Monday, February 27, 2012

ማቅ - ስመ ቅዱሳንን የያዘው ማህበር

ስለዚህ ማኅበር አወላለድ በመምህር ጽጌ ስጦታው(ይነጋል) እና በዲያቆን ሙሉጌታ /ገብርኤል (ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሰይጣን) መጽሐፍ  ብዙ ብዙ ስለተገለጠ ለጊዜው ከዚያ የምጨምረው የለኝም ከተወለደበት የዝሙት ህይወቱ ባሻገር አሁን ባለው የገንዘብ አፍቅሮቱና ያልበላውን የሚያክበት የቤተክርስቲያንን ታዛ የተጠለለበትን መሰሪ አካሄዱን በተመለከተ ጥቂት ለማለት እወዳለሁ።
ማቅ መሰሪ የሚባልበት ዋናው ምክንያት በምሁራን እውቀትና ያለእውቀት ጭፍን የክርስትና አፍቅሮት ባላቸው አላዋቂዎች መጠቀም መቻሉ ነው። የቅዱሳንን ስያሜ በለበሰው ማቅ ተሸፋፍኖ እውቀት ባላቸው እና  በፍቅረ ክርስትና በሰከሩ ማይማን እንዴት እንደሚጠቀም አንድ ባንድ እንመልከት።
በምሁራን እውቀት መጠቀም ይህ ኃይል ማዕከላዊ የበላይነትንና አንድ ወጥ ተዓዝዞትን ለማስፈን ከአዲስ አበባው ማቅ ማዕከላዊ ቢሮ ጀምሮ በክልል ፤በዞን፤ በወረዳና በአጥቢያ የእስትንፋስ ሴሎችን የሚያዋቅር፤ የሚያደራጅና የሚመራ የኅልውናው አንቀሳቃሽ  ዋና ሞተር  ነው። ከላይ ወደታች ይተነፍሳል፤ ከታች ወደላይ እስትንፋስ ይቀበላል። የደም መልስና የደም ቅዳ(circulation) ዓይነት ሥራ የሚከውን ማቅ ማዕከላዊ ልብ ነው። ይህ አካል ማዕከላዊ የበላይነትን ሳይሸራርፍ ሌሎች አመላላሽ የደም ሥሮችን ገጥሞ በቤተክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ሕይወቱን ያመላልሳል። ይኸውም፣
1/ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህግ በድንግልና ሳይኖሩ በድብቅ ልጅ የወለዱ፤ የእህቴ ልጅና የአክስቴ ልጅ እያሉ በቤታቸው ቅምጥ ያላቸው፤ በልጅነት ጊዜያቸው አግብተው የፈቱ፤ ከጊዜ በኋላም አዳማዊ ተፈጥሮ አሸንፎአቸው የጭናቸውን እሳት ለመተንፈስ የተገደዱ፤የቤተክርስቲያን ሙዳየ ምጽዋት በመገልበጥ የታወቁ፤ ከዜሮ ተነስተው ሃብታም የሆኑ ጳጳሳትንና መነኮሳትን ከገቡበት ገብቶ ማቅ አባል ማድረግ ዋና ስልቱ ነው። ይህ የሚጠቅመው የቤተክርስቲያን አመራርን የመቆጣጠርንና ላዩ ላይ ተጠምጥሞ የመተንፈሻውን ሳንባ ወደ ማቅ ማዕከላዊ ቢሮ ሳንባ ለመቀየር ሲባል ነው።
እነዚህ ልዩ ልዩ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ለመያዝ መፈለጉ በግብር ከመመሳሰላቸውም በላይ ትርጉሙ ቀላል አይደለም። ይህ ማቅ በቅድሚያ የሰዎቹን የግል ማኅደር አገላብጦና በርብሮ በቂ መረጃ ከያዘ በኋላ ለአባልነት ሲመለምላቸው ግለሰቦቹ ይህ ከሳሽ ድርጅት መሆኑንና ገመናቸውን ጸሓይ ላይ ከማስጣት እንደማይመለስ አሳምረው ስለሚያውቁ አንድም ከባቴ አበሳ ከሆነው ከእግዚአብሔር ይልቅ ይህ ድርጅት እንዲሸሽግላቸው አለያም ከሌሎች ኃይሎች ጋሻ መከታ እንዲሆንላቸው በነዚህ ሁለት ምክንያት አገልጋይ ለመሆን ይገደዳሉ። ብዙዎቹ የዚህ ቡድን ደጋፊ ጳጳሳት በዚህ ጉዳይ የሚታሙ ብቻ ሳይሆን የሚታወቁ፤ ከፊሎቹም በቤተክርስቲያኒቱ ስም ከሚያንቀሳቅሰው የንግድና የልመና  ሼር ተቋሙ በጥቅም ያንበረከካቸው አንዳንዶቹም ፓትርያርክ ጳውሎስን ፈንግለን እናንተን ፓትርያርክ እናደርጋችኋለን በሚል የህልም የሹመት ፈረስ ያሰከራቸውን ታማኝ አገልጋዮቹም የአባሎቹ መነሻ ነጥብ ነው።በሶስተኛ ምክንያት ሊጠቀስ የሚችለው ደግሞ ከዚህ ከሳሽ ድርጅት ጋር መጋጨት ለቤተክርስቲያን የመሪነት ዕድገትና ለጵጵስና ሹመት ከመድረስ በአጭሩ እንዳይቀሩ ይህን ቡድን ወደመጠጋት ይሄዳሉ። ቡድኑም ገመናቸው የቱንም ያህል አስቀያሚ ሆኖ ለሹመት የማያበቃቸው ቢሆንም እንኳን የእርሱ ታማኝ አገልጋይ እስከሆኑ ድረስ የክስና የማሳሳቻ እስትንፋሱ በሆነው «ስምዓ ጽድቅ» እና «ሐመር» መጽሔቱ ላይ ቃለ መጠይቅ በማብዛት፤ የልማት አባት በማለት ዲስኩር በመርጨት፤ ተከታዮቹንና አገልጋዮቹን ሁሉ በማንቀሳቀስ እንዲሾሙለት ያስደርጋል። በተቃራኒው ደግሞ የሚታገሉትንና የክፋት አፉን ለመዝጋት ሌት ከቀን የሚደክሙትን ደግሞ ጥላት በመቀባት፤ የሃሰት ስም በማውጣት፤ ከመኮነንና ከመማስኮነን አልፎ ተርፎም ከድብደባ እስከግድያ የዘለቀ ሰይጣናዊ አገልግሎቱን ለመፈጸም የማይመለስ ለመሆኑ ድብደባውን የቀመሱ፤ ዛቻውን ፈርተው የተሰደዱ፤ የሞት ዕቅድ የተደገሰላቸው ከማንም በላይ ያውቁታል፤ እኛም ህያው ምስክሮች ነን።
2/ ሌላው በምሁራን የመጠቀም ብቃቱ የዓላማና የዕቅዱን መዳረሻ ማስፋት ሲሆን ይህም አባላትን አብዝቶ በመመልመል መጠመድ ነው። ይህም በዩኒቨርሲቲዎችና በኮሌጆች ነጠላ ለባሽ ተማሪዎችን ማደራጀት ነው። ከሃሺሽ የከፋ አለማወቅን በልባቸው ዘርቶ ዘሩን እንዲያባዙ የታማኝ አገልጋይነትን ባርኮት በላያቸው መተንፈስ ነው።
3/የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ልብ በመስረቅ የአጥቢያ ቤተክርስቲያንን የልብ ትርታ ማዳመጥ ሲሆን የካህናቱን ማንነትና ምንነት፤ የሰበካ ጉባዔ አባላትንና የአስተዳዳሪውን ተግባር በነዚህ ወጣቶች በኩል በመቆጣጠር የማይመስለው ነገር ከተገኘ ማሳደም፤ ስም ማስጠፋት፤ ማስከሰስ የመሳሰለውን ሁሉ መጠቀም መቻል ነው።
4/ከላይ እንደተመለከትነው የቤተክርስቲያን መሪዎችን (ሲኖዶስ) የተባለውን አካል ጭምር ከመቆጣጠር አልፎ፤ የልዩ ልዩ ክፍል ተማሪዎችን በአባልነት ከመመልመልና የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በእጁ  ከማስገባት ቀጥሎ ሌላው ጥበባዊ የመሄጃ መንገዱ በስጋዊ አስተዳደር ያሉትን ክፍሎች መቆጣጠር ነው። ይህም ፖሊሶችን፤ዳኞችን፤ መንግስታዊ ባለሥልጣናትንና ሹማምንትን በአባልነትም ይሁን በደጋፊነት ዙሪያውን ማሰለፍ መቻሉ ነው። ይህም እሱ የሚፈልገውን ለማስፈጸም፤ በእሱ ላይ የሚመጣውን ለማወቅና ለመከላከል፤ እሱ የማይፈልገውን ለማስወገድና ለማስመታት፤ ተከላካይ መንግስታዊ ኃይልን ከጀርባው ከማሰለፍም በላይ ጊዜ፤ ሁኔታና አጋጣሚ ከተመቸውም መንግስታዊ ስልጣኑን ከክህነታዊ ሲመት ጋር ተስፈንጥሮ ለመቅለብ ጥርጊያውን እያዘጋጀ ለመሆኑ የማይጠረጥር ሰው ከመጋረጃው ጀርባ ያለውን የዚህን ቡድን ማንነት ያለማወቅ ችግር አለ ማለት ይቻላል። በጭፍን ክርስትና ለዚህ ማኅበር የሚሟገቱ(የድርጅቱን ማይማንእንዴትነት ለሌላ ጊዜ ላቆየውና ለዚህ ድርጅት አልያዝ ያሉትን የጋለ ብረት ክፍሎች ጠቅሼ ጽሁፌን ልቋጭ።
በየትኛውም አጥቢያ ያሉት አብዛኛዎቹ ቀሳውስት፤ ዲያቆናትና አገልጋይ መነኮሳት ይህን ድርጅት የሚጠሉት እንደጠላት ነው። ምክንያቱ ምን ይሆን?

ስሙን ካልገለጸ አንባቢ የተላከ

No comments:

Post a Comment