Saturday, April 28, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችና አባላት ጭፍን እይታ

Click here to read in PDF

መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ ሲል መንፈሳዊ እይታችን ሚዛናዊ በሆነና እውነት ባለው ነገር ላይ እንዲመሠረት ይመክረናል (1ተሰ. 5፡20-21)። ይህን ሐዋርያዊ ቃል መመሪያው ያላደረገ ሰው ግን የሚያምነውና የሚኖረው በጭፍን ነው። በማኅበረ ቅዱሳን ዘንድ ወንጌል ስሙ ብቻ እንጂ ግብሩ ፈጽሞ የማይታወቅ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን ማለት ደግሞ የእነርሱ ማኅበር ይመስላቸዋል። እነርሱ በጥላቻ ተሞልተው “መናፍቅ” የሚሉት ማንኛውንም የማኅበሩ አባል ያልሆነውን ሰው ነው። “እገሌ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነው። እንዴት መናፍቅ ትሉታላችሁ” ተብለው ሲጠየቁ “ማኅበራችን አያውቀውም ስለዚህ መናፍቅ ነው” የሚል ነው መልሳቸው።

ለእነርሱ የምንፍቅና መመዘኛ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማ አይደለም፤ የማኅበራቸው አባል መሆን አለመሆን ነው። መናፍቅ የሚለው ስም ትርጉሙ ቢገባቸው፣ በሀሳቡ መንፈስ ቅዱስ ከተስማማ ሰውዬውን ከመንግስተ ሰማያት የሚያስወጣ ቃል ነው። ስለዚህ ይህን የማለት ስልጣን ያለው አንድ የፅዋ ማህበር ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን ናት። ቤተክርስቲያንም ሸክሙ ስለሚሰማት ዝም ብላ መናፍቅ አትልም። የነገሩን መነሻና መድረሻ መዝና፣ ባለጉዳዩን አናግራ፣ አስተምራ፣ ጥፋት ቢገኝበት ንስሀ እንዲገባ ነግራ፣ አልመለስ ካለና በሀሳቡ ከጸና ብቻ ነው መናፍቅ የምትለው። ምክንያቱም የአንድ ሰው ነፍስ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ጠንቅቃ ታውቃለች እና ነው። ማህበረ ቅዱሳን ግን በሆነ ባልሆነው፣ መሽቶ እስኪነጋ ሰውን መናፍቅ ለማለት ብቻ የሚደክም፣ ሰውየው ቢመለስ እንኳ መመለሱን የማይፈልግ፣ በጭፍን ጥላቻ የተሞሉና ጥላቻቸውን የሃይማኖት ካባ የሚያለብሱ ተራ አስተሳሰብ የዋጣቸው አመራሮችና እነርሱን በጭፍንንነትና በቅንንነት አምነው የሚከተሉ አባለት ያሉት ማኅበር ነው።

ማህበረ ቅዱሳኖች እገሌን መናፍቅ ነው ለማለት ምክንያት የማስፈልጋቸው መሆኑ በተደጋጋሚ ታይቷል። እገሌ እዚህ ቦታ ታይቷል፤ ይህን ቀምሷል፣ ያን ነክቷል፤ በሚሉ እርባና ቢስ ምክንያቶች ብቻ ሰውን መናፍቅ እያሉና እያሰኙ መኖር የሚያረካቸውና የእነርሱ ህልውና ሰውን ሁሉ መናፍቅ ከማለት ጋር የተያያዘ የሚመስላቸው አመራሮቹ፤ ለ20 ዓመታት ሲጋቱት የኖሩት ወግንና ልማድን፣ የፈሪሳውያን እርሾ የሆነው ግብዝነትንም በመሆኑና መንፈሳዊነትን ከቶ ስላልፈጠረባቸው፣ ለህልውናቸው መቀጠል ሲሉ ለሚፈጽሟቸው ወንጀሎች እግዚአብሔር ምን ይለኝ ይሆን? የማይሉ ተንኮልና ማስመሰል ቀለባቸው የሆነ ከንቱዎች ናቸው።
ደግነቱ እስካሁን ድረስ መንፈስ ቅዱስ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር አልተስማማም፤ አይስማማምም እንጂ ስንቱን የቤተክርስቲያን ልጅ የማኅበራችን አባል ለምን አልሆንክም በሚል ጥላቻ ከመንግስተ ሰማያት አስወጥተው በጣሉት ነበር።
ለዲያቆን በጋሻው ጥብቅና የመቆም ሀሳቡም ፍላጎቱም የለንም። ነገር ግን ከበጋሻውና ከዘሪሁን መናፍቁ ማነው? አልዓዛርን የፈወሰው ኢየሱስ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ በሉ፤ ስላሴ አትበሉ። በስሙ ጥሩት የሚለውን ትክክለኛ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊና የቤተክርስቲያን ትምህርት ነው። ነገር ግን ሁልጊዜም ክፋትና ተንኮል ምቀኝነትና ቅናት ተግባሩ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ግን፣ በጋሻው ስላሴን ተቃወመ በማለት ቃሉን ከአውዱ ውጭ ተርጉሞ ፊልም ቆርጦና ቀጥሎ መናፍቅ ለማለት ማንም አልቀደመውም። ዘሪሁን በጋሻውን ተቃወምኩ ብሎ እመቤታችን ስላሴን ወልዳለች በማለት በኦርቶዶክሳዊትዋ ቤተክርስቲያናችን እንደ ትልቅ ምንፍቅና የሆነ እንክርዳዱን በምእመናን ላይ ሲዘራ በቸልታ ማለፍ ጤነኛነት አይደለም። ማህበሩ ለጥቅሙ እንጂ ለቤተክርስቲያን ትምህርት እንዳልቆመም የሚያሳይ ትልቅ ማስረጃ ነው።
እውነት በልቡ አይደለም በሰፈሩ እንኳ ያለፈች ሰው ይህን ልዩነት በሚገባ ያስተውላል ብለን እናምናለን። ማህበረ ቅዱሳን እኛን ውደድ እንጂ እንደፈለክ ሁን፤ የፈለከውን ኑፋቄ ተናገር፤ ከሚል አባዜ ነፃ ሊወጣ ይገባል። ለዚህ ነው የማህበሩ አባላትና አመራሮች በጭፍን ጥላቻ የተሞሉ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለራሳቸው የሚያስቡና የሚሰሩ ክፉዎች ሰራተኞች ናቸው የምንለው። (ፊልጵስዩስ 3፡2)

