Friday, January 17, 2014

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በህዳር 12 ከተሰበሰበ ገንዘብ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ተመዘበረ፡፡

በደብረምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የደብሩ አስተዳዳሪ የዓመት ፍቃድ በመሆናቸው በቆጠራው ላይ ስላልተገኙ ይህንንም እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠርና የሰበካ ጉባዔ ምክትል ሊቀ መንበር ስልክ ተደውሎላቸው ቆጠራውን አቋርጠው በመውጣታቸው የደብሩ ዋና ጸሐፊ መ/ስ አብርሃም አቧይ  የወረዳው ስራ አስኪያጅ የአባ አእምሮ የቅርብ ዘመድ ከወረዳ የተወከሉት ወ/ሮ አባይ እና የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊ ወ/ሮ አዲስ ዓለም እንዲሁም በአዲስ አበባ ሙስናና ዘረፋን በማበረታታት እነ የካ ሚካኤልን እንዳያገግሙ አድርጎ በዘረፋ ባዶ ያስቀራቸው በአዲስ አበባ ከተማ ለተለያዩ የውጪ ሀገር ኗሪዎች 7 ፎቅ ቤቶችን በተለያዩ አካባቢዎች  ሰርቶ የሚያከራየው ቀድሞ አለቃ የአደራው ንጉሤ ሴት ልጅ  ወ/ት እጸገነት አደራው በገንዘብ ያዥነት እንዲሁም በካቴድራሉ መልካም ሰው በመምሰል ለሁሉ ወዳጅ የሆነው አቶ ፋንታሁን ምረቴ እና ሊቀ ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ በጋራ ዘረፋውን ማከናወናቸው ታውቋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ቅ/ሚካኤል በህዳር 12 ቀን ከምእመናን የተሰበሰበውን ገንዘብ ግማሹን በመቀነስ 280 ሺህ ብር ብቻ ወደ ደብሩ ባንክ እንዲገባ ሲደረግ ሌላውን ግን በቆጠራው የተገኙት ስማቸው የተዘረዘሩት ግለሰቦች ተካፍለውለታል፡፡ የደብሩ ጸሐፊ አብርሃም አቧይ ለአቡነ እስጢፋኖስ ቀራቢ ነኝ በማለት ደብሩን እየበጠበጠ ሲሆን፤ በትዳሩ ላይ በመወስለት እና ከሙስሊም ሳይቀር ዲቃላ በመውለድ ቤተክርስቲኒቱን ያሰደበ ተግባር መፈጸሙንና በአባ እስጢፋኖስ ዘንድ አለኝ በሚለው ተሰሚነት ሰራተኛውን እያስፈራራና እያሸበረ እንደሚገኝ ለማወቅ ተእሏል፡፡

በደብሩ ሰንበት ት/ቤት ተማሪ የነበሩና በኋላ በግል ጥቅም ታውረው የምዷየ ምጽዋት ገንዘብ የጣማቸውና ወደ ሰራተኛነት ያደጉት ዲ/ን ዳዊት ወርቁ ከሰበካ ጉባዔ አባልነት በተጨማሪ የደብሩ የእለት ገንዘብ ሰብሳቢ ተደርጎ የተመደበ ሲሆን ሌላዋ ሰንበት ተማሪ የመ/ር እንቁ ባሕርይ ቅምጥ የደብሩ ምክትል ሒሳብ ሹም በመሆን ስትሰራ የነበረቸው ወ/ት ምንጭቱ ከሒሳብ ሹሙ ጋር  ባለት የፍቅር ግንኙነት ቤተክርስቲኑ ውስጥ ያልተገባ ተግባር በመፈጸሟ ወደ ሌላ ቤተክርስቲያን መዛወሯን ለማወቅ ተችሏል፡፡

1 comment: