Saturday, March 15, 2014

ፍርድ ቤት ችሎት ላይ አይደለም የተቀመጠው “አሜን!” የማይለው፡፡

ከዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
(መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ወደ አውደ ምህረት ከተመለሰ በኃላ እርር ያሉት የማቅ ብሎጎች እሱን “መናፍቅ” ለማለት የሚያስችለን ነው ብለው ያመኑበትን ስድ ስድብ እየደረደሩ ይውጣልን ይጥፋልን የሚያሰኝ ዛር ነግሶባቸው እየተክለፈለፉ ይገኛሉ፡፡ መቸም ለዲያቢሎስ ጭንቀቱ የሚድነው መብዛቱ እና የሱ መንግስት ጠላቶች የመንግስቱን ሀሳብ ሲያፈርሱ ማየት ነው፡፡ ተከታዮቹም በጌታቸው መንግስት ላይ የተቃውሞ ሀሳብ ያለውን ክርስቲያን ሁሉ ማሳደድን እምቢኝ ብለው አያውቁም፡፡
ለማኅበረ ቅዱሳን መሪዎች የዲያቢሎስን አሰራር ለማፍረስ በተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ አምኖ የዲያቢሎስን አሰራር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ ክርስቲያን ሁሉ ጠላታቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው ሰሞኑን በሁሉም ብሎጎቻቸው እንደገና መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ላይ መዝመት የጀመሩት፡፡ የወላይታ ሶዶው ጉባኤ እንዳይካሄድ ያደረጉት ጥረት ሁሉ  ከሽፎ ጉባኤው ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት መካሄዱ ቢያቃጥላቸው “ስህተት” ብለው ያገኙትን ነገር ነቅሰው አወጡ፡፡ ታዲያ በማቅ መመዘኛ ትልቁ ምንፍቅና በ10 ደቂቃ 20 ጊዜ አሜን ማለት ሆኖ ተገኘ፡፡ ከታወሩ አይቀር እንዲህ ነው እንጂ!!!
ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል አሜን ለምን ይባላል አሜን ማለት የሊቅነት ማነስ ውጤት ነው የሚለውን የአንድ አድርገን ዘገባ እንዲህ ይተቻል፡፡ መልካም ንባብ!! )
ነዋሪነታቸው ጀርመን ፍራንክፈርት  የሆነ አንድ በአካባቢው የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ምእመን ባሳለፍነው ሳምንት በኢሜይል አድራሻዬ “ … እርስዎስ ምን ይላሉ?” ሲሉ ነበር የጠየቁኝ። አያይዘው ከላኩልኝ ሊንክ በተጨማሪ ለይተው አውጥተው አስተያየቴን የጠየቁበት ጽሑፍ እንደሚከተለው ይነበባል።
ሊቃውንቱ ሲሰብኩ ሰው ወደ ውስጡ እንዲመለከትና በጥሞና እና በአስተውሎ የእግዚአብሔር ቃል እንዲያደምጥ ሲያደርጉ ነበር እኛ የምናውቀው፤ አሁን አሁን በአስር ደቂቃ ጊዜ ውስጥ 20 ጊዜ በላይ ‹‹አሜን›› የሚያስብለውን ሆነ ‹‹አሜን›› በማያስብለው ምዕመኑን ጮኻሂ የማድረግ አዝማሚያ እየታየ ነው፤ መናፍቃን ቤት የሚገኝው ጩኽት እኛ ቤትም ለመግባት ደጃፍ ላይ እያኮበኮበ ይገኛል፡፡[http://www.andadirgen.org/2014/02/blog-ost_5495.html]
እኚህ ወንድም አያይዘው በላክሉኝ መልዕክት የእግዚአብሔር መንጋ ለመበተን የሌሊት እንቅልፍ የማያውቀው ራሱንማኅበረ ቅዱሳንበማለት በሚጠራው ቡድን የሚዘወርአንድ አድርገንየተባለ መካነ ድር ነበርና ከዚህ የሽፍታ ድረ ገጽ ያነበቡትን ጽሑፍ ተንተርሰው የተፈጠረባቸው ጥያቄ ሲጨመቅ ፍሬ ነገሩ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።
የመጀመሪያ ጥያቄአቸው በደረቁ በስብከት ጊዜ አሜን ማለት ይቻላል አይቻልም?” አክሎውም የሚቻል ከሆነስ በአንድ ስብከት ውስጥ ስንት ጊዜ ነው አሜን ማለት የሚቻለው?” ባነበቡት እንግዳ ትምህርት የተደናገጡ ስለሆነም ለመሆኑ አሜን ማለት ምን ማለት ነው? አሜን የአማርኛ/የግዕዝ ቋንቋ ነው ወይስ ከሌላ ቋንቋ የተገኘ ቃል?” በማለት በአሜን “… ዙሪያ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ትምህርት ያካፍሉን ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ። እግዚአብሔር አገልግሎትዎን ይባርክ።ስም አለው።!