Monday, December 31, 2012

ካህናቶቻችሁን አትበድሉ: ካህን ማለት የእድር ዕቃ ማለት አይደለምና!

Read in PDF: kahematocacehun
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
መግቢያ:
የተራበ እንጅ የጠገበ ሰው ባያሳዝንም የሀገሬ ሰው "ከተራበ ይልቅ የጠገበ …" እንዲል ሰው ሲባል ሆዱ ሞልቶ/በልቶ ካደረ መጀመሪያ ጸብ የሚጀምረው ከፈጠሪው ጋር ለመሆኑ ስለሚበላና ስለሚጠጣ ጨርሶ ሃሳብ ለሌለው/የማይገባው ሰው ነገሩን ማውሳት በራሱ ቀባሪን የማርዳት ያክል ነው የሚሆነው። አንድ ሰው ስለሚላው፣ ስለሚጠጣውና ስለሚያርፍበት መጠሊያ ስፍራም የሚያሳስበው ነገር ከሌለ ባለቤት ከሌለው ከሜዳ አህያ የሚለየው በተፈጥሮ ብቻ ይሆናል። አንድ እውነት አለ ይኸውም: አንድ ከድህነት ወለል በታች ይኖር የነበረ ሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀድሞ በነበረው ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ ይኖር ሳለ ያላየውን ሀብትና ንብረት ማፍራት ሲጀምር የቀድሞ ህይወቱን የዘነጋ እንደሆነ በቀላሉ የነበረውን ታላቅህን የማክበር ባህሪ፣ በሰዎች መካከል የነበረውን ፍቅርንና ይታይበት የነበረውን ትህትና በአጠቃላይ ፈሪሐ እግዚአብሔርን አጥቶ ሣር ቅጠሉ ሁላ "ምን አልክ አንተ? ..." እያለ ግዑዙን አካል ሳይቀር እያገላመጠ ከራሱ ጥላ እስከመጣላት ድረስ መሄዱ የማይቀር ነው።
ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ ዘንዳ በዛሬው ዕለት ላካፍላችሁ ወደ ወደድኩት ወደ ቅድመ ፍሬ ነገሬ/መልዕክት ሳልፍ ለጽሑፌ መነሻ የሆነኝን ነጥብ እንደሚከተለው በአጭሩ ላስቀምጥ። በዕረፍት እንዲሁም በአንዳንድ ጉዳዮች ምክንያት በአሜሪካ ጥቂት የማይባሉ ክፍለ ግዛቶች ለመዘዋወር ዕድሉ ገጥሞኝ በማደርጋቸው ጉብኝቶች ሁሉ በሄድኩበት ክፍለ ግዛት እናት ቤተ ክርስቲያኔን ጎራ ሳልል የተመለስኩበት ዕለት የለም። በጉብኝቴ ወቅትም በርካታ መጠሪያ ያላቸው አብያተ ክርስትያናት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት አገልጋዮችና ደቀ መዛሙርት እንዲሁም የምእመናን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ችያለሁ። ታድያ በእነዚህ ሁሉ ቀናት ለመታዘብ እንደቻልኩ በሀገር ቤት የምትገኘውን "ቤተ ክርስትያን" የራሱ መልክና ገጽታ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተዘፍቃ እንደምትገኝ ሁሉ በውጭው ዓለም በተለይ በሰሜን አሜሪካ የምትገኘው "ጉባኤም" እንዲሁ ራሱ በቻለ ሌላ ገጽታ ያለው በቀላሉ የማይታለፍና ምናልባትም አሉ በማለት ልንዘረዝራቸው የምንችላቸው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮች ሁሉ እንደ ምንጭ ሊወሰድ የሚችል ትርጉሙ የጠፋበት "የቤተ ክርስቲያን" ምስረታ፣ በአገልጋዮች ካህናትና በምእመናን መካከል ያለውን መራራ ግኑኝነት እንደው ካህን እንደ ምጻተኛ፣ የእድር ዕቃ ያክልም ክብር የሌለውና በአንጻሩ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ያላቸው ባለሀብቶች በገንዘባቸው ብዛት፣ በቀድሞ መንግሥት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በቀድሞ መጠሪያቸውና ማዕረጋቸው፣ በአስኳላው ሚዛን የሚደፉ ግለሰቦችም እንዲሁ ነን/አለን በሚሉት ሁሉ ፍጥጥ ባለ መልኩ እንደፈለጉ የሚሆኑበትን አሳዛኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁኔታ አንስተን በአጭሩ እንወያያለን።  

Friday, December 28, 2012

ቤተክርስቲያንና የገባችበት አጣብቂኝ

Read in PDF:Erke

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በታሪክዋ የተለያየ ፈተናዎች ገጥመዋት የሚያውቁ ቢሆንም እንደ አሁኑ አይነት ግን የተለየ መልክ ያለው አደጋ ገጥሟት አያውቅም። የቤተክርስቲያን አባቶች ቤተክርስቲያኒቱ ከገባችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ መውሰድ የሚገባቸው ጥበብ የተሞላበት እርምጃን ሲወስዱ እየታዩ አይደለም። በዙሪያዋ ተሰብስበው የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሱ ያሉ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ማኅበራትም ችግሩ የሚጋጋልበትን መንገድ በመፈልግ ነገሮችን ከማራገብ በተሻለ እያደረጉት የሚገኝ ገምቢ እንቅስቃሴ የለም።
የሁለቱም ሲኖዶስ አባላት ከአንዳንድ አስተዋይ አባቶች በስተቀር ለእርቁ ተገቢውን ትኩረት እየሰጡ አይደለም። የዜና ማሰራጫዎችም “ጎሽ እንኳን አልተስማማችሁ” ከሚል የዘለለ ገምቢ ሚና ሲጫወቱ አይታዩም። በሁሉም ነገር የራሱን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈጸም ከመሯሯጥ የዘለለ በእውነት ለቤተክርስያኒቱ አንድነት በቅንነት ተገቢ ሚና የሚጫወት አለ ለማለት በማያስደፍር ሁኔታ ነገሮች ሲጦዙ እየተመለከትን ነው። በአዲስ አበባው ሲኖዶስ በኩል ከመንፈስ ቅዱስ ሀሳብ ይልቅ የቁጥር ስሌት አንገብጋቢ ሁኖ ይታያል። በአሜሪካው ሲኖዶስ በኩልም ወደ እርቅ የማያደርሱ እርምጃዎች በአንዳንድ ጳጳሳት አማካኝነት እየተወሰደ ይገኛል። በቅርቡ ኤርትራ ሄደው የመንግስትን ተቃዋሚዎች ባርከው የተመለሱት ጳጳስ እንቅስቃሴም ይብዛም ይነስም በእርቁ ላይ ጠባሳ ማሳደሩ አይቀርም። በዚህኛው ሲኖዶስ በኩልም እርቅ እየተወራ በምርጫ ጉዳይ ጊዜ ማጥፋቱ በእርቁ ላይ የተደቀነ ስጋት ነው።

Saturday, December 22, 2012

ራሱን እንደ ግብጹ ሙስሊም ብራዘርሁድ የሚቆጠረው ማኅበረ ቅዱሳን የብጥብጥ አዋጅ አወጀ

Read in PDF: muslim brotherhood

ምርጫውን በተመለከተ የነገሮች አካሄድ እንደፈለገው ያልሆነለት ማኅበረ ቅዱሳን ተስፋ የቆረጠ በሚመስል ስሜት ህዝቡ ይፋ ተቃውሞ እንዲያሰማ ጠየቀ፡፡ በአንድ አድርገን ብሎጉ በኩል የ”ግልጽ የአካል ተቃውሞ” ጥሪ ያቀረበው ማህበሩ አባላቱ ብላቴ ላይ የሰለጠኑበት ወታደራዊ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ለማድረግ ጊዜው እየደረሰ መሆኑን ፍንጭ የሚሰጥ ጥሪ ነው ተብሎለታል፡፡ “በተግባር ተቃውሞዋችንን እንግለጽ” በሚል ርዕስ የወጣው ጽኁፍ አላማው የማኅበሩን ኦሪታዊ ደጋፊዎች አዲሱን ኪዳን በማያውቀው ማንነታቸው ለአመጽ እና ለብጥብጥ ማነሳሳት መሆኑ ታውቋል፡፡
አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ስልጣናቸው እንዲመለሱ እንደማይፈልጉ እና ይልቁንም እርቁን እሳቸው መጥተው በማረፊያ ቤት በሚቆዩበት አሰራር ብቻ እንደፈታ እንደሚፈልጉ በአሜሪካ ሬዲዩ ላይ በዘወርዋራ መንገድ የገለጡት የማኅበሩ ዋና ሰዎች እና የሴት ነገር የማይሆንላቸው ዳንኤል ክስረት እና አባይነህ ዋሼ ማኅበሩ የአዲስ አበባውን ሲኖዶስ ተቆጣጥሮ የሚፈልገውን ነገር የማድረግ ህልሞ እንደሚፈጸም ቢያምኑም ሳይሆንላቸው ቀርቷል፡

