Thursday, July 26, 2012

ማህበረ ቅዱሳን እና የወደፊት እቅዱ

about mk: Read in PDF
(ሐምሌ 19 2004 ዓ.ም.፣ ዐውደ ምሕረት/www.awdemihret.blogspot.com) (ይህን ጽሁፍ ያገኘነው ፌስቡክ ላይ ነው። ጸሀፊው ራሱን ማህበሩ ውስጥ ሆነን የማህበሩን አደጋ ገልጠን የጠቆምን የቁርጥ ቀን የቤተክርስቲያን ልጆች” ሲል ይገልጻል። ጸሃፊው አለኝ በሚላቸው መረጃዎች መሰረት ጽሁፉን አዘጋጅቷል። የማኅበሩን የኑፋቄ ትምህርት ጨምሮ ጊዜ የምጠብቅላቸው ሌሎች መረጃዎች አሉኝ የሚለው ጸሐፊ እንደ ውስጥ አዋቂ የማኅበሩ እቅዶች እነዚህ ናቸው ሲል ይነግረናል። እንደ ጸሐፊው እምነት ማኅበሩ ከቤተክርስቲያን ተገንጥሎ እስከ መውጣት የጨከነ “ራዕይ” ያለው ነው። ለዚህም የሚረዳውን ጥናት የጨረሰ ሲሆን ተጨማሪ ጥናቶችን ለማድረግ ግብጽ ድረስ ሰው ልኳል ይለናል። በብሎጋችን እንዲወጡላችሁ የምትፈልጉዋቸው ጽኁፎች ካሉዋችሁ awdemihret@live.com ብላችሁ ብትልኩልን ይደርሰናል።  መልካም ንባብ)

ማህበረ ቅዱሳን ሁለት አይነት እቅድ አለው። አንደኛው ቤተክርስቲያኒቱን መቆጣጠር ሲሆን አሱ ካልተሳካ ደግሞ ሁለተኛውን ማለትም ሂደቶችን አይቶ በቂ የሚለውን አቅም ከገነባ በኃላ ወደፊት ተገንጥሎ የመውጣት ድብቅ ራዕይ አለው፡፡ ሁለተኛው አላማውም በቤተክርስቲያን ላይ አደጋ ለመፍጠርና አባላቱን ይዞ የራሱን ቤተ እምነት መመስረት ሲሆን ጉዞውን 40 በመቶ አድርሷል፡፡ ይህን እቅዱን ለማሳካት የተጠና እስትራቴጂ አዘጋጅቶ ተግባር ላይ አውሏል፡፡ ከእቅዶቹ ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተሉት ይቀርባሉ

1- ወደፊት ማህበሩ ቤተክርሰቲያኒቱን ከተቆጣጣረ ወይም ደግሞ ከተገነጠለ የራሱ አገልጋዮችን ብቻ መጠቀም ስለሚፈልግ ለሚገነጥለው ቤተ እምነት አገልጋይ እንዲሆኑ ካህናትንና መነኮሳትን በገዳማትና በአብነት /ቤቶች በጥንቃቄ ማሰልጠን እንዲቻል ከፍተኛ በጀት መድቧል፡፡ ይህን ስውር ተልእኮ ሊቃነ ጳጳሳቱ ነቅተው እንዳያስቆሙት በዘዴና በጥንቃቄ መያዝ
2- ጵጵስና ለቀሳውስት እንዲሰጥ በቅ/ሲኖዶስ ግፊት እንዲያደርጉ የማህበሩ አባላት የሆኑ ጥቂት ጳጳሳትን ማሳመን በዚህ ጉዳይ ጥናት እንዲሰሩ ስንታየሁ የተባሉ አንድ ቄስ ግብጽ ሃገር ተልከዋል፡፡
3- በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ የማህበሩን አላማ በስውር የሚያስፈጽሙ ጳጳሳት እንዲሾሙ ማህበሩ መነኮሳትን መልምሎ በምርጫው ግዜ አባቶች ድምጽ እንዲሰጣቸው በየቤታቸው እየዞሩ የማግባባት ስራ መስራት፡፡ ማግባባቱ ለሃገረስብከታቸው እስከ ሁለት መቶ ብር በጀት ድጎማ ማድረግን፣ በግል እጅ መንሻ ማዘጋጀትን በአንዳንድ በልማት እቅዶቻቸው ውስጥ የማማከር ድጋፍ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ለቤተክርስቲያን ቢጠቅሙም ለማህበሩ አካሄድ ግን አደገኛ ናቸው ያሏቸው አባቶች እንዳይሾሙ አባላት በሆኑ ጥቂት አባቶች በኩል መታገልና በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት በእያንዳንዱ ሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ ተሰሚ የሆኑ አባላትንና አንዳንድ ባለጸጎችን በመላክ የማሳመን ስራን መስራት፡፡ እንቢ ያሉትን ማስፈራራት
4- የማህበሩን አካሄድ ትክክል አይደለም መታየት አለበት የሚሉ ጳጳሳትን ሰባኪያንን የአስተዳደር ሰዎችንና የመንግስት አካላትን ህዝቡ እንዲጠላቸው መናፍቃን ሆነዋል ተወግዘዋል ሌላ ተልእኮ አላቸው ወዘተ የመሳሰሉትን ቀለሞች በመቀባት ሃይላቸውን ለማድክም መሞከር፡፡ ይህን በአሜሪካና በአውሮጳ በገንዘብ የሚደግፍ ኮሚቴ በነያሬድ /መድህን በነዳንኤል ክብረት በነህብረት የሺጥላ በነፋንቱ ወልዴ በነዶ/ መስፍን የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው የማህሩን የጥፋት አላማ የሚያደናቅፉትን ሁሉ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድባቸው በፋይናንስ መደጎም ሲሆን በስውር ሲዲ እያዘጋጁ መበተን፣ ስብሰባ እያዘጋጁ ባለጠጎችን ቤተክርስቲያን ልትፈርስ ስለሆነ እንድረስላት ገንዘባችሁን ስጡን በማለት የማህበሩን አቅም ማደራጀት፣
5- ለጥምቀት ምንጣፍ የሚያነጥፉ የዋህ ወጣቶችን ቀስ ብሎ ወደ ማህበሩ በማስገባት ቤተክርስቲያን አደጋ ላይ ነች ድረሱላት በማለት የአመጽ ትምህርታቸውን አስተምሮ ወደ ነውጥ እንቅስቃሴ እንዲገቡ በማድረግ ተጨማሪ ሃይል እንዲሆኑ ማሰልጠን፣
6- በአዲስ አበባ እና በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የሰንበት /ቶች ሰርጎ መግባትና የማህበሩን መሰረት ማስፋት ካልተቻለ በየአጥቢአው ቢሮ በመክፈት ሰንበት ትምህርት ቤቶችን መበጥበጥ እና ማፈራረስ
