Friday, December 28, 2012

ቤተክርስቲያንና የገባችበት አጣብቂኝ

Read in PDF:Erke

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በታሪክዋ የተለያየ ፈተናዎች ገጥመዋት የሚያውቁ ቢሆንም እንደ አሁኑ አይነት ግን የተለየ መልክ ያለው አደጋ ገጥሟት አያውቅም። የቤተክርስቲያን አባቶች ቤተክርስቲያኒቱ ከገባችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ መውሰድ የሚገባቸው ጥበብ የተሞላበት እርምጃን ሲወስዱ እየታዩ አይደለም። በዙሪያዋ ተሰብስበው የራሳቸውን አጀንዳ ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሱ ያሉ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያሉ ማኅበራትም ችግሩ የሚጋጋልበትን መንገድ በመፈልግ ነገሮችን ከማራገብ በተሻለ እያደረጉት የሚገኝ ገምቢ እንቅስቃሴ የለም።
የሁለቱም ሲኖዶስ አባላት ከአንዳንድ አስተዋይ አባቶች በስተቀር ለእርቁ ተገቢውን ትኩረት እየሰጡ አይደለም። የዜና ማሰራጫዎችም “ጎሽ እንኳን አልተስማማችሁ” ከሚል የዘለለ ገምቢ ሚና ሲጫወቱ አይታዩም። በሁሉም ነገር የራሱን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈጸም ከመሯሯጥ የዘለለ በእውነት ለቤተክርስያኒቱ አንድነት በቅንነት ተገቢ ሚና የሚጫወት አለ ለማለት በማያስደፍር ሁኔታ ነገሮች ሲጦዙ እየተመለከትን ነው። በአዲስ አበባው ሲኖዶስ በኩል ከመንፈስ ቅዱስ ሀሳብ ይልቅ የቁጥር ስሌት አንገብጋቢ ሁኖ ይታያል። በአሜሪካው ሲኖዶስ በኩልም ወደ እርቅ የማያደርሱ እርምጃዎች በአንዳንድ ጳጳሳት አማካኝነት እየተወሰደ ይገኛል። በቅርቡ ኤርትራ ሄደው የመንግስትን ተቃዋሚዎች ባርከው የተመለሱት ጳጳስ እንቅስቃሴም ይብዛም ይነስም በእርቁ ላይ ጠባሳ ማሳደሩ አይቀርም። በዚህኛው ሲኖዶስ በኩልም እርቅ እየተወራ በምርጫ ጉዳይ ጊዜ ማጥፋቱ በእርቁ ላይ የተደቀነ ስጋት ነው።

እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያለ ማኅበርም በተገኙ አጋጣሚዎች የራስን ፋላጎት ለማስፈጸም ከመድከም በተለየ በእውነት የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲፈጠር ፍላጎት ያለው አይደለም። የውጪውን ሲኖዶስ ከአዲስ አበባው ሲኖዶስ ቀድሞ ያወገዘው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። በአስራ ዘጠኝ ዘጠናዎቹ ውስጥ በሚታተም ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ የአሜሪካውን ሲኖዶስ ደጋግሞ ማውገዙ የሚታወስ ነው። ማኅበሩ በአሜሪካው ሲኖዶስ ላይ የጣለውን ወፈ ግዝት ማንሳቱን በተመለከተም በይፋ የነገረን ነገር የለም።
ምርጫውን በተመለከተም ቢሆን በጥቅምቱ ሲኖዶስ የምርጫው ህግ እንዲሻሻል ከፍተኛ ግፊት ያደርግ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን ነው። የምርጫውን ህግ ያረቁ ከነበሩት ሰዎች መካከልም አንዱ የማኅበሩ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰሙ ነው። የህግ አማካሪ የነበረውም ብዙ አየሁ የተባለው የማኅበሩ ሰው ነው። መቼም የምርጫ ህግ የሚሻሻለው ለምርጫ መሆኑ ግልጽ ነው። ታድያ ማኅበሩ የምርጫ ሕጉን ለማሻሻል ያን ያህል ደክሞ አሁን ለምን አስመራጭ ኮሞቴ ሲቋቋም ተቃዋሚ ሆነ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው።
ብዙዎቻችን እንደምናውቀው ማኅበሩ የምርጫ ህጉን ለማሻሻል ኮሚቴው ውስጥ ከመካተት አልፎ የራሱን የምርጫ ህግ ረቂቅ አዘጋጅቶ ለሲኖዶሱ አባላት እና ለምርጫ ህግ አርቃቂ ኮሚቴ አቅርቦ ነበር። የምርጫው ህጉ ረቂቅ ተሰናድቶ ለሲኖዶሱ ሲቀርብ የቀረበበት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የማኅበሩን ፍላጎት በሚያስጠብቅ ሁኔታ ነበር። ስለዚህም ሲኖዶሱ በምርጫ ህጉ ላይ በሚወያይበት ጊዜ ጊዜው አይደለም በማለት አንዳችም ተቃውሞ አላሰማም። ተቃውሞ ማሰማት የጀመረው ማኅበሩ የራሱን ሰው ፓትርያርክ የማድረግ ህልሙን በሚያስጨነግፍ መልኩ የምርጫ ህጉ በመጽደቁ ነው።
እኔ ያልፈለጉት ሰው ሊመረጥ ይችላል በማለት ሂደቱን ሳይቃመም የሂደቱን ቀጣይ ጉዞ ግን መቃመም ጀመረ። በጥቅምቱ ሲኖዶስ የምርጫ ህግ መሻሻል ጉዳይ አጀንዳ ሲሆን ማኅበሩ ፈጽሞ አልተቃመም። እንዲያውም በአርቃቂው ኮሚቴ ላይ የማኅበሩን ሰብሳቢ ጨምሮ የማኅበሩ ሰዎች እንዲካተቱ አስደረገ። ህጉ በሲኖዶሱ መወያያ ሲሆንን ፈጽሞ አልተቃወመም። ህጉ ጽድቆ አስመራጭ ኮሚቴ ሲቋቋም ግን ተቃውሞውን ማሰማት ጀመረ። ለምን? ህጉ ማኅበሩ በሚፈልገው መልኩ ስላልጸደቀ በድንገት የእርቁ ደጋፊ ሆኖ ተከሰተ። መጀመሪያውኑ የምርጫ ህጉ ጉዳይ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ላይ መወያያ ሲሆን መድረሻው ዕኮ አስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም እንደ ነበረ ግልጽ ነው። እንዲህ ያለው ነገሮችን ከራስ ጥቅም አንጻር ተመልክቶ መደገፍ እና መቃወም ለቤተክርስቲያን አንድነት የሚበጅ አይደለም።
አውደ ምሕረት የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲመጣ እርቁ አማራጭ የሌለው መሆኑን ታምናለች። ለእርቅ የሚያስፈልገው ልብ በሌለበት ሁኔታም እርቁን ተግባራዊ ማድረግ ከባድ መሆኑን ትገነዘባለች። እንደ ማኅበረ ቅዱሳን አይነቱንም ከራስ ጥቅም አንጻር ነገሮችን የሚመዝን አካሄድንም ትቃወማለች። እርቁ ከተፈለገ አሁንም አልረፈደም። አባቶችም ሆኖ ክብሪት ጫሪ ወገኖች ነገሮችን እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ ለማስኬድ ለእውነተኛ እርቅ የተሸነፈ ልብ ይዞ መቅረብ ያስፈልጋል። አሁን ባለው ሁኔታ ግን እርቁን ምንም ብንመኘውም ብንፈልገውም የእርቁ የመሳካት እድል የተመናመነ መሆኑ ግልጽ ነው። ጋራ ላይ ቆሞ ማዶ ለማዶ እየተያዩ  በአየር ላይ ለመተቃቀፍ መሞከር አየር ከመዝገን የተለየ ነገር የለውም።
 

3 comments:

  1. demo menafik sile tewahedo min agebah?!

    ReplyDelete
  2. endematawotaw awkalhuna yemtsfew lante lerash new lmhonu ayiselchihm? betsaf qutir mahbrekidusann mabteltel? yematreba mahberkidusan anten lemin endetkawomeh/hasbihin/ asamreh tawqwalh betkirstiyann seltekawomh bicha new ahunmako hulum awukobhal teselcheh yihew lesint amet mahiberekidusann abteletelh gin minm teb alalehm nufakehn beandand yewuhan lay kemzrat bsteker khulu yemiyasaznew ebakih "betkirstiyanachin" eyalh atitrat bichalh band ken endtferars yemtfelgat yihch betkirstiyan yante lithon atichilm manineth eyetawoke lemin rasihn tattailaleh? anten bilo yezichin betkirstiyan andinet felagi dinkem yilkis nisha giba

    ReplyDelete
  3. gerume sehufe new

    ReplyDelete