Monday, February 27, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን የሃይማኖት ወይስ የስለላ ድርጅት? - - -

ብዙዎች ለኦርቶዶክሳዊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅርብ የሆኑ እንደሚያውቁት ማህበረ ቅዱሳን የተባለው ማህበር ከምድር ተነሥቶ ስም ያጠፋል፣ በሰው ነገር እየገባ እርስ በርስ ያጋጫል፣ ይደበድባል፣ ካስፈለገም ይገላል ለዚህ ሁሉ በመቶ የሚቆጠር ማስረጃ አለን። አሁን እጅግ የከፋውና በጣም አሳሳቢ የሚሆነው ፐርሰናል የሆኑ ጉዳዮችን ወደ አደባባይ ማውጣቱ፣ የግለሰብን ሕይወት ከትውልድ እስከ ዘር ማንዘር አስተሳሰቡና ጠቅላላ ሕይወቱ እየተሰለለ ለማን እንደሚሰጥ በማይታወቅበት ሁኔታ ለአደጋ መጋለጡ ነው።
ይህ መንፈሳዊ ነኝ ብሎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ድርጅት በስለላ ሥራ ብቻ እንደተሰማራ የራሱን አባላት እንኳ እንደሚሰልል ዲያቆን ዳንኤል አጋልጧል። መንግሥት የግለሰብን ሕይወት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ማህበሩ እንዲሰልል ፈቅዶለት እንደሆነ አናውቅም፣ ነገር ግን የግለሰቦችን ሕይወት በምሥጢር እየሰለለ እንደሚሰበስብ ካገኘናቸው በርካታ መረጃዎች ውስጥ አንዱን ከዚህ በታች ባለው ደብዳቤ ይመልከቱ ።

 
የመንግሥት ያለህ?
የሀገራችን ሕገ መንግስ ይህንን ጉዳይ እንዴት እያየው ይሆን? ሕገ መንግሥት የዜጎችን መብት ለማስጠበቅና የሕዝቦችን ደህንነት ለማረጋገጥ በሕዝብ የጸደቀ የሀገር ሰነድ ነው። ይህን ሕገ መንግሥት ለማስፈጸም የሚሠሩ ሕዝብ ይሹማቸው ወይም በጉልበት ይሾሙ ከላይ እስከ ታች ባለ ሥልጣኖች አሉ። ታዲያ እንደዚህ አይነት ዓይን ያወጣ ወንጀል በምድሪቱ የተፈቀደ ነውን?  በአደጉ አገሮች እንኳንና እንደ ማህበረ ቅዱሳን አይነቱ ማህበር ይቅርና መንግስት ራሱ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍቃድ አስፈቅዶ፤ ምክንያትን አብራርቶ ነው ዜጎቻቸው ላይ ስላለ ማካሄድ የሚችሉት። ያውም ከባድ ወንጀል እየሰራ እንደሆነ ከታመነበት።

1 comment:

  1. እኔ እምለው ብሎጉ የተከፈተው ማቅን ለመዎንጀል ብቻ ነው እንዴ??? አይይይይ

    ReplyDelete