Monday, April 30, 2012

ኤፍሬም እሸቴ: ብትስማማ ነው እንጅ የሚያስደምመው ባለመስማማትህ ምን ይደንቃል? ክፍል 2

click here to read in PDF
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
 በጽሑፉ ክፍል አንድ ንባብ ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ምእመናን "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት: አንዲት ጥምቀት" ሲል በጻፈላቸው መልእክት በማንሳት አቶ ኤፍሬም ከግንዛቤ ማነስ እንዲሁም ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውቀት እጥረት የተነሳ በደመነፍስ ያኮላሸውን የክርስትና አስተምህሮ የዓውዱን ታሪካዊ ስዋስዋዊና ስነ ጽሑፋዊ መልኩ ጠብቆ የመልእክቱን መንፈስ መጨበጣችንና ማግኘታችን የሚታወስ ነው::

ወደ ዋና ርእሰ ጉዳዬ ከማለፌ በፊት ግን በአንዳንዶች ዘንድ የተፈጠረውን የተሳሳተ ግምት ለማጥራት ያክል አንዳንድ ነጥቦች ለማለት እወዳለሁ። በተለይ ኤፍሬም እሸቴ "አቶ" በማለቴ ለተበሳጩ አንባቢዎቼና ለኤፍሬም የኤፍሬምን “የድቁና/ቅስና” ማዕረገ ክህነት በተመለከተ ትንሽ ልበል:: በመሰረቱ እኔ ኤፍሬም በዲቁናም ሆነ በቅስና ማዕረግ ስትጠራ ሰምቼ አላውቅም:: አባሪ ተደርጎ የተላከልኝና ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኘሁት "አደባባይ" የሚል ስያሜ ያለው ድረ ገጽም "ኤፍሬም እሸቴ" እንጂ ሌላ ተጨማሪም ሆነ ተደራቢ ቀሚስ አላየሁም አላነበኩምም:: በጻፍከው ጽሑፍም የተቀመጠው ስምህ ነው ስለዚህ "አቶ" ብዬ መጥራቴ የሀገሬን ባህልና ወግ መጠበቄ እንጂ በሌላ መልኩ መወሰድ የለበትም ስል በትህትና እጠይቃለሁ::

ላያገለግሉበት ብቻ ሳይሆን ከየት እንዳገኙት በግልጽ የማይታወቅ የቅስናም ሆነ የድቁና ማዕረግ ይዘው በቅስና፣ በድቁናና በሌሎች የቤ/ያን መጠሪያ ቀሚሶች ስር ተሸሽገው የሚኖሩ እንደ'ነ ስንታየሁ አባተ፣ዳንኤል ክብረት፣ ብርሃኑ ጎበና፣ ዶ/ር መስፍን ተገኝ፣ ሙሉጌታ ሃይለማርያም፣ ግርማ መታፈሪያ፣ ባያብል ሙላቱ፣ ሳምሶንና ሌሎች የማህበረ ቅዱሳን አባላት በቤ/ያን የክህነት ማዕረግ የሚጠሩ ዕጣን ሲሸተን ያፍነናል፤ አስሜ ትነሳብኛለች፤የዕጣን አላርጅክ ነኝ፤ የአጥንት ካንሰር አለብኝ፤ በማለት ሳይቀድሱ ሳያስቀድሱ የሚንቀሳቀሱ “ዲቁናቸውን” እና “ቅስናቸውን” በጋዜጣ ብቻ የምናነበው ግለሰቦች ግን “ማዕረጋቸው” እንደተጠበቀ ነው::

ኤፍሬም እሸቴ፡- “በጠቅላላውም ካየነው የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ መታየት ያለበት “በቤተ ክህነቱ እና በቤተ ክህነቱ ብቻ” ነው ብዬ አምናለሁ።”  ላልከው

በመጀመሪያ ደረጃ "ማኅበረ ቅዱሳን" ሲል ራሱን የሚጠራ ድርጅት አባቶችን በማጭበርበር ያስፈረመው ማህበሩ አለኝ በሚለው መተዳደሪያ ደንብ “የማህበሩ ሙሉ ተጠሪነት ማኅበሩ ለሚያቋቁመው የበላይ የስራ አስፈጻሚ አካል ይሆናል።” ይላል እንጅ የት ስፍራ ነው "ማኅበረ ቅዱሳን" የቤ/ያን ለመሆኑ የሚያሳየው? የቤተ-ክርስቲያን ሲሆን አይደለም ወይ ጉዳዩ ቤተ-ክርስቲያን የሚታየው? ከመቼ ወዲህ ነው "ማኅበረ ቅዱሳን" ተጠሪነቱ ለቤተ-ክርስቲያን የሆነው? የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን የአስራር መዋቅሮችን ጠብቆ የተገነባና የሚንቀሳቀስ ድርጅት የሆነውስ መቼ ነው? መቼ ነውስ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ላቀረበችለት ጥያቄ ተገቤ የሆነ መልስ ሰጥቶ የሚያውቀውና ጉዳዩ ቤ/ያን የሚታየው? እንግዲህ እነዚህና ሌሎች ጥያቄዎች ለማድበስበስ አቶ ኤፍሬም እንዲህ ነበር ያለው “በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት ማለት የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉዳይ ለራሷ መተው ነው።” በሌላ አገላለጽ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ ነገር ላያደርጉ በፓርላማ በግላጭ አልተናገሩምና መሞታችን ላይቀር ገድለው ሳይቀብሩን በሚል ስሌት ጠቅላይ ሚኒስተሩ "ማኅበረ ቅዱሳንና" የግንዛቤ እጥረት ሰለባ የሆኑ የማኅበሩ አባላት ላይ በማነጣጠር ያደረጉት ንግግር በቤተ-ክርስቲያን ላይ እንደዘመቱ በማስመሰልና ከዚህም በመነሳት ደግሞ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃይማኖታችን ጣልቃ መግባታቸው ነውና ምእመናን ሆይ! ምን እስከምንሆን ድረስ እየጠበቅን ነው?” የሚል የተለመደውን የማህበሩ የዓመጽና የግርግር ማንሰራሪያ ዘዴ ደወል መደወሉ ነው:: ኤፍሬም ቆየን ከነቃንባችሁ።

በመሰረቱ መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው መንግሥት ቤተ-ክርስቲያን ጉዳይ ቤተ-ክርስቲያን በመንግሥት አሰራር ላይ በሌላ አነጋገር አንዳቸው በሌላኛው ጣልቃ አይገቡም ማለት ምን ማለት ነው? ውድ አንባቢያን:-
በዋናነት ስለ እነዚህ ሁለት አካላት ማወቅ የሚገባን ነጥብ ቢኖርም ሁለቱም ተጠባብቀው የሚሔዱ የየራሳቸው ሥልጣንና ሃላፊነት ያላቸው አካላት እንጂ ቤተ-ክርስቲያን በመንግሥት መንግሥት በቤተ-ክርስቲያን ላይ አንዱ በሌላው አንዳችም ልዩ ሥልጣን የላቸውም:: ይህ ማለት ሁለቱም በየፊናቸው እንዳሻቸው ይሆናሉ ማለትም አይደለም:: ሁለቱም ባላቸው የማይበላለጥና በማይተናነስ ሥልጣን ድርሻቸውን ይወጣሉ ማለት እንጅ መንግሥትም ሆነ ባለሥልጣናቱ ሥልጣናቸውን ተገን አድርገው በሀገርና በሕዝብ ጥፋትና ውድመትን ሲያደርሱ ቤተ ክርስቲያን እጇንና እግርዋን አጣጥፋ ትቀመጣለች ማለት አይደለም:: ቤተ ክርስቲያን ያለሽንገላና አድልዎ ጽድቅንና እውነትን የምታውጅ ቤት እንደ መሆንዋ መጠን በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ አመፀኞችን ትገስፃለች ክፋትን ትቃወማለች::

በተመሳሳይ መልኩ “መንፈሳዊያን” መሪዎች መንፈሳዊ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ከአንድ መንፈሳዊ ተቋምም ሆነ ግለሰብ የማይጠበቅ ሀገርንና ዜጋን የሚጎዳ ማንኛውም ዓይነት ተግባርና ድርጊት ሲፈጽሙ፣ ቤተ ክህነትም የሰላምና የፍትህ ቤት መሆኑ ቀርቶ የእሳት መከፋፈያ ጣቢያ ሆኖ ሲገኝ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ግለሰቡ እንደ አንድ ዜጋ በሕግ ፊት አቅርቦ የእጁን የማይሰጥበት ምንም ምክንያት የለም:: ይህም መንግሥት የሥልጣን ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተሰጠው (ያገኘው) ሥልጣን ነው:: (ለበለጠ "ምሥጢረኛዋ ሳንቲም" በሚል በጸሐፊው ከዚህ ቀደም በመንግስትና በቤተ-ክርስቲያን መካከል ሊኖር ስለሚገባ ግኑኝነት በማስመልከት የተዘጋጀውን ጥልቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ በጽሐፉ ግርጌ አባሪ ተደርጎ የቀረበውን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ)[1]

ኤፍሬም እሸቴ “ከዚህ አንጻር ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ የወጣ እምነት ይዘው ቤተ ክርስቲያኒቱን እና ትምህርቷን በመለወጥ የራሳቸው ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች፣ ቡድኖች እና ድርጅቶች መኖራቸው እየታወቀ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እና በዕውቀቱ ለቤተ ክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን ለአገሩም በቅንነት የሚያገለግለውን አንድ ትውልድ ጨፍልቆ በአክራሪነት ስም መፈረጅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና ላይ ትልቅ የሚዛን መናጋት ያስከትላል ብዬ በድፍረት መናገር እችላለኹ።” ላልከው

 ምላሳችን እስኪደማ ተናግረን ሰሚ ብናጣም ከአስር ወራት አከባቢ በፊት በአንድ የማኅበሩ ነባርና የስራ አመራር አባል የነበር ዳንኤል ክብረት የተባለ አውሬ (እኔ አይደለሁም ራሱ ያለውን ነው) የማህበሩ ዋና ጸሐፊ ከአንድ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዳንኤል ክብረት ስለ ተባለው ግለሰብ ከማህበሩ ጋር ያለው ወቅታዊ ግንኙነት ተጠይቀው "ዳንኤል ከቦታው የተነሳ ከድክመት የተነሳ ነው" ሲሉ ቃል በቃል የሰጡትን ሁለት አንድምታ ያለው ቃለ ምልልሳቸው የዳንኤል ክብረት ማንነት በአደባባይ አዝረክርከው በመናገራቸው ዳንኤልም በበኩሉ ከተዋረድኩ አይቀር ማኅበሩን ጭምር በሚል መንፈስ "ምንም የማያውቀውን የተኛውን በሬ ነካክተው ነካክተው አደረጉት አውሬ" ሲል በጻፈው የማህበሩ ውስጣዊ አሰራርና ማንነት የፈተሸ ጽሁፉ ካነሳቸው ነጥቦች መካከል “ማኅበረ ቅዱሳን ተሃድሶ ተሃድሶ የሚለው ችግር ሲገጥመው ከገባበበት አዘቅት ለመውጣት የሚፈበርከው ማደናገሪያ ስልቱ ነው” በማለት ጽፎ እንደነበር ሁላችን የምናስታውሰው ነው:: ታድያ “ከዚህ አንጻር ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ የወጣ እምነት ይዘው ቤተ ክርስቲያኒቱን እና ትምህርቷን በመለወጥ የራሳቸው ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች፣ ቡድኖች እና ድርጅቶች መኖራቸው እየታወቀ” የሚለውን የአቶ ኤፍሬም ማደናገር ምን ይሉት ቅጥፈት ነው?

ደግሞስ “በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እና በዕውቀቱ ለቤተ ክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን ለአገሩም በቅንነት የሚያገለግለውን” የሚባልልኝ ማንን ነው? ለመሆኑ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን "ከማኅበረ ቅዱሳን" አባላት ትምህርት ልጆችዋን ከማጣት: ከመለያየትና ከጸብ ያተረፈችው በጎ ነገር ምንድነው? ለዚህ የአቶ ኤፍሬም የዋዛ ንግግር "የማህበረ ቅዱሳን ዲግሪና የካንጋሮ እጅ አንድ ነው![2] የሚል ከጽሐፉ ግርጌ አባሪ ተደርጎ የቀረበውን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ::

ሌላው ማህበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት ስም መፈረጅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና ላይ ትልቅ የሚዛን መናጋት ያስከትላል ብዬ በድፍረት መናገር እችላለኹ።” ባቄላ አለቀ ቢሉ … ቀለለ ብለን ጥርግ ይበል! እንዳንል የአቶ ኤፍሬም መልእክት ሌላ ነው:: ልብ ይበሉ! ይህ አነጋገር አንድ መሰረታዊ የክርስትና ትምህርት እያፋለሰ ነው ይኸውም: የቤተ-ክርስቲያን ህልውና በመንፈስ ቅዱስ እጅ መሆኑ ቀርቶ ለህልውናዋም ለመጥፋትዋም "በማኅበረ ቅዱሳን" እጅ ነው ተብሎ መታመኑ:: በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃላቸው ተግባራዊ ቢያደርጉ "ማኅበረ ቅዱሳንን" ከምንጩ ለማድረቅ ቢንቀሳቀሱ ሊገጥማቸው ስለሚችለው ፖለቲካዊ ኪሳራም በእርግጠኝነት እየተነበየም ነው:: እንኳን ደህና መጣህ! ታሪክ ሳይሆን ራሱ የሚደግመው ፍጥረት የእግዚአብሔር ህልውናን ያያል:: የእግዚአብሔር ሰው “እኔስ የእግዚአብሔር
ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፥ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ አለው እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎቹን በላች” እንዲል (መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 1: 10)

ኤፍሬም እሸቴ: አንተንም መላ የማህበሩ አባላት ከሰማይ እሳት ወርዳ እንድትበላ ሳይሆን መንግስት በቁርጠኝነት "ማኅበረ ቅዱሳን" ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ቢነሳና ቢጥለውም "ከማኅበረ ቅዱሳን" ጋርም በተያያዘ መንግስት ይገጥመዋል ስትል የተነበይከውን የትርምስ ትንቢታዊ ቃልህ እንዳለ ሆኖ እኔ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ በመንግስት ህልውና ላይ አንዳች ሊፈጥር የሚችል የጎላ ክፍተት ሊኖር እንደማይችል ስገልጽ ይህችን ጦማር አግኝቶ የማንበብ ዕድሉን የገጠማት ነፍስ ሁሉ ይህቺን ቀንና ቃሌን በማስታወሻው ያስፍር:: በድፍረት የተናገርከው ያክል የማምነው ብቻ ሳይሆን በእኔ የሚታመነውን እግዚአብሔር ይህን ባያደርግ ምላሴ ትታጠፍ! ባሳለፍኩትና በከፈልኩት ዋጋም ወደኋላ ተመለሼ ሐዘን በላዬ ባልጠራም ቀሪውን ዘመኔን ጨለማ ያድርገው!!
ደመና እያየህ ጉዞ እስከ መቼ!

ኤፍሬም እሸቴ በርግጥ ገዳማትንና አብነት ት/ቤቶችን ከጥፋት መታደግ አክራሪነት ነውን? ወጣቱ ትውልድ ሃይማኖቱን አውቆ በሥነ ምግባር ታንጾ አገሩንና ቤተ ክርስቲያኑን በቅንነት እንዲያገለግል ማድረግ አክራሪነት ነውን? በገንዘቡ፣ በዕውቀቱና በጉልበቱ በነጻ የትውልድ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚሞክር ትውልድ መፍጠር አክራሪነት ነውን? በጭራሽ!!! ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ማኅበሩ ባሉት ሐሳብ አልስማማም።” ላልከው

ማኅበሩ በተለያዩ ያማሩ ስሞች ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ የሚዘውራቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ድረ ገጾች መካከል አንዱ "አንድ አድርገን" በመባል የሚታወቀውን ተጠቃሽ ነው:: ይህ መካነ ድር እነዚህ በአቶ ኤፍሬም "አክራሪነት ነውን?" እየተባሉ የተነሱ ጥያቄዎችን በተመሳሳይ መንገድ በአንድ ስሜት ያየለበት የዋህ ጸሐፊ የተነሱ ጥያቄዎች ያዘለ ጽሑፍ አስነብቦ ነበር:: መጽሐፍ ቅዱስ በአንደኛው ክፍለ ዘመን ከዛም በፊት ስለ ነበሩ ፈሪሳውያን በመባል ስለሚታወቁ ሃይማኖተኞችና እክራሪዎች/ጽንፈኝች የሚለውን እንመልከት::

ፈሪሳውያን፥
ü የሙሴን ሕግ ጠንቅቀው የሚያውቁ:
ü ሰማይ የተዘገባቸው:
ü መንፈሳዊ መገለጥ የሌላቸው:
ü ጽድቅን በራሳቸው ሚዛን የሚለኩ:
ü ህይወት በሚሰጠው በሀዲስ ኪዳን ትምህርት የማይመሩ:
ü ወግ አጥባቂዎች:
ü ሰው ለመግደል ጾም ጸሎት የሚይዙ ነፍሰ ገዳዮች:
ü አፈ ወርቆች ልበ ደንዳኖች:
ü ኃይማኖተኞች: ዳሩ ግን ፍቅር ርህራሄ የሌላቸው አውሬዎች:
ü ለማወቅም ሆነ ለመማር ፍቃድም ሆነ ፍላጎት የሌላቸው ትምክህተኞች:
ü የመልካም ነገር ጸበኞች ነበሩ::
እንግዲህ ይህን ማንነታቸው በሚገባ ያየና የተገነዘበ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር ጌታ ደግሞ ምንም በነሱ ቤት ለእግዚአብሔር የቆሙ ቢመስላቸው: ሰው ሲያያቸውም የሚያስቀኑ ቢመስሉም ኢየሱስ ግን እውነተኛ ማንነታቸን ገልጾ ድርጊታቸው የሚያስከትልባቸውን ቅጣት አክሎ በማያሻማ ቋንቋ እንዲህ ነበር ያላቸው:- (በማቴዎስ 23፡ 1 – 36)
Ø መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ:
Ø በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ:
Ø አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት:
Ø ፍርድንና ምሕረትን፥ ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ:
Ø በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ:
Ø በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጥ ግን የሙታን አጥንት ርኲሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ:
Ø የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ ፥ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና ወዮላችሁ! ሲል ካማረና ከተቀባ መቃብር[3] ጋር ዛሬ ክርስትናን ከጨለምተኝነት አስተሳሰብ መለየት ያቃታቸው አቶ ኤፍሬምና ሌሎች የማህበሩ ከበሮ መቺዎች "ሰው ሀይማኖቱን ሲጠብቅ እንዴት አክራሪ ይባላል?" በማለት ቢጠይቁ ምን ይደንቃል? "ማህበረ ቅዱሳን" እንደሆነ ማሰብ ያቆመ ዜጋ የተከማቸበት መካን ለመሆኑ ማን ቢስተውስ ነውና ስለ መስማማትና አለ መስማማት የሚነገረው? አቶ ኤፍሬም: “ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ማኅበሩ ባሉት ሐሳብ አልስማማም።” የሚለውን አባባልህ ቀድሞውኑ መስማማት ያቃተህ ከጠቅላይ
ሚኒስትሩ ብቻም ሳይሆን ለዚህ ሁሉ ስህተት ራስህንም ጭምር እንዳታይ ያደረገህ ከመጽሐፍ ቅዱስን ጋር ያለህን ትውውቅ እጅግ አናሳ በመሆኑና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤም ስለሚያንስህ ነው:: እዚህ ላይ ከአንዳንዶቹ “ለእውነት የቆሙ” መስሎዋቸው ማኅበሩን ከሚከተሉ የዋሆች በስተቀር "ማኅበረ ቅዱሳንና" አባላቱ እውቀት ላይ ያልተመሰረተ ስሜት የወለዳቸው ጽንፈኞች/ነፍሰ ገዳዮች መሆናቸውን ልብ ይሏል::

ኤፍሬም እሸቴ “አንድ አገር” ሲባልም ሥጋት የሚገባው ዜጋ ሊኖር አይገባም። … ኢትዮጵያውያንም እንደ አሜሪካኖቹ “ከፈጣሪ በታች ያለች አንዲት አገር/ one nation under God” አለችን ብንል የሚያሳፍር አይሆንም። ላልከው

መልሱ ግልጽና አጭር ነው "አንድ አገር አንድ ሃይማኖት" ለሀገርም ለወገንም ጠንቅ ነው። እንዲህ ያለ ዘመቻም በፖለቲካ አካባቢ የሚያስከትለው ጠንቅ እንደተጠበቀ ሆኖ ክርስትናን የጥላሸት የሚቀባ: በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ስምና በምእመናን ትከሻ ላይ ተንጠላጥሎ ሀገርን በማተረማመስና ሕዝብን በማወክ ምኞቱ የማስፈጸም ድብቅ ዓላማ ያለው ሃይል: የክርስትና ስም የሚያጠፋ የሀሳዌ መሲህ አጀንዳ ነው ተባለ እንጅ "አንድ ሀገር!" በጥሬው አትበሉ ያለ ማን ነው? አንድ አገር ማለትስ እንዴት ነው አሳፋሪ የሚሆነው?

ማነውስ በዚህ ቃል የሚያፍር? እሳትና ጭድ ማጎራበት ዋ![4] ተባለ እንጅ እሳት በእሳትነቱ ጭድም በጭድነቱ ላይ የተነሳ ማን ነው?
ውድ አንባቢ: ከዚህ በላይ ግንዛቤ ማነስ ምን አለ? የሚያሳዝነው የአቶ ኤፍሬም ትንታኔ አንብቦ ደስታውን በመግለጽ ተባርከናልና እግዚአብሔር ይባርክህ የሚል ምእመን ነው::
ኤፍሬም እሸቴ “ማኅበረ ቅዱሳን “እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከበርበት” ማኅበር ሲሆን አገልግሎት መስጠት ከጀመረ እነሆ 20 ዓመት ሆነው። ማኅበሩም ያለውን ዓላማ፣ ግብና ርዕይ በመጽሔቶቹ፣ በጋዜጦቹ፣ በዐውደ ርእዮቹ፣ በኦዲዮ እና ቪዲዮ ውጤቶቹ ደጋግሞ ጽፏል፣ ተናግሯል፣ አስተምሯል። ከዚህ አንጻር ማኅበሩ አገርንም ሆነ ፖለቲካን፣ ሌሎች እምነቶችንም ሆነ ተቻችሎ መኖርን በተመለከተ ከማንም በላይ በሰፊው፣ በበሰለ እና ጤናማ በሆነ መንገድ ሐሳቡን አስተጋብቷል።” ላልከው

አሁን አሁን እየቀለድክ ሁሉ ይመስለኛል ያለኸው:: የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት ስትል የዘረዘርካቸው ታሪካቸው እኮ የሌብነት የሽፍትነት ስራ በመስራታቸው ሳይሆን የመስቀሉን ቃል ኑረውበት ያለፉ ለመሆኑ ጭራሽ ዘንግተኸዋል:: እስቲ አሁን "ማኅበረ ቅዱሳን" የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት ዝክር የሚዘክረው ቅዱሳንን በማሳደድ በመግደልና በማሳጣት ነው? "ማኅበረ ቅዱሳን" መጽሐፍ ቅዱስ የካቶሊክ: የጴንጤ ነው አያለ ከማውገዝና ከማንቋሸሽ አልፎ በ20 ዓመታት ውስጥ የቤተ-ክርስቲያን ጉልላትና መሰረት: የነገር ሁሉ ምንጭና የበላይ ባለስልጣን የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ አሰራጭቶ ያውቃል? የማህበሩ ልሳኖች እንደሆኑ ጸብን ከመዝራትና የቤተ-ክርስቲያን አገልጋዮች ስም ከማጥፋት አልፈው "ማህበረ ቅዱሳን" በዛሬው ዕለት በዚህ ስፍራ ላይ ይህን ያክል መጽሐፍ ቅዱስ ለተቃዋሚዎች አሰራጨ የሚል ዜና አስነብበው ያውቃሉ? እንደው ይህን የአቶ ኤፍሬም ጥብቅና ሳነብ ትዝ ያለኝ ታሪክ ልንገራችሁና ሐሳቤን ልቋጭ::

በአንድ ወቅት ነው ይህ ማህበር ("ማህበረ ቅዱሳን") አንድ ለትርፍ ያልቆመ ዓለም ዓቀፍ ክርስቲያናዊ ድርጅት በሩ ድረስ በማንኳኳት ማህበሩ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ወሳኝ አካልና የጀርባ እጥንት: እንዲሁም ቤተ-ክርስቲያኑቱ ይህን ተልዕኮ ያከናውን ዘንድ አደራ እንደጣለበት በማስመሰል በእንግሊዝኛ ሰነድ አዘጋጅቶ መጽሐፍ ቅዱስ አሰራጫለሁ በማለት በመቶ ሺህ የሚቆጠር የተለያዩ የአማርኛ ትርጉሞችና መጠን ያላቸው ካገኘ በሃላ አጭበርብሮ በእርዳታ በነጻ ያሰራጨው ዘንድ ያገኘውን መጽሐፍ ቅዱስ በመላ አገሪትዋ ቱባ ቱባ ደላላዎችን በማሰማራት ተመልሶ ለሌሎች የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያንና እንዲሁም ሱቅ ቤቶች በመቸብቸብ ከፍተኛ ገንዘብ ያግበሰበሰት አስታውሶኛል:: እንዲህ ያለውን ነገር ነው እንግዲህ ኤፍሬም ማኅበሩ ለቤተክርስቲያን የሰራው ስራ የሚለው!!
 እውነት መንገድም ህይወትም የሆነው የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ሰላምና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!
ዛሬም እጄ በጠላቶቼ ደንደስ ላይ ነች!
/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
yetdgnayalehe@gmail.com

[1] "ምሥጢረኛዋ ሳንቲም" http://www.ethiomedia.com/broad/secret_coin.pdf
[2] የማኅበረ ቅድሳን ዲግሪና የካንጋሮ እጅ አንድ ነው!!
http://awdemihret.blogspot.com/2012/04/blog-post_6660.html

[3] መቃብር ምንም ውጩ ቢቀባ ቢያምርም በውስጡ የያዘው ግማቱ አገር የሚያስተው ብስባሽ አጥንት ነው!
[4] ጸሐፊው እሳትና ጭድ በምሳሌነት ሲጠቀሙ ሁለቱ በሚፈጥሩት ውህደት ላይ የሚያስከትለው አደጋ ላይ ለማሳየት እንጅ ሀገርና ሃይማኖት አንዱ እሳት ሌላኛው ጭድ የሚል አንድምታ የለውም::

18 comments:

  1. የተዛባ አመለካከት አገልግሎታችንን አያደናቅፈውም
    ግንቦት 16፣2003ዓ.ም

    በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ 19 ዓመታት ተጉዟል፡፡
    ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡

    ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

    ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ወዳጆች አፈራ? ጠላቶችስ ለምን ተነሡበት?

    ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ፈቅዶ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ ወጣቶችን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በማደራጀት ከመደበኛው ትምህርታቸው ጎን ለጎን በየአካባቢው ወደሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሔደው መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲማሩ በማድረግ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁና ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው እንዲያገለግሉ በማድረግ፤ በተጨማሪም ወጣቱ ሀገሩንና ሕዝቦቿን አክባሪ፣ በሥነ ምግባር የታነጸ እንዲሆን በማስቻሉ ብዙ ወዳጆችን አግኝቷል፡፡

    ከዚህም ሌላ የመናፍቃኑንና ቤተ ክርስቲያኒቱን እናድሳለን ብለው የተነሡትን የመናፍቃኑ ተላላኪ ቡድኖችን ሴራና የአክራሪ እስልምናውን እንቅስቃሴ በመረጃ አስደግፎ በማጋለጡ፣ ከክፉ ትምህርታቸው መመለስ ያልፈለጉ የተሐድሶ ቡድን አባላት ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ ስለተወሰነባቸው እና ሌሎችንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግሮች እየተከታተለ ለዕድገቷና ለብልጽግናዋ በመሥራቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆችን አፍርቷል፡፡

    ከዚህ በተቃራኒው የተሰለፉት ወገኖች ደግሞ ወጣቱን እንደጠፍ ከብት ወደ ማያውቀው የመናፍቃን አዳራሽ የመንዳት ልምዳቸው በመቋረጡና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት የሚያደርጉት ሥርዓቷን የማፋለስ እንቅስቃሴ፤ እንዲሁም አገልጋዮቿንና ምእመናኖቿን የማስኮብለሉ አካሔድ ማኅበሩ በክትትል በተለያዩ መረጃዎች ስለገለጠባቸው ማኅበረ ቅዱሳንን በጠላትነት በማየት ማኅበሩ እንዲፈርስ የማይቧጥጡት ዳገት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

    እነዚህ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች ለጥቂት ጊዜ ጋብ ብለው የነበሩ ቢሆንም አሁን ባገኙት አጋጣሚ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጀራዋን እየበሉ የሚኖሩ ወዳጆቻቸውን በማጠናከርና በማስፋፋት በሚሊዮን የሚቆጠር በጀት ከወዳጆቻቸው ተመድቦላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓት ለማዛባትና በጎቿን ለመበታተን ሌት ከቀን እየሠሩ ነው፡፡

    ይኼ ዕቅዳቸው የሚሳካው እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እምነትና ሥርዓት መጠበቅ የሚቆረቆሩ ማኅበራትን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አጀንዳ በማድረግና እንዲበተኑ ክፉ ሥራ በመሥራት ነው፡፡ እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ይሔንን ከንቱ ቅዠታቸውን እውን ለማድረግም በቤተ ክርቲያኒቱ የተለያየ ሓላፊነት ላይ የሚገኙትን የዓላማቸው አስፈጻሚዎች ሁሉ እየተጠቀሙ እንደሚገኙም ይታወቃል፡፡

    ከዚህም ሌላ ድብቅ ዓላማቸው እንዲሳካ ተላላኪዎቻቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚሆን ነገር ግን ስውር ዓላማ ያለው ማኅበር እንዲመሠርቱና ከዚህ በፊት ከንቱ ተግባራቸው ታውቆ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታግደው የነበሩ ማኅበራት ሁሉ ከሞቱበት እንዲቀሰቀሱ እየሠሩም እያደረጉም ይገኛሉ፡፡

    በቤተ ክርስቲያን ስም ድብቅ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ያቋቋሟቸውና የሚያቋቁሟቸው፣ ማኅበራትንም ሕጋዊ ዕውቅና ለማሰጠት እንዲያመቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከኔ ሌላ ሌሎች አያስፈልጉም የሚል አቋም ያለው ማኅበር እንደሆነ ያስወራሉ፡፡

    በእርግጥ ማኅበረ ቅዱሳን በትክክል የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓትና ደንብ ተከትለው በሚቋቋሙት ማኅበራት ላይ የማኅበሩ ጠላቶች ከሚያወሩትና ከሚያስወሩት አሉባልታ የተለየ አቋም አለው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርቲያን የሁለት ሺሕ ዓመታት ታሪክ ያላት ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ትሁን እንጂ መንበሯ ከሊቀ ጵጵስና ደረጃ ወደ ፕትርክና ለማሳደግ አንድ ሺሕ ስድስት መቶ መራራ ዓመታትን አሳልፋለች፡፡ በዚህ ማለፏ ደግሞ ሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት የደረሱበት ዘመናዊ የአደረጃጀት ደረጃ ላይ ለመድረስ አልቻለችም፡፡ ልጆቿንም ጊዜው በሚጠይቀው መንገድ ለመምራት ሳትችል ስለቆየች እነዚህን ክፍተቶች የሚሞሉ አንድ አይደለም በርካታ ማኅበራት እንደሚያስፈልጓት ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ነገር ግን እኩያኑ እንደሚሉት ሳይሆን እነዚህ ማኅበራት ሲቋቋሙ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ዕድገትና የአገልግሎት ሥምረት የሚንቀሳቀሱ ተልእኮአቸውና ዓላማቸው ተለይቶ የሚታወቅ፣ መንፈሳዊ ተግባርን ብቻ የሚፈጽሙ፣ የሚናበቡና በስልት ለአንድ ውጤት የሚተጉ ሊሆኑ ይገባቸዋል የሚል ጽኑ አቋም አለው፡፡

    ይሔንን አቋሙን ደግሞ በርካቶች የሚደግፉት እንደሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ የመናፍቃኑ ተላላኪዎች በቤተ ክርስቲያን ስም ያቋቋሟቸው ማኅበራት ከዚህ በፊት በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥለውት የሔዱት ጠባሳ የሚታወቅ ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን በማኅበራት ላይ ግልጽ አቋም አለው፡፡ ከዚህም ሌላ እነዚህ የውስጥ ዐርበኞች ይኽ ስውር ዓላማቸው ያልታወቀባቸው ይመስል ማኅበሩን ለመወንጀል የማይለጥፉለት ታፔላ፣ የማይለፍፉት ወሬ የለም፡፡ ነገር ግን እነዚህ የቤተክርስቲያን ጠላቶች ስለማኅበሩ የሚያወሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ እና ሁሉም የሚገነዘበው ግልጽ እውነታ መሆኑን ባለማወቃቸው እናዝናለን፡፡

    ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ስውር ዓላማ የለውም፤ ከማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ የጸዳና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያን ሳያዛንፍ እየሠራ ያለ፤ በተሰጠውም መተዳደሪያ ደንብና ሓላፊነት መሠረት ከአባላቱና ከበጎ አድራጊ ምእመናን የሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪ እያሰላ በውስጥ ኦዲተሮችም እያስመረመረ በመሥራት ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ማኅበር እንጂ በወሬ የሚኖር አይደለም፡፡ ይሔንን አሠራሩንም ቀርቦ ማየት ይቻላል፡፡ አባላቱም በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው በጉልበታቸውና በመላ ሕይወታቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉ እንጂ እንደ መናፍቃኑ ተላላኪዎች ለሆዳቸው ያደሩ፣ ሆዳቸው አምላካቸው የሆነባቸው እዚህም እዚያም ደሞዝ የሚቀበሉ አይደሉም፡፡

    ማንኛውም አካል እንዲያውቅልን የምንፈልገው ሐቅ ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰጠው ሓላፊነትና አባላቱም ለገቡለት ቃል ኪዳን ሃይማኖታቸው የሚፈቅደውን መስዋዕትነት ለቤተ ክርስቲያን ልዕልናና ክብር ለመክፈል የተዘጋጁ እንጂ በተዛባ አመለካከት ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉ አለመሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

    ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱ የሚታይ አሠራሩም ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም የመናፍቃኑ ተላላኪዎች መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከአገልግሎታችን አንዲት ጋት ወደ ኋላ እንደማይመልሰን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፡፡ ርእይና ተልእኮአችንን ለማሳካት ዛሬም ነገም እንሠራለን፤ ትናንትን ያሻገረን እግዚአብሔር ዛሬንም ያሳልፈናልና፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. በቅድሚያ ይህ መግለጫ መሰል አስተያየት የማኅበሩ ነው ወይስ የአስተያየት ሰጪው? ምን እያደረገ እንዳለ የሚታወቀውን ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲህና እንዲያ ነው በማለት ስለማኅበሩ የሌለ ሥዕል ሰጥቶና ማኅበሩን በሌለበት የቅድስና ማማ ላይ ለመስቀል ይህን ያህል መዘብዘብ ራስን ትዝብት ላይ ከሚጥል ያለፈ ፋይዳ የለውም። አስተያየት ሰጪው ስለማኅበሩ መግለጫ ከመስጠት ይልቅ በተጻፈው ጽሑፍ ላይ ተመሥርቶ ማኅበሩ ከአቡነ ጎርጎርዮስ ጋር ስለመተዋወቅ አለመተዋወቁ ሊነግረን በተገባ ነበር። እርሱ ግን ይህን ጉዳይ ፈጽሞ አላነሣውም። ለእኔ ይህ የሚነግረኝ በጸጋ የተጻፈው ጽሑፍ ማኅበሩ ያልጠበቀውና ያላሰበው እንደሆነበት ነው። የተነሡት ሁለቱ ነጥቦች በቂ ናቸው። ማኅበሩና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በዘመንም በትምህርትም ፈጽሞ አይተዋወቁም። አስተያየት ሰጪው /ማኅበሩ(?)/ ለዚህ ምላሽ ቢኖራቸው ኖሮ ይነግሩን ነበር። ስለሌላቸው ግን በሰው ፊት ያልተገለጠውን እነርሱ ብቻ ዘወትር እንደ ዳዊት የሚደጋግሙትን የማኅበሩን ግብዝነት የተሞላ ኩሸት ይኳሻሉ።
      በአስተያዩ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን ጠላት ያፈራው ተሐድሶዎች “ወጣቱን እንደጠፍ ከብት ወደ ማያውቀው የመናፍቃን አዳራሽ የመንዳት ልምዳቸው በመቋረጡና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት የሚያደርጉት ሥርዓቷን የማፋለስ እንቅስቃሴ፤ እንዲሁም አገልጋዮቿንና ምእመናኖቿን የማስኮብለሉ አካሔድ ማኅበሩ በክትትል በተለያዩ መረጃዎች ስለገለጠባቸው ማኅበረ ቅዱሳንን በጠላትነት” ይመለከቱታል ያለው አስገራሚ ነው፡፡ ለሰዎች ከቤተክርስቲያናቸው መኮብለል ዋና ተጠያቂው ተሐድሶዎች ሳይሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ነው። የእኔ አባል ካልሆነ ሰው በቀር ሌላ ሰው አልይ፣ ሌላ ማኅበር በተለይም ሃይማኖተ አበውን ፈጽሞ አልይ የሚል ስለሆነ ብዙዎች በሐገ ወጥ መንገድ እናት ቤተክርስቲያናቸውን ጥለው ወደ ሌላ ለመፍለስ ተገደዋል። ስለዚህ በራሳቸው መንገድ ከወጡትና ወደሌላ ከሄዱት ይልቅ “በሃይማኖት ፈረሰ” ሰበብ ማኅበረ ቅዱሳን የገፋቸውና ከእናት ቤተክርስቲያናቸው ሳይወዱ በግድ የለያቸው ጥቂቶች አይደሉም። ዛሬ የወንጌልን እውነት በመግለጥ የጎን ውጋት የሆኑበትና የጨለማ ሥራውን በወንጌል እውነት እየገለጡ ያሉት ያለስማቸው ስም ሰጥቶ ያሳደዳቸውና ስልታቸውን ቀይረው በእናት ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ለቤተክርስቲያኗ እውነተኛ ተሐድሶ እየተጉ ያሉ ልጆቿ ናቸው። ዛሬ ነገሩን ማኅበረ ቅዱሳን የሚቆጣጠረው አይደለም።
      ባለፈው መስከረም ግሸን ተገኝተው ስለተሐድሶ ግንዛቤ እናስጨብጣለን ያሉት የማኅበሩ ሰዎች እነ ያረጋልና ዘመድኩን “ተሐድሶ ተሐድሶ ትላላችሁ ለምን ተሐድሶ የተባሉትን አታሳዩንም?” ተብለው ሲጠየቁ፣ “እገሌና እገሌ የሚባል አይደለም የተሐድሶ መንፈስ በቀዳሾቻችን፣ በሰባኪዎቻችን፣ በመዘምራኖቻችን፣ በሰንበት ተማሪዎችችን፣ … ውስጥ ገብቷል” የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት። በርግጥም ዛሬ በወንጌሉ እሳት የተቀጣጠሉ ከማኅበረ ቅዱሳን እይታም ሆነ ቁጥጥር ውጪ ናቸው። እንዳሉትም “መንፈሱን” በስለላም ሆነ በሌላ የተለመደ ስልታቸው ሊይዙት አይችሉም። አገልግሎቱ ወደዚህ አቅጣጫ ያደገው ግን ማኅበረ ቅዱሳን ሲያደርግ በቆየው ግፊት ነው። ዛሬ እንደ ቀድሞው ስላይደለ ማኅበረ ቅዱሳን በዚያው ስልት መዋጋት አይችልም።
      “ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ስውር ዓላማ የለውም፤ ከማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ የጸዳና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያን ሳያዛንፍ እየሠራ ያለ፤ በተሰጠውም መተዳደሪያ ደንብና ሓላፊነት መሠረት ከአባላቱና ከበጎ አድራጊ ምእመናን የሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪ እያሰላ በውስጥ ኦዲተሮችም እያስመረመረ በመሥራት ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ማኅበር እንጂ በወሬ የሚኖር አይደለም፡፡ ይሔንን አሠራሩንም ቀርቦ ማየት ይቻላል፡፡” እዚህ ውስጥ ምን እውነት አለ? ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ እንዳለው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። የሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪውን ለማደራጃ መምሪያው ለማሳወቅ ፍላጎቱም ዝግጁነቱም እንደሌለው አስመስክሯል። ጠቅላይ ቤተክህነት የጻፈለትን ደብዳቤም ውድቅ ማድረጉና በእንቢታው መጽናቱ ከዚህ ቀደም ተገልጾአል። ስለዚህ ምናለ እውነታውን ብንነጋገር።

      Delete
  2. እስቲ አሁን "ማኅበረ ቅዱሳን" የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት ዝክር የሚዘክረው ቅዱሳንን በማሳደድ በመግደልና በማሳጣት ነው? "ማኅበረ ቅዱሳን" መጽሐፍ ቅዱስ የካቶሊክ: የጴንጤ ነው አያለ ከማውገዝና ከማንቋሸሽ አልፎ በ20 ዓመታት ውስጥ የቤተ-ክርስቲያን ጉልላትና መሰረት: የነገር ሁሉ ምንጭና የበላይ ባለስልጣን የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ አሰራጭቶ ያውቃል? የማህበሩ ልሳኖች እንደሆኑ ጸብን ከመዝራትና የቤተ-ክርስቲያን አገልጋዮች ስም ከማጥፋት አልፈው "ማህበረ ቅዱሳን" በዛሬው ዕለት በዚህ ስፍራ ላይ ይህን ያክል መጽሐፍ ቅዱስ ለተቃዋሚዎች አሰራጨ የሚል ዜና አስነብበው ያውቃሉ?

    ReplyDelete
  3. በአንድ ወቅት ነው ይህ ማህበር ("ማህበረ ቅዱሳን") አንድ ለትርፍ ያልቆመ ዓለም ዓቀፍ ክርስቲያናዊ ድርጅት በሩ ድረስ በማንኳኳት ማህበሩ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ወሳኝ አካልና የጀርባ እጥንት: እንዲሁም ቤተ-ክርስቲያኑቱ ይህን ተልዕኮ ያከናውን ዘንድ አደራ እንደጣለበት በማስመሰል በእንግሊዝኛ ሰነድ አዘጋጅቶ መጽሐፍ ቅዱስ አሰራጫለሁ በማለት በመቶ ሺህ የሚቆጠር የተለያዩ የአማርኛ ትርጉሞችና መጠን ያላቸው ካገኘ በሃላ አጭበርብሮ በእርዳታ በነጻ ያሰራጨው ዘንድ ያገኘውን መጽሐፍ ቅዱስ በመላ አገሪትዋ ቱባ ቱባ ደላላዎችን በማሰማራት ተመልሶ ለሌሎች የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያንና እንዲሁም ሱቅ ቤቶች በመቸብቸብ ከፍተኛ ገንዘብ ያግበሰበሰት አስታውሶኛል:: እንዲህ ያለውን ነገር ነው እንግዲህ ኤፍሬም ማኅበሩ ለቤተክርስቲያን የሰራው ስራ የሚለው!!so true MK is a gang group.

