Friday, April 27, 2012

ኤፍሬም እሸቴ: ብትስማማ ነው እንጂ የሚያስደምመው ባለመስማማትህ ምን ይደንቃል?

Click here to read in PDF
 በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

ጥብቅ ማሳሰቢያ: ጽሑፉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመደገፍ የተጻፈ ጽሑፍ አይደለም:: ጽሑፉ ኤፍሬም እሽቴ የተባለው አንድ "የማህበረ ቅዱሳን" የስራ አመራር አባል ግለሰብ “ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም” ሲል ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ በጻፈው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምህሮ የማይወክል ዝርው ይዘት ያለው ጥሬ ጽሑፍ አስቸኳይ እርምት እንዲደረግበትና በክርስትና ስም በአንባቢያን ላይ የፈጠረውን ብዥታ ግምት ውስጥ በማስገባት የተጣራ ምስል ለመስጠት ኩልል ቅልብጭ ባለ መልኩ የተዘጀ ጽሑፍ ነው::

"ማህበረ ቅዱሳን" የቤተ-ክርስቲያን የቆሎ ት/ቤት ያልቀመሰ፣ የዜማ፣ የቅኔ፣ የመጽህፍት ትርጓሜያት፣ የቅዳሴ፣ የአቡሻክር … ወዘተ ባህር ያልዳሰሰ የቤተ-ክርስቲያን ጥንተ ታሪክ ያልመረመረ፣ ጥምጥም ያለው ጥቁር ጎረምሳ፣ ሆኖ እያለ እምነበሃን የማያውቅ ዲያቆን፣ አሀዱ አብን የማያውቅ ቄስ፣ አአትብ ገጽየን የማያውቅ ክርስቲያን፣ የሴቶችና የወንዶችን መግቢያ በር በቅጡ የማያውቅ፣ ሱቅ ከፍቶ ቄስ ቀጥሮና አቁሞ ስለ ነገደ ቄስ የሆነ የሚመስለው ጠባቂ ነኝ የሚል አጽራረ ቤተ-ክርስቲያን ጿሚ መሳይ አጋሰስ፣ የማይሰግድ አሰጋጅ፣ ለማስተማር የማይበቃ አቃቤ መቃብር ባለ ዲግሪ፣ አስራት የማይከፍል በዝባዥና አስከፋይ፣ የማይቀድስ አስቀዳሽ፣ ያልተለወጠ ለዋጭ አስመሳይ የጎበዝ ጥርቅም ማኅበር ነው ሲባልኮ ተራ ውንጀላ ወይንም ደግሞ ክስ ሳይሆን ምስክርነታችን ጭብጥ ላይ የተመሰረተ እውነት ነው::

ይህች ጦማር የቀድሞ የማህበሩ አውራ ቂስ ኤፍሬም እሸቴ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም በፓርላማቸው ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እግረ መንገዳቸውን ያነሱትን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አክራሪነትበክርስቲያኑ በኩል ይወክልልናልብለው የጠቀሱትን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ እኔም እንደ አንድ አባል የማምንበት አቀርባለኹ። ማኅበሩ በኃላፊዎቹ በኩል የሚሰጠው መልስ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሁለት አሥር ዓመታት አባል የሆንኩበት እና መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ማኅበር አክራሪአለመሆኑን በግሌ ለመመስከር እገደዳለኹ።” ሲል ባልዋለበትና ባላለፈበት የቅዱሳት መጻህፍት ቃል ዓውዱን ባላገናዘበ አኳኃን ምክርን ለማጨለም ባደረገው ሙከራ የተፋለሰውን የክርስትና አስተምሮና በማን አለብኝነት መንፈስ የፈጠረውን እጅግ ግዙፍ የሆነ ስህተት ኩልል ባለ መልኩ ታስቃኘናለች::

መልካም ንባብ! 
ግለሰቡ ምንም እንኳን ራሱ እንደ አንድ ተራ የማህበሩ አባል አድርጎ ለመቅረብ ቢሞክርም ለረጅም ዓመታት በማህበሩ የስራ አመራር አባል: በማህበሩ የተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎችም ሲሰራ የቆየ: አሁንም ቢሆን ከቤተ-ክርስቲያን ጫንቃ ያልወረደ: በቤተ-ክርስቲያን የምጽዋት ገንዘብ ኑሮውን ያደላደለ በዋናነት ከተጠያቂነት የማያመልጡ የማህበሩ ልሂቃን መካከል ለመሆኑ የማህበሩ ስም በተነሳ ቁጥር ይህን እውነታ ሳያውቅ የሚቀር ያለ አይመስለኝም:: ግለሰቡ ወደ አሜሪካ እንዴት መጣ አሁንስ የማህበሩን ተልዕኮ ከማከናወን አንጻር ምን እየሰራ ይገኛል የሚሉትና ሌሎች ተጓዳኝ ጥያቄዎች በቅርብ በስፋት የምንመለከተው ይሆናል:: ለጊዜው ግን የተነሳንበትን ዋና ርእስ በዝርዝር እናብራራለን::

“በመጀመሪያ “አንድ ሃይማኖት” የሚለው መሠረታዊ ሐሳብ ለብዙ ውይይቶች በር የሚከፍት ትልቅ ጉዳይ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን እና የጥምቀት አክባሪ ክርስቲያኖች በቲ-ሸርቶቻቸው ላይ አትመውት በፎቶግራፍ የተመለከትኩት ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ የጻፈው “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚለው ሐዋርያዊ ቃል ነው። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል እንጂ የጥምቀት አክባሪዎቹ የፈለሰፉት አይደለም። የትኛውም ክርስቲያን “አንድ ሃይማኖት” ቢል የሐዋርያውን ቃል መጥቀሱ እንጂ ሌላ እምነት ላላቸው ኢትዮጵያውያን ጥላቻ አለው ማለት አይደለም።

የጥምቀት አክባሪ ወጣቶች ቲ-ሸርቶች ላይ የተጻፈውን የሐዋርያውን ቃል የምረዳው በዚህ መንፈስ ነው።” (ውድ አንባቢ: የዚህ ጽሐፍ ዋና ዓላማ የኤፌሶን መልዕክት መንፈሱን በሚገባ መተንተን: መመስከር ነው)::
ይህ ሰው ሌላው ቢቀር የተጠቀሰውን ቃል ፊደላትን ከማንበብና ከማነብነብ ባልዘለለ መልእክቱን በሚገባ አለመረዳቱና አለማወቁ ብቻ ሳይሆን የፈጠረውን ስህተትና ያፋለሰውን አስተምህሮ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ሊቃውንት ጨምሮ አባባሉን ሌሎች እንደሚጋሩት ሃፍረት ሳይሰማው እንዲህ ሲል መግለጽ ነው “በዚህ የሐዋርያው ቃል ውስጥ ያለው “አንድ ሃይማኖት” የሚለው አገላለጽ የሚናገረው ስለ ክርስትና ሃይማኖት ነው። ሌሎች እምነቶች የሉም፣ መኖርም የለባቸው የሚል የጨፍላቂነት ትምህርት አለመሆኑን ሊቃውንቱ አምልተው አስፍተው ሲያስተምሩ ኖረዋል፤ እያስተማሩም ነው። አሁን ደርሶ የሚለወጥ ነገር የለም።” እዚህ ላይ ሊቃውንት የሚላቸው በሰው የአእምሮ ንብረት ስርቆት ላይ የተሰማሩ እንደነ ዳንኤል ክብረት የመሳሰሉ በጠራራ ጸሐይ ፎቶግራፍ የሚያነሱ ከሆነ እስማማለሁ::

