Saturday, May 10, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን የማተራመስ ሥራውን በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረስብከትም ቀጥሏል።

ላለፉት 20 ዓመታት ቤተክርሰቲያንን እያተራመሰ እያመሰ እየበጠበጠ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ለማኅበሩ የማያሸረግዱ ብጹአን አባቶችን መቃወሙን እና ወጣቶችን ደግሞ ማሳደዱን አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል። በተለይም በሄዱበት ሀገረ ስብከት ሁሉ ለማኅበረ ቅዱሳን ባለማንበርከክና ቤተክርስቲያንን በዱርዬ መንጋ እንዳትወረር ነቅተው በመጠበቅ የሚታወቁትን ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስንም አላማቸው ገንዘብ በሆኑ አባላቱና ደጋፊዎቹ አማካኝነት መቃወሙን ቀጥሏል። ከአባላቱ መካከልም በተለይም  ሳሙኤል ደሪባ እና ጌታሁን አማረ የተባሉና ገንዘብ በማጭበርበርና ሙዳይ ምጽዋት በመገልበጥ የታወቁ ሁለት ግለሰቦች የሚያደርጉት የማበጣበጥ ሥራ ብዙ ቢሆንም የተፈለገውን ውጤት ግን ላስገኝላቸው አልቻለም።
ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ ከቅዱስ ፓትራርኩ ጋር
 ሳሙኤል ድሪባ ባካ ቅድስት ማርያም በምትባለው እና በወሊሶ ወረዳ ከምትገኘው ቤተክርስቲያን በሀገረ ስብከትም ሆነ በወረዳው ቤተክህነት ሳይታዘዝ ራሱ ሂሳብ ሹም መርጦ ገንዘብ ያዥ አስቀምጦ እና ቁጥጥር አድርጎ በሊቀ ጳጳሱ ከተፈቀደላቸው ኮሚቴዎች ውጭ በራሱ የሚታዘዝ ኮሚቴ በማን አለበኝነት በመፍጠር ከዘጠና ስምንት ሺህ ብር በላይ አጉድሏል። ይህም በኦዲተር ማስረጃ የተረጋገጠ ነው።

ከሱ ጋር መሳ ለመሳ ሆኖ ቤተክርሰቲያንን ኦየበደለ ያለው የማህበሯ ሰብሳቢ የሆነው መምህር ጌታሁን አማረ የሚባል ግለሰብም ስድስት ዓመት ሙሉ ወሊሶ ቅዱስ ኡራኤል ማረሚያ ቤት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጸሀፊነት ሰርቶ የስድሰት ዓመት ሂሳብ ኦዲት ሳያስደርግ ሳያወራርድ የቤተክርሰቲያንዋን ብር ሙልጭ አርጎ በልቶ በህዝብ ግፈት ከስልጣኑ ወርዶ በሚያስተምርበት ትምህርት ቤት ውስጥ በመሆን የማህበረ ቅዱሳንን የተንኮልን የውንብድና ሥራ እንደቀጠለ ይገኛል። መቼም ለማኅበርዋ ኃጢአት በአባለትዋ የተሰራ እንደሆነ እንደ ጽድቅ ይቆጠራል እና አባላትዋ የሚሰሩትን ግፍና በደል ሁሉ ተዉ የማለት አቅም ሊኖራት እንደማይችል የታወቀ ነው። አቶ ጌታሁን የቤተክርስቲያንዋን ብር ሙልጭ አርጎ በልቶ በህዝብ ግፊት ከስልጣኑ ወርዶ በሚያስተምርበት ትምህርት ቤት ውስጥ በመሆን እና ቤተክርስቲያንን ጥግ ጥግ በመዞር የማህበረ ቅዱሳንን የተንኮልና የውንብድና ሥራ ዛሬም እየሰራ ይገኛል።
ይህ ግለሰብ በጥባጭና አበጣባጭ በመሆኑ እና ከስድብ እና ከድፍረት ንግግር የተሻለ የወንጌልም እውቀት ስለሌለው በወረዳው ቤተክህነት አውደ ምህረት ላይ እንዳያስተምር ታግዶ ይገኛል። ግለሰቡ በጸሀፊነት ይሰራ በነበረ ጊዜ ካህናቱ ላይ ያደርስ የነበረውን ግፍ አስመልክቶ ካህናቱ ተደጋጋሚ አቤቱታ ለወረዳው ቤተክህነት አቅርበው እንደነበር የሚታወስ ነው። ይህ ግለሰብ እንደ አባቱ ማቅ ስድስት አመት ሙሉ አንድን ቤተክርስተያን በዝብዞ እና ኦዲት አላስደርግም ብሎ ቆይቶ አሁን ደግሞ የማኅበሯ ሰብሳቢ በመሆን በህዝብና በቤተክርስቲያን ላይ ግፍ እየፈጸመ ይገኛል።
ይህ ግለሰብ ከዘራፊው እና ከወንጀለኛው ሳሙኤል ደሪባ ከቢጤዎቹ ዳኜ አካሉ ጌታሁን ገነነ ዘላለም ደሴ አለማየሁ ጌታሁን ሽፈራው ሀጎስ ተመስገን ጥበቡ ደረጄ በዳዳ አቶ ደጀኔ ደበሬ እና ሌሎችም ጋር በመሆን አቅጣጫ ጠፍቶበት ዱርዬ እያከማቸ ያለውን ማኅበር በመደገፍ እና ከእርሱም ጋር በመንገታገት ላይ ይገኛል።
ይህ ስበስብ በአባቱና በሁከተኛው ማህበረ ቅዱሳን እየተመራ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሥራ አስኪያጅና ጸሀፊ ይነሱ በማለት ቤተክርሰቲንን ለመበጥበጥ እየሞከሩ ይገኛሉ። መቼም ማኅበሯ ወደ እርሰዋ ፊቱን አዙሮ ያልሰገደውን ሰው ከጳጳስ እስከ ምዕመን ማሰዳድዋ የማይቀር ስለሆነ ነው እንጂ የመንጋ ዱርዬ ስብስብ ሁሉ እየተነሳ ሊቀ ጰጳሱ ይነሱልኝ ለማለት የሞራልም የመንፈሳዊነት ብቃት አይኖረውም የለውምም።
ለማኅበሯ ያልታዘዙት ሊቀ ጳጳሱን እና ሥራ አስኪያጁን “ተሃድሶ” ናቸው በማለት ስማቸውን እያጠፉ ይገኛሉ። ይህ የተለመደ ተራ እና የከሰረ የሸፍጥ አካሄድ በሀገረ ስብከቱ ህዝብ ላይ ያመጣው ምንም አይነት ለውጥ እንደሌለ ግን በአካባቢው ሊቀ ጳጳሱም ይሁን ሥራ አስኪያጁ ባላቸው ተቀባይነት የታወቀ እውነት ነው። እነርሱ እነቆጣጠረዋለን ብለው በሚያምኑባቸው አብያተ ክርስቲያናትም አመታዊ የፐርሰንት ክፍያን ወደ ሀገረ ስብከት ከመላክ ይልቅ ለማኅበሩ ዋና ማዕከል በመላክ በቤተክርስቲያን እና በመንፈሳዊ መዋቅሩ ላይ እየቀለዱ ይገኛሉ። አልተሳካላቸውም እንጂ የብጥብጥና የነውጥ መመሪያም ከዋና ማዕከሉ እየተቀበሉ እንደሚንቀሳቀሱ የታወቀ እውነት ነው።
ባለፈው ታህሳስ 20 ቀን እነዚህ ስማቸው ከላይ የተጠቀሱት የማህበሩ አባላት ብጹዕነታቸው አቡነ ሳዊሮስ ከቅዳሴ በኃለ ሊያሳርጉ ሲሉ እርስዎ አያሳርጉም አንቀበልዎትም እዚህ ቤተክርስቲያን እንዳይደርሱ ጥምቀተ ባህር እርስዎ ከመጡ እንገድልዎታን እናጠፋዎታለን በማለት ሁከት ለመፍጠርና ህዝቡን ለማበጣበጥ ቢሞክሩም ህዝቡ ግን ስላልተቀበላቸው ሁከት የመፍጠር እንቅስቃሴያቸው ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
ለቤተክርስቲያን እና ለቅዱሳን አባቶችዋ ከመታዘዝ ይልቅ እኔ የምላችሁን ፈጽሚ እያለች ያለችው ማኅበሯ ይኅ የግፍ ጽዋ ሞልቶ በመፍሰሱ ዋጋውን የሚያገኝበት ቀን በደጅ ቀርቧል።

No comments:

Post a Comment