Thursday, October 17, 2013

ማኅበረ ቅዱሳን በአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በደረሰበት ተቃውሞ ተወካዮቹ ስብሰባ ረግጠው ወጡ

ምንጭ- አባ ሰላማ
32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ከየሀገረ ስብከቱ የተወከሉ የአህጉረ ስብከቶች ሥራ አስኪያጆች፣ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎችም በተገኙበት ጥቅምት 3/2006 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡ በስብሰባው ላይ ከየአህጉረ ስብከቶች በመጡ ሥራ አስኪያጆች የሥራ ሪፖርት እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ውይይትም እየተደረገ ነው፡፡

 በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የካህናት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ሊቀ ካህናት ኃይለ ስላሴ ዘማርያም ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን ምን ያህል አስጊ ኃይል እንደ ሆነና ከተለያዩ የንግድ ተቋማቱ የሚሰበስበውንና በቤተክርስቲያን ስም ከአገር ውስጥና ከውጭ የሚሰበስበውን ገንዘብም ኦዲት እንደማይደረግ የገለጹ ሲሆን፣ በዚህም ማቅ ኪራይ ሰብሳቢ ድርጅት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 በትናንትናው ዕለት ደግሞ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ – ወሊሶ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መልአከ ገነት አባ አፈወርቅ ዮሐንስ በሀገረ ስብከታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በዓመቱ ከገጠሟት ችግሮች መካከል ዋና አድርገው የጠቀሱት ማኅበረ ቅዱሳንን ሲሆን፣ ማኅበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ ቤተ ክርስቲያኗ የራሷ መተዳደሪያ ቃለ አዋዲ እያላት ቃለ ዐዋዲውን አሻሽሎ ሌላ መተዳደሪያ በማውጣትና የቤተክርስቲያንን መዋቅር በማዳከምሕዝበ ክርስቲያኑ ፐርሰንት እንዳይከፍሉና ሕዝቡ ለማኅበሩ በአባልነት ተመዝግቦ ለማኅበሩ እንዲከፍል በመቀስቀስ በቤተ ክርስቲያን ላይ ደባ መፈጸሙን ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም የሀገረ ስብከቱ የሆነውን ሱቅ እንደማንኛውም ምእመን ተከራይተው ኪራይ አንከፍልም በማለት ማመጻቸውንና ሕዝብን ማነሳሳታቸውን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ማኅበሩ እንደ ትልቅ ስልት የያዘው የሕዝብ ተመራጭ በመምሰል በሰበካ ጉባኤ፣ በሰንበት ትምህርት ቤቶች በልማትኮሚቴና በስብከተወንጌል ኮሚቴነት በመግባት የበላይ መመሪያን አለመቀበልንና መዋቅር ማዳከምን ነው ብለዋል፡፡ ለማሳያነትም በወንጪ፣ በወሊሶ፣ በሰበታ አዋስ ወረዳ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሕዝብን የመከፋፈልና የማሳመፅ ድርጊት በመፈጸም ላይ መሆናቸውን በማስረጃ አስደግፈው አጋልጠዋል፡፡ ከዚህም ሌላ በ11ዱ ወረዳዎች ኔትዎርክ በመዘርጋት የራሳቸውን ሥራ በመተው በሀገረ ስብከቱ ላይ ሰዎችን በማደራጀት ላይ እንደሚገኙ በማስረዳት ቅዱስ ሲኖዶስ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

በተለይ ምእመናን ለቤተክርስቲያን አስራት በኩራት እንዳያወጡ መንቀሳቀሱንና የካህናትንና የአባቶችን ክብር የሚነካና “ለማንም ቄስ መስከሪያ ነው የሚሆነው” በማለት ለቤተክርስቲያን አንድነትና እድገት ፀር እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ይህን የሰማ የጉባኤው ታዳሚ በሙሉ ዘለግ ላለ ጊዜ አዳራሹን በጭብጨባ አናግቶታል፡፡ ይህም ችግሩ በወሊሶ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ አገር በሁሉም አህጉረ ስብከቶች ያለ መሆኑንና በማቅ ምን ያህል ምሬት ውስጥ እንደገባ የሚያሳይ ሆኗል፡፡
  በዛሬው (ረቡዕ ጥቅምት 6) ዕለትም የመክፈቻ የትምህርት እንዲሰጡ የተመደቡት የማቅ ወዳጅ አባ ቄርሎስ ወንጌልን ትተው ጀንበር እየጠለቀችበት ያለውን ማኅበረ ቅዱሳንን ለመስበክ በመሞከራቸው ከጉባኤው ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው ሲሆን፣ አንዳንድ የጉባኤው አባላት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “እርሱ አሸባሪ ነው፤ ያቁሙ” በሚል ተቃውመዋቸዋል፡፡ እርሳቸውም ጉባኤውን “አጨብጫቢ” ብለው መሳደባቸው ተሰምቷል፡፡ የጉባኤውን ተቃውሞ ለማፈን ያደረጉት ጥረትም የባሰ ተቃውሞ ስለቀሰቀሰና የተሰጣቸውን ወንጌል የመስበክ ዕድል ለማቅ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ በማዋላቸው በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ንግግራቸውን እንዲያቆሙ ተደርገው ንግግራቸውን አቋርጠው ከመድረኩ ወርደዋል፡፡
 በተጨማሪም በዛሬው ዕለት የቀረቡትም ሪፖርቶች የማኅበረ ቅዱሳንን ህገ ወጥነትና ፀረ ቤተክርስቲያንነት ያጋለጡ ነበሩ፡፡ በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የመናገር ዕድል የተሰጣቸውየደቡብ ምዕራብ ሸዋ – ወሊሶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሥራ አስኪያጃቸው ያቀረቡት ሁሉ ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ በሀገረ ስብከታቸው ላይ ማቅ እያደረሰ የሚገኘው ችግር በመረጃ የተደገፈ መሆኑን አበክረው ያስረዱ ሲሆን፣ አባቶች በዚህ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ማኅበሩ እየፈጠረ ባለው ችግር ላይ አንዳች እልባት እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡ ብፁዕነታቸው ማኅበሩ በመንግሥትም በሽብርተኛነት የሚጠረጠር ማኅበር መሆኑን አስታውሰው ጉዳዩ የግለሰብ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡
 ብፁዕነታቸው አክለውም ዛሬ ጠዋት (ረቡዕ) አቶ ባያብል የተባለ የማቅ አባል በሪፖርታቸው የማቅ እኩይ ተግባር ያጋለጡትን ሥራ አስኪያጃቸውን መልአከ ገነት አባ አፈወርቅ ዮሐንስን በመኪና የመግደል ሙከራ ማድረጉን ለጉባኤው ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩንም ሕግ እንዲያውቀው መደረጉን አስረድተዋል፡፡ የባያብልን ድርጊት ብዙዎችን ያሳዘነ ሲሆን የመግጨት ሙከራው የአጥፍቶ መጥፋትም ባይሆን የአጥፍቶ ማምለጥ ድርጊት ነው ሲሉ የማቅን አሸባሪነት ለመግለጽ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ ጉባኤው የብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ንግግር በከፍተኛ ጭብጨባ የደገፈ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዚህ በመንግሥትም ሆነ በቤተክርስቲያን ሕግ በማይገዛ አክራሪ ማኅበር ምን ያህል ስቃይና መከራ ውስጥ እንዳለች የታየበት አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡     
 አንድ የማቅ ተወካይ በተለይ በመጀመሪያው ቀን በማኅበሩ ላይ ለቀረበው ክስ ምላሽ ለመስጠት የሞከረ ሲሆን በተለይ ከሊቀካህናት ኃይለሥላሴ ዘማርያም ለቀረበው ክስ “ኦዲት የማናስደርገው የጠቅላይ ቤተክህነት ኦዲተሮች በሕግ በኩል ተቀባይነት የሌላቸው በመሆናቸው ነው” በማለት ለቤተ ክህነቱ ያለውን ንቀት በማንጸባረቅ ጽርፈት የተሞላው ምላሽ ሰጥቷል፡፡
 ማቅ በተጨማሪ በሌሎችም አህጉረ ስብከቶች ሥራ አስኪያጆች ከፍተኛ ተቃውሞ ስለገጠመውና በዚህ ማንነቱ፣ ድብቅ ሴራውና አሸባሪነቱ በጉባኤው ሁሉ የታወቀ መሆኑን ሲረዳ የማቅ ዋና ጸሐፊ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም ምላሽ እንዲሰጥ እጁን ቢያወጣም፣ ከስብሰባ ሕግ ውጪ ሳይፈቀድለት ተነስቶ ለመናገር ቢሞክርም በጠቅላይ ቤተክህነቱ ሥራ አስኪያጅ ስለተከለከለ ሁሉንም የማቅ አባላትን አስከትሎ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትንና በጠቅላላ የጉባኤውን አባላት በማቃለል ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ ይህም ማቅ ምን ያህል በማንአለብኝነት የተሞላ የጋጠወጦች ስብስብ መሆኑንና በቤተክርስቲያን ሕግ ሳይሆን በራሱ መንገድ የሚመራ ለቤተክርስቲያን ጉባኤም ክብርን የማይሰጥ መሆኑን በተግባር አሳይቷል፡፡
   በስብሰባው ላይ ማቅን አስመልክቶ የቀረበው ወቀሳና ክስ የብዙዎችን ስሜት የነካ ስለነበር ብዙዎች ከስብሰባው ሲወጡ በደስታ ይጨባበጡ፣ ተቃቅፈውም ይሳሳሙ እንደነበር መታዘብ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም የማቅ ቀንበር ቤተክርስቲያኒቱ ላይ ምን ያህል እንደ ከበደና በአክራሪና በአሸባሪ ድርጊቱ ለብዙዎች ስጋት መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡ የማቅ ወኪሎች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን ተከትሎ ስብሰባው በሚካሄድበት በጠቅላይ ቤክህነት ቅጽር ግቢ ውስጥ ስብሰባው ከተጀመረ ወዲህ ታይቶ ባልታየ ሁኔታ የፖሊስ ኃይል ጥበቃውን ማጠናከሩን ምንጭቻችን የተናገሩ ሲሆን ይህም ከማቅ አክራሪነት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ከዚህ ቀደም እነ ታደሰ ወርቁ እንደነገሩን ማቅ ለክፉ ቀን ያስቀመጣቸውን የጥምቀት ተመላሽ ቅምጥ ኃይሉን ተጠቅሞ ቤተ ክህነቱን ቢያስወርርስ?
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የማቅ ደጋፊ የነበሩ አንዳንድ ጰጳሳት ዝምታን የመረጡ ሲሆን በተለይም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን የማቅ መፈንጫ ያደረጉትና በታሪክ ተጠያቂ ከመሆን የማያመልጡት አባ እስጢፋኖስ ዝምታን መምረጣቸው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ማቅ ለጥቅሙ እንጂ ለሌላ እንደማይፈልጋቸው አንዳንድ ጳጳሳት ከደረሰባቸው ክዳት ሳይማሩ አልቁ ይሆናል ተብሎ ተገምቷል፡፡
 በዚህ የተበሳጨው የማቅ ስውር ብሎግ ሐራ ዘተዋሕዶ ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት ባላቸው ቁርጠኝነት የሚታወቁትንና ማቅ በጥቅም ግጭት የተጣላቸውንና ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከቤተክርስቲያን ካልተባረሩ እያለ ዘወትር የሚያሳድዳቸውን የቤተክርስቲያን ልጆች ሊባረሩ አይገባም፤ ችግር ካለም ለቅዱስ ሲኖዶስ ይቅረብና ይታይ፤ አሊያ እንዳያገለግሉ ማድረግ አትችሉም በሚል ተራ ውንጀላቸውን ባለመቀበላቸው ብቻ አለስማቸው ስም ሰጥቶ ብፁዕነታቸውንና የማቅን እኩይ ተግባር ያጋለጡትን ሥራ አስኪያጅ ላይ ተራ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶባቸዋል፡፡ ይህም ማቅ በዚህ ስብሰባ ላይ የደረሰበትን ኪሳራ ለማወራረድ ታስቦ የተደረገ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡   
 ይህ በእንዲህ እንዳለ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ ጥቁር በግና ፍየል በማረድ ጋኔን ሲስቡ የነበሩት የጉድ ሙዳዩ አባ አብርሃም በመስዋእቱ አቀራረብ ላይ ሳይፈጽሙ እንዳልቀረ በተገመተው ስህተት ምክንያት፣ ለወዳጁ የማይሆነው ጋኔን በጥፊ አጠናግሮ አጣሞ እንደጣለቸውና በስብሰባው ላይ አፋቸው ተጣሞና በልብስ ሸፍነዉት እንደታዩ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ ደግሞም ጋኔን ሳቢ መሆናቸውን በቅርብ የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ፡፡ አባ አብርሃም ከዚህ ቀደም የኢየሱስን ስም ሲቃወሙና “ኢየሱስ ኢየሱስ አትበሉ” ሲሉ እኚህ ሰው በሌላው መንፈስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ጠርጥረን ነበር፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ሲመሰክር “ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፥ ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፥ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።” ይላልና (1ቆሮ. 12፥3)፡፡
 በዚህ አጋጣሚ አባ አብርሃም ካልተላቀቃቸው የድብትርና መንፈስ ነጻ እንዲወጡና ስለኃጢአታቸው በሞተው “ስሙን አትጥሩብኝ” ባሉት በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት እንዲያምኑ ወንጌልን እየመሰከርንላቸው፣ እግዚአብሔር ምሕረት እንዲያደርግላቸውና ወደጤንነታቸው እንዲመልሳቸውም እንመኛለን፡፡
 ቀጣይ የስብሰባውን ውሎ እየተከታተልን ለመዘገብ እንሞክራለን፡፡