Tuesday, December 18, 2012

ጽንስ የሚያጨናግፍ ወረተኛ ምላስ!

Read in PDF: Sense


/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
የሰው ልጅ በባህሪው ንጹሕ ፍጥረት ለመሆኑ ምንም አያጠያይቅም። ከልደት በኋላ ህይወት የማይገኝበት ኃይማኖት ጨምሮ በተለያዩ ውጫዊ ተጽዕኖዎች ራሱ "እኔ" ሲል የሚገልፀው/በሚቀርጸው ማንነት ግን ስብዕናው ከእውነት ይልቅ ሁለመናው ለሐሰት/ለስህተት እጅግ ቅርበት ያለውና በእንግዳ ነፋስ ለመወሰድም ጊዜ የማይፈጅበት ፈጣን ፍጥረት ለመሆኑ አንባቢ ይህን ጽሑፍ በሚያነቡበት ቅጽበት ለአፍታ ቆም ብለው የገዛ ራስዎትን ህይወት ቢመረምሩ ነገሩ በቀላሉ ሊያረጋግጡት የሚችሉት ሐቅ ነው። "የሐሜተኛ ሰው ቃል እንደ ጣፋጭ ምግብ ደስ እያሸኘ እስከ ውስጥ ሰውነት ይወርዳል" እንዲል።
ውሸትና በውሸት የሚፈጸሙት ወንጀሎች፣ እንዲሁም ውሸት በቁሙ ከአንድ ግለሰብ/ዜጋ ህይወት አልፎ በቤተሰብና በሀገር ደረጃ የሚያደርሰውና/የሚያስከትለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት አንስተን ተወያይተናል። በዛሬ ዕለት የመወያያ ርዕሳችንም በተመሳሳይ ሚድያና የሚድያ ሰዎች የተበላሽች፣ ሰላምና አንድነት የራቀባት በአንጻሩ ትርምስ ሁከትና የእርስ በርስ ጦርነት የማይለይባት ሀገርና ዓላማ የለሽ፣ ነህዘላል፣ ቀቢጸ ተስፋ ከዚህም አልፎ ወንድሙን አጋድሞ አንገቱን ከመቀንጠስ የማይመለስ በደም የሰከረና ደም የተጠማ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ትውልድ በመፍጠርና በማፍራት ረገድ ሚድያ እያበረከተው ያለና የሚድያ ሰዎች የሚያበረክትቱን የጎላ አስተዋጽኦ/ድርሻ በመጠኑ በመዳሰስ በተለይ በያዝነው ዓመት የእምነት ተቋሞችን ወቅታዊ እንቅስቃሴዎችና የውስጥ ሃይማኖታዊ አሰራሮችን በማነጣጠር ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸውን የሚያመዝኑ ሥራዎችን በመስራት ስም እያተረፈ የሚገኘው "ኢሳት" በመባል የሚታወቀው "የዜና" ማሰራጫ ማዕከል ሥራዎች መካከል የኢ////ያን ወቅታዊሰጥገባ በተመለከተ በዚህ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ያሰራጨውን መሰረተ ቢስ ውንጀላ የሚያጠነጥን ይሆናል። ሙሉ የሐተታውን ይዘት ለማዳመጥ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ሊያዳምጡት ይችላሉ http://ethsat.com/video/?tubepress_video=HU2rYkmS3-c&tubepress_page=1
የራስህ ያልሆነ፣ ያልተገባህ ረብና የግል ጥቅምም ለማስጠበቅ/ለማግበስበስ፣ ከመቃብር የማያልፍ ጠፊ ሀብተ ንብረት ለመሰብሰብ ሲባልም ከምንም በላይ ደግሞ ቅንና የዋህ ልብ በቀላሉ ማዋለል ይቻል ዘንድ ጠማማ/ዋሾ አንደበት የጎላ ሚና ይጫወታል። በሰለጠኑ የዓለማችን ምዕራቡ ክፍል እንዲህ ዓይነቱን የሥራ መስክ ማለት መረጃዎችን ከማዛባት ጎን ለጎን የፈጠራ ወሬዎችን በመንዛት ረገድ በሚኒስትር ቢሮ ደረጃ የሚመራ ሲሆን በዘርፉ የሰለጠኑ፣ የፈጠራ ታሪክ በመስራት የተካኑ፣ የራሳቸውን ጥቅም እንጂ የሌላውን ሰው መጎዳት ትርጉም የማይሰጣቸው፣ ሐዘኔታም ሆነ ርህራሄ ብሎ ያልፈጠረባቸው፣ ማንኛውም ትልቅም ሆነ ትንሽ የሚሹትን ነገር ለማግኘት ሲባል ብቻ ነፍስ መጣል ካለባቸው በተፈጥሮው ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ መግደል ማለት ንጹሕ ውኃ ከመጠጣት የተለየ ስሜት በማይፈጥርባቸው ባለሞያዎችም የተደራጀ ነው።

Wednesday, December 5, 2012

ኢካቦድ!!! የመንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ክብር ከቅዱስ ሲኖዶስ ተለየ




·        የኅብረተሰብዓዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ስለቤተክርስቲያን ሲል በቀድሞው ፓትርያርክ በአቡነ ቴዎፍሎስ ላይ የወሰደውን እርምጃ ደግፈናል. . . (አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ ፊሊጶስ፣ አቡነ ቄርሎስና ሌሎችም የዛሬው ሲኖዶስ አባላት )

·        ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ እየተመራ አይደለም

·        አስቆሮቱ ይሁዳውያን ሊቃነጳጳሳት በዛሬዋ ቤተክርስቲያን

በቀደመው የቤተክርስቲያናችን ወርቃማ ዘመን፣ ሊቃነጳጳሳት ማለትም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በክርስትና ሕይወታቸው ለሃይማኖታቸውና ለእግዚአብሔር ያላቸው ታዛዥነት ታላቅ ነበር፡፡ እንደዛሬው እግራቸው ጫማ ሳይለምድ ጋራ ሸንተረሩን እየተዘዋወሩ ወንጌልን ይሰብኩ፣ ሃይማኖትን ያቀኑ ነበር፡፡ በዚያን ወርቃማ ዘመን በአመዛኙ አገልጋዩም ምዕመኑም በተቻለው መጠን መንፈሳዊ ተጋድሎው የበረታ፣ ተንኮል የሌለበትና ቅን ነበር፡፡

 በዛሬው ዘመን ያሉት አንዳንድ ሊቃነጳጳሳት ድሎትን ለምደው፣ ወገናዊነትን ተጠግተው የሚሰብኩት ሌላ፣ የሚኖሩት ሌላ እየሆነ፣ "አይጥ የማይጨርስ ድመት" ይመስል ክፋት፣ ዘረኝነት፣ ተንኮል፣ ሙስናና ጠብ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሲንሰራፋ ዝም እያሉ፣ ነገር ግን አባ እከሌ ለምን ተነኩብን፣ አባ እከሌ ለምን "ማኅበረ ቅዱሳን" ይነኩብናል በማለት ከሥልጣን ለማውረድና ለማውገዝ የሚያደርጉት መሯሯጥ እጅጉን አስገራሚ ነው፡፡

 ጨፍጫፊው ደርግ፣ ሃይማኖት አጥፊው ደርግ፣ አምባገነኑ ደርግ፣ ፋሽስቱ ደርግ፣ አቡነ ቴዎፍሎስን ያለ ፍርድ በገመድ አንቆ ሲገድል ዛሬ የሲኖዶስ አባል የሆኑ ሊቃነጳጳሳት ደግፈውት እንደነበረ ስንቶቻችን እናውቃለን? ስንቶቻችንስ ይህንን ዜና እናምነዋለን? ነገሩ ግን እውነትና እውነት ነው፡፡