Thursday, February 21, 2013

ኢሳት ይጠየቅልኝ!

ዝርዝር ጥልቀት ያለው ሐተታ ቀርቶ የውጣ ቃልም ብትሆን ስለ ኢሳት አንጻራዊ አመለካከት ማንጸባረቅ፡ ተቋሙ እየተከተለው ያለውን አሰራርና እየሄደበት ያለው ማንንም የማይጠቅም መንገድ እንደ ዜጋ በግልጽ መናገር: ትንፍሽ ማለት በተለይ "ይውደም!" ከተባለ "ይውደም!"- "ይቅደም!" ከተባለም እንዲሁ በተመሳሳይ ድምጽ "እንዴትና? ለምን?" በሌለበት ሁኔታ "ይውደም!" በማለት ድምጹን በማስተጋባት በሚታወቀው ማህበረሰብ አካባቢ ዘንዳ ምን ዓይነት ስም ሊያሰጥ እንደሚችል በሚገባ ጠንቅቄ አውቃለሁ። የደርግ ወታደራዊ መንግስት ቀን ጨለማ ሳይል የንጹሐን ዜጎች ደም ደመ ከልብ ሲያደርግና በገዛ ሕዝቡ በአደባባይ በጥይት ሲደበድብ/ሲረሽን አገኘሁበት የሚለው ክስ አንዱ "ጸረ አብዮት ነው!በማለት ነበር ሲሉ ከሞት ያመለጡ ምስክሮች እንደሚናገሩት ማለት ነው። ያም ሆነ ይህ መስመሩ ስለ ለቀቀና አቅጣጫው ክፉኛ ስቶ ስለሚገኘው: ታማኝነት የጎደለበት፡ ከምንም በላይ ደግሞ የሞያው ስነ ምግባር በሚጣረስ መልኩ ሆነ ተብሎ እየተደረገ ያለው የኢሳት አሰራር ጭብጥ ላይ የተመረኮዘ ተጨባጭ ሃሳብ ይዤ መመጎቴ ተከትሎ በጸሐፊው /ለሚለጠፉ ታቤላዎች አግባብነት የለውም ችግሩም ይቀርፈዋል የሚል እምነት የለኝም።
የኢ////ያን በተመልከተ በተለይ ከወቅቱ ጋር በተያያዘ የሃይማኖት መሪዎች የእርስ በርስ የመተረማመሱ ነገር እንዲሁም
በሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች በኩል ከመንፈሳዊነት ይልቅ እልከኝነት የተሞለበት ስብእናቸው አይሎ ከመውጣቱ የተነሳ የከሸፈውን እርቀ ሰላም በኢሳት በኩል ያለ አንዳች ተጨባጭና ደረቅ ማስረጃ የኢትዮጵያ መንግስት ተጠያቂ ለማድረግ የተሰሩ "ዜናዎችና ሐተታዎች" ብዛቱ ስፍር ቁጥር የለውም። ይህ የምለው ደግሞ እንደ ወንጌል አገልጋይነቴ እውነቱ እውነት ለማለት እንጅ ለመንግስት ጥብቅና ለመቆም ቃጥቶችም አይደለም። ቀደም ሲል በእኔ በኩልም ሆነ በሌሎች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆችና መምህራን አማካኝነት ከዚህ ሁሉ የሃይማኖት መሪዎች ትርምስ ጀርባ ለመልካም ነገር የሚያበቃ አቅም ባይኖረውም ለሁከትና ለረብሻ ግን የሚስተካከለው የሌለው "ማህበረ ቅዱሳን" በማለት ራሱን የሚጠራ ስመ መንፈሳዊ አጽራረ ጽድቅ ድርጅት የኢ////ያን የማፈራረስ ዓላማ አንዱ ስትራቴጂ መሆኑ በተጨባጭ ሲነገር መክረሙን የምንዘናጋው እውነት አይደለም።
 
