Tuesday, May 29, 2012

ኢካቦድ: ከመሰደድ ይልቅ ማሳደድን ለመረጠ ሲኖዶስ!!

   Click here to read in PDF                                                     በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

በዚህ ርዕስ ውድቀትን የሚያበሰር፣ ሰላምንና መረጋጋትን እንደ ሰማይ ከዋክብት የሚያርቅ በፈንታው ሁከትንና የሽብር ድርጊት የሚያሰፈን፣ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ውድቀት በሚጠባበቁ ልሂቃን ከብዙ ዓመታት በፊት የታቀደውን ዕቅድ ተግባራዊነት የሚያረጋግጥ፣ ወንጌላውያንም በማሳደድ ወንጀለኞች ለመሾም የተላለፈውን ውሳኔና የሚያስከትለውን ውድቀትና ድቀት አንስተን በጥልቀት እንዳስሳለን። መንሸራሸሪያ ሀሳባችንም በወርሐ ግንቦት 15/2004 የተጠናቀቀውን የሲኖዶስ ስብሰባ በተላለፈው ባለ አስር ነጥብ የአቋም መግለጫ በተለይ በተራ ቁጥር ስድስት ላይ  የሰፈረው ይኸውም ራሱን “ማህበረ ቅዱሳን” በማለት ስለሚጠራ አጽራረ ቤ/ያን በተመለከተ የተላለፈውን ጊዜያዊ ውሳኔ ይሆናል።
“የዔሊም ልጆች ምናምንቴዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁም ነበር፤ የካህናትም ልማድ በሕዝቡ ዘንድ እንዲህ ነበረ፤ ሰው ሁሉ መሥዋዕት ሲያቀርብ ሥጋው በተቀቀለ ጊዜ የካህኑ ሎሌ ይመጣ ነበር፥ በእጁም ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ነበረ፤ ወደ ድስቱም ወይም ወደ ምንቸቱ ወይም ወደ አፍላሉ ወይም ወደ ቶፋው ይሰድድው ነበር፤ ሜንጦውም ያወጣውን ሁሉ ካህኑ ለእርሱ ይወስደው ነበር። ወደዚያም በመጡት በእስራኤላውያን ላይ በሴሎ እንዲህ ያደርጉ ነበር፤ ደግሞም ስቡን ሳያቃጥሉ የካህኑ ሎሌ መጥቶ የሚሠዋውን ሰው። ጥሬውን እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይወስድምና እጠብስለት ዘንድ ለካህኑ ሥጋ ስጠኝ ይለው ነበር፤ ሰውዮውም አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት ኋላም ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ትወስዳለህ ቢለው፥ እርሱ አይሆንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፤ እንቢም ብትል በግድ እወስደዋለሁ ይለው ነበር ሰዎቹም የእግዚአብሔርን ቍርባን ይንቁ ነበርና የጎበዛዝቱ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበረች። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2: 12

