Thursday, March 8, 2012

ነጋዴው ማኅበረ ቅዱሳን በገጠር አድባራትና ገዳማት ስም የሚሰበስበው መባ መግቢያው የት ይሆን?


በመንፈሳዊ ስም ተሰባበስቦ በንግድ ስራ የተሰማራው ማኅበረ ቅዱሳን ካለፈው ዓመት ወዲህ ካሉት የገቢ ምንጮች በተጨማሪ በተለያዩ አርእስት የገቢ ምንጮቹን ማስፋፋት መቀጠሉን እየታዘብን ነው፡፡ ባለፈው ዓመት “ሁለት ልብሶች ያሉት” የሚል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር “በአብነት ት/ቤቶችና ገዳማት ስም” አልባሳት ሲያሰባስብ እንደ ነበረና በጊዜው ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል ተግባሩ ህገወጥ መሆኑ ተገልጾ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ‹‹አድሮ ቃሪያ፣ ከርሞ ጥጃ›› የሆነው ማህበረ ቅዱሳን ግን አባ ሠረቀ ተነስተውልኛል፣ ባይነሱስ ማን ምን ያመጣል? እድሜ ለነአቡነ … በሚል ማን አለብኝነት ዘንድሮም አዲስ የገቢ ማስገኛ ርእስ ከፍቷል፡፡ ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት መባ ስጡ የሚል፡፡

ቤተክርስቲያን ባለጠጋ ናት፤ ለሌላው የምትተርፍ እንጂ ሌሎች የሚረዷት አይደለችም፤ ሁሉ በተገቢው መንገድ መከናወንና መደላደል ቢችል አንዱ ቤተክርስቲያን ሀብታም ሌላው ደሃ ባልሆኑም ነበር፡፡ የከተማ አብያተ ክርስቲያናት ከምእመናን የሚሰበስቡትን መባ፣ ስእለት፣ መዋጮና ሌሎችንም ልዩ ልዩ ገቢዎች የሚያደርጉበት አጥተውና ለምዝበራና ለአንዳንድ ግለሰቦች መከበሪያነት አውለውት ባለበት ሁኔታ፣ የገጠር አድባራትና ገዳማት በገንዘብ እጦት ሲዘጉ ማየት አሳዛኝ ነው፤ ከዚህ በላይ ግን ቀደም ብሎ የቤተክርስቲያንን ችግር ለመለመኛነት አደባባይ ላይ አስጥቶና አስተዛዝኖ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር የለመነውንና የሰበሰበውን ገንዘብ ደብዛውን ያጠፋው ማህበረ ቅዱሳን፣ በአካፋ አስገብቶ በማነኪያ እንኳ የማያቀምሰው ማህበረ ቅዱሳን ዛሬም የተለመደ ተግባሩን እንዲፈጽም በእርሱ በኩል መባ መስጠት እጅግ ያማል፡፡
ልብ በሉ! መባ ለቤተክርስቲያን አይሰጥ አልተባለም፤ እየተዘጉና እየተዳከሙ ያሉ የገጠር አብያተ ክርስያናትን መደገፍና አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ይህን የማድረግ ሥልጣኑ ያለው ግን በቃለ አዋዲው መሰረት በጠቅላይ ቤተክህነት የተቋቋሙና ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምሪያዎች ናቸው እንጂ ማህበረ ቅዱሳን አይደለም፡፡ ማህበሩ እነዚህን ተግባራት እንዲያከናውን ከቤተክርስቲያን በኩል የተሰጠው ፈቃድም ሆነ እውቅና አለመኖሩ ግልጽ ቢሆንም ቤተክርስቲያን ያቋቋመቻቸውን መምሪያዎች እንደሌሉ እንዲቆጠሩና ለቤተክርስቲያኒቱ ከእርሱ በቀር ማንም አሳቢ እንደሌላት እንዲታሰብ እያደረገ ነው፡፡

የማህበሩ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ሙሉጌታ ‹‹እንደ ሌሎች እህት አብያተክርስቲያናት ለወደፊቱ ቅዱስ ሲኖዶስ በደንቡ አጥንቶት ቤተ ክርስቲያናችን ራሷን አደራጅታ መባዎችን ለእግዚአብሔር እንደሚገባ በጥራት አዘጋጅታ ከሌሎች ጥገኝነት የምትላቀቅበት ጊዜ እስከሚመጣ ለጊዜውም ቢሆን ያለውን ችግር መቅረፍ እንድንችል በተለይ በዚህ የፆምና የጸሎት ሠዓት ከእኛ ብዙ ይጠበቃል›› ማለቱን ከማህበሩ ድረገጽ ላይ አንብበናል፡፡
ይህ ምን ማለት ነው? ለመሆኑ ቤተክርስቲያን በገንዘብ በኩል የማን ጥገኛ ናት? የቤተክርስቲያን ጠቅላላ አገልግሎት የሚከናወነው ምእመናን በሚሰጡት መባና ልዩ ልዩ አስተዋጽኦ አይደለም እንዴ? ነው ወይስ ማህበረ ቅዱሳን ጥገኛዬ ሆናለች ለማለት ዳድቶት ይሆን? ቤተክርስቲያን ከራሷ ተርፋ ለማህበረ ቅዱሳንም እንኳ ታላቅ የገቢ ምንጩ መሆኗን ሰብሳቢው ልብ አላለው ይሆን? ባይሆን አልጠግብ ባዩ ማህበር ነው በቤተክርስቲያን ስም ኮሮጆውን ይዞ ከአገር ውስጥ እስከ ውጭ አገር በስሟ በመለመን ጥገኛ የሆናት፡፡
የቨርጂኒያ ደብረ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊና ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት ቆሞስ አባ ሃይለሚካኤል ወልደ ተክለ ሃይማኖት ባለፈው ጊዜ ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በተያያዘ አሜሪካ ውስጥ ከሚገኝ አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፣ ማህበረ ቅዱሳን በውጪ ገንዘብ የሚለምነው ለፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት፣ ለገዳማት፣ ለተራቡ ሰዎች ወዘተ በሚል እንደሆነ ጠቁመው፣ ማህበሩ ይህን ማድረጉን ቤተክርስቲያንና አስተዳደራዊ መዋቅሯ ፈጽሞ እንደማያውቁትና ሁሉንም ነገር ማህበሩ አየር በአየር እንደሚያከናውን አስረድተዋል፡፡ ምሳሌ አድርገው የጠቀሱት በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ማህበረ ቅዱሳን ፈጸመ ያሉትን ደባ ነው፡፡
በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የበጎ አድራጎት የሚባል ኮሚቴ አለ፡፡ ኮሚቴው ከምእመናን በብዙ ድካም አገር ቤት ለሚገኙና በችግር ውስጥ ላሉ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት በማህበረ ቅዱሳን ሀላፊነት ይሰጣል፤ ገንዘቡ ከመለቀቁ በፊት ማህበረ ቅዱሳን በገጠር አድባራትና ገዳማት ስም ፕሮጀክት ቀርጾ ይልካል፤ ገንዘቡም ይለቀቅለታል፤ ከዚያ ገንዘቡ ወደተባሉት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ለመድረሱ ምንም ማረጋገጫ የለም፤ ከማህበረ ቅዱሳን ቢሮ ግን ‹‹ገንዘቡ ደርሶናል፤ ወደፊት በቪዲዮና በምስል ቀርጸን እንልክላችኋለን›› የሚል የምስጋና ደብዳቤ ይላካል፤ ይህ ግልጽነት የጎደለው አሰራር ጥርጣሬ ያሳደረበት የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ቦርድ የሰጠውን ገንዘብ ማህበሩ እንዳቀለጠው ሲረዳ፣ ማህበረ ቅዱሳንን እናንተ እነማናችሁ? እኛ የምንፈልገው ከዚያው ገንዘቡ ከደረሰው ከገዳሙ እንጂ ከአንድ ማህበር ደብዳቤ አንፈልግም ብለው ሲያፋጥጡት፣ ማህበሩ አካኪ ዘራፍ ማለት ጀመረ ይላሉ፡፡
ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን እነዚህን ችግሮች የሚፈታ መዋቅር የሌላት አስመስሎ በማቅረብ የምእመናንን የድጋፍ ትኩረት ወደራሱ ለመሳብ ጥረት ቢያደርግም፣ የፈረሱ አብያተክርስቲያናትን የሚሰራ፣ የሚደግፍ፣ መምሪያ እንዳላት ቆሞስ አባ ሀይለ ሚካኤል ጠቅሰዋል፡፡ ማህበሩ ግን ሲኖዶስ እስኪንቀሳቀስ ድረስ እኔ ክፍተቱን እየሞላሁ ነው ብሎ በድፍረት ገቢውን ለማሳደግ በተደጋጋሚ ተንቀሳቅሷል፡፡ ሲንቀሳቀስም ቤተክህነቱ እንዲጠላና ድጋፉ ለእርሱ እንዲሰጥ ሲያግባባ መስተዋሉን ‹‹ለቤተ ክህነት አትስጡ ለመንግስት፣ ለወታደሮች ይሰጡታል፤ ለተለያየ ነገር ያውሉታል፤ … መኪና ይገዙበታል ስለዚህ ወደ እኛ ገቢ አድርጉ›› የሚል ቅስቀሳ እንደሚያደርግ አባ አብራርተዋል፡፡
የሰሞኑ ‹‹የመባ ሳምንት›› ድራማ ምንም አዲስ ነገር ይዞ አልመጣም፤ ያው እንደተለመደው ርእሱን ለውጦ በቤተክርስቲያን ስም የማህበሩን ገቢ ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡ መባው የሚውለው በስማቸው ለተነገደባቸው የገጠር ገዳማትና አድባራት ሳይሆን እንደተለመደው ለማህበሩ ነው፡፡ ስለዚህ የቤተክርስቲያን ልጆች ሁሉ ማህበሩ ለጸረ ወንጌል እንቅስቃሴውና ለግለሰቦች መጠቀሚያነት እንዲያውለው በህገወጥ መንገድ የጠየቀውን መባ ባለመስጠት ከቤተክርስቲያን ጎን መሰለፍ አለበት፡፡ በገጠር በችግር ውስጥ ላሉ አድባራትና ገዳማት ሊረዳ የሚገባውን ሁሉ የቤተክርስቲያንን መዋቅር ተከትሎ ሊረዳ ይገባል፡፡ ከዚህ ውጪ የሚደረግ ሁሉ ወደማህበሩ ኪስ እንጂ ወደተቸገሩት አብያተ ክርስቲያናት እንደማይደርስ ከላይ የተጠቀሰው የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ልምድ ብዙ መማር ይቻላልና በማህበረ ቅዱሳን ልንነቃበት ይገባል፡፡    

14 comments:

  1. Menafiqan hulgizem YeMahibere Kidusan Menfesawi Sira ende esat yaqatilachewal enam kemetechet bozinew Ayawuqum. Egna Bariyawochu Tenesten Enseralen Yesemay Amlakim Yakenawunlinal. Menafiqan BeMahibere Kidusan Menfesawi ena Semayawi Sira gena Yiqatelalu.

    ReplyDelete
    Replies
    1. መስሎሽ ነው ቆማጢት! አለ ያገሬ ሰው

      Delete
  2. oooooooo we are very happy to c such kind of blog. bertu bertu bertu.

    ReplyDelete
  3. ....ለቤተክርስቲያኒቱ ከእርሱ በቀር ማንም አሳቢ እንደሌላት እንዲታሰብ እያደረገ ነው፡፡
    ....ለቤተ ክህነት አትስጡ ለመንግስት፣ ለወታደሮች ይሰጡታል፤ ለተለያየ ነገር ያውሉታል፤ … መኪና ይገዙበታል ስለዚህ ወደ እኛ ገቢ አድርጉ›› የሚል ቅስቀሳ እንደሚያደርግ አባ አብራርተዋል፡፡

    በማህበረ ቅዱሳን እንደህ መቅናችሁ ያስገርማል

    ReplyDelete
  4. bertulen yihen sew bela mahebere beewenet tekawemut. beewenet eretut. egziabehere yirdachu.

    ReplyDelete
  5. Mahiberu yebetekirstian mewakir wust endehone tsehafew yeteredu aymeslegnm. ebakwon tsehafe tiezaz endet yihen mawek yisanwotal.
    Lela comment Every article is about MK why dont u change the name from 'audemihret' to 'mk'. kkkkk

    ReplyDelete
  6. Betam yemiasazenew drom seytan tiru yemenfesawi sera yemiseran sew lematfat new yemiterew selezih bezum aydenkem lemehonu egna lebtekrstian men aderegen belachehu erasachehun megemeria ateteyekum sewen kemnkfacheu befit degmo yehen aynet astyayet kand krstian yemitebek aydelem megemeria erasacheun meremeru mahberekdusan tiru silimisera akatelacheu lemen betekrstian endtfers selemtfelegu dgmo menem betelu mahberun ende enante yale menafek yetelaw endehon enji manem aytelawom menm betelu mahberun Egziabher selmiredaw ayfersem lenantem lebona yestacheu.

    ReplyDelete
  7. i am very happy to see such kind of interesting blog.

    ReplyDelete
  8. አውደ ስድብ!!! በራሳችሁ ጊዜ አንደበትና ሥራ ማንነታችሁን እንድናውቅ ያደረገ የተዋሕዶ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን!!! ከፍሬዎቻቸው ታውቁአቸዋላችሁ አይደል የሚለው ታለቁ መጽሐፍ! እናንተንም ሆነ ማህበረቅዱሳንን በሥራችሁ አያየን ነውና እውነተኛውንና ሀሰተኛውን አትነግሩንም!

    ReplyDelete
  9. የማ/ቅ አክስዮን ድርሻህ ስንት ነው?

    ReplyDelete
    Replies
    1. We have lots of evidences that MK has been collectig money in the name of Waldiba, Asebot, Ziquala, etc and a penny is not given from many of the project docuemnts that they collected money for.

      Delete
  10. Ante min agebah? You are from your father Jude eskorotha! tikatelaleh enji yemisemah yelem, wolde Debora, wolde satan. Please change your name, you don't deserve to use that name!

    ReplyDelete
  11. የቤተ ክርስቲያን መዥገሮች (የናት ጡት ነካሾች)ቅጥ እያጡ በመሄድ ላይ ናቸው የእግዚአብሔርን ቃል መነገጃ አድርገውታል፤
    የሚለው ጽሑፍ እንዳለ ሆኖ በቤተ ክርስቲያን ስም መባእ እያጠራቀሙ የእግዜርን ሳይሆን የራስን ቤት መገንባት የጀመሩና
    እያጧጧፉ የሚገኙት የዘመኑ ቅዱሳን መዳረሻ የትና መቼ ይሆን ያውደ ምሕረት የመጻጻፍ ትግልስ ውጤቱ እንዴት ይሆን
    ያነንም ይህነንም ለማየት መጀመሪያ የፈጣሪ ቸርነት ቀጥሎ የዕድሜ መስታይት ከዚያም ትክክለኛ የፍርድ ዕለት ያስፈልጋል፤

    ReplyDelete
  12. ቤተክርስቲያን ባለጠጋ ናት፤ ለሌላው የምትተርፍ እንጂ ሌሎች የሚረዷት አይደለችም antena meselochih eyebotebotachihuwat diha honalech

    ReplyDelete