3 comments:

  1. ስለዚህ ኢየሱስ በሉ፤ ስላሴ አትበሉ። Yeselassie fekadachew andit aydelechimin? Selassie bibal min chigir norot new atibelu yalew? That is wrong. I don't have any intention of supporting anybody or judging anyone for I am not a judge. Yes, the Lord Jesus Christ is Son of God, He raised Alazar from the dead in His Power, He is perfect God and perfect Man, Emanuel. We believe that there is no Christianity without Christ the Lord, the Only Begotten Son of the Father, we cannot speak of Christ without the Holy Virgin, His Mother Saint Mary. He chose her to be His Mother. He is Her son. He is the Incarnated God, the only Begotten Son of the Father. Jesus yemilew sim rasu eko sime segawe new. Tadya endet emebetachin selassen woledech yibalal, yih ayibalim. Honom gin, this should not be spoken to justify the errors of Begashaw. Forget about MK; I don't know both of you. I don't see any reasonable critic from your side either. You tried to justify Begashaw and rebuke and anathematize Zerihun. Who is Begashaw, who is Zerihun for me? I don't want to hear about Mk or the two guys; I want to hear the teachings of the Apostles Athanasius, John Chrysostom....I As your audience I don't want to words like: የማህበሩ አባላትና አመራሮች በጭፍን ጥላቻ የተሞሉ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለራሳቸው የሚያስቡና የሚሰሩ ክፉዎች ሰራተኞች ናቸው in this Resurrection season. I want to read about redemption, salvation,... If you want to teach your audience about the Holy Trinity or Incarnation or other mysteries of the church just do so without mentioning the name of an association or an individual. Your name is good, but your writings does speak something else... We want to read about the blessings and mercy of God, not the history of one association or one individual... If you want to transfer any message that you believe is important for the improvement of some one like me, do it in a more appealing and humble manner... Why am supposed to read about Zerihun or Begashaw, if both of them are wronged you have to say it in a balanced way... you are just looking something from either of the two guys that you think will defend your claim that Mk is not doing the right thing... That is really very absurd and destructive. I don't have the authority or the power to judge you or anybody else including Mk or the guys you mentioned in your piece, but I get nothing from your article, just accusation, zelefa...Take care of your name,ዐውደ ምሕረት, and work for the souls of the flocks of the Holy Church. Really you are preaching Mk and Begashaw and Zerihun, not Christ the Lord. So, there is no reason for me to follow you and send you my personal email to receive your writings. Lib yalew yidinal! I don't want to corrupt my soul by reading your articles that always carry messages about an association or an individual...

    ReplyDelete
  2. አዎን ጭፍንነት አይጠቅምም

    ReplyDelete
  3. ይህ ሀሳብ ሁሌም በልቤ የሚመላለስ ነበር። በጥሩ መንገድ ስለገለጻችሁት አመሰግናችሁዋሉ። በተለያዩ ብሎጎቹ ወንድሞችን በሀሰት የሚከስ ማህበርን እንዲህ በምክንያት ማንነቱን መግለጽ ያስፈልጋል።

    ReplyDelete