Wednesday, May 23, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ በታሪክ ፊት ተጠያቂ የሚሆንበትን ስህተት ፈጸመ

Click here to read in PDF
  • ውሳኔው አባ ሰረቀብርሃንና ዲ/ን በጋሻው አይመለከትም
  • ማቅ ከሰንበት ማደራጃ ውጭ ሆኗል
  • የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመትንም በሐምሌ ሲሰባሰቡ እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡

ማህበሩ በተሀድሶነት የከሰሳቸው ግለሰቦች ጉዳይ በተገቢው መንገድ ተጠንቶ ስላልቀረበና ግለሰቦቹም ተጠርተው ስላልተጠየቁ እንዲሁም ምላሻቸው ስላልተሰማ፣ ጉዳዩ በዚህ የህግ አግባብ ተሰርቶ ወደፊት እንዲታይ የተባለውን፣ አቅላቸውን በሳቱና የሚያደርጉትን በማያውቁ ጳጳሳቱ አማካኝነት ማኅበረ ቅዱሳን  አስገልብጦ ግለሰቦችንና ማኅበራትን የሚመለከተውን ውሳኔ ወሰነ፡፡ በዚህም ሲኖዶሱ በታሪክ የሚጠየቅበትን ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል፡፡
ምንም እንኳ ይወገዙ ከተባሉት ውስጥ ከዚህ ቤተክርስቲያን የተለዩ፣ ኦርቶዶክሳውያን ያልሆኑና እራሳቸውም ኦርቶዶክሳውያን አይደለንም ብለው አፋቸውን ሞልተው የሚናገሩ ማኅበራትና ግለሰቦችንን ቀላቅሎ ያቀረበ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም አላማው ያደረገውም በእነርሱ አስታኮ እውነተኞቹን የቤተክርስቲያን ልጆች መምታት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ቤተክርሰቲያኒቷ መኖርዋን እንኳ የዘነጉ ግለሰቦችና ማኅበራት ተወገዙ አልተወገዙ ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለው የሚያውቀው ማቅ እነርሱን አስታኮ አውነተኞቹን የቤተክርስቲያን ልጆች ለማስጠቃት ያደረገው ሙከራ ተሳክቶለታል፡፡
ጉዳያችንን በትክክለኛ መንገድ አልታየልንም፡፡ ተጠርተን እንኳ አልተጠየቅንም፡፡ ክሳችን ምን እንደሆነ እንኳ አናውቅም፡፡ ሲኖዶሱ የሊቃውንት ጉባኤው አካሄድ ፍትሀዊነት የጎደለው መሆኑን አውቆ ነገራችንን በማስተዋል ይይልን፡፡ ያሉ ሰዎችንም ጉዳይ ቸል በማለት የሲኖዶሱ ለእንዲህ ያለ ውሳኔ መፋጠን በታሪክ ፊት የሚኖረውን ተጠያቂነት ያጎላዋል፡፡  ማንም ይሁን ማን ቤተክርስቲያን ሊኖራት የሚገባው ድርሻ የመግፋት የማባረር ሳይሆን የማስተማርና የመምከርና መሆን ነበረበት፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ ተናግሮ የሚያሳምን መክሮ የሚመልስ አባት የሌላት መሆኑን መረዳቱም እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ ሰው አጥፍቶዋል በሚል የሀሰት ምስክር ሳይሆን ማጥፋት አለማጥፋቱን በሚያረጋግጥ እውነተኛ ዳኝነት ጉዳዩ ታይቶ መወሰን ሲገባው እንዲሁ በደመ ነብስ በማቅ አሳሳች ባህሪ ተታለው እነርሱ ያጠኑት ይበቃል በማለት ሲኖዶሱ የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ መገኘቱ ያስተዛዝባል፡፡ 
የጉዳዩ ባለቤት ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና ስለተከሰሰበት ጉዳይ ድምጹ ሳይሰማ በአለማዊ ፍርድ ቤት እንኳ ተደርጎ የማያውቅ የስህተት አሰራር ላይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ወድቋል፡፡ በዚህም የመንፈስ ቅዱስን የመሪነት ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ለማኅበረ ቅዱሳን ሰጥቷል፡፡ ሲኖዶሱ የቤተክርስቲያንንም ውድቀት በዛሬው ዕለት በይፋ አውጇል፡፡አንዳንድ እንደ መንፈሳዊ ሰው ማሰብና ነገሮችን መመልከት ያቆሙትና ራሳቸው የሃይማኖት ሕጸጽ ያለባቸው ጳጳሳት ውሳኔው ካልጸደቀ እያሉ ቤቱን እያመሱት የዋሉ መሆኑ ሲታወቅ ትላልቆቹ ጳጳሳት እነ ብጹአቡነ ፊሊጶና እነ ብጹዕ አቡነ አረጋዊ አረ ተዉ ምንድን ነው ተሸቀዳድሞ ለውሳኔ መቸኮል ተጠርተው ያልተጠየቁ ሁሉ ተጠርተው ይጠየቁ ቢሉም በጎረምሶቹና ጊዜያቸውን ቤተክርስቲያንን በማገልገል ሳይሆን በነውር በሚያጠፉ ጳጳሳት ግፊት ሰነዱን አጽድቀው ወጥተዋል፡፡