አፍኒን እና ፊንሐስ (“ማህበረ ቅዱሳን”):
v የእግዚአብሔርን ህግ በመናቅ ቅድሚያ መሰጠትና መቅረብ የሚገባውን የእግዚአብሔር መስዋዕት ትተው ቅድሚያውን ለራሳቸው ይሰጡ እንደ ነበር፣ 1ኛ ሳሙ. 2: 16-17
v የመስዋአቱን ስርኣት ያስተጔጉሉ እንደ ነበር፡
v በመገናኛው ድንኳን ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋር የክብሩ ዙፋን ባለበት በእግዚአብሔር ማደሪያ ውስጥ ያመነዝሩ እንደ ነበር፡
v አስፀያፊ የከነዓናውያን የቤተ ጣዖት ዓይነት አምልኮ ይፈጽሙ እንደነበር:
v እንዲሁም የዔሊ ልጆች ምግባረ ብልሹዎች ከመሆናቸው በተጨማሪም ሌቦች እንደነበሩ ነው። (ቁ. 17)
ይህ ሁሉ የዔሊ ልጆች አስነዋሪ ድርጊታቸው በዋናነት የሚያመላክተው ነገር ቢኖር አንድና አንድ ነው። ይኸውም በእግዚአብሔር ላይ ያሳዩት ድፍረትና ልክ ያጣ ጣሪያ የነካ ብልግና ነበር። “ምናምንቴ” ማለት በቁም ሲተረጎም እግዚአብሔር የማይፈራ፣ እግዚአብሔርን የማያውቅና የማያምን አጉራ ዘለል ማለት ነው። ታድያ በዚህ ሁሉ ዓይኑ ያፈጠጠና ልክ ያጣ የሃጢአት መዓት ኤሊ ልጆቹን ለመቅጣት ከአገልግሎታቸውንም ለማገድ ያደረገው ጥረት አለመኖሩ ነው። ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ድምጽ
ወዲ ዔሊ እንዲህ ሲል መጣ “ከእኔ ይልቅ ልጆችህን ለምን አከበርክ? ... ክንድህን የአባትህን ቤት ክንድ የምሰብርበት ዘመን ይመጣል”
ክንድ ስልጣን/ጉልበት/ሐይል ነው የሚያመላክተውና ይህ ሁሉ እንደሚወስድበት ነው የሚናገረው። ለምን?
v ዔሊ የቤቱ አባወራ/የቤተሰቡ መሪ፣ የበላይ አስተዳዳሪ ነው።
v ዔሊ በሕዝቡም ሆነ በቤቱ ከእግዚአብሔር ሙሉ የሆነ ሐላፊነትና ስልጣን የተሰጠው ሰውም ነበርና።
በአጭሩ በዔሊ ላይ የነደደች የእግዚአብሔር ቁጣ ዋና ምክንያት፣
v አንደኛ: እግዚአብሔር ባዘነበትና በተቆጣበት ጉዳይ ላይ ዔሊ በህጉ መሰረት በልጆቹ እርምጃ ካለመውሰዱና ሐላፊነቱንም በአግባቡ ካለመወጣቱ የተነሳ:
v ሁለትኛ: ልጆቹ የጥፋት አገልግሎትን ከወትሮ በበለጠ እየገፉበት በሄዱ ቁጥር ሁኔታዎች የቱንም ያህል ቢከፉ ዔሊ ለጠራው፣ ለሾመውና ለቀባው እግዚአብሔር ባለመቅናቱ የተነሳ የሚከተለው ዓይነት ክብር የሌለው ሞት ሞቷል።
 “ዔሊም የጩኸቱን ድምፅ በሰማ ጊዜ ይህ ጫጫታ ምንድር ነው? አለ ሰውዮውም ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው ዔሊም የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበረ፤ ዓይኖቹም ማየት እስኪሳናቸው ድረስ ፈዝዘው ነበር ሰውዮውም ዔሊን ከሰልፍ የመጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰልፍ ኮበለልሁ አለ እርሱም ልጄ ሆይ፥ ነገሩሳ እንዴት ሆነ? አለው ወሬኛውም መልሶ እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ደግሞ በሕዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖአል፥ ሁለቱም ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም ታቦት ተማርካለች አለ። ሰውዮውም ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ ዔሊ በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸምግሎ ደንግዞም ነበርና አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ።”  

ዔሊ አንገቱ ተሰብሮ የሞተበት ምክንያት በዘጸአት 13: 13 ላይ “የአህያውን በኵር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ባትዋጀውም አንገቱን ትሰብረዋለህ፤ የሰውንም በኵር ሁሉ ከልጆችህ መካከል ትዋጀዋለህ።” በሚለው የእግዚአብሔር ሕግ መሰረት ነው።

