Wednesday, May 16, 2012

የሰንበት ማደራጃና መምሪያው ለማኅበረ ቅዱሳን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጻፈ

ደብዳቤውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ

  • የ2002 ዓ.ም. ውሳኔ በ10 ቀን ውስጥ እንዲፈጸም ያዛል።
የሰንበት ማደራጀና መምሪያ መምህር ዕንቁ ባሕሪን በዋና ኃላፊነት ካገኘ በኃላ ወሳኝ የሚባሉ አስተዳደሪያዊ ውሳኔዎችን መወሰን ጀምሯል። እንደሰናዖር ግንብ የማይደፈር መስሎት ሲኮፈስ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳንም ከሕግ በላይ ሊሆን እንደማይችል በግልጽ የሚረዳበት ዘመን መጥቷል። አመጸኛውና ሕግና ሥርዓትን ጠብቅ ያለኝ ሁሉ መናፍቅ ነው የሚለው ማሕበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ውጭ መሆን እንደማይችል የሚገልጸውን ደብዳቤ ለመዋጥ እየተናነቀው ይገኛል።
ከተመሰረትኩ 20 ዓመቴ ነው የሚለውና እንደ 20 ዓመት ጎረምሳ በትዕቢት የተወጣጠረው ማሕበር ቤተክርስትያን እኔ ነኝ የቤተክርስቲያን ዶግማ ቀኖናና ሥርዓት የኔ መተዳደሪያ ደንብ ነው። ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን ሲገቡ ሳይሆን ወደ ማሕበረ ቅዱሳን ሲገቡ ነው የሚድኑትና የቤተክርስቲያን ልጆች ቁጥር እጅግ ጨመረ የሚባለው። ህዝቡ ክርስትና ገባው የሚያባለው አሥራት በኩራቱን ለቤተክርስቲያን መስጠቱን አቁሞ ለማኅበሩ ሲሰጥ ነው። የማኅበረ ቅዱሳን አባል ያልሆነ ሁሉ መናፍቅ ነው። ከሲኖዶሱ በላይ ስለሆንኩ ሲኖዶሱ እኔ ያልኩትን መፈጸም አለበት እያለ እንደ ፊጋ በሬ ቤተክርስቲያንን እያመሰ ቢቆይም ዛሬ ልኩን የሚያውቅበት ቀን መጥቷል።
የማኅበሩ አልታዘዝ ባይነት ወሰን ከማጣቱም በላይ ሥርዓት እንዲይዝ የሚሞክሩትን የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች እያዋከበ አላስቆም አላስቀምጥ በማለት ማንም ሊያዘኝ አይችልም በማለት መሬት እርቆት በደመና ላይ እየተንሳፈፈ ቢቆይም አሁን እነርሱም ከሕግ በላይ መሆን እንደማይችል ያሳየና መሬት የሚያስረግጠው ደብዳቤ መጻፉ ተገቢ መሆኑ ታውቋል።

በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው የማደራጃ መምሪያው ደብዳቤውን ለመጻፍ የተገደደበትን ምክንያት ሲገልጽ “…ስለዚህ በሕገ ቤተክርስቲያኑ፤ በቃለ ዓዋዲው እና በማኅበሩ ውስጠ ደንብ የተቀመጠውን መብትና ግዴታን ባለማጤን የሥርዓት፤ የግብረ ገብነት እንዲሁም የዲስፒሊን መገኛ በሆነችው በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ውስጥ እየሰራችሁ መሆናችሁን በመዘንጋት የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ሕገ ደንብና የበላይ አካላትን ትዕዛዝ በመቃረን ላይ እንደምትገኙ የተደረሰበት ስለሆነ ይህን ማስተዋል የጎደለውን እንቅስቃሴ ማስተካከል ለነገ የማይባል ተግባር ሁኖ አግኝተነዋል።” በማለት ነው።
አክሎም በ2002 ዓ.ም. የተወሰነውን ውሳኔ በ10 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያዛል።
በ2002 ዓ.ም. መስከረም ወር ላይ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግስት ተወካዮችና የማኅበሩ አመራሮች በተገኙበት ተወሰነው ውሳኔና መምሪያ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለማስወገድ ሰላምና ፍቅር የሚሰጠውን ጠቀሜታ ለማጎልበት አንድነትና ኅብረት የወሳኝነት ሚና አለው፡፡ ተቻችሎ መሥራትና ተከባብሮ መኖር ከቤተ ክርስቲያኒቱ የአመራር መርሆዎች መካከሌ ተቀዲሚውን አጃንዲ ይዞ የሚገኝ ስለሆነ ታጋሽና ልበ ሰፊ ሆኖ መሥራት ብሩህ ተስፋን የሚያስገኝ ውጤት እንጂ ጠባብ አመለካከትን የሚያሰተናግድ ተልእኮ የለውም፡፡
ከዚህ አንፃር በድርጅቶቻችን ማለትም በመመሪያ ሰጭው በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና በመመሪያ ተቀባዩ በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የተከሰተው የሥራ አለመግባባት ችግር ለዚህ ከፍተኛ የሰላም ጉባኤ ቀርቦ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን ከተፈቀደለት መተዳደሪያ ደንብ ሳይወጣ ከማደራጃ መምሪያው የሚተላለፍለትንን መመሪያ እየተቀበለ ይሠራ ዘንድ የሚከተለውን መመሪያ ሰጥተናል፡፡
መመሪያ
የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ዘርፍ በሆነው በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና በሥሩ በሚንቀሳቀሰው በማኅበረ ቅዱሳን ማኅበር መካከል በሚታየው አንዳንድ የሥራ አፈጻጸም ግድፈት ለመወያየትና ዘላቂ መፍትሔን ለማምጣት ዛሬ በተደረገው የሰላም ውይይትና ምክክር ብዘ ጠቃሚ ጉዳዮችን ለማየት ችለናል፡፡
ማኅበሩ ስለነበረው አጠቃሊይ ሥራና እንቅስቃሴም በሰፊው ተብራርቷል፡፡
ይሁንና ከዚሁ ከተገነዘብነው አንጻር የማኅበሩ ቀጣይ እንቅስቃሴ ምን መምሰል እንዲለበት የመፍትሔ መመሪያዎች ማስቀመጡ በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡
ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመ እንደመሆኑ መጠን በሥራው ሁሉ መሰናከል እንዳያጋጥመው መጠበቅ ከቤተ ክርስቲያን ይጠበቃል፡፡
ከዚህ አንጻር ማኅበሩ በቀጣይ የሥራ እንቅስቃሴው የሚከተለውን ጠብቆ እንዲሠራ ያስፈልጋል፡፡

1. ማኅበሩ ከዚሬ ጀምሮ ግንኙነቱ በመተዳደሪያ ደምቡ መሠረት ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ጋር ብቻ ይሆናሌ፡፡ ከመምሪያው ዕውቅና ውጪ የሚፈጸመው ከሦስተኛ ወገን ጋር ግንኙነት ሕገ ወጥ መሆኑን እንዱገነዘብ፣
2. የቤተ ክርስቲያኒቱን የፋይናንስ አስተዳደር ማበልጸግ የሚቻለው ገቢውንና ወጭውንም በትክክል እየተቆጣጠሩ መሥራትና ማሠራት የሚቻለው በየሥራ ዘርፉ ያለት የባለድርሻ አካላት በማዕከላዊው አስተዳደር በታተመና አንዴ ወጥ በሆነ የገቢና የወጭ ካርኒ መሥራት ሲችሉ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ከዚህ አንፃር የማኅበረ ቅደሳን አባላት እንደሌሎቹ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሥሪያ ቤቶች ሁለ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እያሳተመ በሚያሰራጫቸው የገቢና የወጭ ካርኒ እንዲሠሩ
3. ማኅበሩ ከመምሪያው በሚሰጠው መመሪያ መሠረት በእጁ የሚገኘው የሀብትና የንብረት እንቅስቃሴ ሁኔታ በዝርዝር ኦዲት እንዲደረግ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ከመምሪያው በሚቀርብለት ጥያቄ መሠረት ሕጋዊ ኦዲተር በመሰየምና በማቅረብ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት እንዲፈጽም
4. ከዚህ በፊት ከመተዳደርያ ደንቡ ድንጋጌ ውጭ የተደረገው በቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና በፖለቲካ ጉዳዮች ጣሌቃ የመግባት እንቅስቃሴ ከቤተክርስቲያኗ ፍላጎትና ከመተዳደሪያ ደንቡ ውጭ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ ማኅበሩ በፖለቲካ ጉዳዮችና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጣልቃ የመግባት አዝማሚያ ማቆም አለበት፡፡
5. የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ የማደራጃ መምሪያውና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያናችን ተቅዋማት የማኅበሩን መተዲደደርያ ደንብ ማዕልድ ባደረገ ሁኔታ ማኀበሩ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የሚያቀርብላቸውን ጥያቄ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ዛሬ በስፋት የተገነዘብነው ነገር ቢኖር በሁሉም አቅጣጫ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በወጣው መተዳደሪያ ደንብ ያልተሠራ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ከመተዳደሪያው ደንብ ውጭ መሥራትና መንቀሳቀስ ሕገ ወጥ መሆኑን ሁሉም ተገንዝቦ በመተዳደሪያ ደንቡ ብቻ እንዲሠራ ይህን መመሪያ አስተላልፈናል፡፡

ይህን ውሳኔ ማቅ 10 ቀን ውስጥ ካልፈጸመ የሚፈጸምበት አስተዳደሪያዊ ውሳኔ ምን ይሆናል የሚለው ከወዲሁ አጓጊ ሆኗል።
 

5 comments:

  1. የቤተክርስቲያናችንና የሐገራችን የካንሰር በሽታ የሆነው እራሱን ማህበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው የማፊያ፣ የወሮበላ፣ የአሸባሪ፣ የመሰሪ ድርጅት የተሰጠው ደብዳቤ ብጣም አስፈላጊ መሆኑ ፍፁም ጥርጥር የለውም። ሆኖም ግን ቤተክርስቲያናችንን ሐያ አመት ሙሉ የገዘገዛትና ምዕመኑን በእምነትና በቤተክርስቲያን ሥም ሲዘርፍ ለኖረ የሠይጣን ድርጅት በአሁኑ ጊዜ ግን በቃህ ሊባል ይገባው ነበር እንጂ የማስተካከል ደብዳቤ ብቻ መቀበል የለበትም። ማህበሩ ባጠቃላይ ለቤተክርስቲያናችንና ለሐገራችን ፈፅሞ አስፈላጊ አይደለም። ማቅ ካልተዘጋ በቀር በየጊዜው የማፊያ ስትራቴጁን እየቀያየረ የቤተክርስቲያንን ደምና የክርስቲያኖችን ደም ሲመጥ ለመኖር አላማ ስላለው እባካችሁ የቤተክህነትና የሲኖደስ አባቶች ይህንን መሰሪ የሰይጣን ማህበር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከካንሰሩ እንድትታደጉት በህያው እግዚአብሔር ሥም እንለምናችኁለን።

    ReplyDelete
    Replies
    1. እናንተ በስራቹህ ካመናቹህ ለምን ራሳቹህን አትገልጡም፡፡ እና ምን ይጠበስ!

      Delete
  2. እግዚአብሔር ግዜ አለው

    ReplyDelete
  3. የቤተክርስቲያን ካንሰሮች እማ እናንተ እራሳችሁ ናችሁ!! ግድላችሁም እናንተ መናፍቃኖች በቤተክህነት ውስጥ ተሰግስጋችሁ ተዋህዶን የምታጠፏት የምስላችኋል ?!አይምሰላችሁ ምክንያቶም መሰረቷ ጠንካራ ነው እና!! አቤት መሃበረ ቅዱሳን ባይኖር ኖሮ የ ቤተክርስቲያናችን እጣ ፈንታ ምን ይሆን እንደነበር ሳስበው ይዘገንነኛል!! እናንተም ምዕመኑን ለመንጠቅ እንዳትችሉ እንቅፋት ስለሆነባችሁ ነው እንዲህ እንደ እብድ ውሻ ያክለፈለፋችሁ!! እግዚኦ ነው የዲያቢሎስ ስራ!!ግን በውስጤ ማህበሩ ይፈርሳል ብዬ ቅንጣት ታህል ስጋት የለኝም!! አይሆንም እንጂ እንደው ሲኖዶሱ እንካን ይፍረስ ቢል በፍጹም አይፈርስም ምክንያቱም ማህበሩ በየአንዳንዱ የተዋህዶ ልጅ ልብ ውስጥ ታተሞ አለና!! እናም በከንቱ ባትደክሙ ምናለ

    ReplyDelete