በዚህ ሳይገታም (ጽሑፉ የሚያጠነጥነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እስከ ሆነ ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጎንተሉ ነው) በትልቁ ከቃሉ ጋር ፈጽመው የማይታወቁ ራሱ አቶ ኤፍሬም ጨምሮ ማህበሩና አባላቱ እያሉ በተጨማሪም አራት ገጽ ያስጻፈበት ምክንያት ፊደል እንደቆጠረ እንደማንኛው ሰው መልእክቱ ሲያነበው (ኤፌ. 4:5 ለማለት ነው) ነገር ቆስቋሽ ሰላም ነሺ የአመጽ ቋንቋ ሆኖም ስለተሰማው ጳውሎስ ወይንም ደግሞ እግዚአብሔርን ላለማሳፈር “አንድ ሃይማኖት የሚለው አገላለጽ ከሃይማኖት ጋር በማይተዋወቁ ሰዎች ዓይን ከተመለከትነው መቻቻልን ለማስተናገድ ፈቃደኝነት የጎደለው አገላለጽ ሊመስል ይችላል።” በማለት አጉል ጥብቅና በመቆም ለመገንባትና ለማጣጣም በሚያደርገውና ባደረገው ሙከራ ቃሉን ማፋለሱ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማሰደቡ ስመለከት አገላለጹ በቀላሉ የአብዬን ለምዬ አስብሎኛል::

ውድ አንባቢ: እንግዲህ እስከ አሁን ድረስ ያለነው መግቢያ ላይ ለመሆናችን ለመግለጽ እወዳለሁ ወደ ሚቀጥለው የጽሑፉ ዋና ክፍልና ዓላማ ስንሸጋገርም ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው እንዲሁ ህይወት የሆነውንና ህይወትን የሚሰጥ የመልእክቱ መንፈስ እናገኘው ዘንድ በታላቅ እርጋታና ማስተዋል ጽሑፉን እናነበው ዘንድ በድጋሜ በወንድማዊ መንፈስ በትህትና እጠይቃለሁ::

“እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።” ኤፌ. 4: 5

ጳውሎስ እንዲህ ያለ መንፈስ ያለው የአማኞች ህብረትንና አንድነትን የሚያጠነክር መልእክት ሲጽፍ ለመጀመሪያ ጊዜው አይደለም:: የአማኞች በቁጥር መበራከትና ከተለያየ ልማድና ወግ መምጣታት ተከትሎ ይፈጠርው የነበረውን ችግር በማስመልከት ጳውሎስ በርካታ ገንቢ መልእክቶችን ጽፏል:: ለምሳሌ የተመለከትን እንደሆነ በኤፌሶን ከተማ ሳለ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የጻፈውን አንደኛ መልእክቱ ለርእሳችን ተጠቃሽ ማጣቀሻ ነው::

የቆሮንቶስ ቤተ-ክርስቲያን ከተከሰቱ በርካታ ችግሮች መካከል ትልቁና ዋነኛ ችግር በእግዚአብሔር ቃል ካለማደግና ካለመብሰል ቃሉንም በሚገባ ካለማጥናት የተነሳ "እኔ የጳውሎስ ነኝ" "እኔ የኬፋ ነኝ" እያሉ ለአራት ተከፍለው ጎራ ለይተው እርስ በርሳቸው መቧቀሳቸው ነበር:: ይህንን የሰማ ጳውሎስ "ነገር ግን ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ ሃሳብም ተባብራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ:: ወንድሞቼ ሆይ በእናንተ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰቦች አስታውቀውኛል:: ይህንም እላለሁ እያንዳንዳችሁ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ እኔስ የአጵሎስ ነኝ፥ እኔ ግን የኬፋ ነኝ፥ እኔስ የክርስቶስ ነኝ ትላላችሁ ክርስቶስ ተከፍሎአልን?
ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን? …" (1ኛ ቆሮ. 1: 10) እያለ ይቀጥላል:: የቆሮንቶስ ሰዎች በክርስቶስ ስም በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ መሰባሰባቸው ሲያበቁ ኑሮአቸው ግን ፈጽሞ የምስራች (ወንጌል) ካልሰሙት አህዛብ በማይተናነስ ድርጊት ተጠምደው ወደ ቀድሞ ኑሮአቸው በመመለስ/ተመልሰው ልምምዳቸውን እየገፉበት መሆናቸው ሲሰማ የሰማውንም ሁሉ እውነት መሆኑን ሲያረጋግጥ የጻፈው መልእክት የቆሙበት ስፍራ ለማመላከት ነበር::