ከ1000 አመት በፊት የተወገዘው አውጣኪ የተወገዘው ትክክለኛ ዳኝነት ሳያገኝ ነው ብለው የሚከራከሩት የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎችም ዋናው ዳኝነተ ሳይሆን ውግዘት ነው ብለው ለውግዘት ተፋጥነዋል፡፡ በርግጥ ማቅ ነገሮችን የሚያየው ከንግድ ህግና ከጥቅም አንጻር ስለሆነ በሚታይም በማይታይም መንገድ ነጋዴ ባህሪውን ያቀጨጩበትን ወገኖች ቀላቅሎ ሰነዱን ማስጸደቁ ከባህሪው አንጻር ባያስገርምም ለትክክለኛ ዳኝነት የተዘጋጀ ልብ ከአባቶች ዘንድ መጥፋቱ አስገርሟል፡፡
መቼ ይሆን ቤተክርስቲያን ልጆችዋን ከመግፋት ተቆጥባ ስህተት አለባቸው የምትላቸውን መክራና ገስጻ ጌታችን በቃሉ ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ ባለው መሰረት የሚድኑት እንዲበዙ መፋጠን የምትጀምረው?መቼ ይሆን ከሌላው በረት ለመንጠቅ የጠፉትን በእውነት መንገድ የመምራት ልብ የሚኖራትስ? መቼ ነው የራስን በረት እያራቆቱ ያንን ደግሞ በድል ዜማ ማስነገር የሚያበቃው? እንዲህ ያለው ድርጊት ህሊና ላለው ሰው አሳፋሪ ነገር ነው፡፡
ባለፈው የህዝብ ቆጠራ ቤተክርሰቲያናችን ከስምንት ሚሊየን ህዝብ በላይ አማኝ ማጣትዋ ሳያስደነግጠንና መፍትሔ ለመፈለግ ሳያንቀሳቅሰን እንደገና ያለበቂ ምርመራ ልጆችዋን መግፋትዋ አስተዛዛቢ ጉዳይ ሆኗል፡፡
ቤተክርስቲያን በታሪክዋ ኑፋቄ ስታወግዝ ብቻ አይደለም የኖረችው፡፡ አጠፉ የተባሉትን ጉዳይ አጥንታ መክራ መመለስ ዋና አጀንዳዋ ነበር፡፡  ማቅ ራሱ ለወሬ ማድመቂያ ከጨመራቸው በቀር የከሰሳቸው ሰዎች ትክክለኛ ዳኝነት ቢያገኙ ምንፍቅና እንደማይገኝባቸው ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ አባቶች የማቅን ቂምና ጥላቻ አክብረው ትክክለኛ ዳኝነት ሳያሳዩ የወሰኑት ውሳኔ በምድራዊ መንግስት ትዝብት ላይ ሲጥላቸው በሰማያዊው መንግስት ደግሞ ያስጠይቃቸዋል፡፡ ለመንጋው የማይጠነቀቁ ሙያተኞች ሆነው በእግዚአብሔር መንግስት ላይ የሀሰተኛው ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ በሆነው ማኅበረ ቅዱሳን እጅ ላይ መውደቃቸው በእጅጉ የሚያሳፍርና የሚያሳዝን ነው፡፡ ቤተክርስቲያን የእውነት ወገን ሆና በእውነተኛ ዳኝነት ልጆችዋን መጠበቅ ሲገባት ለመንጋው በማይራሩ እረኞች ስር መውደቅዋ በታሪክዋ ትልቁ ውድቀትዋ ነው፡፡
ውሳኔው አባ ሰረቀብርሃንንና ዲ/ን በጋሻውን እንደማይመለከት ታውቋል፡፡
በሌላ ዜናም ማኅበረ ቅዱሳንም ከሰንበት ማደራጃ ሥር ወጥቶ እንደ ልማት ኮሚሽን ራሱን ችሎ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡ ማቅ በዚህ ውሳኔ ጮቤ ቢረግጥም ሲፈራውና ሲሸሸው የነበረው ሂሳቡ በውጭ ኦዲተር የመፈተሹ ጉዳይ አይኑን አፍጥጦ መጥቶበታል፡፡
የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመትንም በሐምሌ ሲሰባሰቡ እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡

10 comments:

  1. maferi leba hula!!!zemebelehe tultula awera

    ReplyDelete
  2. Asafari sehette nwe abte Yatce betekerestiyan honaleche afereyalu azegalu.

    ReplyDelete
  3. mk will be defeated by the power of God. we will c that soon. we stand against any move which is out of our church dogma.mk is against Gods will so we all witness its failer.

    ReplyDelete
  4. you never never, never succeed with your devil-led agenda. there is a real demarcation b/n protestant & orthodox. why the wolves supported and drawn by/from protestant organization want to make havoc in our church?b/c their leader is not god but dabilos. our church and MK will exist serving us everlasting. go down, you wolf!!!!!!

    ReplyDelete
  5. ተወጋዦች አውጋዦች፣ አውጋዦች ተወጋዦች የሆኑባት ቤተክርስቲያን
    ውግዘት ከእውነተኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርትና በእርሱ ላይ ከተመሰረተው እውነተኛ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ በተቃራኒ የቆመን የቤተክርስቲያን አባል (አገልጋይ/ምእመን) ቤተክርስቲያን መክራና ዘክራ አልመለስም ብሎ አቋሙን በግልጽ ሲያሳውቅና በእንቢተኛነቱ ሲጸና መጨረሻ ላይ ቤተክርስቲያን ያን አባሏን ከአንድነቷ ለመለየት የምትወስደው እርምጃ ነው። ይህም ሲሆን ቤተክርስቲያን ቅድሚያ የምትሰጠው ለውግዘት ሳይሆን አባሏን በንስሃ ለመመለስ ነው። ሁሉንም አማራጮች ተጠቅማና ሊያስወቅሳት የማይችለውን እድል ሰጥታ አባሏ አልመለስ ብሎ በኑፋቄው/በክህደቱ ሲጸና እያዘነች የምታስተላለፈው የከበረ ውሳኔዋ ነው። በዚህ መንገድ የተላለፈ ውግዘት ተቀባይነት አለው። ከዚህ ውጪ በቂም በቀል፣ በጥላቻ፣ አንዱን ወገን አስደስቶ ሌላውን ለመጉዳት የሚደረግ ውግዘት ግን ተቀባይነት የለውም። የማቅና እርሱ አእምሮአቸውን የተቆጣጠረው ጳጳሳት እንዱ ችግር ውግዘት ምን እንደሆነና በምን ምክንያት እንደሚተላለፍ አለማወቃቸው ነው። ውግዘት ለእነርሱ ቂምን መወጫ፣ ጠላትን ማጥቂያ መሣሪያ ነው።
    ውግዘት እጅግ የተራከሰባት ቤተክርስቲያን ብትኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ናት። በገጠር ቀሳውስቱ በትንሽ በትልቁ «ገዝቼሃለሁ» እያሉ አርሶአደሩን ሲያስፈራሩ ነው የኖሩት። ዋና ምክንያታቸው ደግሞ በበአል አረስክ፤ ቆፈርክ ነው። ሊያስወግዝ በሚችል ለምሳሌ ጠንቋይ ቤት ቢሄድ ግን ቃልም አይናገሩትም። እነርሱም ወደዚያው ጎራ ማለታቸው አይቀርምና። ይኸው በትንሽ በትልቁ፣ በሆነው ባልሆነው የማውገዝ ልማድ ስር በመስደዱ ፈጽሞ ሊያስወግዝ በማይገባ ምክንያት ማውገዝ ስልጣን በሌላቸው አካላት ሁሉ ሲተላለፍ ነው የኖረው። በተለይም በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን ብዙዎች የቤተክርስቲያን ልጆች «ተወግዘሃል» የተባሉት፣ ተገኘባቸው ስለተባለው የሃይማኖት ሕጸጽ ተጠርተው ሳይጠየቁና ምላሽ ሳይሰጡ፣ ሳይከራከሩና ሳይረቱ፣ ስሕተታቸው በሚገባ ሳይነገራቸውና ሳይቀበሉት፣ በማኅበረ ቅዱሳን ከሳሽነት ብቻ «ተወግዘሃል» ይባላሉ። ማኅበረ ቅዱሳንም የሚወገዙ ሰዎችን ሰልሎ ማቅረብን እንደጽድቅ ነው የሚቆጥረው። እንዲህ ባለ ግብር እነሆ 20 ዓመታትን አስቆጠረ እኮ።
    ባለፉት 20 ዓመታት ተወግዘው የተባረሩ ሁሉ በሕጋዊ አካል ተወግዘው የተባረሩ አይደሉም። በህገወጦችና በማያስወግዝ ምክንያት በህገወጥ መንገድ «የተወገዙ» ናቸው። የህግ የበላይነት ባልሰፈነባትና ሁሉም አዛዥ በሆነባት ቤተክርስቲያን ውስጥ መወገዝ የሚገባቸው ሰዎች መወገዝ የማይገባቸውን ሰዎች ሲያወግዙ ኖረዋል። ይኸው አሰራር አሁንም ቀጥሏል። ቤተክርስቲያኗ ምን ያህል እንደዘቀጠች፣ ምን ያህል አንቱ የሚባል ሰው እንደታጣባት፣ ምን ያህል ከክርስቶስና ከሐዋርያት፣ እንዲሁም ከሰለስቱ ምእት ትምህርት እንደራቀች ያሳያል። ወደዚህ ደረጃ እየወረደች የመጣችው፣ ጳጳሳትን በሃይማኖታዊ ዕውቀት ብቁነታቸውን፣ በመንፈሳዊነት ኑሯቸውን መዝና መሾም ካቆመችበት ዘመን አንስቶ ነው። የዛሬዎቹ እነአባ አብርሃም «የራጉኤልን ፎቅ ሰሩ» ተብለው የተሾሙ ዕለት ጵጵስና እጅግ መውረዱን ገምተን ነበር። እንደገመትነውም ይኸው ለተቀመጡበት መንበረ ጵጵስና በማይመጥን አኳዃን በማኅበረ ቅዱሳን ጭንቅላት እያሰቡ ማኅበሩ «እነእገሌን እንድታወግዙ» ሲል የሰጣቸውን ተልእኮ ለመፈጸም የሲኖዶሱን ስበሰባ ሲያውኩ ዋሉ።
    ለመሆኑ የቅባት እምነት ተከታይ የሆኑትና ከትምህርተ ቤት በቅባትነታቸው ተባረው የነበሩት፣ ከቅባት ባህለ ትምህርት ያልወጡት አባ አብርሃም፣ ራሳቸውን በደብተራ ስራ በርቀት (በግዘፍ አይደለም) «ጃንደረባ» አድርገው የቆዩትና አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ የአዲስ አበባ ጥቂት የማይባሉ መነኮሳት እንደ ሕጉ ከሴት ርቀው ንጽሕ ጠብቀው የማይኖሩ መሆናቸውን ሲገነዘቡ፣ ያን በርቀት ጃንደረባ ያደረጋቸውን ደብተራ ካለበት አስመጥተውና ዳጎስ ያለ ብር ከፍለው ያሰረውን እንዲፈታ አድርገው ከጃንደረባነት ወደ … መሸጋገራቸውን ድፍን የራጉኤል ቤተክርስቲያን ካህናት የሚያወራው እውነት ነው። ስሟን ለጊዜው መጥቀስ ከማያስፈልግ አንዲት ሴት ጋር ስለነበራቸው ግንኙነትም ቢጠየቁም የሚናገሩት ብዙ ምሰጢር አለ። ሙት ወቃሽ አያድርገንና በአጭሩ ከተቀጩት ከሟቹ አቡነ መልከጼዴቅ ጋርም ከዚህች «ቆብ አስጥል» ሴት ጋር ጦርነት ውስጥ ገብተው እንደነበርም አክለው መናገራቸው አይቀርም- ካህናቱ። ውግዘት ካስፈለገ ይህ የእምነትም የምግባርም ጉድለት አባ አብርሃምን ባስወገዛቸው ነበር። ከላይ እንደተገለጸው ግን ቤተክርስቲያናችን መወገዝ ያለባቸው አውጋዦች የሚሆኑባት የፍርደገምድሎች፣ የህሊናቢሶች መናኸሪያ ሆናለች።

    ReplyDelete
  6. Yemahberekidusan degafiwoch comment sisetu Endemenfesawi sewTiru ena metfo kaLat merto mawrat lemindinew yemisaNachew?newur yehonewun leytew yemayaweru newreGnach.

    ReplyDelete
  7. ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት አብረን እንስራ!!!

    ReplyDelete
  8. This is the beginning !! Betekiristianachin sew yelelat eskimesil dires menafikanoch mebere patriarick dires gebatachihu cheferachihual. Egzihabiher gize alew !! Genna yekerut rizirajochachihum tetergew ke kidist betachin yiwetalu !! Begashaw,sereke,Ejigayehu,abba paulos will be out next ! cuz they are not orthodox ! rather protestant and weyane brokers !!

    ReplyDelete
  9. Sima? Ante balege kezih belay asteyayet yesetehew
    Le afh leket yelewm? Yekidus sinodosn menber yemimerutn abat defreh yemtnagerew? Kante gara yekolo guadegna nachewn? Ere egzi'abhern fra? Gibre geb yinurh tihitinan temar. Abaten Atakalilu amlakachew yiferdbachewal .yemahberekidusan abal mehon mallet yemengistesemayat zega mallet endaydele ewok. Aba paulos Betam tagash abat bemehonachew Mikniat yebetekristianitun Talak mery atizlef tikesefaleh

    ReplyDelete
    Replies
    1. በጣም ደስ የሚለው ነገር እምነትን ከልብ አውጥቶ የሚወስድ ማንም የለም። ተወገዙ አልተወገዙ ምንም ትርጉም
      አይሰጥም። ምክንያቱም ለእውነተኛ ክርስቲያኖች እንዲህ ተበሎ ተፅፉአልና፤ በኔ ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ክፉውን
      ሁሉ በውሸት ቢናገሩባችሁ፣ መከራም ቢያበዙባችሁ፣ የምታምኑትን ታውቃላችሁና እንዲሁም እኔ ዓለሙን ሁሉ
      አሸንፌዋለሁና አይዙአችሁ፣ በመከራም ደስ ይብላችሁ እስከ መጨረሻው የፀና እርሱ ይድናል ብሎ ጌታችን አምላካችን
      መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ አስጠንቅቆናልና ከምንም አንቆጥረውም። ድሮም እኮ ማቅ የግብር አባቱን
      የዲያቢሎስን ሥራ ለመስራት ነው የሚሩሩጠው ይህ እኮ የታወቀ ነው። ነገር ግን ድሉ የኛ የተገፋነው ክርስቲያኖች ነው።

      ማቅና ግብረአበሮቹ እንኩአን አሁን ጌታችንንም ሰቅለው ሲሳለቁና በትዕቢት ተወጥረው ሲሳደቡ የነበሩ ናቸው። ታዲያ
      ማቅ ያልገባሽ ነገር ቢኖር ድሉ ማታ ነው ድሉ ሲባል ሰምተሻል አይደል\ የኛ ጌታ እኮ የአሸናፊዎች አሸናፊ ነው።
      እንኩአን በክርስትናቸው የበሰሉትን ወንድሞቻችን ቀርቶ ገና ወተት የሚመገቡ በክርስትና ያልበሰሉትን እንኩአን ከእጁ
      ማንም ፈልቅቆ ሊያወጣቸው አይችልም። አሜን። ማፈሪያው ማቅ ኪ...ኪ....ኪ.................

      Delete