ከራስ ጠጉራቸው እስከ እግራቸው ጥፍር በርኩሰት የተከደኑ ከዔሊ ልጆች የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው ከሕዝቡ ጋር በመውጣታቸው እስራኤል ተበተነ፣ በፍልስጥኤማውያን ፊትም ተመቱ፣ ብዙ ሕዝብም ሞተ፣ ከምንም በላይ ደግሞ የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከች። የባልዋና የአማትዋ ሞት የተደራረበባት የፊንሐስ ሚስትም “የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከች ስለአማትውና ስለባሏም ክብር ከእስራኤል ለቀቀ ስትል የህፃኑ ስም ኢካቦድ ብላ ጠራችው። እርስዋም የእግዚብሔር ታቦት ተማርካለችና ክብር ከእስራኤል ለቀቀ አለች።” (1ኛ ሳሙ. 4: 19-22)
ዛሬም እየተሰማ ያለው ድምጽ ይሄ ነው። ኢካቦድ ከመሰደድ ይልቅ ማሳደድን ለመረጠ ሲኖዶስ!  የሚል። አንድ ሃላፊነት የተጣለበት ባለ ሙሉ ስልጣን ዔሊ የተባለ ሊቀ ካህን የተጣለበትን ከባድ ሃላፊነት በአግባቡ አለመወጣት ይኸውም በማንኛውም ዓይነት የቤተ-መቅደስ አገልግሎት ላይ ተሰማርተው መቆም የማይገባቸው ነውር እንደ ሽልማት የተጎናጸፉ አፍኒን እና ፊንሐስ ከአግልግሎት ማገድና ማስወገድ ሲገባው ሊቀ ካህን ዔሊ ይህንን ባለማድረጉ ከፍ ስንል የተመለከትናቸው አራት ዓበይት ጥፋቶችን ኪሳራዎች በእስራኤል ሕዝብ እንዳስከተለ ዛሬም የሲኖዶሱ አባላት አመኑበትም አላመኑበትም በሁኔታዎች ጫና ተገፋፍተው ባስተላለፉት ውሳኔ ሰደዱ ከቤተ-ክርስቲያኒቱ አልፎ በመላ ሀገሪቱ የሚያስከትለውን ዋይታ ግልጽና ግልጽ ነው።

የዔሊ ውሳኔ በሕይወቱ መጨረሻ ለከፋ ውድቀት እንዳደረሰው አባቶች ሆይ! የእናንተም መጨረሻ ከዚህ የተለየ አይሆንም። አባቶች ሆይ! በቀራንዮ የፈሰሰውን ደም ያላማከለና ገሸሸም ያደረገ መሰሪዎች የሸረቡትን ጸረ ወንጌልና በክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ላይ የተቃጣውን አንቀጽ እንደ ራሳችሁ ቃል ስታነበንቡት መጀመሪያውኑ ሰላማችሁን ነስቶ ዕረፍት እንደሚያሳጣችሁ እንዴት ዘነጋችሁት? ካደረጋችሁት ዘንዳም ከሞት በፊት ውድቀት ይቀድማችኋል! ስል በተሰበረ ልብ ነው።

