Sunday, May 6, 2012

እጅግ በጣም ብርቱ ሚስጥር!!!


"ማኅበረ ቅዱሳን" ጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎችን መሣሪያ በማድረግ አቡነ አብርሃምን ወደ ሀዋሳ በማዛወር አቡነ ገብርኤልን የማፈናጠር የድጋፍ ዕምፅ (Petition) እያስፈረመ ነው
                                            ምንጭ፥ http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com

ሀዋሳ እና አካባቢውን እንደ ገዢ መሬት ለመቆጣጠርና ከሕዝብ የተፈጠረበትን ተቃውሞ ለማፈን ሌት ተቀን የሚፍጨረጨረው "ማኅበረ ቅዱሳን" ከጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎች ጋር በማበር አቡነ አብርሃምን ከሐረር ወደ ሀዋሳ ለማዛወርና የሕዝቡን ሰቆቃ እንዲባባስ ለማድረግ እጅግ ሚስጥራዊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ውስጡን የድጋፍ ድምፅ በማሰባሰብ ላይ መሆኑን እዚያ ያሉ የመረጃ ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡

ማኅበሩ ከከተማው ነዋሪዎች ድጋፍ ማሰባሰብ ባይችልም፣ አባላቱን በተለይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ልዩ ካምፓስ የግቢ ተማሪዎችን በማሳተፍ የሀዋሳ ምዕመናንን ጥያቄ አስመስሎ ለማቅረብ ማቀዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በቤተክርስቲያን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ራሱን የዘፈቀውና ጭራሽ ሐፍረት የሚባል ነገር ያልተፈጠረበት "ማኅበረ ቅዱሳን" ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ያለግብራቸው ግብር እያሸከመ፣ ያለ ስማቸው ስም እየሰጠ ሀገረ ስብከቱን ለቀው እንዲዛወሩ ግፊት ካደረገባቸው በኋላ፣ አቡነ ገብርኤልን በድርጅታዊ አሠራር ሀዋሳ ላይ አስመድቦ የፈላጭ ቆራጭነትን ሚና በጋራ ሲጫወቱ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የመባረር ጽዋው ወደ አቡነ ገብርኤል ዞሮ "ማኅበረ ቅዱሳን" እንዲነሱለት ውስጥ ውሰጡን ሲደግስላቸው መክረሙ ታውቋል፡፡  

Friday, May 4, 2012

አንዳንድ የማቅ አባላት የሲ. አይ. ኤ. ሰላዮች ሆነው ተገኙ


Click here to read in PDF
  • በዋናነት ቤተ ክህነት አካባቢ “የቀን መጋኛ” የሚባለው ባያብል ሙላቱ የሰጠውን መረጃ ዊኪሊክስ ይፋ አድርጓል 
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
በርካታ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ሌሎች ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው። ማኅበሩ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ በቅድሚያ ቤተክርስቲያንን ከዚያም የመንግስትን ሥልጣን ለመያዝ በግልጾቹም በስውሮቹም አመራሮች እየተደገፈ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን አባላቱ በቅጡ አልተረዱም። ቤተክርስቲያን እኛ ባንኖር ኖሮ ጠፍታ ነበር። ያለንላት እኛ ነን። ቤተክርስቲያን ሰው ስለሌላት አስራታችሁን ለማኅበረ ቅዱሳን አውጡ በማለት የሚያሰወራውን ወሬ  እና በአካፋ ተቀብሎ በማንኪያ የሚሰጠውን ስጦታ በማመን የተታለሉ ወገኖች ይገኛሉ። እውነቱን ከማህበሩ ጋር ለበርካታ አመታት በቅርብ የሰሩ ወገኖችና እንቅስቃሴውን በሙላት የተረዱ የቤተክርስቲያን ልጆች ያውቁታል።

ማኅበሩ ፖለቲካ ውስጥ ያለው ሚና እስከ ምን ድረስ እንደሆነ ብዙዎቻችን አናውቅም። መንግስት ፓለቲካው ላይ ያለውን ፍለጎት በሌላ መንገድ እንዳይጠረጥረው ከመንግስት  ጋር የመንግስት ሰው መስሎ ለመስራት ይሞክራል። ከተቃዋሚዎች ጋር ደግሞ እነርሱን መስሎ ይመላለሳል። ይህን እውነት ምርጫ 97 ላይ የማኅበሩ አመራሮች ከቅንጅት ጋር የነበራቸው ግንኙነት በቂ ማስረጃ ነው። አሁን ደግሞ እነርሱ esatን esat ደግሞ ደጀ ሰላምን እየጠቀሱ የዋልድባን ነገር ለማጮህ የሚሄዱበትን መንገድ ማስተዋል በቂ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ ማህበሩ ከውጭ አገር መንግስታትና ከሲ አይ ኤ ጋር ያለው ግንኙነት እስከ ምን ድረስ እንደሆነ አናውቅም ነበር። እድሜ ለዊኪ ሊክስ እውነታውን አውቀናል። ይህን ነገር እኛ ብንዘግበው ውሸታም ትሉን ይሆናል። ዊኪ ሊክስ ግን ነገሩን ያገኘው ከአሜሪካ መንግስት ምስጢራዊ ፋይሎች ውስጥ ነው። የአሜሪካ መንግስት ወሬ አቀባይ አድርጎ ባያብል ሙላቱ የሚባል ሰውን እንደሚጠቀም ነግሮናል።
ወሬ በማመላስና በመቅለስለስ ልዩ ችሎታ አለው የሚባለው ባያብል ባለፈው የጥቅምት ሲኖዶስ ላይ እንቅልፍ አጥቶ የማቅን አጀንዳ ለማስፈጸም አንዳንድ አባቶችን ከመግባባት አልፎ መመሪያም በመስጠት የስብሰባውን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲደክም እንደነበር ይታወቃል። አንዳንዶች ከኋላ ሆኖ የሲኖዶስን ስብሰባ ለመምራት የሚሞክር “ደፋር” ሰው ነው ይሉታል። ባያብል የቤተክርስቲያን ጉዳዮችን በሚመለከት የአሜሪካን መንግስትን በራሱ አቅጣጫ (ማኅበሩ በሚፈልገው መንገድ) ይመራው እንደነበር የዊኪ ሊክሱ ዘገባ ያስረዳል። ይህ የዲ/ን ሙሉጌታ ጽሑፍም ይህን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃዎችን ያስነብበናልና በትኩረት እናንብበው።

Wednesday, May 2, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግርና የአንድ አድርገን ዘገባዎች

Click here to read in PDF
አንድ አድርገን የተባለው የማኅበረ ቅድሳን ብሎግ በማኅበሩ “ግልገል ካድሬዎች” የሚዘጋጅ  ብሎግ ነው። ማኅበርዋ በተለመደው እናንተ ባትኖሩ ቤተክርስቲያን ትጠፋለች የሚለው አታላይና ስሜት ቀስቃሽ “ወንጌሏ” ቀልባቸውን ሰልባ ለሥራ ያነሳሳቻቸው ሕጻናተ አእምሮ አባላትዋ የማኅበረ ቅዱሳን ስውሩም ግልጹም አመራሮች የሚያዙባትና እንቅስቃሴዋን በንቃት እየተከታተሉ ከማኅበሩ የመረጃ ክፍል የሚገኙ መረጃዎችን እንደ ወረደ በግልብ ስሜት ባልታረመ ብዕር ተጽፈው የሚቀርቡባት ስድ ብሎግ ስትሆን የአጻጻፍ ስልትዋና የቋንቋ አጠቃቀምዋ ከማህበሩ ሌሎች ብሎጎች ለየት ያለ ነው።

ጸሀፊዎቹ “ሕጻናት” ስለሆኑ በአፃፃፍ ስልታቸው በማስመሰል እንኳ ሊደብቁት የሚገባቸውን ከማኅበሩ ጋር ያለቸውን ግንኙነት ለመደበቅ አልተቻላቸውም። ሕጻን መች ይደብቃል። ለማህበራቸው ማኅበረ ቅዱሳን ያላቸው አመለካካት ከጭፍን ፍቅር የመነጨና በተለይ ማኅበሩ የተወቀሰ ዕለት እሳት እንደበዛበት ሽሮ በቶሎ የሚገነፍል ነው። 

