Sunday, January 27, 2013

ካህን ይመራሃል እንጂ አይከተልህም!

Read in PDF:kahene
በዲ/ ሙሉጌታ ወልድገብርኤል
የጽሑፉ ዓላማ:
ምንም አንኳን ለሺህ ዘመናት አብረው ቢኖሩና አሁንም አብረው ቢመላለሱ ዳሩ ግን በሚገባ ያልተዋወቁ
በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ምእመናንን አግብርተ እግዚአብሔር ከሆኑ እውነተኛ የእግዚአብሔር ካህናት ጋር ለማስተዋወቅ ተጻፈ።
ማሳሰቢያ:
በዋናነት በጽሑፉ ለማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት ምእመናን እንደ አማኞችና ተከታዮች መጠበቅ የሚገባቸው ዋኖቻቸውን ይለዩና ክብር ለሚገባቸውም የሚገባቸውን ክብር ይሰጡ ዘንድ ተጻፈ እንጅ በክህነት ስም በቤተ ክርስትያን የመሸገውን ሰርጎ ገብ ወረበላ ሁላ እንዳሻው ይናጣችሁ የሚል መልዕክት የለውም:: ይህን ይሆን ዘንድም አልጻፍኩላችሁም።
በተጨማሪም ጽሑፉ በይዘቱ ኑሮ ለመሸወድ ተመሳስለው የተቀላቀሉ፣ ሁሉን በሚያውቅ በእግዚአብሔር ፊት መንዳቢያንሳሉ በሰው ዘንድ እንደ መጋቢያን የሚታወቁና እንደ መጋቢም የሚጠሩ፣ "አባ/አቡነ እገሌ" ተብለው በሚጠሩ ጊዜም "አቤት" ለሚሉ መነኮሳት አይመለከትም። እውነተኛ ካህን ሲጠራ አቤት አይልም አይደለም አንድምታው ቁምነገሩ ያለው ወዲህ ነው። ያዕቆብ በስጋ ወላጅ አባቱ ከሆነው ከይህሳቅ ዘንድ እንዴት ምሩቃት እንደወሰደ እናውቃለን። ያዕቆብ ከአባቱ ምርቃት የወሰደበት መንገድ ትክክለኛ በሆነ መንገድ ሳይሆን ወንድሙን በመምሰልና በአባቱ ፊትም በቀረበ ጊዜም ያዕቆብ ሳለ ኤሳው ነኝ በማለት አባቱ በማታለል ነበር ምርቃቱን ሊያገኝ የተቻለው። ታድያ ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ነበር እግዚአብሔርም ይባርከው ዘንድ "ስምህ ማነው?” ባለው ጊዜ በአባቱ ላይ ያደረጋትን የማታለል ድርጊት በእግዚአብሔር ፊት አልሞከራትም። ለማስተላለፍ ተፈለገው መልዕክት ይሄ የሚያምነው የማያውቅ፣ ድግስ የማያመልጠው፣ እንደ ወርሀ መስከረም ዝንብ በዙሪያችን የሚያንጃብበውና ለሰውም "ለእግዚአብሔርም" ፈተና የሆነ ከማደሪያው ኮብልሎ ለከተመ "ፈላሲ" አይመለከትም ነው።


በአንጻሩ ይህ ጽሑፍ መጠራቱ ነፍሱ ለምትመሰክርለት፣ በእግዚአብሔር ፊት "ስምህ ማን ነው?” ተብሎ
በሚጠየቅበት ወቅትም ያተርፍበት ዘንድ የተሰጠውን የመክሊት ልክ እየጠራ "በፊትህ የቆምኩ ባሪያህ ነኝ" የማለት መብት ያለው፣ እግዚአብሔር ሲጠራውም ልጁ ኢየሱስ/ባሪያው ሙሴን በሚጠራበት ድምጽ "ባሪያዬ ... " ብሎ ለሚጠራው የእግዚአብሔር ካህን ብቻ የሚመለከት ይሆናል።
የጽሑፉ ውሱንነት:
ቀደም ሲል "ካህናቶቻችሁን አትበድሉ፡ ካህን የዕድር ዕቃ አይደለምና!" በሚል ጽሑፍ "ካህን ማለት ማን ነው?” ተብሎ በአንባቢ ለሚነሳ ጥያቄ "ካህን" የሚለው ቃል በማስመልከት ቀደም ሲል የተሰጠውን ትንታኔ ማለትም ዝርዝር ሐተታው የኢ////ያን ሥርዓተ ትምህርት መሰረት ያደረገ ለመሆኑ ግልጽ ለማድረግ እንደተሞከረ አሁንም ቢሆን ይህ ጽሑፍ የካህን ማንነት በሰፊው የሚያስረዳ እንጂ "ካህን ማለት ማን ነው?” ተብሎ ከአንባቢያን ዘንድ ለሚነሳ ጥያቄ ምላሽ አይሰጥም።
ሐተታ:
መቼ? እንዴትና በምን ዓይነት ሁኔታ? የሚሉት ጥያቄዎች በተጨባጭ መልስ መስጠት ባይቻልም የክርስትና እምነት በመቀበል ረገድ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀደምትነት ከሚጠቀሱ አፍሪካውያን ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናት። ሀገራችን ኢትዮጵያ እስከ 16 ኛው /ዘመን አከባቢ ድረስ በመጠኑም ቢሆን ያልተከለሰና ያልተበረዘ ሕገ ወንጌል ከመቀበልዋና የራስዋ ከማድረግዋ በፊትም ቀደም ባሉ ዘመናት አሁንም መቼ? እንዴትና በምን ዓይነት ሁኔታ ለሚሉ ጢያቄዎች ቁርጥ ያለ መልስ መስጠት በማይቻልበት በሕገ ኦሪት/በብሉይ ኪዳይ ስትገለገል የኖረች ሀገር ናት።
እንደው በገጠሪቱ የሀገራችን ኢትዮጵያ የሚኖር ሕዝብ ካህናትን በማቃለልና ቤተ ክርስቲያንን በማወክ ረገድ ጨርሶ የማይታማና የትም ተፈልጎ በቀላሉ የማይገኝ ከከበረ ማዕድን ይልቅም እጅግ ውድ የሆነ ምሥጋና የሚገባው ሕዝብ ለመሆኑ በዚህ አጋጣሚ ላወሳው እወዳለሁ። ከተሜውም እንደሆነ ከእውቀት የሆነ እግዚአብሔር የሚፈራ፣ ካህናቶቹንም የሚያከብርና እግር የሚጠብቅ ምእመን የለም እያለኩ እንዳይደለም በአንባቢ ዘንድ ግልጽ እንዲሆን ተስፋ አደርጋለሁ።
ቢሆንም ግን በአማኞች መካከል መራራ ዘር ሲበቅል ተገቢ የሆነ እርምጃ ካልተወሰደና በጊዜው ካልተቆረጠም የሚበላውን ከበላና ካጠፋ በኃላ ወዮ! ማለቱና መፍጨርጨሩ ዋጋ ስለማይኖረው በተለይ በምዕራቡ ዓለም በአንድም በሌላም መንገድ አፍ የሌለውን ካህን "የታባክ" እየተባለ ማገላመጥና አፍ አፉን ማለት እንደ ጀብድነት እየተቆጠረ ያለ ልክ በአብያተ ቤተ ክርስቲያናት መካከል እየተንሰራፈ እየመጣ ያለውን/የሚገኘውን በሽታ የእምነቱ ተከታይ የሆነውን ሕዝብ ከእንዲህ ዓይነቱ በሽታ ራሱን ይጠብቅ ዘንድም ተጻፈ።
በማስቀደም ግን አንባቢ ስለ ርዕሰ ጉዳዩ የጠራ ምስል ይኖረውና ጸሐፊው እንደሆኑም ስለ የትኛው ካህን
እየተናገሩ እንዳሉ አንባቢ ግልጽ ይሆንለት ዘንድ በቅድሳት መፃህፍት እንደ ተፃፈ እውነተኛ የእግዚአብሔር ካህንን ከአስመሳዩን ለይተን ማወቅ ይቻለን ዘንድ በመጠኑም ቢሆን እውነተኛ የእግዚአብሔር ካህን የሚታወቅበት መለያ የሚከተለውን ይመስላል። እውነተኛ የእግዚአብሔር ካህን:
ለእግዚአብሔር ያደረ፣
ስፍራው የሚያውቅ፣
በስሜት የማይኖግድ፣
ተጽፎ የተሰጠውን መዓት ይዞ የባጡ ቁጡ የሚዘላብደውን ሳይሆን የሚናገረውን የሚያስተውል ጭምት፣
ሲናገርም በቃሉ (በቅድሳት መፃሕፍት) እንደተጻፈ፣ እግዚአብሔር እንደተናገረም የሚናገር እንጅ ከራሱ የማይናገር፣
የማንም ምድራዊ ዓላማ ያለው የፖለቲካ ድርጅት ትጥቅና ስንቅ አመላላሽ ያይደለ፣
ከእግዚአብሔር እጅ በቀር የማንም እጅ የማያይ፣
ከሰው ዘንድ አጉል (ከልኩ ያለፈ) የቅንጦት ክብር የማይሻ ነው።
ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮሃለች! የእግዚአብሔር ካህን ማለት እግዚአብሔር ባስቀመጠው ስፍራ ላይ ቁሞ ከላከው ከእግዚአብሔር የሰማውን በታማኝነት ሳይጨምርና ሳይቀንስ ሰሚን የሚያንጽ ቃል ለቤተ ክርስቲያን መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው።
የእግዚአብሔር ካህን ቢፋቅ ቢገለበጥ ካህንነትቱን አያጠያይቅም።
እውነት ጽድቅና ፍትሕ የሚያደርግ፣ የሚመሰክር፣ የሚናገርና የሚሰራም ነው።
የእግዚአብሔር ካህን ለግለሰቦች ግላዊ ጥቅምና ረብ መጠቀምያ፣ መገልገያ፣ ተላላኪና ተለጣፊም ሆኖ ራሱን በመሸጥ ሽርጉድ በማለት አይታወቅም።
የእግዚአብሔር ካህን ማለት ከዘመኑ የጎጠኝነትና ጠባብ አስተሳብ የተፈሰ ነው።
የእግዚአብሔር ካህን ማለት ሰውን ሁሉ በእኩል ዓይን ቤተ ክርስትያን በደሙ በመሰረታት የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በተቀባው በኢየሱስ ደም የሚያይና ሁሉንም በእኩልነት ያለአንዳች አድልዎ ዝቅ ብሎ በታላቅ ትህትናና በሙሉ ልብ የሚያገለግል ነው።
የእግዚአብሔር ካህን ማለት ሰውን ሁሉ የሚያከብርና እግዚአብሔርን የሚፈራም ነው። ቀለል ባለ አማርኛ ልብሰ ተክህኖ የለበሰ፣ መስቀል የጨበጠ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም እየተባለ ነው።
ይህን ካወቅን ዘንዳ እንግዲህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ካህን:
ራስ እንጅ ጅራት አይደለም።
ይህ ካህን ትከተለዋለህ እንጅ አይከተልህም።
ይመራሃል እንጅ ከፊት ቀድመህ በማለት አትመራውም።
ቀድሞህ ይሻገራል እንጂ ቀድመኸው አታልፍም።
ይህ ካህን ሲናገር ትሰማዋለህ እንጅ አንተ ቁጭ በል እኔ ልናገር አትለውም። በተረፈ ትውልድ ይህን ሐቅ
የማወቅ፣ አምኖም የመቀበልና ተገባራዊ የማድረግ ግዴታ እንዳለው የሚያጠያይቀን አይሆንም። ሀገራችን ኢትዮጵያ ሆነች ሕዝባችን ሊፈወስ የሚችለውም እያንዳዳችን በስፍራችን ስንቆማና የሥራ ድርሻችንም በአግባቡ ስንወጣ ብቻ ነው የሚሆነው።
/ ሙሉጌታ ወልድገብርኤል
E-mail yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America44

No comments:

Post a Comment