9 comments:

  1. We know Who U are.

    ReplyDelete
  2. we will send you documents about mk is terrorist in America soon

    ReplyDelete
  3. we will send you documents about mk is terrorist in America soon

    ReplyDelete
  4. Ayeeee Menfekan!! Bhilme yelfelchu!!! Mahebere kidusanen afersalhu belachu erasachu eyeferaresachu new.....yikerta meteyeke...masemsel minamin.....alhonlachum hulum neger!! Egnan lekeke adergachu ezawe adarashachu esksetachun beteweredu min alebete lengeru Diblose megebaru men honena melkam megbaren ,k Egzeabher yhonen neger lemtefate metare aydel!!! selzhi aydenkenem Dengil mengezem kegonachin nate,y tewahedo lijoche endew mengezem K Mahebere Kidusan ga nachew!! Meknyatum yenantenem megbare yemhaberunem megebare tenkekew yawekalu ena!! Amlke k Maheberu ga new enate gena bemgebarachu teshemakachu Maqe! telbsalchu!!!

    ReplyDelete
  5. sitasazinu ewinetun kenanite kedimen semitenewal silezih wishetachihun lerasachihu eshi tehadisowoch egna abatochavhinin bedenib eniwedalen enanet seytanoch

    ReplyDelete
  6. ere tew menafikan min aderegu ....melikam beseru.........

    ReplyDelete