    ReplyDelete
  4. መልሱ ግልጽና አጭር ነው "አንድ አገር አንድ ሃይማኖት" ለሀገርም ለወገንም ጠንቅ ነው። እንዲህ ያለ ዘመቻም በፖለቲካ አካባቢ የሚያስከትለው ጠንቅ እንደተጠበቀ ሆኖ ክርስትናን የጥላሸት የሚቀባ: በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ስምና በምእመናን ትከሻ ላይ ተንጠላጥሎ ሀገርን በማተረማመስና ሕዝብን በማወክ ምኞቱ የማስፈጸም ድብቅ ዓላማ ያለው ሃይል: የክርስትና ስም የሚያጠፋ የሀሳዌ መሲህ አጀንዳ ነው ተባለ እንጅ "አንድ ሀገር!" በጥሬው አትበሉ ያለ ማን ነው? አንድ አገር ማለትስ እንዴት ነው አሳፋሪ የሚሆነው? ማነውስ በዚህ ቃል የሚያፍር? እሳትና ጭድ ማጎራበት ዋ![4] ተባለ እንጅ እሳት በእሳትነቱ ጭድም በጭድነቱ ላይ የተነሳ ማን ነው? ውድ አንባቢ: ከዚህ በላይ ግንዛቤ ማነስ ምን አለ? የሚያሳዝነው የአቶ ኤፍሬም ትንታኔ አንብቦ ደስታውን በመግለጽ ተባርከናልና እግዚአብሔር ይባርክህ የሚል ምእመን ነው::I like the logic!

    ReplyDelete
  5. ጽሑፍህን አላነበብኩትም ርእሱን ሳይው ስለተናነቀኝ!!
    ምክንያቱም ራስክን ዲ/ን አድርገህ ነገርግን ድቁናን የሰጠችህን ቤተክርሰቲያንን ለመውጋት ፍላጻፍን እየወረወርክ እንደሆነ ስለተመለከትኩ፡፡ ይቅርታ ስለመሰለኝ እንጂ ዲ/ን፤ቄስ፤… ስለተባሉ ከየት እነደሆኑ ማወቅ የሚያሰቸግርበት ሰዓት ላይ በመሆናችን መጽሐፍ እንዳስጠነቀቀን ብዘዎችን የሚያስቱ አሳይመሲሆች የተበራከቱበት፤የተመረጡትንም የሚያስቱበት ሰዓቱ በመሆኑ ብዙ ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ሰዓት ነው፡፡ ይህችን ቤተክርስቲያን ከውጭና ከውስጥ ሆነው በምንፍቅናና በምዝበራ ያስቸገራትን ታጥቆ እየተዋጋቸው ያለውን ማህበረ ቅዱሳንን የተጣላ፡ የጠላ፡ የነቀፈ ሁሉ መታወቂያው ከየት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህ በቀጥታ አሰላለፉ ከየት እንደሆነ ጊዜውን ሳያጠፋ ራሱን መግለጥ፡ ታረጋውን ማሰቀየር ይኖርበታል፡፡ ከዝያ ለራሱም ቀላል ይሆንለታል፡፡
    እስከመቼ በማጭበርበር በሁለት ታርጋ(መታወቂያ)

    ReplyDelete
  6. ያንተን ጽሁፍ ጨርሼ ለማንበብ ፍጹም አልቻልኩም ምክንያቱም ሳያነቡት ገና መልክቱ ምን እንደሆነ ይታወቃል! ጅል የመጨረሻ ጅል ነህ!! ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደዛ ስለተናገሩ መሃበሩ የሚፈርስ መስሎህ/ መስሏችሁ ጮቤ እየረገጥክ/እየረጋጣችሁ ነው አይደል? ማህበሩ መቼም አይፈርስም ጠቅላይ ሚንስትሩም የማፍረስን ነገር መቼም እንደማይሞክሯት በአስር ጣቴ እፈርማለሁ የሚከተለውን ጠንቅቀው ስለሚያውቁት በፍጹም አይሞክሯትም!እኔ ማንም አይደለሁም ብታምኑም ባታምኑም አንድ ተራ ምዕመን ነኝ የማህበሩ አባልም አይደለሁም ማህበሩን ግን ከመሰረቱ ጀምሬ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ ለቤተክርስቲያናችንም እያደረገ ያለውንም ነገር እንደዚሁ!! ለእናንተም ለተኩላዎችም ምን ያህል እንቅፋት እንደሆናችሁም ጭምር እኔ ብቻ ሳልሆን 99% የኦርቶዶክስ ምዕመን ሁሉን ያውቃል!! ማንነታችሁን ምዕመኑ ምንያህል እነዳወቀው ያኔ አቤቱታችሁን ለሲኖዶስ ላመቅረብ በሄዳችሁ ጌዜ በሰንበት ተማሪዎች እና በምዕመናን ምን ያህል ተቃውሞ ደርሶባችሁ ሰሚ አጥታችሁ እንደተመለሳችሁ እረሳችሁት እንዴ?!!ዳንኤል ክብረት ሰውነውና አንድ ጊዜ ተሳስቶ የጻፈውን እሱም ስህተቱን አምኖ ምዕመኑን ሆነ ማህበሩን ይቅርታ የጠየቀበትን ልክ እንደእግዚያብሄር ቃል ደግማማችሁ ትጽፉታላችሁ ምን ታደርጉ ወዲህ ብትሉ ወዲያ የሚያምናችሁ አጣችሁ!! መሃበሩ የሚጠላበትን ምክንያት ልታገኙ አልቻላችሁም ምክንያቱም መሃበሩ ስራው ሁሉ መልካም ነውና አፈረድባችሁም!! እኔም አሁንም ሺ ጌዜ ደርቤ ደረቤ አስምሬ እነግርሃለሁ/እንገራችሁላሁ ማህበረ ቅዱሳንን ማንም አያፈርሰውም አይፈርስምም/ መፍረስ ያለበት ፈርሷል ተፈረካክሷል/ አገራችንን እና ሃይማኖታችንን ለማፍረሰ የተናሳችሁ የይሁዳ መልክተኞች ናችሁ! ልቦና ይስጣችሁ ( አስተያየቴን እነደማታወጡት አውቃለሁ እኔም ለእናተ ነው የጻፍኩት እንጂ ለማንም አይደለም)

    ReplyDelete
  7. http://www.ahatitewahedo.com/2012/04/blog-post_1837.html

    ReplyDelete
  8. በእግዚአብሔር ፈቃድ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሁንታ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለመደገፍና ለማጠናከር የተመሠረተው ማኅበረ ቅዱሳን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አያሌ ፈተናዎችን እያሳለፈ 19 ዓመታት ተጉዟል፡፡
    ማኅበረ ቅዱሳን በዓመታት ጉዞው ባከናወናቸው መልካም ተግባራት ታላላቅ የቤተክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ወዳጆችን እንዳፈራ ሁሉ ጥቂት በተቃራኒው የቆሙ ስሙን በየጊዜው በክፉ የሚያነሱ ቡድኖችም ተነሥተውበታል፡፡

    ወዳጆቹ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች ናቸውና በአገልግሎቱ ተማርከው በሚሠራቸው መልካም ሥራዎች ተስበው ቤተ ክርስቲያን ያለባትን የአገልግሎት ክፍተት ለመሙላት በጋራ ከማኅበሩ ጋር በመሥራት ሲተባበሩ፤ በአንጻሩ ጠላቶቹ ደግሞ የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያስታከኩ ማኅበሩን ለመወንጀል እየተጣጣሩ ይገኛሉ፡፡

    ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ወዳጆች አፈራ? ጠላቶችስ ለምን ተነሡበት?

    ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ፈቅዶ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ ወጣቶችን በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በማደራጀት ከመደበኛው ትምህርታቸው ጎን ለጎን በየአካባቢው ወደሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሔደው መሠረታዊውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲማሩ በማድረግ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁና ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው እንዲያገለግሉ በማድረግ፤ በተጨማሪም ወጣቱ ሀገሩንና ሕዝቦቿን አክባሪ፣ በሥነ ምግባር የታነጸ እንዲሆን በማስቻሉ ብዙ ወዳጆችን አግኝቷል፡፡

    ከዚህም ሌላ የመናፍቃኑንና ቤተ ክርስቲያኒቱን እናድሳለን ብለው የተነሡትን የመናፍቃኑ ተላላኪ ቡድኖችን ሴራና የአክራሪ እስልምናውን እንቅስቃሴ በመረጃ አስደግፎ በማጋለጡ፣ ከክፉ ትምህርታቸው መመለስ ያልፈለጉ የተሐድሶ ቡድን አባላት ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ ስለተወሰነባቸው እና ሌሎችንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግሮች እየተከታተለ ለዕድገቷና ለብልጽግናዋ በመሥራቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆችን አፍርቷል፡፡

    ከዚህ በተቃራኒው የተሰለፉት ወገኖች ደግሞ ወጣቱን እንደጠፍ ከብት ወደ ማያውቀው የመናፍቃን አዳራሽ የመንዳት ልምዳቸው በመቋረጡና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት የሚያደርጉት ሥርዓቷን የማፋለስ እንቅስቃሴ፤ እንዲሁም አገልጋዮቿንና ምእመናኖቿን የማስኮብለሉ አካሔድ ማኅበሩ በክትትል በተለያዩ መረጃዎች ስለገለጠባቸው ማኅበረ ቅዱሳንን በጠላትነት በማየት ማኅበሩ እንዲፈርስ የማይቧጥጡት ዳገት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

    እነዚህ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች ለጥቂት ጊዜ ጋብ ብለው የነበሩ ቢሆንም አሁን ባገኙት አጋጣሚ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጀራዋን እየበሉ የሚኖሩ ወዳጆቻቸውን በማጠናከርና በማስፋፋት በሚሊዮን የሚቆጠር በጀት ከወዳጆቻቸው ተመድቦላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓት ለማዛባትና በጎቿን ለመበታተን ሌት ከቀን እየሠሩ ነው፡፡

    ይኼ ዕቅዳቸው የሚሳካው እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እምነትና ሥርዓት መጠበቅ የሚቆረቆሩ ማኅበራትን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አጀንዳ በማድረግና እንዲበተኑ ክፉ ሥራ በመሥራት ነው፡፡ እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ይሔንን ከንቱ ቅዠታቸውን እውን ለማድረግም በቤተ ክርቲያኒቱ የተለያየ ሓላፊነት ላይ የሚገኙትን የዓላማቸው አስፈጻሚዎች ሁሉ እየተጠቀሙ እንደሚገኙም ይታወቃል፡፡

    ከዚህም ሌላ ድብቅ ዓላማቸው እንዲሳካ ተላላኪዎቻቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚሆን ነገር ግን ስውር ዓላማ ያለው ማኅበር እንዲመሠርቱና ከዚህ በፊት ከንቱ ተግባራቸው ታውቆ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታግደው የነበሩ ማኅበራት ሁሉ ከሞቱበት እንዲቀሰቀሱ እየሠሩም እያደረጉም ይገኛሉ፡፡

    በቤተ ክርስቲያን ስም ድብቅ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ያቋቋሟቸውና የሚያቋቁሟቸው፣ ማኅበራትንም ሕጋዊ ዕውቅና ለማሰጠት እንዲያመቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ከኔ ሌላ ሌሎች አያስፈልጉም የሚል አቋም ያለው ማኅበር እንደሆነ ያስወራሉ፡፡

    በእርግጥ ማኅበረ ቅዱሳን በትክክል የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓትና ደንብ ተከትለው በሚቋቋሙት ማኅበራት ላይ የማኅበሩ ጠላቶች ከሚያወሩትና ከሚያስወሩት አሉባልታ የተለየ አቋም አለው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርቲያን የሁለት ሺሕ ዓመታት ታሪክ ያላት ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ትሁን እንጂ መንበሯ ከሊቀ ጵጵስና ደረጃ ወደ ፕትርክና ለማሳደግ አንድ ሺሕ ስድስት መቶ መራራ ዓመታትን አሳልፋለች፡፡ በዚህ ማለፏ ደግሞ ሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት የደረሱበት ዘመናዊ የአደረጃጀት ደረጃ ላይ ለመድረስ አልቻለችም፡፡ ልጆቿንም ጊዜው በሚጠይቀው መንገድ ለመምራት ሳትችል ስለቆየች እነዚህን ክፍተቶች የሚሞሉ አንድ አይደለም በርካታ ማኅበራት እንደሚያስፈልጓት ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ነገር ግን እኩያኑ እንደሚሉት ሳይሆን እነዚህ ማኅበራት ሲቋቋሙ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ዕድገትና የአገልግሎት ሥምረት የሚንቀሳቀሱ ተልእኮአቸውና ዓላማቸው ተለይቶ የሚታወቅ፣ መንፈሳዊ ተግባርን ብቻ የሚፈጽሙ፣ የሚናበቡና በስልት ለአንድ ውጤት የሚተጉ ሊሆኑ ይገባቸዋል የሚል ጽኑ አቋም አለው፡፡

    ይሔንን አቋሙን ደግሞ በርካቶች የሚደግፉት እንደሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ የመናፍቃኑ ተላላኪዎች በቤተ ክርስቲያን ስም ያቋቋሟቸው ማኅበራት ከዚህ በፊት በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥለውት የሔዱት ጠባሳ የሚታወቅ ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን በማኅበራት ላይ ግልጽ አቋም አለው፡፡ ከዚህም ሌላ እነዚህ የውስጥ ዐርበኞች ይኽ ስውር ዓላማቸው ያልታወቀባቸው ይመስል ማኅበሩን ለመወንጀል የማይለጥፉለት ታፔላ፣ የማይለፍፉት ወሬ የለም፡፡ ነገር ግን እነዚህ የቤተክርስቲያን ጠላቶች ስለማኅበሩ የሚያወሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ እና ሁሉም የሚገነዘበው ግልጽ እውነታ መሆኑን ባለማወቃቸው እናዝናለን፡፡

    ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ስውር ዓላማ የለውም፤ ከማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ የጸዳና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያን ሳያዛንፍ እየሠራ ያለ፤ በተሰጠውም መተዳደሪያ ደንብና ሓላፊነት መሠረት ከአባላቱና ከበጎ አድራጊ ምእመናን የሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪ እያሰላ በውስጥ ኦዲተሮችም እያስመረመረ በመሥራት ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ማኅበር እንጂ በወሬ የሚኖር አይደለም፡፡ ይሔንን አሠራሩንም ቀርቦ ማየት ይቻላል፡፡ አባላቱም በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው በጉልበታቸውና በመላ ሕይወታቸው ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግሉ እንጂ እንደ መናፍቃኑ ተላላኪዎች ለሆዳቸው ያደሩ፣ ሆዳቸው አምላካቸው የሆነባቸው እዚህም እዚያም ደሞዝ የሚቀበሉ አይደሉም፡፡

    ማንኛውም አካል እንዲያውቅልን የምንፈልገው ሐቅ ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰጠው ሓላፊነትና አባላቱም ለገቡለት ቃል ኪዳን ሃይማኖታቸው የሚፈቅደውን መስዋዕትነት ለቤተ ክርስቲያን ልዕልናና ክብር ለመክፈል የተዘጋጁ እንጂ በተዛባ አመለካከት ወደ ኋላ የሚያፈገፍጉ አለመሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

    ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱ የሚታይ አሠራሩም ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም የመናፍቃኑ ተላላኪዎች መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከአገልግሎታችን አንዲት ጋት ወደ ኋላ እንደማይመልሰን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፡፡ ርእይና ተልእኮአችንን ለማሳካት ዛሬም ነገም እንሠራለን፤ ትናንትን ያሻገረን እግዚአብሔር ዛሬንም ያሳልፈናል

    ReplyDelete
    Replies
    1. በቅድሚያ ይህ መግለጫ መሰል አስተያየት የማኅበሩ ነው ወይስ የአስተያየት ሰጪው? ምን እያደረገ እንዳለ የሚታወቀውን ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲህና እንዲያ ነው በማለት ስለማኅበሩ የሌለ ሥዕል ሰጥቶና ማኅበሩን በሌለበት የቅድስና ማማ ላይ ለመስቀል ይህን ያህል መዘብዘብ ራስን ትዝብት ላይ ከሚጥል ያለፈ ፋይዳ የለውም። አስተያየት ሰጪው ስለማኅበሩ መግለጫ ከመስጠት ይልቅ በተጻፈው ጽሑፍ ላይ ተመሥርቶ ማኅበሩ ከአቡነ ጎርጎርዮስ ጋር ስለመተዋወቅ አለመተዋወቁ ሊነግረን በተገባ ነበር። እርሱ ግን ይህን ጉዳይ ፈጽሞ አላነሣውም። ለእኔ ይህ የሚነግረኝ በጸጋ የተጻፈው ጽሑፍ ማኅበሩ ያልጠበቀውና ያላሰበው እንደሆነበት ነው። የተነሡት ሁለቱ ነጥቦች በቂ ናቸው። ማኅበሩና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በዘመንም በትምህርትም ፈጽሞ አይተዋወቁም። አስተያየት ሰጪው /ማኅበሩ(?)/ ለዚህ ምላሽ ቢኖራቸው ኖሮ ይነግሩን ነበር። ስለሌላቸው ግን በሰው ፊት ያልተገለጠውን እነርሱ ብቻ ዘወትር እንደ ዳዊት የሚደጋግሙትን የማኅበሩን ግብዝነት የተሞላ ኩሸት ይኳሻሉ።
      በአስተያዩ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን ጠላት ያፈራው ተሐድሶዎች “ወጣቱን እንደጠፍ ከብት ወደ ማያውቀው የመናፍቃን አዳራሽ የመንዳት ልምዳቸው በመቋረጡና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት የሚያደርጉት ሥርዓቷን የማፋለስ እንቅስቃሴ፤ እንዲሁም አገልጋዮቿንና ምእመናኖቿን የማስኮብለሉ አካሔድ ማኅበሩ በክትትል በተለያዩ መረጃዎች ስለገለጠባቸው ማኅበረ ቅዱሳንን በጠላትነት” ይመለከቱታል ያለው አስገራሚ ነው፡፡ ለሰዎች ከቤተክርስቲያናቸው መኮብለል ዋና ተጠያቂው ተሐድሶዎች ሳይሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ነው። የእኔ አባል ካልሆነ ሰው በቀር ሌላ ሰው አልይ፣ ሌላ ማኅበር በተለይም ሃይማኖተ አበውን ፈጽሞ አልይ የሚል ስለሆነ ብዙዎች በሐገ ወጥ መንገድ እናት ቤተክርስቲያናቸውን ጥለው ወደ ሌላ ለመፍለስ ተገደዋል። ስለዚህ በራሳቸው መንገድ ከወጡትና ወደሌላ ከሄዱት ይልቅ “በሃይማኖት ፈረሰ” ሰበብ ማኅበረ ቅዱሳን የገፋቸውና ከእናት ቤተክርስቲያናቸው ሳይወዱ በግድ የለያቸው ጥቂቶች አይደሉም። ዛሬ የወንጌልን እውነት በመግለጥ የጎን ውጋት የሆኑበትና የጨለማ ሥራውን በወንጌል እውነት እየገለጡ ያሉት ያለስማቸው ስም ሰጥቶ ያሳደዳቸውና ስልታቸውን ቀይረው በእናት ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ ለቤተክርስቲያኗ እውነተኛ ተሐድሶ እየተጉ ያሉ ልጆቿ ናቸው። ዛሬ ነገሩን ማኅበረ ቅዱሳን የሚቆጣጠረው አይደለም።
      ባለፈው መስከረም ግሸን ተገኝተው ስለተሐድሶ ግንዛቤ እናስጨብጣለን ያሉት የማኅበሩ ሰዎች እነ ያረጋልና ዘመድኩን “ተሐድሶ ተሐድሶ ትላላችሁ ለምን ተሐድሶ የተባሉትን አታሳዩንም?” ተብለው ሲጠየቁ፣ “እገሌና እገሌ የሚባል አይደለም የተሐድሶ መንፈስ በቀዳሾቻችን፣ በሰባኪዎቻችን፣ በመዘምራኖቻችን፣ በሰንበት ተማሪዎችችን፣ … ውስጥ ገብቷል” የሚል ምላሽ ነበር የሰጡት። በርግጥም ዛሬ በወንጌሉ እሳት የተቀጣጠሉ ከማኅበረ ቅዱሳን እይታም ሆነ ቁጥጥር ውጪ ናቸው። እንዳሉትም “መንፈሱን” በስለላም ሆነ በሌላ የተለመደ ስልታቸው ሊይዙት አይችሉም። አገልግሎቱ ወደዚህ አቅጣጫ ያደገው ግን ማኅበረ ቅዱሳን ሲያደርግ በቆየው ግፊት ነው። ዛሬ እንደ ቀድሞው ስላይደለ ማኅበረ ቅዱሳን በዚያው ስልት መዋጋት አይችልም።
      “ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ስውር ዓላማ የለውም፤ ከማንኛውም የፖለቲካ አስተሳሰብ የጸዳና በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያን ሳያዛንፍ እየሠራ ያለ፤ በተሰጠውም መተዳደሪያ ደንብና ሓላፊነት መሠረት ከአባላቱና ከበጎ አድራጊ ምእመናን የሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪ እያሰላ በውስጥ ኦዲተሮችም እያስመረመረ በመሥራት ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ማኅበር እንጂ በወሬ የሚኖር አይደለም፡፡ ይሔንን አሠራሩንም ቀርቦ ማየት ይቻላል፡፡” እዚህ ውስጥ ምን እውነት አለ? ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ እንዳለው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። የሰበሰበውን ገንዘብ ገቢና ወጪውን ለማደራጃ መምሪያው ለማሳወቅ ፍላጎቱም ዝግጁነቱም እንደሌለው አስመስክሯል። ጠቅላይ ቤተክህነት የጻፈለትን ደብዳቤም ውድቅ ማድረጉና በእንቢታው መጽናቱ ከዚህ ቀደም ተገልጾአል። ስለዚህ ምናለ እውነታውን ብንነጋገር።

      Delete
  9. ወንድሜ ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል፤ እንዳንተ ያሉ ክርስትና የገባቸውና እግዚአብሔር የባረካቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች አንድ አሥር ወገኖች ቢኖሩ እኮ ቤተክርስቲያናችንና እምነታችን እንዴት በምህረት እንደምትጎበኝ እጅግ እምነቴ ፅኑ ነው። መቼም እንዴት አድርጌ ላንተ ያለኝን አድናቆት ለመግለፅ ቃላቶች ያጥሩኛል።
    እንደው ግን በጥቅሉ እግዚአብሔር እስከ መጨረሻው የፀና የክርስቶስ አገልጋይ ያደርግህ ዘንድ የዘወትር ፀሎቴ ነው።

    አላዋቂዎችና ግብዞች ፈሪሳዊያን \ማቅ\ በክርስቲያንና በክርስትና ላይ የሚሠሩትን ተንኮል ከማጋለጥ አትቆጠብ። የሚፈልጉትን ሁሉ በአንተ ላይና አንተን በመሰሉ የተዋህዶ ልጆች ላይ ቢናገሩ ምንም አይሰማህ፣ ያመንከውን እውነትና የቆምክበትን አለት መሠረቱ ፅኑ መሆኑን ታውቃለህና። እንኩአን እኛን ደካማዎችንና ታናናሾችን ይቅርና፤ ለአምላካችን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንኩአን ያላረፉ የእፉኝት ልጆች ናቸውና።

    አንተ ግን ወንድሜ አይዞህ እግዚአብሔርን ይዘሃልና ፈፅሞ ብርታቱን ይሰጥሃል። እግዚአብሔር ተዋጊ ነው። የምትፅፋቸው ፅሁፎች ሁሉ እጅግ በጣም ጠቃሚና አስተማሪዎች ናቸው። ነቀፋና ስድብ ቢመጣም እንኩአን ከጥፋት ልጆች ከማቅ መሆኑን እወቅ። አሁን አሁንማ ማንነታቸው ስለተነቃባቸው እኔ ወይም እኛ የማህበሩ አይደለንም ግን እንደግፋቸዋለን የሚል ራስን የደበቀ አንጋገር ተጀምሮአል። ገና ገና እንደ ጴጥሮስ ይህ የምትሉትን ማህበር አላውቀውም የሚሉበት ጊዜ ይመጣል። የተመሠረተው፣ የኖረው በክፋት፣ በአመፅ፣ በስውር ሴራ ነውና ለሰይጣንና ለሠራዊቱ በተዘጋጀው እሳት ውስጥ መጣላቸው አይቀርም። ማቅ የአውሬው ምልክት ማህበር በመሆኑ ለክርስቲያኖች ፈተና መሆኑ ግልፅ ነው። ላላወቁትና በጭፍን ለሚከተሉት ማሳወቅና መገለፅ ያስፈልጋል። ሌባን ሌባ ካላሉት ከመስረቁ አያርፍምና።
    በተረፈ ዲ\ሙሉጌታ እግዚአብሔር ዘወትር ከሰይጣን ፈተና ይጠብቅህ ትላለች በክርስቶስ እህትህ።

    ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

    ReplyDelete
  10. man you are good. it is a very nice explanation. this people must understand the truth if they want to be the follower of the truth.

    ReplyDelete
  11. you are smart man.

    ReplyDelete
  12. እህሳ ኤፍሬም ወዴት ነህ? መልስ የለም። ነው ልክህን ስታውቅ ጭንቅላትህን አፈር ውስጥ ዸበክ?

    ReplyDelete
    Replies
    1. እናንተ ማቅ እንዲህ የምታብጠለጥሉት እነማናችሁ
      ማቅ ጥፋት ቢኖርበት እንኳን መናገር ያለባችሁ እውነትን እንጂ መልካሙን ነገር ደብቃችሁ አይደለም
      እግዚአብሔት ብዙ ሐጢአታችንን ደብቆ ጥቂቷን ጽድቃችንን ይዞ ምህረቱን ያበዛልናል
      እኛ ደግሞ በተቃራኒው ብዙውን የሰውን መልካም ስራ በትንሽ ጥፋት መበረዝ መልካሙን ስም ማጥፋት ይሆንልናል
      ይሔ የሐጢዓት ብዛት ደግሞ አሣልፎ ለጠላቶቻችን እየሰጠን መሆኑን እወቁ
      ሁላችን በአንዲት ኦርቶዶክስ ስር ከሆንን ልብ ብለን ልናስብ ይገባናል
      መወነጃጀል የትም አያደርስም
      ቴክኖሎጂው ተመቸን ብለን ወደ ተራ ስድብ መሔድ ያለብን አይመስለኝም

      Delete
  13. ay kentu mignot! Le mk gin tsegawn abezachihulet bertu ketilu awgizut.

    ReplyDelete
  14. Yidres le diyaqon mulugeta;
    From your writings I know you have a difference with MK by proxy to its members. However members are different from each other.
    I read here what you wrote about Ephrem. I know from your writings that you do not know him at all in his spiritual as well as his other life. About his kiristina hiwet fetariw bimesekir yishalal. Yenem miskirinet yesew yihonalina. Please tinish te aqibo adirig in addressing people.
    For your info I am not a member of MK. I commented here based on my knowledge of the situation.

    ReplyDelete