“ሳሙኤልም ሳኦልን አለው በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እቀባህ ዘንድ እግዚአብሔር ላከኝ፥ አሁንም የእግዚአብሔርን ድምፅ ስማ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን እበቀላለሁ። አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል። ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ በግብጽ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው። የአማሌቅንም ንጉሥ አጋግን በሕይወቱ ማረከው፥ ሕዝቡንም ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው። ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ ለአጋግ፥ ለተመረጡትም በጎችና በሬዎች ለሰቡትም ጥጆችና ጠቦቶች፥ ለመልካሞቹም ሁሉ ራሩላቸው፥ ፈጽሞ ሊያጠፉአቸውም አልወደዱም፤ ነገር ግን ምናምንቴንና የተናቀውን ሁሉ ፈጽመው አጠፉት። የእግዚአብሔርም ቃል። ሳኦል እኔ ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት ተጸጸትሁ ብሎ ወደ ሳሙኤል መጣ። ሳሙኤልም ተቈጣ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ ሳሙኤልም በነጋው ሳኦልን ለመገናኘት ማለደ። ሳኦልም ወደ ቀርሜሎስ መጣ፤ እነሆም፥ የመታሰቢያ ዓምድ ባቆመ ጊዜ ዞሮ አለፈ፥ ወደ ጌልገላም ወረደ የሚል ወሬ ለሳሙኤል ደረሰለት።
ሳሙኤልም ወደ ሳኦል መጣ፤ ሳኦልም። አንተ ለእግዚአብሔር የተባረክህ ሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ አለው። ሳሙኤልም ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ጩኸትና የበሬዎች ግሣት ምንድር ነው? አለ። ሳኦልም ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ መልካሞቹን በጎችና በሬዎች አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አምጥተዋቸዋል፤ የቀሩትንም ፈጽመን አጠፋን አለው። ሳሙኤልም ሳኦልን። ቆይ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ሌሊት የነገረኝን ልንገርህ አለው፤ እርሱም። ተናገር አለው። ሳሙኤልም አለ። በዓይንህ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ። እግዚአብሔርም። ሄደህ ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ውጋቸው ብሎ በመንገድ ላከህ። ለምርኮ ሳስተህ ለምን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህም? ለምንስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረግህ? ሳኦልም ሳሙኤልን የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቻለሁ፥ እግዚአብሔርም በላከኝ መንገድ ሄጃለሁ፤ የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን አምጥቻለሁ፥ አማሌቃውያንንም ፈጽሜ አጥፍቻለሁ። ሕዝቡ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ይሠዉ ዘንድ ከእርሙ የተመረጡትን በጎችንና በሬዎችን ከምርኮው ወሰዱ አለው። ሳሙኤልም በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፥ መታዘዝ ከመሥዋዕት፥ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል። ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ። ሳኦልም ሳሙኤልን። ሕዝቡን ስለ ፈራሁ፥ ቃላቸውንም ስለ ሰማሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና የአንተን ቃል በመተላለፍ በድያለሁ። አሁንም፥ እባክህ፥ ኃጢአቴን ይቅር
በለኝ፥ ለእግዚአብሔርም እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር ተመለስ አለው። ሳሙኤልም ሳኦልን የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃልና ከአንተ ጋር አልመለስም አለው። ሳሙኤልም ሊሄድ ዘወር ባለ ጊዜ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፥ ተቀደደም ሳሙኤልም እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀደዳት፥ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጣት፤ የእስራኤል ኃይል እንደ ሰው የሚጸጸት አይደለምና አይዋሽም አይጸጸትምም አለው።” (1ኛ ሳሙ. 15: 1- 29)

ይህ ምዕራፍ ሳኦል በእግዚአብሔር ፊት መናቁን የሚያሳይ ክፍል ነው። የመናቁም ምክንያት ሳኦል አማሌቃውያን (ማህበረ ቅዱሳን”) ፈጽሞ እንዲያጠፋቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን ትዕዛዝ አንደታዘዘው አለመፈጸሙ/አለማድረጉ ነበር። በዋናነት ይህ ያላደረገበትም ምክንያት የከበቡትን ወፋፍራም አማካሪዎቹና ሕዝቡን ፍርቶ በሁኔታዎች ተገፋፍቶ የወሰነውን ውሳኔ ነበር።

ታድያ የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲያሻሽለው ሳይሆን “ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ” የሚለውን በተሰጠው ሃላፊነት ቃል በቃል ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ታማኝነቱን ማሳየትና መግለጥ ሲገባው መልካም የሚመስል ዳሩ ግን ትክክል ያልሆነውን ስራ በመስራት በራሱ ላይ ውድቀትን እንደጠራ ነው የምንመለከተው።
አማሌቅ (“ማህበረ ቅዱሳን”) ማን ነው?
አማሌቅ ማለት በኔጌብና በሲና ምድር ይኖሩ የነበሩ ከኤሳው ዘንድ የሆኑ የምድረ በዳ ሰዎች ሲሆኑ እግዚአብሔር ያገለግለው ዘንድ ከግብጽ ምድር በድንቅና በተአምራት ከባርነት የታደገውን ህዝብ (እስራኤላውያንን) የተቃወሙ አመጸኞች ነበሩ። በተመሳሳይ “ማህበረ ቅዱሳን” ማለት በ1984 ዓም በወቅቱ የሽዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና የካህናት ማሠልጠኛ የበላይ ጠባቂ በነበሩበት በብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ አማካኝነት ተመሰረትሁ እያለ ከሞቱ ከሁለት ዓመት በኃላ መሰረቱኝ እያለ የሚዋሽ የቤተ-ክርስቲያን ትምህርት ተምሬአለሁ በማለት ታሪኩን ለማያውቅ የዋህ የሚያደናግር በቀድሞ መጠሪያ ስሙ አጠቃላይ ጉባኤ በማለት የሚታወቅ ፓትሪያሪክ ብጹእ አቡነ ቲዎፍሎስ ጨምሮ በብዙሐን የቤ/ያን መምህራንና ሊቃውንት ነፍስ ተጠያቂ የሆነው ድርጅት ብስባሽ ውስጥ የበቀለ ነፍሰ ገዳይ ድርጅት ነው።

 “ማኅበረ-ቅዱሳን” በሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያው ስር ህጋዊ እውቅና አግኝቻለሁ፣ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮችን ለማከናወን ብቃትና ቅድስና አለኝ፣ ወጣቶችን በአባቶች እግር ስር እተካለሁ፣ ወጣቶችን በገንዘባቸው በዕውቀታቸው በጉልበታቸው ቤተ-ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ አመቻቻለሁ፣ የቤተ-ክርስቲያኗን ሊቃውንት ዝናና ክብር እጠብቃለሁ በሚል ቁልምጫ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን “ሉዓላዊነት”፣ የአባቶችን ክብር፣ የወጣቶችን መልክና አስተሳሰብ፣ የህጻናት የእርስ በእርስ ፍቅር እንደ ገና ኳስ በማተረማመስ እርስ በርስ እንዲካሰሱ እንዲተፋፈሩ በማድረግ ቤተ-ክርስቲያንን የሁከት ስፍራ ያደረገ አገር በቀል አሸባሪም ነው። “ማህበረ ቅዱሳን” ማለት ዕቅድ አውጥቶ ፕላን ነድፎና በጀት በጅቶ በማኅሌት፣ በኪዳን፣ በስግደት ያደሩትን አባቶችን ለህዝቡ ትምህርት ለመስጠት እንቅልፋቸውንና ጊዜአቸውን ሰውተው መዝሙር በማጥናት ያደሩትን ወጣቶችን፣ ተቃቅፈው ያደሩትን ባለ ትዳሮችን ለማተረማመስ፣ ለመክሰስና ጥላቻ ለመዝራት በሰዎች ዓይን ዘንድ እውቅና “ያገኘና/የተሰጠው” ሕጋዊ ሽፍታም ነው።
በአንዳንድ ጥንታውያን መጻህፍት በቁጥር 15 ላይ “ሕዝቡ” የሚለውን ቃል “ሰራዊቱ ከአመሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው ምርጥ ምርጡን በጎችና በሬዎች ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መስዋዕት እንዲሆኑ ሳይገደሉ የተዋአቸው ናቸው” በማለት ተጽፈዋል። ታድያ ፓትርያርኩም ቢሆኑ ሃላፊነቱን ካራስዎት አውርደው ያደረጉትን ያደርጉ ዘንድ ለገፋፋዎት  ለሲኖዶሱ አባላት ቢሰጡም ቃሉ በማያሻማ መልኩ የሚለው ይህንኑ ነው።
የሚያሳዝነው ሳኦል እግዚአብሔር አማሌቅን ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ የታዘዘውን ትእዛዝ በሙላት አለመፈጸሙ ብቻ ሳይሆን በ2ኛ ሳሙ. ምዕ. 1 ተጽፎ እንደምናገኘው የሳኦል ነፍስ ያለፈችው በአንድ ተራ አማሌቃዊ እጅ መሆንዋን ነው። በቁ. 11 “ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች ሁሉ ልብሳቸውን ይዘው ቀደዱ። በሰይፍም ወድቀዋልና ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን ለእግዚአብሔርም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፥ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።” እንዲል አባ ሆይ! ተገድዶውም ሆነ እጅዎትን ተጠምዝዘው የወሰኑትን ውሳኔ በመቀመጫዎት ላይ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳውን አጥፊና አውዳሚ ፈንጅ የጠመዱ ያክል ይቁጠሩ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ላሳስቦት እወዳለሁ።

