Thursday, April 25, 2013

የቤተ ክህነቱ የሰሞኑ ሁኔታ እና የማኅበረ ቅዱሳን ጫጫታ



 http://awdemihreet.blogspot.com/
ከጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ወዲህ በአሉበት ሁኔታ መቆየት አለመቆየታቸው እያሰጋቸው የመጣው አቶ ተስፋዬ ውብሸት እና አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ ከሥራ ከመሰናበታቸው በፊት ጠቀም ያለ ገንዘብ ለማግኘት እያደረጉ ያለው እንቅስቃሴ ሁሉ እየከሸፈባቻ ሲቸገሩ ያላቸውን ቀሪ የገንዘብ ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚያስደስት እቅድ ይነድፋሉ፡፡ እሱም ለቅዱስ ፓትርያርኩ የውጭ ግንኙነት ኃላፊን ከማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች መካከል መንግስት ሾመልዎ በማለት ማስቀመጥ ነው፡፡
ይህንን እቅዳቸውን ከማኅበሩ አመራር ጋር ከተነጋገሩበት በኋላ በአዲስ አበባ መስተዳድር የሚሰራውን አቶ ታምሩ አበራ የተባለውን ግለሰብ ያጫሉ፡፡ ይህን ግለሰብ ለፓትርያርኩ መንግስት መደበልዎ ብሎ ማቅረብ እና ከዚያም በመንግስት ስም ተከልሎ የማኅበረ ቅዱሳንን ፍላጎት በመንግስት ስም ለማስፈጸም  አስፈላጊውን ሁሉ አድርገው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ያቀርባሉ፡፡ ይህ አካሄድ እውነት እንዳልሆነ የተረዱት የቤተክርስቲያን ልጆችም ሁኔታውን በትኩረት በመከታተል ሀሳቡን የሚያከሽፍ እንቅስቃሴ ይጀምራሉ፡፡ እንቅስቃሴው ውጤት አግኝቶም መንግስት የመደበውም ሆነ የሚመድበው ሰው እንደሌለ ለቅዱስ ፓትርያርኩ በአቶ አባይ ጸሀዬ በኩል ያስታውቃል፡፡ 

በዚህ የተናደዱት እነ ተስፋዬ እና እስክንድር ከማኅበረ ቅዱሳን አንጃ ብሎግ ከሆነችው ሐራ ተዋህዶ ጋር በመቀናጀት የስም ማጥፋት ሥራውን ጀመሩ፡፡
ሀራ ተዋህዶ ሲቆጫት ሲያንገበግባት፣ የሚያደርጋትን ሲያሳጣትና ማኅበረ ቅዱሳን የፈለገው ነገር አልሳካ ሲላት ያረረውንም የመረረውንም፣ ያልተባለውንም ነገር ሁሉ “ሰበር” ደንገር እያለች እንደ ታላላቅ ወንድሞችዋ እነ ደጀ ሰላም መዘባረቅ ጀምራለች፡፡

ያለሥፍራቸው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቦታ የሚፈልጉት እና ያለአቅማቸው ቤተ ክርስቲንያንን ለመምራት የሚፈልጉት የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች በቤተክርስቲያን ትምህርት ዕውቀትም ሆነ በአስተሳሰብ ሙሉነት ያላቸውን የቤተክርስቲያን አባቶችን በመተቸት እና ስፋራችሁን ልቀቁ እና የላመውን አቡኩተን ያማረውን አበላሽተን ብቃታችንን እናሳያችሁ በሚል ደንባራ ሀሳብ እየተውተረተሩ ይገኛሉ፡፡
በዚህ እንቅሰውቃሴ ላይ የጎላ ሚና ያላቸው እነ እስክንድር ቤተክርስቲያንን እንዴት እየቀለዱበት እንደሆነ ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር እናቅርብ፡፡
የእስክንድር አባት ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ያላቸው በጥሩ ሥርዓተ ምንኩስና ይኖሩ የነበረ እና ቤተ ክርስቲያንን ያስተዳድሩ በነበሩበት ወቅት በቤተክርስቲያን በነበረው የመጀመሪያው የተሀድሶ እንቅስቃሴ ውስጥ የነበሩ ሲሆን፣ በዚሁ አቋማቸው ምንኩስናን አፍርሰው አግብተው 6 ልጆችን  ወልደዋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤ ያዥ የሆኑት የእስክንድር አባት ሊቀ ትጉሃን ገብረ ክርስቶስ ምንኩስናቸውን ካፈረሱ በኋላ አቶ ተብለው ከሚጠሩ በሚል ሊቀ ትጉሃን የሚል ለምዕመናን የሚሰጥ ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ምንኩስናው የከበደው ሰው ለቤተክርስቲያን አስታውቆ በህጋዊነት መወሰን ስለሚችል ማግባታቸው ስህተት ነው ባንልም ከትዳር በኋላ በምንኩስና ጊዜ የነበራቸውን ቅድስና ጠብቀው መኖር ግን አልቻሉም፡፡ ከህጋዊ ባለቤታቸው 6 ልጆችን ቢወልዱም እንኳ ከበርካታ ሴቶች ጋር ያልተገባ ግንኙነት እንዳላቸው ልጆቻቸውን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ይናገራሉ፡፡ እሳቸው ለቤተ ክህነቱ ባላቸው ቀረቤታም ይሰራበት ከነበረው ቀበሌ በብቃት ማነስ የተባረረው ልጃቸው እስክንድርን በቤተ ክህነት እንዲቀጠር አስደርገዋል፡፡ እስክንድር በዓለማዊውም በመንፈሳዊም ትምህርት ልበ ሰንካላ መሆኑ ሲታወቅ በዓለማዊ ትምህርት 12ኛ ክፍልን ያልጨረሰና በመንፈሳዊ ትምህርት ደግሞ የዘወትር ጸሎትን እንኳ በቅጡ መድገም የማይችል ሰው ነው፡፡ እንዲህ ያለው ግለሰብ በሞላ ጨዋነቱ ላይ ሥልጣን ተደርቦለት በመንፈሳዊ ትምህርት ቢጤዎቹ ከሆኑት ከማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች ጋር በመሆን ቤተክርስቲያንን እያመሰ ይገኛል፡፡
እስክንድር የተቀመጠበት ስልጣን በሕገ ቤተክርስቲያንም ይሁን በቃለ ዓዋዲው የማይታወቅ  ሲሆን ባለቤቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዝን ዜና አንባቢ ስለሆነች ሙያ በትዳር ይተላለፍ ይመስል የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡ በነ ዳንኤል ክብረት የሚመራው የማኅበረ ቅዱሳን አንጃ የተከሰተችው ሐራ ተዋህዶ በዳንኤል ክብረት የልብ ወዳጅ አሉላ ጥላሁን ዘጋቢነት እና በነ እስክንድር ገብረክርስቶስ ወሬ አመላላሽነት ሥራ ከጀመረች ወዲህ በእስክንድር አማካኝነት በርካታ ወሬዎችን የምታገኝ ሲሆን የተገኘውን ወሬ በብዕሩ እየቆለመመ እና ሀቁን እየጠቀጠቀ በመጻፍ በሚታወቀው አሉላ አማካኝነት ወሬው ተዛብቶ እንደሚጻፍ ይታወቃል፡፡ እስክንድር ለወታደር ነኝ ባይዋ ሐራ በሰራው ውለታ ምክንያትም ሀራም ሰሞኑን ገልጽ የሆነ የሙስና አሰራር የነበረበት የመጽሔት ማሳተሚያ የእስፖንሰር ሺፕ ጥያቄ በፓትርያርኩ በመታገዱ ለደረሰበት የልብ ስብራት ማካካሻ የሚሆን ጭብጡን የሳተ የአለሁልህ  ዘገባ አውጥታለታለች፡፡
በፒያሳና በአራት ኪሎ አካባቢ ከቀኑ 6 ሰዓት ሳይሆን አረቄ ቤት በመሾም የሚታወቀው የዚህ ግለሰብ ታናሽ ወንድምም በአቶ ተስፋዬ ውብሸት አማካኝነት በኪራይ ቤቶች ተቀጥሮ ለተስፋዬ እና ለእስክንድር ገንዘብ የማቀባበል ሥራውን በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡
ሌላኛዋ የእስክንድር እህት ደግሞ ብዙ ግለሰቦችን እና መነኮሳትን ባልተገባ ሥራ በማባባል የምትታወቅ ስትሆን ይበልጥ አባቶችን እንድታስት በያሬድ ቤተክርስቲያን ተቀጥራ እየሰራች ትገኛለች፡፡
በርካታ ከመንፈሳዊ  ኮሌጅ ተመርቀው የወጡ ወጣቶች ሥራ አጥተው እየተንገላቱ ባሉበት በዚህ ወቅት አንድ ሥራ ብቻ ለምን ባለኝ ሥልጣን ተጠቅሜ ሥራ አስጨምርልሻለሁ እንጂ በማለት ኢቲቪ የምትሰራው የእስክንድር ባለቤት በቃሊቲ ገብርኤል በጸሀፊነት ተቀጥራ እየሰራች ትገኛለች፡፡
እናታቸው እንኳ በስተርጅና ቤት እንዳይውሉ በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በጽዳትነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
እነዚህን ብቻ ገለጽን እንጂ የአጎት እና የአክስት ልጆቹን ጨምሮ ከ24 የሚበልጡ የእስክነድር ቤተ ዘመዶች በተለያዩ አድባራት እና ገዳማት ተቀጥረው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የእስክንድር ቤተሶቦች ያልተቀጠሩባቸውን አብያተ ክርስቲያናት የተስፋዬ ቤተሰቦች እንዲቀጠሩበት በማድረጋቸው እስክንድር እና ተስፋዬ በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚሰራውን ሥራ ሁሉ እናውቃለን በቂ ሰላይ መድበናል እያሉ መናገር ጀምረዋል፡፡ እንዲያውም በቅርቡ ተስፋዬ “እንኳን ቤተክህነት መንግስት እንኳ ሊበጥሰው የማይችለውን ኔት ወርክ ዘርግተናል” እያለ ሲናገር ተስምቷል፡፡
አሁን ያለው ሁኔታ አቶ ተስፋዬ ውብሸት እና እስክንድር ገብረክርስቶስን በቤተክህነቱ የመቆየት እድላቸውን ስላጠበበባቸው ተስፋ በቆረጠ ስሜት ለወረዳ ምክር ቤት ለመመረጥ ተወዳድረዋል፡፡
እነዚህ ሁለት ግለሰቦች በመንፈሳዊ ዕውቀት የጨዋዎች ዋሻ ከሆነው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር  በመሆን በርካታ ለቤተክርስቲያን የሚሰሩ የቤተክርስቲያን ልጆችን ስም በማጥፋት ከየመምሪያው እንዲፈናቀሉ በማድረግ መምሪያዎችን በአቶዎች እንዲሞሉ አድርገዋል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ በታሪክዋ እንደዚህ ጊዜ በአቶዎች ተሞልታ አታውቅም፡፡ ይህም የሆነው በጥቅምቱ ሲኖዶስ ወቅት አቶ ተስፋዬ የያዘው ስልጣን ለአቶዎች የሚገባ አይደለም ይልቀቅ ተብሎ ከተወሰነበት በኋላ የአቡነ ፊሊጶስን እግር ይዞ በማልቀስ በቦታው እንዲቆይ የተወሰነለት አቶ ተስፋዬ እኔን በአቶነቴ ከወቀሳችሁ መምሪያውን ሁሉ በአቶዎች እጥለቀልቅላችኋለሁ በማለት ባደረገው እንቅስቃሴ ነው፡፡
ይህ ግለሰብ በምርጫው ወቅት አቡነ ማትያስ እንዳይመረጡ ከፍተኛ በጀት መድቦ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀራረቡ ነው የሚሻል በማለት ከፓትርያርኩ ጋር ልዩ ቅርርብ እንዲፈጥሩ ለማድረግ ቢያንስ በሳምንት ሁለት ቀን ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንዲገቡ በማድረግ በማኅበሩ የተሰጠውን ቤተክርስቲያኗን በማኅበረ ቅዱሳን እዝ ስራ የማዋል ተልእኮን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ፓትርያርኩ የአቶዎቹ አካሄድ ስለገባቸው እና በተወሰነ ደረጃም ፊት ስለነሱዋቸው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመመካከር ለማኅበሩ የሚሆን ልዩ  ቦታን ፈጥረው መንግስት የመደበልዎ በማለት በቃለ አዋዲውም ሆነ በሕገ ቤተክርስቲያን በማይታወቅ የመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ የሚል ልዩ የስራ መደብ በመፍጠር በአዲስ አበባ መስተዳድር ይሰራ የነበረ የማቅ ሰው እንዲሾምበት አድርገዋል፡፡  
ይህ መደብ በቤተክርስቲያን ሥርዓት የማይታወቅ መሆኑ ሳያንስ የውጭ ግንኙነት ኃላፊውን እና የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊን ሊቁን መጋቤ ሰናይ አሰፋን ትተው የዘወትር ጸሎት እንኳ ያልደገመውን ሰው አምጥተው መንግስት የመደበልዎ በማለት አሹመዋል፡፡
እኚህ ግለሰብ ቢመደቡ እንኳ ሊመደቡበት የሚችሉት በቅርቡ ፓትርያርኩን እንዲይዙላቸው በነተስፋዬ ውብሸት ተመድበው የነበሩት እና በጉቦ ቅሌት የተባረረው አቶ ሰለሞን ቶልቻ የነበረበትን የውጭ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ቦታ እያለ ለምን አዲስ ቦታ ተቋቁሞ አዲስ በጀት ተበጅቶ መኪና እና ቢሮ ተዘጋጅቶ እንዲመደብ ማድረጉ ራሱን የቻለ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው፡፡  
በአሜሪካ ያሉት አቡነ መልከ ጼዴቅ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው እኚሁ ግለሰብ ፓትርያርኩን በምርጫው ወቅት በአስተዳደር ችሎታ ከወቀሱት ከአባ ሳሙኤል እና ከአባ አብርሃም ጋር እንደሚግባቡ ሲታወቅ ምናልባትም ለአባ ሳሙኤል መመረጥ በከፍተኛ ሁኔታ ሥራ ሲሰሩ ከነበሩት ከነተስፋዬ እና እስክንድር ጋር ያለው መግባባት እና ቅርርብ እና የአባ አብርሃምን እና የአባ ሳሙኤልን ትንቢት እውን ለማድረግ የተቀጠረ ግለሰብ ነው የሚሉ ወገኖችም አልጠፉም፡፡
ይህ ቦታ አላማው ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ የሚገቡ ደብዳቤዎች ሁሉ ከቅዱስ ፓትርያርኩ በፊት ይህ ግለሰብ እንዲያያቸው እና የማኅበረ ቅዱሳንን ጥቅም የማያስከበሩ ከሆነ ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ እንዳይቀርቡ ለማድረግ እንዲሁም ግለሰቡ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ፈጥሮ ተሰሚነት ካገኘ በኋላ፦
Ø ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ሊነሱ የሚችሉ ተቃውሞዎችን ሁሉ ለማፈን
Ø መንግስትም ሆነ ቤተክህነት በማኅበሩ ላይ በቅርቡ ሊወስዱ የሚችሉትን ህጋዊ እርምጃ ለማስቀረት
Ø መንግስት በማህበሩ ላይ ያለውን አቅጣጫ ለዘለቄታው ለማስቀየር
Ø የቤተክርስቲያኒቱ አንድነት እንዲጠበቅ ወንጌል እንዲሰበክ የሚደክሙትን እና ለአባቶች ታዘው ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑትን በአለማዊውም ሆነ በመንፈሳዊው ትምህርት ብቃቱ ያላቸውን አገልጋዮች ከሥፍራው ለማግለል እና የተባሉትን ሰምተው የታዘዙትን ፈጽመው የሚኖሩ እንደ ተስፋዬ እና እስክንድር ያሉ እበላ ባይ ጎጋዎችን በየቦታው ለማስቀመጥ
Ø ማንኛውንም ሥራ ማኅበሩ ሳያውቀው እንዳይሰራ ለማድረግ
Ø ፓትርያርኩ ሊፈጥሩ የሚችሉትን ለውጦች ለማጨናገፍ
Ø በነ ተስፋዬ የሚመራውን የማፍያ ቡድን ዕድሜ ለማራዘም
Ø በፓትርያርኩ ተቀባይነት ያላቸውን ማኅበሩ ህግ እና ሥርዓት አክብሮ እንዲሰራ የሚታገሉ የቤተክርስቲያን ልጆችን አጣልተው የሚፈልጉትን ለማድረግ መንግስትን ታከው በመንግስት ስም እየነገዱ በዓላማ ያስገቡት ግለሰብ ነው፡፡
ይሁን እንጂ የቤተ ክረስቲያኒቱ እውነተኛ አገልጋይ የሆኑ እና ማኅበሩን ከእነ እኩይ አጀንዳው በመታገል የሚታወቁ የቤተክርስቲንዋ አባቶች እና ወንድሞች ከህገ መንግስቱ አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 27 አንጻር እኒህን ሰው በትክክል መንግስት እንዳልመደባቸው፣ ሊመድባቸው እንደማይችል እና ከመደባቸውም ትክክለኛ አካሄድ እንዳልሆነ በማሳየት እና ከብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በመነጋገር እኚህ መጡ የተባሉት ግለሰብ ብቃት ካላቸው ለሲኖዶሱ ቀርቦ ሲኖዶሱ ሲያምንበት ብቻ እንዲቀጠሩ እንዲደረግ እንዲያደርጉ ባደረጉት ጥረት አቶ አባይ ጸሀዬ መጥተው