7- በመንግስት ፖለቲካ ውስጥ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት በተጠና ሁኔታ ማጠናከር ይህም በሃገር ውስጥ ያሉ አባላት መንግስት እንዳይመታቸው የቤተክርስቲያኑን ጉዳይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ በውጭ ያሉት ግን የተለያዩ ሚዲያዎችን እየተጠቀሙ መንግስትን እንዲቃወሙ ተደርጎ እስትራቴጂው ተቀርጿል፡፡ ደጀ ሰላም፣ አንድ አድርገን፣ደቂቀ ናቡቴ፣ savewaldeba, ecadforum … የተባሉትን ድረ ገጾች በመጠቀም ጸረ ሰላም ቅስቀሳዎችን ማጠናከር ፡፡
8- ማህበረ ቅዱሳንን ራሱን ችሎ እንዲወጣ የገንዘብ አቅሙን ቋሚ በሆነ ሁኔታ ማጠናከር ይህም የማህበሩን ህንጻ መገንባት፣የቤተክርስቲያን ልጆች በተለይ መንግስት ሰራተኞች ለቤተክርስቲያናቸው ሳይሆን ለማህበሩ አስራት አንዲከፍሉ ማድረግ፣ በተለያዩ ቦታዎች የንግድ ተቋማትን መመስረት፣ አንድ ባንክ በአባላቱ አክስዮን (እንቅስቃሴው ተጀምሯል።) መክፈት ወዘተ
9- በቤተክርስቲያን መድረኮችና በግል ሚዲያዎች ላይ የህዝብን ሰላም የሚያውክ የጽንፈኝነት ቅስቀሳ ማጠናከር፡፡ ይህን እንዲመሩ የተወሰኑ መምህራንን መድቦ ጽንፈኝነትን በሃይማኖት ቤተሰቦች ላይ ሽብርን እና ቅራኔን በሃማኖቶች መካከል የማስፋት ስራን አጠናክሮ መቀጠል፣ እንዲሁም በአንዳንድ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ አርባ ምንጭ፣ደሴ፣ በአውሮፓ አሜሪካ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባሉ ትላልቅ አብያተክርስቲያናት ያሉ መምህራንን በጥቅም በመደለል በቤተክርስቲያን መድረክ ማህበሩን ማስተዋወቅ ችግር ተፈጥሯል፣ ቤተክርስቲያን መሪ የላትም ሲኖዶሱ የሞተ ነው መንግስት ቤተክርስቲያንን እየገደለ ነው እያሉ ሁከት በመፍጠር ህዝቡ እንዲታወክ ቤተክቲያንን እንዲሰለችና እረኞቹን ከበጎቹ ነጥለው ወደ አዲሱ ቤተእምነታቸው እንዲቀላቀሉ መሳብ
10- ቤተክርስቲያን በራሷ እንዳትተማመን በስነ ልቦና ጦርነት ማሽመድመድ ይህም ጠንከረው የሚሰሩ ሰባኪዎቿንና ሰራተኞቿን በሃይማኖት ስም ከስሶ በማዳከም ፈሪ እንድትሆን ማድረግ ዝም ማሰኘት፡፡ ልጆቿን በየአሉበት ፈልጋ እንዳታስተምር ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ ሰብካ ወደ በረቷ መስብሰብ እንዳትችልማከላከል የንስሃ አባቶች እንኳ ልጆቻቸውን በየቤታው ሄደው እንዳያስተምሩ፣ በቤተክርስቲያን ግቢ የሚደረጉ ጉባኤዎችን የመናፍቃን እጅ አሉባቸውና ምእመናን እንዳይሄዱ ቅስቀሳ ማድረግ፣ማህበረ ቅዱሳን ከጠራው ጉባኤ ውጭ ሌሎቹ የተሳሳቱ አድርጎ ማቅረብ፣ መዝሙር እንዳይዘመር፣ ሰባኪዎችን ሁሉ ሰው እንዲፈራቸው፣ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ ቤተክርስቲያን ዝም እንድትል እና ሌሎች እንዲቀድሟት ለማድረግ አባቶችንም ስርአት ተጣሰ ህግ ፈረሰ ብለው በማደናገር ለክፉ ተልኮአቸው ተባባሪ እንዲሆኑ ማድረግ። በአዲስ አበባ አሁን የሚታየው የመናፍቃን ሩጫ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን ያሉ አገልጋዮችንን አገልግሎት ማዳከም እና ሜዳውንም ፈረሱንም መጋለብ ለሚፈልግ ሁሉ ባዶ የመተዉ ውጤጥ ነው። የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ሁል የማኅበረ ቅዱሳን አባል ካልሆኑ ማገልገል የለባቸውም በሚል አቋሙ ቤተክርሰቲያኒቱን ባዶ እያስቀራት ይገኛል። ሎሎች ሀይማኖቶችም ያለጠባቂ ያገኙትን ሕዝብ ወደ እራሳቸው ቤተ እምነት ያለ ከልካይ እያጋዙት ይገኛሉ። ይህን ለማረጋገጥ ወጣ ብሎ በዚህ ወር ብቻ በየመንገዱ የተለጠፉ ፖስተሮችን ብዛት ማየት ይበቃል።

