Saturday, March 15, 2014

ፍርድ ቤት ችሎት ላይ አይደለም የተቀመጠው “አሜን!” የማይለው፡፡

ከዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
(መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ወደ አውደ ምህረት ከተመለሰ በኃላ እርር ያሉት የማቅ ብሎጎች እሱን “መናፍቅ” ለማለት የሚያስችለን ነው ብለው ያመኑበትን ስድ ስድብ እየደረደሩ ይውጣልን ይጥፋልን የሚያሰኝ ዛር ነግሶባቸው እየተክለፈለፉ ይገኛሉ፡፡ መቸም ለዲያቢሎስ ጭንቀቱ የሚድነው መብዛቱ እና የሱ መንግስት ጠላቶች የመንግስቱን ሀሳብ ሲያፈርሱ ማየት ነው፡፡ ተከታዮቹም በጌታቸው መንግስት ላይ የተቃውሞ ሀሳብ ያለውን ክርስቲያን ሁሉ ማሳደድን እምቢኝ ብለው አያውቁም፡፡
ለማኅበረ ቅዱሳን መሪዎች የዲያቢሎስን አሰራር ለማፍረስ በተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ አምኖ የዲያቢሎስን አሰራር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ ክርስቲያን ሁሉ ጠላታቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው ሰሞኑን በሁሉም ብሎጎቻቸው እንደገና መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ላይ መዝመት የጀመሩት፡፡ የወላይታ ሶዶው ጉባኤ እንዳይካሄድ ያደረጉት ጥረት ሁሉ  ከሽፎ ጉባኤው ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት መካሄዱ ቢያቃጥላቸው “ስህተት” ብለው ያገኙትን ነገር ነቅሰው አወጡ፡፡ ታዲያ በማቅ መመዘኛ ትልቁ ምንፍቅና በ10 ደቂቃ 20 ጊዜ አሜን ማለት ሆኖ ተገኘ፡፡ ከታወሩ አይቀር እንዲህ ነው እንጂ!!!
ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል አሜን ለምን ይባላል አሜን ማለት የሊቅነት ማነስ ውጤት ነው የሚለውን የአንድ አድርገን ዘገባ እንዲህ ይተቻል፡፡ መልካም ንባብ!! )
ነዋሪነታቸው ጀርመን ፍራንክፈርት  የሆነ አንድ በአካባቢው የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ምእመን ባሳለፍነው ሳምንት በኢሜይል አድራሻዬ “ … እርስዎስ ምን ይላሉ?” ሲሉ ነበር የጠየቁኝ። አያይዘው ከላኩልኝ ሊንክ በተጨማሪ ለይተው አውጥተው አስተያየቴን የጠየቁበት ጽሑፍ እንደሚከተለው ይነበባል።
ሊቃውንቱ ሲሰብኩ ሰው ወደ ውስጡ እንዲመለከትና በጥሞና እና በአስተውሎ የእግዚአብሔር ቃል እንዲያደምጥ ሲያደርጉ ነበር እኛ የምናውቀው፤ አሁን አሁን በአስር ደቂቃ ጊዜ ውስጥ 20 ጊዜ በላይ ‹‹አሜን›› የሚያስብለውን ሆነ ‹‹አሜን›› በማያስብለው ምዕመኑን ጮኻሂ የማድረግ አዝማሚያ እየታየ ነው፤ መናፍቃን ቤት የሚገኝው ጩኽት እኛ ቤትም ለመግባት ደጃፍ ላይ እያኮበኮበ ይገኛል፡፡[http://www.andadirgen.org/2014/02/blog-ost_5495.html]
እኚህ ወንድም አያይዘው በላክሉኝ መልዕክት የእግዚአብሔር መንጋ ለመበተን የሌሊት እንቅልፍ የማያውቀው ራሱንማኅበረ ቅዱሳንበማለት በሚጠራው ቡድን የሚዘወርአንድ አድርገንየተባለ መካነ ድር ነበርና ከዚህ የሽፍታ ድረ ገጽ ያነበቡትን ጽሑፍ ተንተርሰው የተፈጠረባቸው ጥያቄ ሲጨመቅ ፍሬ ነገሩ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።
የመጀመሪያ ጥያቄአቸው በደረቁ በስብከት ጊዜ አሜን ማለት ይቻላል አይቻልም?” አክሎውም የሚቻል ከሆነስ በአንድ ስብከት ውስጥ ስንት ጊዜ ነው አሜን ማለት የሚቻለው?” ባነበቡት እንግዳ ትምህርት የተደናገጡ ስለሆነም ለመሆኑ አሜን ማለት ምን ማለት ነው? አሜን የአማርኛ/የግዕዝ ቋንቋ ነው ወይስ ከሌላ ቋንቋ የተገኘ ቃል?” በማለት በአሜን “… ዙሪያ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ትምህርት ያካፍሉን ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ። እግዚአብሔር አገልግሎትዎን ይባርክ።ስም አለው።!

በስብከት ጊዜ አሜን ማለት ይቻላል አይቻልም?”

መልሱ ግልጽና አጭር ነው። የእግዚአብሔር ቃል ተገልጦ በሚነገርበት ስፍራ፣ የህይወት ቃል በሚሰበክበት ጊዜ ሰሚ ከመባረኩ የተነሳ ደስ እያለው ይሁንታውን በእልልታ ከፍ ባለ በታላቅም ድምጽ አምላኩን ያመሰግን ዘንድ የተገባ ነው። ምነው ቢሉ ምዕመኑ በአምላኩ ፊት አንጂ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ አይደለም እና የተቀመጠው። እየተነገረ ያለው ቃል ሕያው፣ የሚሠራ፣ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ፣ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ የሚወጋ፣ የልብንም ስሜትና አሳብ የሚመረምር የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የተደረገለት፣ የገባው፣ የምህረት እጁ የዳሰሰችው ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ በደስታ በእግዚአብሔር ፊት ይቅለጥ። ዳኛው እግዚአብሔር ነው። ታድያ ጭብጨባ፣ አምልኮ፣ ዕልልታና ውዳሴ ከሰማይ ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ተብሎ ማንነቱ የተመሰከረለት ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ ብቻ ነው። በታላቅ ጭኸትና በደስታ በጭብጨባ ከማምለክና የምስጋና መስዋዕት ካቀረብክ አይቀር ዋጋ ለሚያሰጥ ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ ክብር አድርገው። ቅድሳት መጻህፍትም የሚመሰክሩት ይህንኑ ሐቅ ነው።

አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት፥ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ፥ ተቀመጠባቸውም። ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር። የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ። ይህ ማን ነው? ብሎ ተናወጠ። ሕዝቡም ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው አሉ።(የማቴዎስ ወንጌል 21 7-11)

መጽሐፍ ቅዱስመጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 1529 “የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች ንጉሡም ዳዊት ሲዘፍንና ሲጫወት አይታ በልቧ ናቀችውካለ እና ሊናቁ የሚገባቸው ናቁ ብሎ ከነገረን ማኅበረ ቅዱሳንደግሞ ‹‹አሜን›› ‹‹አሜን›› ማለትየመናፍቃን ነው!” ቢል ምን ይደንቃል? “ማኅበረ ቅዱሳንእንደሆነ የቅዱሳን ደም ለማፍሰስ ካልሆነ በስተቀር የእግዚአብሔር ስም አንስቶ እግዚአብሔርን ለመባረክና ለማመስን አሜን አይልም። በየት አልፎ? የኢየሱስ ጌትነትና አምላክነት ለማወጅ የኮሌጅ ዲግሪ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ነው የሚጠይቀው። ማኅበረ ቅዱሳንደግሞ ይህችን ኬላ ማለፍ አይችልም።

ሊቃውንቱተብሎ የሰፈረው ቃል ይመልከቱልኝማ። አይተውልኛል? ለመሆኑ እነዚህ ሊቃውንት እነማን ናቸው? ግዕዝና አግአዚ የማይለዩ እንደ እነ ዳንኤል ክብረት የመሳሰሉ የማኅበሩ ግሳንግስ ግለሰቦችን እንደሚሉን አምናለሁ።! እንዲህም አርጎ ሊቅነት የለ!!

አሜን ማለት ምን ማለት ነው?”

እውነት ነውአሜንየሚለው ቃል የአማርኛ ወይም የግዕዝ ቋንቋ አይደለም።አሜንየሚለው የግሪክ፣ የግዕዝ ሆነ የአማርኛ ቃል መሰረቱየተረጋገጠና የታመነከሚል ከዕብራይስጡ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውምይሁን”“መልካምየሚል ነው። አሜን በረከት፣ እርግማን፣ ጸሎትወዘተ ከቀረበ ወይም ከተነገረ በኋላ ተደጋግሞ አገልግሎት ላይ የሚውል ቃልም ነው። በተጨማሪም አሜን የሚለው ቃል በተነገረው ቃል ላይ መስማማትን የሚያመላክት ነው። ለምሳሌ ያህል በሐዲስ ኪዳን (ዮሐንስ 1 51 ይመልከቱ) ኢየሱስ በተደጋጋሚአሜንየሚለውን ቃልእውነት እውነትበሚል ተተክቶ ወይም ተተርጉሞ እናገኘዋለን።!

ስንት ጊዜ ነው አሜን ማለት የሚቻለው?”

እንደማኅበረ ቅዱሳንደርቆ የሚያደርቅ የልምድ አዋላጅ በፊትዎ እስካልተገተረ በስተቀር በሰሙት ቃል የተባረኩ ያህል አሜን የማለት የልጅነት ሥልጣን ተሰጥቶታል። እዚህ ላይ በቁጥር የሚወሰን ነገር የለም። ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ ሙላት፣ ደስታና በአምልኮ የተነሳ ሰባት ጊዜ ሰባ ሰባት አሜን ቢሉ እርር ድብን ቅጥል የሚለው የሰው ልጅ መልካም ነገር ማየት የማይሆንለትና የማይወድ የወንድሞች ከሳሽ ሰይጣንና ጭፍሮቹ ናቸው።ማኅበረ ቅዱሳንእንደሆነ በር ዘግቶ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሲራገምና ደማቸውንም ለማፍሰስ ሲማማል አንጀቱ እስኪሳብ ምላሱም እስኪደርቅ ድረስ ማቆሚያ በሌለው ሁኔታ አሜን ሲል ነው ጸሐይ የምትጠልቅበት።! እናንተ ሰው ለማጥፋት አሜን በሉ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ግን ለጌታቸው ክብር ልባቸው በተነካ ቁጥር አሜን ይላሉ፡፡ ለተረፈ ሚልኮሎች እድል መስጠት አይገባም፡፡ የእነርሱ ድርሻ  በጌታ ፊት የሚሆኑትን በአምላካቸው የሚደሰቱትን መናቅ ነው ነው፡፡ ምላሹ ደግሞ በትልቁ ጌታ በእግዚአብሔር መተው መረሳት ነው፡፡ ለወደዳችሁ ከኃጢአትም በደሙ ለዋጃችሁ ጌታ እልል በሉለት፡፡ አሜን!!!!!
/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

Email: yetdgnayalehe@gmail.com

1 comment:

  1. ዲ/ሙሉ ጌታ የምታቀርበው ሓሳብ ሁሉ ወርቅ ነውና ቀጥል ዕድሜ ከጤና ይስጥህ አሜን

    ReplyDelete