የሳኦል ሁኔታዎችን ያማከላ በአንጻሩ ደግሞ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ወደ ጎን ያገለለ ውሳኔ በቀሪው ዘመኑ ፍርሃት፡ ጭንቀትንና ውጥረትን እንዳስከተለበት ሁሉ አባቶች ሆይ! ደቂቀ አማሌቅ “ማህበረ ቅዱሳን” ሾማችሁና ደግፋችሁ (ባትደግፉትም ተገፋፍታቹ ባስተላለፉችት ውሳኔ ብቻ) በህልማችሁም ሆነ በውናችሁ የሰላም እንቅልፍ እንተኛለን ብላችሁ እንዳታስቡ። ሳኦል ባለመታዘዙ የሁከት መንፈስ እንደገባበትና ከዚህም የተነሳ በየ ጠንቋይ ቤቱ መንከባለል ዳዊትንም ለመግደል እንቅልፍ እንዳጣ ሁሉ ይህም የእናንተ ዕጣ ፈንታ ይሆናል።

በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት የሞላበት ሃጢአትና ርኩሰት በመፈጸም የሚታወቀው፣ ወንጌልን የሚቃወሙ ወንጀለኞች!፣ እርማቸውን ያልቆረጡ ነውረኞች፣ ያለ ክስ ምህረትንና ርህራሄን የማያውቁ ወንጌል ያላለፈባቸው አጥፍቶ ጠፊዎችና ደም የተጠሙ ዛሮች፣ ሰላምንና ዕርቅን የሚያርቁ ሁከተኞች፣ ሽንፈት የተከናነቡ ሽብርተኞች፣ መለያየት ጽብንና ጥላቻን የሚደላቸው ጽንፈኞች ሾማችሁማ እንዴት ይመቻችኋል? ምንም አይመቻችሁም!  እንደው ቃዬልም እግዚአብሔርን አለው እንዲል ወንድሙን አቤል
የገደለ ቃዬል በእግዚአብሔር ፊት በመውጣት “ኃጢአቴ ልሸከማት የማልችላት ታላቅ ናት እነሆ ዛሬ ከምድር ፊት አሳደድኸኝ ከፊትህም እሰወራለሁ በምድርም ላይ ኰብላይና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል" (ዘፍ. 4፥ 13-14) እንዲል አባቶች ሆይ! ዛሬስ ያስተላለፋችሁት ውሳኔ፣ ያሰማችሁት ድምጽ፣ የበደላችሁት በደልና የፈጸማችሁት ስህተት በሰው ላይ ሳይሆን በምድር ክበብ ላይ በተቀመጠው በእግዚአብሔር ላይ ነውና ትልቅ ቅጣት በራሳችሁ ላይ ጠርታችኋል። በሁኔታዎች ጫና ላይ ተመርኩዛችሁ ለወሰዳችሁት እርምጃም ሁሉ ሃላፊነቱን ትወስዳላቹ ያገኛቹ ሁሉ ያሳድዳችኋል! ምን ነው ቢሉ ድልና ጉልበት ያለው በሰዎች ቁጥር ብዛት ሳይሆን ከእውነትና ከጽድቅ ሰፈር ነውና።

በክፉ ላይ እንዳልተኛ አንቃኝ!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E-mail: yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America

1 comment: