንባቢያን ላይ የፈጠረውን ብዥታ ግምት ውስጥ በማስገባት የተጣራ ምስል ለመስጠት ኩልል ቅልብጭ ባለ መልኩ የተዘጀ ጽሑፍ ነው::

"ማህበረ ቅዱሳን" የቤተ-ክርስቲያን የቆሎ ት/ቤት ያልቀመሰ፣ የዜማ፣ የቅኔ፣ የመጽህፍት ትርጓሜያት፣ የቅዳሴ፣ የአቡሻክር … ወዘተ ባህር ያልዳሰሰ የቤተ-ክርስቲያን ጥንተ ታሪክ ያልመረመረ፣ ጥምጥም ያለው ጥቁር ጎረምሳ፣ ሆኖ እያለ እምነበሃን የማያውቅ ዲያቆን፣ አሀዱ አብን የማያውቅ ቄስ፣ አአትብ ገጽየን የማያውቅ ክርስቲያን፣ የሴቶችና የወንዶችን መግቢያ በር በቅጡ የማያውቅ፣ ሱቅ ከፍቶ ቄስ ቀጥሮና አቁሞ ስለ ነገደ ቄስ የሆነ የሚመስለው ጠባቂ ነኝ የሚል አጽራረ ቤተ-ክርስቲያን ጿሚ መሳይ አጋሰስ፣ የማይሰግድ አሰጋጅ፣ ለማስተማር የማይበቃ አቃቤ መቃብር ባለ ዲግሪ፣ አስራት የማይከፍል በዝባዥና አስከፋይ፣ የማይቀድስ አስቀዳሽ፣ ያልተለወጠ ለዋጭ አስመሳይ የጎበዝ ጥርቅም ማኅበር ነው ሲባልኮ ተራ ውንጀላ ወይንም ደግሞ ክስ ሳይሆን ምስክርነታችን ጭብጥ ላይ የተመሰረተ እውነት ነው::

ይህች ጦማር የቀድሞ የማህበሩ አውራ ቂስ ኤፍሬም እሸቴ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም በፓርላማቸው ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እግረ መንገዳቸውን ያነሱትን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አክራሪነትበክርስቲያኑ በኩል ይወክልልናልብለው የጠቀሱትን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ እኔም እንደ አንድ አባል የማምንበት አቀርባለኹ። ማኅበሩ በኃላፊዎቹ በኩል የሚሰጠው መልስ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሁለት አሥር ዓመታት አባል የሆንኩበት እና መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ማኅበር አክራሪአለመሆኑን በግሌ ለመመስከር እገደዳለኹ።” ሲል ባልዋለበትና ባላለፈበት የቅዱሳት መጻህፍት ቃል ዓውዱን ባላገናዘበ አኳኃን ምክርን ለማጨለም ባደረገው ሙከራ የተፋለሰውን የክርስትና አስተምሮና በማን አለብኝነት መንፈስ የፈጠረውን እጅግ ግዙፍ የሆነ ስህተት ኩልል ባለ መልኩ ታስቃኘናለች::

መልካም ንባብ! 

Wednesday, April 25, 2012

የ“ማህበረ ቅዱሳን” ዲግሪና የካንጋሮ እጅ አንድ ነው!

Click here to read in PDF
/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Email: yetdgnayalehe@gmail.com
ጥብቅ ማሳሰቢያ:
በቅድሚያ ጽሑፉን ለምታነቡ ወንዶችንም ሴቶችም የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ሰላም ይሁን! እያልኩ በጽሑፉ ከተካተቱ እውነታዎችና ከጽሑፉ ከፊል ይዘት የተነሳ ጽሑፉ ከጸሐፊው መልእክት ዓላማና ከመልእክቱም ግብ ውጭ ሌላ አንድምታ እንዳይዝና እንዳይሰጠው ይህን ጥብቅ የሆነ ወንድማዊ ማስጠንቀቂያ ለመጻፍ ግድ ብለዋል:: ጸሐፊው በስራ ክቡርነት ያምናሉ: በየትኛውም የስራ መስክ ተሰማርተው ከራሳቸው አልፈው ለቤተሰብና ለሀገር የሚተርፉት ዜጎችንም የላቀ ክብር አላቸው:: ክብር ስለማያውቅ: ሰላሙን አጥቶ በሰላማዊያን ዜጎች የህይወት ጎዳና ላይ እየቆመ እሾክና አሜከላ ስለሚዘራ: እርግማን ቀለብ ስለሆነለት: የራሱ ያለሆነውን በማጭበርበርና በማደናገር የራሱ በማድረግ የሚታወቀው እልል ያለ ህጋዊ ሽፍታ ማህበርና አባላቶቹ ብቻ ላይ ያነጣጠረ እውነታ መሆኑን ተገንዝባችሁ ጽሑፍን በቅንነት ታነቡት ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ::

 ምንም ዛሬ ደግሞ እንደገና ትኩስ ሆኖ ማወያያ ቢሆንም "ማህበረ ቅዱሳን" ከተመታ: ቅስሙ ከተሰበረና ተናዳፊ አንደበቱ ከተመነገለ ከራርመዋል:: ቢሆንም ግን የተመታ: ሞትን የማይቀርለት እባብ በቀላሉ አይገላገልምና ዛሬም ወዲያ ወዲህ በማለት መወራጨቱ አልቀረም:: ይህ በዚህ ሲባል በዚያ: ወድያ ሲባል ወዲህ: ከዚያ ሲታይ ከዚህ እየሆነና እያለ አልያዝ አልጨበጥ በማለት በመሸበት ቁጥር መልኩንና አድራሻውን እየለዋወጠ በሚፈበርካቸውና በሚለቃቸው የማደናገሪያ ወሬዎች በጥቂቶች ዘንድ ብዥታ እየፈጠረ በመምጣቱ ስለራሱ በራሱ ሰዎችና ዓላማውን በሚጋሩ አጨብጫቢዎች በኩል በእጅ አዙር ስለ ማህበሩና የማህበሩ አባላት መልካምነትና ብቃት ነጠላ ዜማ ለቆ ስሙልኝ! አልሰማችሁም ወይ! እያለ ይገኛል:: ከእነዚህ መካከልም የማህበሩ አባላት የትምህርት ደረጃና ብቃት የሚገልጽ መፈክር ማለት “የተማሩ ናቸው!” እየተባለ ማስተጋባት ይገኝበታል::

ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ - ጠ/ሚኒስትሩ ፣ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት ትስማማለህ አትስማማም?

Click here to read in PDF
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቻናል 3 ላይ የሚተላለፍና “እስማማለሁ፣ አልስማማም” የተሰኘ አንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አለ። በዚህ ፕሮግራም ለእድለኛ ከ1 ሳንቲም ጀምሮ እስከ 15 ሺህ ብር ድረስ ሽልማት አለ። በጨዋታው ህግ መሰረት ተጋባዡ እንግዳ ሽልማቶቹ ከተቀመጡባቸው ሳጥኖች መካከል አንዱን በመጀመሪያ ይመርጥና ይቀመጣል። ከዚያ ሌሎቹን ሳጥኖች በየተራ እየጠራ በውስጣቸው ያለው የገንዘብ መጠን ተከፍቶ ይታያል። በየጣልቃው ባንከሩ (the banker) እንዲስማማ የሆነ ብር ያቅርብለታል። እንግዳው አልስማማም ካለ ጨዋታው ይቀጥላል፤ እስማማለሁ ካለ ግን ጨዋታው እዚያ ላይ ያቆምና ባንከሩ የሰጠውን ብር ይወስዳል። ኤፍሬም እሸቴ /ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማምሲል በድረ ገጹ ላይ ከሰሞኑ ፖስት ያደረገው ጽሑፍ ርእስ ይህን የመዝናኛ ፕሮግራም አስታወሰኛና ነው በዚህ የጀመርሁት እንጂ የዚህ ጽሁፍ አላማ ስለእስማማለሁ አልስማማም ለመናገር አይደለም። 

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት ተከትሎ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት መልስ ውስጥ ስለማህበረ ቅዱሳን በተናገሩት ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛል፡፡ የማህበረ ቅዱሳን አክራሪ አካሄድ ሰለባ የሆኑ ብዙዎች የማህበሩ ማንነት ይፋ እየወጣ መሆኑ ደስ ያሰኛቸው ሲሆን፣ በማህበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊዎች ዘንድ ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ብዙም አልተወደደም። ተቃውሟቸውን በየድረገጹ መግለጽ ቀጥለዋል። ለምሳሌ አንድ አድርገን ድረገጽ ሚያዝያ 10 ቀን “ይህ የግሌ አስተያየት ነው ፤ የማንም አቋም አይደለም” በሚል ርእስ ፖስት ያደረገውን፣ እንዲሁም በዚህ ጽሁፍ የምንመለከተውን የኤፍሬም እሸቴን ጽሁፎች መጥቀስ ይቻላል።

Monday, April 23, 2012

ገደል አፋፍ ላይ የቆመ ጎረምሳ ማኀበርን ለማዳን

          Click here to read in PDF                                                          በበከመምህረትከ
       በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማህበራት መካከል አንዱ ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ማህበሩ ከተመሰረተ ሁለት አስርተ አመታትን ጨርሶ እነሆ ጉርምስናውን ተያይዞታል፡፡ ይሁንና ማህበሩ በተለይ ባለፉት ጥቂት አመታት ባልሆነ መስመር ሄዶ ሄዶ ከገደል አፋፍ ላይ ተንገራግጮ ቆሟል፡፡ ወደኋላ ተመልሶ ያለበትን ችግር በጥልቀት መርምሮ የሚሄድበት መስመር ካላስተካከለና በጀመረው መንገድ ከቀጠል ባጭር ጊዜ ውስጥ ወደገደል መግባቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ እንደውጭ ተመልካች ገደል ሲገባ ዝም ብሎ ከማየት እንደ አንድ የቤተክርስቲያን አባል (እና የቀድሞ የማህበሩ አባል) እንዲሁም በፊት በፊት በሰራቸው መልካም ስራዎች አንጻር ችግሮቹን ፈቶ ወደ ቀደመ ክብሩ ይመለስ ዘንድ የመፍትሄ ሃሳቤን ለማቅረብ ወደድኩ፡፡ ማህበሩ 20 አመት ልደቱን ሲያከብር አገር ሰላም ነው ብሎ ሻማ ለኩሶ ኬኩን በመቁረስ ብቻ ሳይሆን ያለበትን አደጋ አስተውሎ ራሱን ይመረምርና መስመሩን ያስተካክል ዘንድ ይጠቅመዋል፡፡ ያን ካደረገ ደሞ ገደል ከመግባት ይተርፍና ካለበት የጉርምስና ጠባይና እድሜ ተሻግሮ ወደ ጉልምስናና እር እንዲደርስ ይረዳዋል፡፡
  
       አንዳንዶች ማህበሩ በስራው የቅዱሳን ስም አርክሷል፤ ለቤተክርሰቲያኒቱ እዳ ሆኗል፤ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ በዝቷልና መዘጋት አለበት የሚል አቋም ሲያራምዱ ይስተዋላል፡፡ እኔ ግን ምንም እንኳን በጥፋት ጎዳና ቢሄድም ተስተካክሎ ለቤተክርስቲያን እንዲያገልግል መደረግ አለበት እንጂ ፈጽሞ ሊዘጋ አይገባውም የሚል አቋም አለኝ፡፡ የማህበሩ አመራር አባላትም መንግሰትና ፓትሪያርኩ ሊዘጉን ነው ሊያጠፉን ነው የሚል ፍራቻ እንዳላቸው በውስጥ አዋቂዎች ተነግሯል፡፡ ይሁንና እንዲቀጥልም ሆነ እንዲዘጋም የሚያደርገው ራሱ ማህበሩ ነው እንጂ ፓትሪያርኩ ወይም መንግሰት አይደለም፡፡ የመቀጠል ዋስትናው ደሞ ያለበትን ችግር በመፍታት የተበላሸ አካሄዱን ማስተካከል ብቻ ነው፡፡

Friday, April 20, 2012

«አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት» የሚለው አባባል “ሕገ መንግሥት” ላይ ብቻ ሳይሆን በክርስትናም ላይ የተቃጣ የጸረ- ክርስቶሱ ሃሳዌ መሲህ አጀንዳ ነው!

                                         በዲ/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
       (ዲ/ን ሙሉጌታ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ተነባቢነት የነበረውና በብዙ እውነተኛ የሰነድ ማስረጃዎች የተደገፈው ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሠይጣን የሚለው መጽሐፍ ደራሲ ነው)

ለመግባባት ያክል የምዕራቡ ዓለም የዕድገትና የስልጣኔ ምስጢር በማውሳት ሐተታዬን ልጀምር:: ለብዙዎቻችን ግልጽ እንደሆነ የምዕራቡ አለም ፖለቲካ ከተቀረው የዓለማችን ክፍል የሕዝብ አስተዳደር የተለየና የላቀ የሚያደርገው ቢኖር የፖለቲካ መሪዎች አስተዋይነትና አርቆ አሳቢነት ለመሆኑ  አያከራክርም:: ለምሳሌ ያክል "የዲሞክራሲ" ተምሳሌት የሆነችውን ሃያልዋ ሀገረ አሜሪካ የወሰድን እንደሆን በተለይ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በየትኛውም መስክ ያለ ተቃናቃኝ በኢኮኖሚውም ሆነ በፖለቲካው መድረክ የበላይነትዋን  እንደያዘች የመዝለቅዋ ምስጢር ስልጣን ላይ የሚወጡትም ሆነ በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉትን የፖለቲካ መሪዎች ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ውጤት ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም:: ይህ ማለት ዲሞክራትም ይሁን የሪፐብሊካን ፓርቲ አቀንቃኝ ሀገራቸው አሜሪካ በዋናነት ልትከተለው በሚገባት ፖሊሲ ላይ የጎላ ልዩነት ቢኖራቸውም የአሜሪካን ሉዓላዊነት እንዲሁም የአሜሪካ ሕዝብ ጥቅም የመጣን እንደሆነ ግን አንዱን ከሌላውን መለየት ፈጽሞ አይቻለንም:: ሀገራዊ ጥቅም በተመለከተ ዲሞክራቱም ሪፖብሊካኑም አሜሪካዊ ነው!! እናማ ከየትም አቅጣ ቢመጡ ጽሐፉን ሲያነቡ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በሰከነ መንፈስና በተረጋገ ልብ እንደሚያነቡት ተስፋ አደርጋለሁ:: 

በያዝነው ሳምንት ከጥቂት ቀናቶች በፊት መሆኑ ነው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በፓርላማቸው ተገኝተው ካደረግዋቸው ንግግሮችና ከተወካዮቹም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡ ካነሱዋቸው ነጥቦች መካከል ሃይማኖትን በማስመልከት መንግስታዊ ትንታኔአቸውና አቋማቸውን ለፓርላማው ግልጽ አድርገዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ማህበረ ቅዱሳን" ከአልቃይዳ ጋር በማመሳሰልም ገልጸውታል:: እንግዲህ ይህን አገላለጽ/ንግግር ያዳመጠ ሰው አልቃይዳ ማለት ደግሞ ማን ነው? ምንስ ማለት ነው? ብሎ የሚጠይቅ አዋቂ ሊኖር እንደማይችል አምናለሁ::