ከዚህ የጳውሎስ መልእክት አንድ ትልቅ ቁምነገር ለመረዳት የሚቻለው ሰው ሲባል በእግዚአብሔር መንፈስ ካልተነካ በስተቀር በሃሳብም ሆነ በቃል አንድ ብሎ ነገር ፈጽሞ የማይታሰብ ነው የሚለውን አንድምታ እንደተጠበቀ ሆኖ የእግዚአብሔር መንፈስ የተቀበሉ: ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የተገለጡባቸው: በአንድ ንግግር በአንድ ልብ በአንድ ሃሳብና ቃል ህብረታቸው ከማንም በላይ ያጠናክሩ ዘንድ የሚጠበቅባቸው የቆሮንቶስ ሰዎች በአንጻራዊ ገጽታ ሆነው ሲያገኛቸው በሌላ አነጋገር የተቀበላችሁት መንፈስ እኮ እንዲህ ለመነታረክ: ለመለያየት: ለመናቆር እርስ በርሳችሁም ለመናካስ ሳይሆን የተቀበላችሁት መንፈስ የተበተነውን የሚሰበስብ/አንድ የሚያደርግ: ልዩነትን በወንድማዊ ፍቅርና በመቻቻል የሚያጠብ: በጸብ ፈንታ ሰላምን ፍጹም መዋደድን የሚሰጥ: እግዚአብሔርን የሚያከብርና የሚያነግስ ነው ታድያ ይህ መንፈስ የት ገባ? ምን ዋጠው? ወይስ የተቀበላችሁትን አታውቁምን? ለመሆኑ እንዲህ ያለ ግርግርና ኢ-ክርስቲያናዊ ምግባር ከማን የተማራችሁ ነው? ይህ ሁሉ ወከባ ምን ለመሆን: የትስ ለመድረስ ይሆን? ምክንያታችሁ ማወቅ እፈልጋለሁ:: ሰው ሲያምን ከስጋ ደዌ ከመንፈስ አባዜ ይፈወሳል እንጅ እንዲህ ያለ ነገርስ ትክክል አይደለም:: አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ 12:13) በማለት ወደ ልቦናቸው ይመለሱ ዘንድ የሚያሳስብ ነው::

አሁን በዚህ መንፈስ ወደ ኤፈሶን መልእክት ተመልሰን እንመጣለን:: የኤፌሶን መልእክት የተጻፈው በተመሳሳይ ጸሐፊ በሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲሆን መልእክቱ የተጻፈበት ምክንያትም እንደ እንዳንዶቹ በሚገጥማቸው ችግሮችና መሰናክሎች የተነሳ ሳይሆን በመጽሐፉ ምዕራፍ አንድና ሁለት በተገለጸው መሰረት መልእክቱ የተጻፈበት ምክንያት በኤፌሶን የምትገኘውን ቤተ-ክርስቲያን ምእመናንና አባላት (ሌሎች) በዘመን ፍጻሜ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ አሳብ ይረዱና ያውቁ ዘንድ: አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ጠንክረው የክርስቶስ ፍቅር ለማስተዋልና ለማወቅ ይበረቱ ዘንድ እንዲሁም በእግዚአብሔር ጸጋ ዕለት ዕለት ወደ ምልዓት ያድጉ ዘንድ የተጻፈ መልእክት ነው::
እንግዲህ ጳውሎስ"አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ሲል በጌታ በማያምኑ: ሃይማኖትም በሌላቸው: ባልተጠመቁ ወገኖች/አካላት ላይ ጣቱ እየቀሰረ ሳይሆን ያለው "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ማለቱ የኤፌሶን ምእመናን በተጠሩበት መጠራት እንደሚገባ በሚገባ እንዲመላለሱ ቀደም ሲሉ ጌታ አምነው በእውቀት ለተጠመቁ ምእመናን በክርስቶስ የያዛችሁትን መንገዳችሁን አጽንታችሁ ያዙ: በትዕግስት በየዋሃትና በፍቅርም እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ: ተዋደዱ ምንም የሚያጨቃጭቃችሁ: የሚያነታርካችሁና እርስ በርሳችሁ የሚያናክሳችሁ ነገር አይኑር የሁላችሁም ጌታ አንድ ጌታ ነው! ሃይማኖታችሁም እውነት መንገድም ህይወትም የሆነ ኢየሱስ አንድ ነው! ሁላችሁም የተጠመቃችሁት ጥምቀት እንዲት ጥምቀት ናት! ይኸውም:
v ግሪኩንም አይሁዱንም አንድ በሚያደርግ:
v ባሪያውን ከጨዋው በሚያስተካክል:
v ሴቱን ከወንዱ እኩል በሚያደርግ (በእምነት)
v ክርስቶስን በሚያለብስ:
v ከክርስቶስ ጋር ሕብረት በሚፈጥር:
v ለምስክርነት የሚያበቃ ጥምቀት ነውና እንግዲህ ይህን መንፈሳችሁን ጠብቁ! በማለት የኤፌሶን ምእመናን
ü ፍቅር አጥብቀው እንዲይዙ:
ü መቻቻል እንዲለማመዱ:
ü በሕብረት/አንድነት የሚገኘውን በረከት ተካፋዮች እንዲሆኑ :
ü ወንድማማችነት እንዲያጣጥሙ:
ü ስለ የክርስትና ህይወት ትርጉም እንዲያውቁ:
ü በጥምቀት ስለተፈጸሙት ስርዓት እንዲያስቡ:
ü ከሁሉም በላይ ደግሞ በጌታ ስም ማመን ምን ማለት እንደሆነ እንዲያውቁ ጸጥ ረጭ ባለ በዝግታ መንፈስ የሚነበብ/የሚደመጥ: ተነቦም/ተሰምቶ ወደ ልብ ስለሚወርድና በልብም ስለሚጠበቅ ከሃጢአት: ከጥፋት: ከአመጽ ስለሚያተርፍ የተበተነውን ስለሚሰበስብ ህያው ቃል ላከላቸው (መከራቸው) እንጂ የኤፌሶን ምእመናን "አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት!" የሚል መፎክር ይዘው በኤፌሶን ጎዳናዎች አቧራ እንዲያስነሱ አይደለም! እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባ ነጥብ ቢኖር አቶ ኤፍሬም እንዳሰበውና እንደተረጎመው "ጥምቀት! ጥምቀት!" እየተባለ የሚጮክ ዝርው ቃል ሳይሆን ጥምቀት ተብሎ የተጠቀሰውን የውሃ ጥምቀት የሚያመላክት ለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል:: አንድም እንዲት ማለቱ ይህችንም ጥምቀት አንዳንዶቻችሁ በውሃ ሌሎቻችሁ በወተት አልተጠመቃችሁም እንዲል ነው::

በሰላም ማሰሪያ: የሚለው ትህትና: የዋህነት: ፍቅር ሁነኛ የአንድ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምን ክርስቲያን መታወቂያዎች ናቸው:: “የማህበረ ቅዱሳን” አባላት ክርስቲያን ናቸው ለማለት በራሱ ቀድሞውኑ በክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነት ሲያምኑ አይደለም ወይ? እንዲሁም በሌላ ስፍራ ጳውሎስ “ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና” እንዲል ኢየሱስን የለበሰ ኢየሱስን ይመስላል!! የሀገሬ ሰው "ከአህያ ጋር የዋለ ኰርማ ሕላ (እንደ አህያ መጮህ) ባይማር ምን ይለምዳል" እንደሚለው እንደ "ማህበረ ቅዱሳንና” አባላቶቹ ያሉት ከቃሉ ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነትና ሕብረት የሌለው ደግሞ ጋንጩር መምሰሉ ሊደንቀን አይገባም::

መቼም በዚህ ሁሉ ሐተታ ጳውሎስ“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” በማለት የጻፈው መልእክትና "ማህበር ቅዱሳንና” አባላቱ ደግሞ በፊናቸው ባልገባቸው “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ማለትና ምን እንደሆነ ግልጽ ነው ብዬ አምናለሁ። የተቀረውን ደግሞ አንድ በአንድ ተለቅመው ለንባብ እስኪበቁ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረት ሰላማና ፍቅር ከሁላችን ጋር ይሁን::

/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Email: yetdgnayalehe@gmail.com
United states of America__

25 comments:

  1. satwared dikunahn wedekibru melsew ante degmo man yemiluh neh?

    ReplyDelete
  2. wendem beselam new tsehufeh hulu sele mahebere kidusan becha new tinshi keyer adergew enji??? lenegeru "ke Egzixbehar yehonut hul fetenana tekawami yibezabachewal " ayidel yemibalew le ene endaregaget redetognal gen lehlina sitel yemayireba menamen tsehuf atilkeke anbabi yelehim eko weyiiiiiiiiiii

    ReplyDelete
  3. Minew Wondimie Zelefkew ? Endih Metsafihs lik yasegnihal ? Badonethin ena chelemtegnitehin Kemasayet wuch min feyde ?

    Libona Yisteh ! yisten !

    ReplyDelete
  4. Ante belo yegziabheren kale awaki yematereba tenektobehal ante belo dakon bebetkrstian yemaereg sem atneged Tehadeso mehoneh seletenekabeh ena MK betekrstian atetadesem selale yemthonuten atachu ahunem yMK meserachu Egziabher selhone ayetfam ante gen besewor yemnserawon yemiyawk amlk yeserahen waga ykefeleh Tehadeso kalhone hulum Yeortodox tewhado lejoch MK men endemesera selemawk atkbateru!!!1

    ReplyDelete
    Replies
    1. የእርግማን መንፈስ ከማን እንደሆነ በግልጥ የሚታወቅ ነው፡፡ የአባትህ የዲቢሎስ ልጅ በመሆንህ የምትለውን አታውቀውም፡፡

      Delete
  5. mechem yediyabilos Tore fit lefit kaltekawemut aysesemena yihene agura zelel mahebre linkawewe yigebal. efrem behasabehe efere. berta mule

    ReplyDelete
  6. aye efrem ezwe seleamerika tere teretehen safe engi minew endi yalewen neger betetew. yeasebariw mk kendga asmache mehonehe endewe yetaweke new

    ReplyDelete
  7. dont give up d/n fight them in the right way. mk has to be destroyed.

    ReplyDelete
  8. D Mulugeta Tetsenkek -Lerasihi ewek mahibere kidusann mekawem malet menor alemefelg new Abune Fanueil Yetebalut papas Mahiber kidusann tekawmew Awasa
    America Kolfe yederesebachewn atawkim D Efiremn Mekawem Mahibere Kidusann Mekawem New Mahibere Kidusann Mekawem Degimo Egiziabherin Mekawm new Arife Nur Ahun Tenkitobhal Abun Abirham- Abune Kerlos Abune Kewstos -Abune Estifanos-Abune Eliyas-Abune Timotewos yeteshefenut Mahibere KIdusann Degifew sile noru new keenersu temar DegoD Efirmin Kihinetun menkat yelbihim Anidand Gize Melkam neger tanesalehi yetemark sewm timesilaleh tehadisonetm yalebih yimeslal Gin Mahibere Kidusann lekek Adirg AHun semonun tayaleho Abune Pawlosna Ato Meles Zenaw yemidersachewn

    ReplyDelete
    Replies
    1. muwaretga tenkuway. yemetewelut ke tenkuway gar mehonachun eko enawekalen . YeEgziabeherene menegeste lemekaweme muwareten tetekemalachu gin aysakalachum. mk ye diyabilos lij new.

      Delete
  9. ሁሉ በፍቅር ቢሆን?

    ያለመታደል ሆኖ ኢትይጵያዊነት/አበሻነት ትርጉሙ አልሸነፍነት ሆኖብናል:: ያውም ለወንድም/ለእህት መልካም ነገር እንጂ ለነጩማ ዳንኤል ክብረት 'ፕሮፌሰር ሳቤት' በሚል ርእስ ባቀረበው አስተማሪ ጽሑፉ እንደጠቀሰው አሜን አሜን ነው የምንለው

    ታዲያ 'ወንድሜ' ኤፍሬም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጠቅሶ በጥምቀት ላይ ስለቀረበው መፈክር ይዘት ሊያስርዳን መሞከሩ እሱ ባለው መንገድስ ቢሆን የትና መቼ ነው እውነተኛ ክርስቲያኖች ይህን መሰል መፈክር ይዘው በአደባባይ በመውጣት የፎከሩት? ክርስትና በፍቅር ፍቅር ስለሆነው ጌታ መመስከር እንጂ በመፈክር ዓለምን አላዳረሰም:: ምናልባት ኢትዮጵያ አገራችንን በዚህ አዲስ ጅማሬ አንደኛ ለማድረግና ሰይፍ ይዘው በመነሳት ከሚስፋፉት ወገኖቻችን ጋር አንድ ለመሆን ይሆንን? ወንጌል በክፉው መንፈስ ተሞልተው የሰው ሁሉ ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ለማገልገል የተነሱትን ሰዎች ሳይቀር እንድንወድ የሚያደርግ የፍቅር አዋጅ እንጂ ሰይፍ አይደለምና በዚህ ማህበር ውስጥ በመሰግሰግ የገዛ የሥጋ ወገኖቻችሁን የምታሳድዱ ወገኖች ልባችሁን ቆም ብላችሁ በመመርመር መልካም ወደ ሆነው የምህረት ጌታ ተመለሱ በማለት የፍቅር ጥሪ እናስተላልፍላችኋለን::

    ዲያቆን ሙሉጌታም ብትሆን ምንም እንኳን የማህበረ ቅዱሳን በትር ያረፈብህና እስከ ሞት ድረስ እርምጃ ሊወሰድብህ የነበርክ ብትሆንም ስለሞተልህ የጌታ ፍቅር ስትል እውነተኛ ይቅርታ በነዚህ ሳያውቁ ያወቁ መስሏቸው('ቢያውቁ ኖሮ የሕይወትን ጌታ ይሰቅሉት ነበርን?' በጥፋት ጎዳና ላሉ ወገኖቻችን አድርገህ ሊመለሱና እውነተኛ የሕዝብ አገልጋይ የሚሆኑበትን መንገድ የሚያመላክት ትምህርታዊ የፍቅር መልእክት ለማስተላለፍ ብትሞክር??

    ማቅንም ልብ ይስጣችሁ

    ሰላም ሁኑልኝ

    እህታችሁ

    ሰላም ነኝ

    ReplyDelete
  10. mene lemalete endetefelege ene salehone tsehafiwe gena megibia laye newe

    ReplyDelete
  11. ...''kefiyachew tawukuachewalachihu''yetebalew endeante lalew new! m sorry eyetesadebu christian negn sitl alemaferh. Dikunahinm befekadih melisew. ante bet ke politica ga magenagnetih ena mewodedik new?

    ReplyDelete
  12. wdfit belelet belenal. berta mule. blogewan wededenat.

    ReplyDelete
  13. dinke new wededkuhe

    ReplyDelete
  14. wendem keawrew kar metagel adkami behonem tesfa alen and ken yewedkal

    ReplyDelete
  15. ወይ ኩልል ቅልብጭ ድንቄም አሉ! መናፍቅ መልሶ ልብ ያደርቅ! እንዳሉት አባቶቻችን አንተን ብሎ የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ እንደ ግብር አባትህ ዲያብሎስ ነህ!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ራስህ ነህ ወሬኛ ማቅ ከፋፋይ፣አድማኛ፣ እንደ ግብር አባትህ ዲያብሎስ ነህ

      Delete
  16. why you ignored my comment aya gelaw'

    ReplyDelete
  17. efrem eshete yeslemna akrarinet yalkewen metsehaf yemaheber kidusan yikerta tessasatkugne yemahebere seyitan belhe keyirew

    ReplyDelete
  18. Ante belo yegziabheren kale awaki yematereba tenektobehal ante belo dakon bebetkrstian yemaereg sem atneged Tehadeso mehoneh seletenekabeh ena MK betekrstian atetadesem selale yemthonuten atachu ahunem yMK meserachu Egziabher selhone ayetfam ante gen besewor yemnserawon yemiyawk amlk yeserahen waga ykefeleh Tehadeso kalhone hulum Yeortodox tewhado lejoch MK men endemesera selemawk atkbateru!!!1

    ReplyDelete
  19. በዚችው የዲቁና እውቀት ሌላ መተቸት ምን ይሉዋል

    ReplyDelete
  20. aye mhabr menemenoch btekekele yengrachu diyaqno mhabr qedusane ymetebalu kalngre lyla atwuqume enda arbakachu wdkerestose tmalsu nagre barezegtachu ymetsbeku enant menamenoch nachu

    ReplyDelete
  21. menafek mohoneh betam yastawukbahal

    ReplyDelete