ሰሙኑ ከወደ አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተ ክህነት /ቤት የተሰጠው ይፋዊ መግለጫ ግልጽ እንዳደረገው ደግሞ ይህ ግብረ እከይ ማህበር ("ማህበረ ቅዱሳን") አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ሳይቀር ራሱ ጨምሮ በአባልነት እንደሚገኝበት ነበር በይፋ የተነገረው። ታድያ ይህን የመሰለ ሕዝብ ሊሰማውና ሊያውቀው የሚገባው ጥብስ የሆነ ዜና በኢሳት ዘንድ በዝምታ መታለፉ ብቻ ሳይሆን የኢሳት የሕዝብ ዓይንና ጆሮ መሆን ታይቶኝ ነገሩ አግራሞት ስለጣለብኝ ነው ኢሳት ይጠየቅልኝ! የሚል ጽሑፍ ይዤ ብቅ ለማለት የወደድኩ።
Ø የኢሳት የሕዝብ ዓይንና ጆሮ መሆን ማለት ሕዝብን በፈጠራ ወሬ ማደናገር ከሆነ:
Ø የኢሳት የሕዝብ ዓይንና ጆሮ መሆን ማለት ሕዝብን የሚያንጽ ስራ መስራት መሆኑ ቀርቶ እውነት እንዳይገለጥ በመትጋት ለአመጸኛ ጥብቅና መቆም ማለት ከሆነ ኢሳት ይጠየቅልኝ! በማለቴ የሚቆጣ አንባቢ ይኖራል ብዬ አላምንም።
Ø እንግዲያውስ ኢሳት ይጠየቅልኝ! ተቋሙ እደርስለታለሁ ለሚለው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታማኝነቱ የሚገልጠው ሕዝብን ከመናቅ የሚመጣ/ንቀት በሚወልደው የግብር ይውጣ ስራ በመስራት ነው?
Ø ኢሳት ይጠየቅልኝ! "ማህበረ ቅዱሳን" ከኢ////ያን አልፎ በሀገር ደረጃ እያደረሰው ያለ በደልና ግፍ ሕዝብ እንዲያውቀው ያልተፈለገበት ምክንያት ምንድ ነው? ማህበሩ በትውልድ ላይ እያደረሰው ያለው ጥፋት እንደ ልማት የሚቆጠርበት ምክንያቱ ምንድ ነው?
Ø ኢሳት ይጠየቅልኝ! "የማህበረ ቅዱሳን" አገር አውዳሚ ትውልድ በታኝ መሰሪ ድርጊት በአደባባይ ተራቁቶ ሳለ "ማህበረ ቅዱሳን" እናንተ ጋር ደርሶ በመልካምነት የሚፈረጀበት ምስጢሩ ምንድ ነው?
Ø ኢሳት ሆይ! ማህበሩ ("ማህበረ ቅዱሳን") ያልሰራውን ሰራ፡ ያልሆነውን ነው በማለት የሌለ የጽድቅ አክሊልና ካባ እየደራረባችሁ ስለ ማህበሩ ጽድቅ ማውራት ያላሰፋራችሁ የተገለጠ ገበናው ለሕዝብ ከማድረስ መቆጠብን የመረጣችሁበት ምክንያት ምንድ ነው?
Ø ጎበዝ! እንደው ኢሳት ምን የሚሉት ውል "ከማህበረ ቅዱሳን" ቢፈራረም ነው ይህን ይክል በእውነት ላይ የጨከነው?
Ø ኢሳት ይጠየቅልኝ! 6ኛው የፓትሪያርክ ምርጫ በተመለከተ የምርጫ ሂደቱ ተቃውሞ ቢገጥመውና ተቃውሞውም "በማህበረ ቅዱሳን" መሪነት ቀርቶ አንዲት ፐርሰንትም ብትሆን "የማህበረ ቅዱሳን" እጅ ኖሮት ቢከናወን ኢሳት ደግሞ ይህችን አግኝቶ ትንሽዋን አግዝፎና አጉልቶ ደህና ዜና ከመስራት ይመልስ ነበር? አጋጣሚውን በመጠቀውም ስለ ማህበረ ቅዱሳን" የሌለውን እየሰጠ ከመናገር ይቆጠብ ይኖር ይሆን? አስችሎት ዝም ይል ነበር ወይ? ጎበዝ ዳኝነትህን ስጥ እንጂ።
Ø ኢሳት ሆይ! የምለው ከተሰማና ጥያቄዬም ግልጽ ከሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን'ነውሳ አሁን ዝም አላችሁ? ሹመቱ በመንግስት ግፊት ከሆነ የመንግስት ስራ ደግሞ "ማህበረ ቅዱሳን" እየሰራ መሆኑን በይፋ ከተነገረ ምን ነው ዝም ያላችሁ? እያለ ነው። የኢ//// የሃይማኖት መሪዎች 6 ፓትሪያሪክ ለመሾም ቅድመ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው በማስመልከት ለሕዝብ በይፋ ባሳወቁበት ሰዓት "ማህበረ ቅዱሳን" የተባለ ድርጅት የሃይማኖት መሪዎቹ አቃም ከመደገፍ አልፎ በመሪነት መሳተፉን በይፋ ሲገለጽ ሳትሰሙት ቀርቶ ይሆን? ወይስ ሊቀ ጳጳሱ በቴሌቪዥን መስኮት መግለጫውን ሲያነበንቡት በዲሲና በአምስተርዳም ሳተላይት የሚያጨልም በረዶ ይዘንብ ነበር?
Ø ኢሳት ይጠየቅልኝ! ያለ አንዳች ጭብጥና መረጃ መንግስትን ከመክሰስ ይልቅስ ፈጥቶ የወጣውን እውነት መዘገብ አይቀልም ነበር ወይ? "ማህበረ ቅዱሳን" የህወሐት ተቋሞች/ኢፈርት በማለት ከሚታወቁ መካከል አንዱ ቢሆን ኖሮ አልያም ደግሞ ባያብል ሙላቱ የተባለ የማህበሩ አውራ የትግራይ ደም ቢኖረው ኖሮ ኢሳት ይህ ዓይኑ ያወጣ "የማህበረ ቅዱሳን" ወንጀል በዝምታ ያልፈው ነበር ወይ? እግዚኦ! እንደው ምላሳችሁ እስኪደማ: ሰሚ ጆሮም እስኪሰላች ድረስ "የማህበረ ቅዱሳን" ነገር ከአፋችሁ አይወጣም ነበር አይገልጸውም።
የመንግስት ባለ ስልጣን ስም ጠርታችሁ "አቶ እገሌ በጳጳሳት መካከል ተገኝተው እንዲህ ብለው ተናገሩ" በማለት አሉባልታ ከመዝራት ያልተመለሳችሁና ያላሳፈራችሁ ሰዎች እውነት ቢያንቃችሁ ምን ይደንቃል? የገዛ ራሳችሁ የፈጠራ ስራ "ተባለ: ተሰምቶል: የተገኘው ዜና ያብራራል" በሚል ፈሊጥ ያልተነገረና ያልተባለ የጽሑፉም ሆነ የድምጽ ማስረጃ በማታቀርቡበት: "ተባለ" ሲል ዜና ሰርቶ ያቀበላችሁ ሃላፊነት የሚወስድ ግለሰብም ሆነ የዜና ምንጭ በሌለበት "ትላንት በአዲስ አበባ በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለተገኙት አባቶች አቶ አባይ ጸሀዬ በግልጽ እንዳስታወቁት አቡነ መርቆሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ ማለት መንግስቱ ሀይለማሪያም ይመለስ ከማለት ተለይቶ አይታይም ማለታቸው ተሰምቶል። ... አንዳንድ ከመንግስት ጋር የሚሰሩ ጳጳሳት በተለይም ብጹዕ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመለሱ ከሆነ እኛም አክሱም ላይ የራሳችን ሲኖዶስ እናቆቁማለን በማለት ቤተክርስቲያኒቱን በግልጽ በዘር መስመር ለማስቀመጥ ሀሳብ መሰንዘራቸውን የተገኘው ዜና ያብራራል።" ለማለት ግን የቀደማችሁ ማንም አልነበረም። (የኢሳት አማርኛ ዜና » ቅዱስ ሲኖዶስ ያካሄደው ስብሰባ ውጥረት የተሞላበትና የመንግስት ግልጽ ጫና የታየበት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮች ገልፁ http://ethsat.com/2013/01/15/ቅዱስ-ሲኖዶስ-ያካሄደው-ስብሰባ-ውጥረት-/) እግዚኦ! ይብላኝ ይህን የፈጠራ ወሬአችሁ "እውነት ነው!" በማለት ከሰማይ እንደ ወረደ መና ሳያልምጥ ቃላችሁን አምኖ ለሚኖር ሕዝብ እንጅ በባለ አእምሮ ሰው ዘንድ እንካን ጨርሶ እንደማይሳካላችሁ ጠንቅቃችሁ ታውቃላችሁ።

/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E- mail- yetdgnayalehe@gamil.com
United States of America

No comments:

Post a Comment