11-
የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነገረ መለኮትን የምታስተምርባቸው መንፈሳዊ ኮሌጆች ማለትም /ጳውሎስ፣ቅ/ሥላሴ፣መቀሌ ከሳቴ ብርሃንን ዝዋይ ሃመረ ብርሃንን የመሳሰሉትን መጠናከር ለማህበሩ መደብዘዝ ትልቀ ሚና ስላለው የኮሌጆቹች አስተዳደር በመቆጣጠር ማዳከም ካልተቻለ የመናፍቃን መውጫዎች ናቸው ብሎ ህብረተሰቡን ውስጥ ጥርጥር መዝራት፡፡ ከጥቂት ከአራት አመት በፊት በቅ/ጳውሎስ ኮሌጅ ለ3 ዓመታት አዲስ ተማሪ እንዳይገባ አስደርጎ ያሉት ከወጡ በኃላ የማኅበሩን አባለት ብቻ ለማስገባት ጥረት ቢያደርግም አሁንም ቢሆን ወንጌልን ጠልቶ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚከተል ደቀ መዝሙር ማግኘት አልቻለም። ጥረቱ ግን እንደቀጠለ ነው።
12- እየደበዘዘ የመጣውን ማህበረ ቅዱሳንን ገጽታ /image/ እንደገና ለመመለስ የቤተክርስቲያንን ሰባኪዎችን ከመድረክ አስወርዶ የማህበሩን መምህራን መመለስ፣ መዘምራኖቻቸውን እና መምህራኖቻቸውን ይዞ በየሃገረስብከቱ የጉዞ ፕሮግራም አዘጋጅቶ መለያየትን ሽብርን ማጠናከር፣ ማህበሩን ማስተዋወቅ እና የኑፋቄ ትምህርቶችን በፈሊጥ ማስተላለፍ

13-
አባቶችን በአስተዳደራዊ ስራቸው ምክር በመስጠት ስም ማደናገር እና ስህተት እንዲጽሙ ግፊት ማድረግ

14-
ማንኛውንም መስዋትነት ለመክፈል አባላቱን ማነቃቃት፣ አላማቸውን የሚያጋልጥባቸውን ሰው ከውስጥም ከውጭም ቢሆን አሳዶ መጣል፡፡ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

አባላቱ እንዲያደርጉት በጥብቅ የሚታዘዙት

1-
አባቶችን በያሉበት በዘዴ እንዲይዙ፣ በየሃገረ ስብከቱ በሚካሄዱ የካህናት ሴሚናሮች ላይ የምሳ ግብዣ(ከገንዘብ ያለፈ አቅም ስለሌላቸው) እንዲያደርጉ ፣ በቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ለአባቶች እራት እንዲጋብዙ ወዘተ
2- በንግግሮቻቸው ሰው እንዳይጠረጥራቸው አባቶች እንዳሉት ቅዱሳን እንዳሉት በማለት የራሳቸውን ሃሳብ እያዋዙ እንዲያስተላልፉ

3-
ሰውን ሲቀርቡ አንገታቸውን ሰበር እንዲያደርጉ እጆቻቸውን እንዲያጣፉ አለባበሳቸውን እንዲጠነቀቁ
4- የኑፋቄ ትምህርቱን ከአክራሪነት ጋር እንዲያዛምዱት ፡፡ ይህም ስርአት ተጣሰ ህግ ፈረሰ በማለት ለህግና ለስርአት የቀኑ በመምሰል የህዝቡን ስነ ልቦና መውሰድና በዚህ ውስጥ የስህተት ትምህርትን ማስገባት፡፡ ይህ ስልት የትኞቹም የመናፍቃን ቡድኖች እስካሁን ያልሞከሩት ሲሆን ለማህበሩ ግን የተሻለ ጥቅም ሰጥቶታል፡፡
5- በየአብያተክርስቲያናቱ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ
6- የቅ/ሲኖዶስ አባላትን፣አገልጋዮችን፣የሰት/ አባላትን ፣አጥቢያዎችን መከፋፈል፡፡ በአንድ ወቅት ዳንኤል ክብረት በስብሰባ እንግሊዝ ከፋፍላ ባትገዛ ኖሮ ታላቅ አትባልም ነበር እንዲሁ በመከፋፈል ካልተሰራ ማህበሩ አይቆምም” ብሎናል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ከተወሰኑ አመታት ወዲህ ተስማምቶ አያውቅም ይህም የማህበሩ መማክርት ከጀርባ ለአንዳንድ አባቶችን እንዳይስማሙ ጥብቅ ምክር ስለሚሠጡ ነው፡፡ ከስብሰባው በኃላ በጥብቅ የሚጠበቀውን ውሎ ቅርብ ከሆኑ አባቶች በመስማት በግል ጋዜጦችና ድረገጾች አዛብቶ በመልቀቅ አማኙን የማሳፈር ሥራይሰራሉ፡፡ በዚህም የቤተክርስቲያንን ገጽታ ያበላሻሉ፡፡ በአሜሪካ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ተከፋፍለው ህዝቡ እንዲማረር የተማረረውም ወደ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ እንዲሄድ ምክንያት አየሆኑ ነው፡፡ ይህ አሰራር እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በሚል ሀሳብ የሚያቀነቅኑት አካሄድ ውጤት ነው፡፡
7- ጥንታዊ ንግግር ካልተናገርክ ጎንደርን አትወስድም የሚል ፈሊጥ ይጠቀማሉ፡፡ በንግግራቸው ሁሉ እንዳይታወቁ ጥንታዊ አማርኛ መጠቀም ያዘወትራሉ። ይህ ከደቡብ ለመጡ ከኦሮሚያ ለመጡ አማርኛ ሁለተኛ ቋንቁዋቸው ለሆኑ አገልጋዮች ምን ያህል ፈተና እንደሚሆን አስቡት። ስለኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት አለመናገር ተጨማሪው አካሄድ ነው፣ ጥቂት የግዕዝ ቃላትን በመሸምደድ አድማጩን ማታለል የጋራ ስልታቸው ነው፡፡
8- ማህበራችን እንዲህ አድርጎ እንዲህ ሰርቶ በማለት የማህበሩን ስም ከቤተክርስቲያን ክብር በላይ እንዲያደርጉና የቤተክርስቲያንን ስራ እኛ ሰራነው ብለው ሪፓርት እንዲያቀርቡ ጥብቅ መመሪያ ወጥቶላቸዋል፡፡

9-
ማንኛውንም ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ በድፍረት ማድረግ ማህበሩን ስለሚያስመታ ከጀርባ ለጥቅም ባደሩ ሰባኪዎች እና ነጋዴዎች በመጠቀም እንዲፈጸም ግዴታ ተሰጥቷቸዋል፡፡
10- ጥያቄና ጫና ሲበዛ /ሲኖዶስ እውቅና ሰጥቶናል እያሉ እንዲከላከሉ መውጫ ተሰርቶላቸዋል፡፡
11- ያለ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን የለችም የሚል አመለካከት በኢንተርኔት እንዲሰራጭ አድርጎ ቤተክርስቲያንን ማስካድ
12- ለፓለቲካውም ለምንፍቅናውም ለጸረ ሰላም እንቅስቃሴውም የዩንቨር ሲቲ ተማሪዎችን እንደ ዋንኛ ግብአት ማድረግ

ቤተክርስቲያን ማድረግ የሚገባት

1-
በኮሌጆችና በዩንቨርስቲ ውስጥ የሚሰጡ የግቢ ጉባኤ ትምህርቶችን የሚቆጣጠርና በሃላፊነት የሚመራ ከሊቃውንቱ ከአብነት መምህራን እና ከኮሌጅ ተመራቂዎች ጋር አቀናጅታ በስብከተ ወንጌል መምሪያው ስር ብታደራጅና በየአህጉረ ስብከቶች መዋቅሩን በዚህ መልክ ብትዘረጋ፡፡

2-
የሰንበት /ቤት ተማሪዎችን የሚያስተምሩ የሚከታተሉ ጠንካራ እና መንፈሳዊ መምህራንን ከአባቶችም ከሊቃውንቱም አደራጅታ በሰንበት /ቤት መምሪያው በኩል ብታስተካክል በተለይ ከላይ ያሉ ከተሞችን ብትከታተል
3-
የጥምቀት ተመላሽ ልጆችን ሰብስባ ትምህርት አግኝተው ወደ /ትቤት እንዲገቡ የማድረግ ስራ በአስቸኳይ ቢሰራ

4-
ተቀጥረውም ሳይቀጠሩም የሚያገለግሉትን ሰባኪያንን በአንድ ላይ አቅፋ እየተቆጣጠረች በአንድነት በህብረት እንዲያገለግሏት የሚያደርግ መዋቅር በአስቸኳይ ብታደራጅ

5-
ለማህበራት የሚሰበሰበው አስራት ወደ እናት ቤተክርስቲያን እንዲመለስ ተደርጎ የቤተክርስቲያን አቅም የበለጠ ቢጠናከር
6-ቤተክርስቲያን ምእመናንን የምታገኝባቸው ሚዲያዎች ተጠናክረው ቢስፋፉ ማለትም ጋዜጦች፣ ድረገጾች፣ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች፣ እነዚህንም ሚዲያዎች በሰፊው ለህዝብ ተደራሽ ማድረግ ቢቻል
7-በኢቲቪ እና በኢትዮጵያ ሬድዮ ማህበረ ቅዱሳንን የሚወክሉ መምህራን ቤተ ክርስቲያንን ወክለው እንዳይቀርቡ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ቁጥጥር ቢያደርግ
8-የቤተክርሰቲያንን አስተዳደራዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን በቅ/ሲኖዶስ ቁጥጥር እና ክትትል ስር ብቻ ቢሆንና እኛን መንጋዎቹን አባቶች ብቻ እንዲመሩን የተሰራው የቀድሞ የአባቶቻችን ድንበር እንዳይፈርስ /ሲኖዶስ ቢያደርግ
                            ማጠቃለያ
ማህበረ ቅዱሳን በጳጳሳት እና በአገልጋዮች መሃል ባሳደረው ከፍተኛ ስም የማጠፋት እና የመከፋፈል ተጽዕኖ ብዙዎቹ ማህበሩን ለመመርመር ድፍረት አጥተዋል፡፡ ጥቂቶችም ማህበሩ ጥፋት የሌለበት ፍጹም አድርገው ስለውታል፡፡ በመሆኑም ማህበሩ ሲዳኝ ሲከስ ሲያበላሽ ያለተመልካች 20 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ማህበረ ቅዱሳን በዚህ ቀጥሎ አምስት አመት ወደ ፊት ከቆየ ሲኖዶሳችን ከሶስት መከፈሉ አባቶችም ቤተክርስቲያንን መምራት ተቸግረው የጎረምሳ ራት መሆናቸው ፣የቤተክርስቲያንም ነገረ ሃይማኖት ማስተካከል እንዳይቻል ሆኖ መበረዙ አይቀርም፡፡

አሁን ግን ሁሉም በያለበት ለሃይማኖቱ እንዲቆም፣ ማህበሩ በስውር ኑፋቄው ብዙዎችን ሳያበላሽ፣ ቤተክርስቲያንን ኢትዮጵያን ፈንጂ የሞለባት ቀጠና አድርጎ ሳይተዋት አባቶች በቅ/ሲኖዶስ ስብሰባቸው ጉዳዩን ሳይፈሩ እንዲመለከቱ፣ የማህበሩንም ክህደት በሊቃውንት ጉባኤ እንዲታይ እንዲያደርጉ፣የሰንበት /ቤት ተማሪዎች /በተለይ የአዲስ አበባ ታላላቅ አድባራት/ ማህበሩ ለቤተክርስቲያን አሳቢዎች አስመስሎ አስርጎ ባስገባቸው ቀሳጢዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁና፣ ምእመናንም በሃይማኖት ስም እያታለለ ቤተክርስቲያንን ለጥፋት እያዘጋጀ ካለው ማህበር እንዲጠበቁ በማህበሩ ውስጥ ያሉ ስውሩ ተልእኮ ያልገባቸው ወንድሞችና እህቶች ከቤተክርስቲያ ጎን እንዲቆሙ ማህበሩ ውስጥ ሆነን የማህበሩን አደጋ ገልጠን የጠቆምን የቁርጥ ቀን የቤተክርስቲያን ልጆች አደራ እንላለን፡፡ ሌሎች ጥብቅ መረጃዎችን የኑፋቄ ትምህርቶችን አስፈላጊ ሆኖ በታየን ጊዜ ግልጽ እናደርጋለን፡፡



8 comments:

  1. የወግና የባልቴቶች ተረት ተረት አሰራርና አስተዳደር ባለቤት ማ/ቅ ቦታ የለውም፡፡ ወንጌልና ወንጀልን የሚለዩ ኦርቶዶክሳውያን ማ/ቅን ከተተከለበት የትዕቢት ሥፍራ ነቅለው ከንስሐ መልስ ቦታ ሊያዘጋጁለት ይገባል ፡;እግዚአብሄር ይመስገን ማ/ቅ የተሐድሶ መፈልፈያ እያለ ስያሜ ሲሰጣቸው ከነበሩት መንፈሳውያን ኮሌጆች የተገኙ ወጣት ምሁራን የማ/ቅን ክህደትና ሌብነት ክምር እየናዱት ነው፡፡ የነገረ መለኮት ወጣት ምሁራን አንድነታችሁን አጠናክራችሁ ለእናታችሁ ቤተ ክርስቲያን በቅንነት ሥሩ ማ/ቅ በክፉ ሥራው እየጠፋ ነው፡፡ እሱ የገንዘብ ልጅ ነው አክስዮን ሆኖ ይቀራል፡፡ እናንተ ግን ተባብራችሁ በእናታችሁ ቤት የእግዚአብሔር ሆናችሁ ኑሩ፡፡፡፡

    ReplyDelete
  2. LEBOCH ENANETEN MATEFAT NEBR

    ReplyDelete
  3. The author clearly identifies the strategy that MK is currently following. Excellent observation!
    Another technique Mk plays is that it sends its members to three types of churches:
    1. To churches that are under the Ethiopian orthodox church.
    2. To churches that are under the Ethiopian Synod in Exile
    3. To churches that are independent or not under the Ethiopian Orthodox Church or the Ethiopian Synod in Exile.

    The mission to send its members to different types of churches is not religious but political. Also the MK preachers create more confusion to the people that attend in the church: The MK preachers sometimes insult with big words even to their active members. They do this to make the other audience not to doubt the insulted person as active Mk members. But, before they come to the church, they always discuss – who to insult and what type of political words to use.
    The sad thing is that – the church fathers are in a state of fear not to correct the obvious situation in the churches. Should we wait until the coming of Jesus and see him get angry in the temple? I would say “no”. Let us do something. So, what should we do?

    ReplyDelete
  4. እውነት ተናግሮ በመሸበት ማደር መልካም ነው። ለተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማቅ የፈጠረው መርዝ በቀላሉ የሚነቀል ባይሆንም ። ለሀያሉ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የምሳነው ነገር የለም። እርሱ ከክፉ ስራው ጋር ገና ይነቅለዋል። ዛሬም በአሜሪካ ምድር በእነ ዳንኤል ክብርት እያደረገው ያለው ስውር ተንኮል ሕዝቡ ስለነቃበት ከጉባኤዎቹ እየሸሸ ይገኛል። የተዋህዶ ሕዝብ ጠንካራ ህዝብ ስለሆነ አሁን ሁሉም ነቅተውበታል። በከንቱ የሰውን ስም መናፍቅ ነው እያለ የሚያጠፋው በዌብ ሳት ላይ ብቻ ነው እንጅ ማንም አያምነውም። ጥቅት የማቅ እስረኞች ብፈራገጡም የትም አይደርሱም።

    ReplyDelete
  5. ከአስርቱ ትዕዛዛት አንዱ “ በሐሰት በባልንጀራህ ላይ አትመስክር ..” ይላል!!

    ReplyDelete
  6. ወይ ጉድ! ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አለ የሀግሬ ሰዉ ማቅ ማለት የሙስሊሞቹ አዲሱ ቡድን አይነት አጀንዳ ያነገበ ቡድን ነዉ እስቲ ምን ልዩነት አላቸሁ? ሁለቱም የዓይማኖትን አና የፖሎቲካሁን ስልጣን መቆጣጠር ከዚያም ትዉልዱን በእሳት ዉስጥ መማገድ ነዉ የሚይፈልጉት ሌላ አጀንዳ የላቸሁም
    እየሱስ ክርስቶስ አዉነተኛ ዳኛ ነዉ ለሁሉም እንደየስራሁ ይፈርዳል ለሁሉም ቀን አለሁ

    ReplyDelete
  7. Yewunetgna ken lijoch egezeabeher yetebekachu. MK gudu gena yewetal dero sewoch be alegebachew geze neber yekeleduben. ahun gen NO More Mahiber Kedusaan to cheat us !!!

    ReplyDelete