ለቅዱስ ፓትርርኩ እና ለብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት መንግስት ሰው እንዳልመደበ እና እንደማይመድብም ገልጸው በመንግስት ስም የሚነግዱ የመንግስትም ሆነ የቤተክህነቱ ያልሆኑ የራሳቸው ልዩ አጀንዳ ያላቸው ግለሰቦች እንዳሉ አስታውቀው፣ መንግስት በስሙ የሚጠቀሙ ግለሰቦች እየበጠበጡት እንደሆነ እና እንዲህ ያለ አሰራር ላይ እጁን እንደማያስገባ አስረድተው እና ተገቢውን ምክር ሰጥተው መመለሳቸው ታውቋል፡፡ መንግስት ራሱን ያጠራል እናንተም ራሳችሁን አጥሩ በስማችን በሚነግዱት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በጋራ እንወስዳለን ብለዋል፡፡
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ህሊናቸውን ሜዳ ላይ ጥለው በልቡሰ ጥላ በሚንቀሳቀሱ ዘጋቢዎችዋ አማካኝነት ሐራ ዘተዋህዶ ከእውነት የራቀ ዘገባውን አላማው የማኅበረ ቅዱሳንን ህገ ወጥ አሰራር በመታገል በሚታወቁ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ስም ማጥፋት የሆነ ዘገባዋን አስነብባናለች፡፡
እንደሚታወቀው ሁሉ ሀራ ዘተዋህዶ አሁን ካለው የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ጋር የጥቅም ግጭት በፈጠሩ በነ ዳንኤል ክብረት እና አባይነህ ካሴ አንጃ የምትመራ መሆኑ ሲታወቅ፣ ዋነኛ ዘጋቢዋም አሉላ ጥላሁን ነው፡፡ ወሬ አመላላሹም ለደጀ ሰላም ዋነኛ ወሬ አመላላሽ የነበረው ማንያዘዋል ነው፡፡ ማንያዘዋል ከማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ሙሉጌታ ጋር ከፍተኛ ቅራኔ ላይ በመሆናቸው ባለፈው ክረምት በነበረው ምርጫ ከእኔ እና ከእሱ አንዳችንን ምረጡ ብሎ ያቀረበው ጥያቄ እሱ በፈለገው መልኩ መልስ ሳያገኝ በመቅረቱ የቂም ሱሱን ለማርካት ወደ አንጃው በወሬ አቀባይነት የተቀላቀለ ግለሰብ ነው፡፡
አካሄዳቸው ከቤተክህነትም ሆነ ከቤተመንግስት ጋር ሊያቆራርጣቸው እንደሚችል የተረዱት ተስፋዬ እና እስክንድርም በወሬ አቀባይነት እና የሰነድ መረጃዎችን በማቀበል ዋናኛ ተባባሪ ምንጮች ናቸው፡፡ አሁን ያለው አካሄድ ያሰጋቸው እነ እስክንድር አካሄዳቸውን ፊት ለፊት እየተቃመሙ የሚገኙትን የቤተክርሰቲያንዋን ሊቃውንት ተቃውመው ዘገባ አሰርተዋል፡፡
1.     ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን
ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን በሰንበት ማደራጃና መምሪያ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት የማኅበሩን እኩይ አሰራር ከሰው ቀድመው በመረዳት ህግ እና ሥርዓት አክብረው እንዲሰሩ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ የነበሩ አባት ሲሆኑ፣ የእኚሁን አባት ስም በከፍተኛ ደረጃ በማጥፋት ማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረው ይታወቃል፡፡ አስተዋይ እና ልበ ሰፊ የሆኑት እኚሁ አባት በአገልግሎት ትጋታቸው የሚታወቁ ሲሆን በቅድስና የሚኖሩ ለመሆናቸው ራሳቸው የማኅበሩ ሰዎች እንኳ ምስክር ናቸው፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን ለቤተክርስቲያን አንድነት እና ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ በቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉ ማኅበራት ቤተክርስቲያንዋን ከማገዝ ባለፈ አሁን ማኅበሩ እንደሚያደርገው የቤተክርስቲያንዋ ቁንጮ እኔ ነኝ የሚል አሰራር እንዳይኖራቸው ለማድረግ ሲታገሉ የነበሩ እና በዚሁም ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ የተካሄደባቸው አባት ናቸው፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው የራሱን ድረ ገጽ ከፍቶም ልዩ ልዩ ትምህርት እና ዜናዎች እንዲወጡበት አድርገዋል፡፡ አሁንም በተመደቡበት የስራ መደብ ቤተክርስቲያንን በትጋት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ቂም አይረሴ የሆነው ማቅ ግን በሁሉ ነገር ከእሳቸው ራስ ላይ አልወርድ እያለ እየተንገታገተ ይገኛል፡፡ በአንድ ወቅት አቡነ አረጋዊ በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ እንደተናገሩት “አባ ሠረቀ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ጠንቅቀው የተማሩ ቢጠየቁ መልስ መስጠት የሚችሉ ቤተ ክርስቲያን የምትኮራባቸው ሰው ናቸው፡፡”
2.    ንቡረ እድ ኤልያስ
በአሁነ ሰዓት የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርም ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ንቡረ እድ ኤልያስ በአስተዳደር ችሎታቸው እና በቤክርስቲያን ትምህርት ባላቸው ሙሉነት የሚታወቁ ናቸው፡፡ እኚህን በሊቅነታቸው አንቱ የተባሉትን አባት ሐራ ዘተዋህዶ የሌለ ስም በመስጠት እምነታቸውን እንኳ ለማሳጣት ያላሉትን እና ከቶውንም ሊሉት የማይችሉትን ቃል በመጠቀም ማኅበሩ ለእሳቸው ያለውን የጥላቻ ልክ አሳይታናለች፡፡
ንቡረ እድ ኤልያስ ማኅበሩን በከፍተኛ ደረጃ የሚታገሉ አባት ከመሆናቸውም በላይ የማኅበሩን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚመለከት ሰፋ ያላ ጥናት ያቀረቡ ሰው ናቸው፡፡ እኔን የተቃወመ ሁሉ ሰይጣን ነው በሚለው ማኅበረ ቅዱሳናዊ ባህል መሰረትም የማኅበሩ የቂም በትር አርፎባቸዋል፡፡
3.    ሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ
ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ በአንድ ወቅት “አንድ አድርገን” እንደዘገበችው ከማኅበሩ ምስረታ ጀምሮ ከማህበሩ ጋር የነበሩ እና ማኅበሩ አሁን ባለበት ደረጃ እንዲደርስ ቅርጽ ካስያዙ ሰዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ ማኅበሩ አካሄዱን በመለወጡ ያም ደግሞ ለቤተክርስቲያን አደጋ መሆኑ ታውቆዋቸው ወዲያውኑ ማኅበሩን ትተው የወጡ ግለሰብ ናቸው፡፡  ተዘግተው የነበሩ መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲከፈቱ ከቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ጋር በመሆን ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ገና ኮሌጁ እንደተከፈተ ኮሌጁ የመናፍቃን ማፍሪያ ነው እና ይዘጋ ብሎ በመጠየቁ ማህበሩን በመቃመም ከማኀበሩ ጋር ከፍተኛ ትግል ማድረጋቸው በወቅቱ በነበሩ ተማሪዎች ይነገርላቸዋል፡፡
በልማት ኮሚሽን እና በጠቅላይ ቤተክህነት በሰሩባቸው 6 አመታትም
-      የኤችኤይቪ መምሪያን በማቋቋም እና በመምራት መምሪያው አሁን ለደረሰበት ደረጃ አብቅተዋል፡፡
-      እንዲሁም የአለም አብያተ ክርስቲያናት ህብረት (WCC) እና የዓለም ሀይማኖቶች ለሰላም ወኪል ሆነው ከብዙ የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች ጋር በመሆን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝዳንት እና የዓለም ሀይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲመረጡ ታላቅ ተጋድሎ ፈጽመዋል፡፡ ማኅበሩ እንደሚለው ሳይሆን አሜሪካን ኢምባሲ በሚሰሩበት ጊዜ ባገኙት የትምህርት እና የስራ ዕድል ወደ አሜሪካ አገር ሄደዋል፡፡ አሜሪካን ሳሉም የአሜሪካን መንግስት በቤተ ክርስቲያን አካባቢ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት እና አሰራርዋንም ለመረዳት የቤተክርሰቲያንዋን ቋንቋ እና እንግሊዚኛ ቋንቋ የሚችል ሰው እንዲመደብላቸው በጠየቁት መሰረት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ጉዳይ ባለሙሉስልጣን ዋና ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነው በማገልገል የሚገኙት ሊቀ ስዩማን ኃለጊዮርጊስ በአንድ ወቅት በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ እንደተዘገበውም በሰሜን አሜሪካ በእነ ዶ/ር መስፍን እና “ቄስ” በላቸው የሚመራውን የማቅን የክፋት መረብ በመበጣጠስ ለውጭ አገር አይሰራም የተባለውን ቃለ አዋዲ ከሊቀ ጳጳሱ ከአቡነ ፋኑኤል ጋር በመሆን በአሜሪካ እንዲሰራ አድርገዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በአሜሪካ 22 ስቴት (ወረዳ) ቤተ ክህነት እና 3 አህጉረ ስብከት መኖሩ ይታወቃል፡፡

ሐራ እንግዲህ በስም ማጥፋት ዘመቻዋ የወቀሰችው እነዚህን ሰዎች ነው፡፡ ለወቀሳውም ብቸኛ ምክንያትዋ የማኅበሩን ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለምን ይታገላሉ የሚል ነው፡፡ ከእንዲህ አይነቱ መንፈሳዊ እውርነት ማኅበሩ የሚላቀቀው መቼ ይሆን?

3 comments:

  1. I am working in betekehenet. this is 100% true. eskender and tesfaye is the true enemy of the church.

    ReplyDelete
  2. የቤተክርስቲያን አባቶች ለምን ተስማምተው ተግባብተው አይሰሩም ከውጪ ንክኪ መህበር ምናምን ምን ይሰራል በጥባጭ እያል ንጹህ አይጠጣምና አባቶች ከጭቅጭቅ እርቀው ለሐገርና ለህዝብ እንዳይ ጸልዩ እንቅፋት ከሚሆን ገለል ማድረግና በራሱ መንገድ የማህበር ስራ ይስራ ገደብ ይኑረው በቤተክህነት መዋቅር ውስጥ ምን ድርሻ አለው እሱ ከማህበርነት ውጭ እነሱ ስለፈቀዱለት ነው ገብቶ የሚበጠብጠው በአለም አልበቃ ብሎዋቸው ቤተክህነት ደግሞ እንበትብጥ ብለው ነው የተነሱት አምላክ ልቦና ስጣቸው ስራቸው ሁሉ ፍንዳታ የሚባለው አይነት ያልበሰለ ሰው የሚሰራው ስራ አዋቂ መስለው ማማዛዘን የጎደላቸው ወይም መቀበት የማይፈልጉ ናቸው ከአብዛኛው መሀበርተኛ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ የተወሰኑ ናቸው ግንምንያደርጋል ለነሱ ተው የሚላቸው ተሐድሶ ስም አለው እነአያልቅበት ናቸው ፡፡
    እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ አሜን!!!!!!

    ReplyDelete