ማኅበረ ቅዱሳን ከመንግስት ጋር ያለውን የአቋም ልዩነት እንደነ ደጀ ሰላምና ገብርሄር አጠይሞ ሣይሆን በግልጽ አቋሙን የሚያሳውቅበት አንድ አድርገን፣ በውስጣቸው ያለውን ፓለቲካዊ ማንነት በግልፅ እንዲታይ ጥረት የሚያደርጉበት አንድ አርገን፣ ከዚህ ማንነታቸው በመነሳትም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ሕፃን በሆነው አእምሮአቸው ለመውቀስ ሞክረዋል ሲጀምሩም እንዲህ ነበር ያሉት። 

Tuesday, May 1, 2012

"የጥንቸል ውሃ ጥም"


ምንጭ፡- ደጀ ብርሃን
                                   በሰላማዊት አድማሱ  Selam.admassu@yahoo.com
 ከእለታት በአንዱ ቀን ዱር ገደሉን ቤታቸው ካደረጉት እንስሳቶች መካከል ትንሿ ጥንቸል ውሃ በእጅጉ ተጠማች፡፡ በማን አለብኝነት ያለስስት ጨረሯን የለቀቀችውን ጸሐይ ጥሟን ስላባሰችባት በኩርፊያ ቀና ብላ ተመለከተቻት፡፡ አጠገቧ ያለው ዙሪያዋን የከበበውም መሬት ከሰማዩ ጋር ያበረ ይመስል በእንፋሎቱ እግሯቿን ጠበሳቸው፡፡ ጥንቸሊት ተንሰፈሰፈች  . . ውሃ ጥሙ አንገበገባት  . . ከዚህ በላይ መታገስ አልቻለችም ፡፡ ያላትን አቅም ሁሉ አሰባስባ በአቅራቢያዋ ወደሚገኝ አንድ ጥልቅ ወንዝ አመራች፡፡ በዚያ በረሃ ውስጥ እያስገመገመ ከሚንዠቀዠቀው ወንዝ አጠገብ ደረሰች፡፡ ውሃውን በምላሷ እየዘገነች ወደ አፏ ከዚያም ወደ ጉሮሮዋ እየላከች ትጠጣ ጀመር፡፡ ጠጥታ  . . ጠጥታ  . . ጠጥታ ስታበቃ ካንገቷ ቀና በማለት ለጥማቷ እርካታ የቸራትን ሽንጠ ረዥም ወንዝ በምስጋና አይን አማተረችው፡፡ ከላይ እየተወረወረ ከሚመጣው ነጭ ፏፏቴ ጀምሮ በእሷ አጠገብ እስከሚያልፍ ድረስ ጠበብ ያለ ነበር፡፡ ከዚያ ትንሽ እንደተጓዘ ግን ሰፊውን ሜዳ ይዞ በጸጥታ ይጓዛል፡፡ አዎን  . . ሰፊ ነው!! . . በእሷ አቅም ለእይታዋ እስኪሰወር ከአድማስ ጥግ እስኪገባ ድረስ ሰፊ ነው፡፡ በጣም ሰፊ!፡፡ ትንሿ ጥንቸሊትም ለቃጠሎዋ ማብረጃ፤ለጥማቷ እርካታ የቸራትን ይህንን ትልቅ ወንዝ እያየች በትልቅነቱም እየተገረመች አንድ ነገር ተናገረች ‹‹ እኔ የቱንም ያህል  ውሃ ብጠማና ከዚህ ወንዝ ደጋግሜ እየተመላለስኩ የቻልኩትን ያህል በየጊዜው ብጠጣ ይህ ወንዝ አንዳችም ሊጎድልበት አይችልም ›› አለች፡፡ ስለዚህ ጥንቸሊትም ወንዙን ሁልጊዜ ለጥሟ እርካታ ውሃ ብትለምነው እንደማይነፍጋት ፤ለእሷ ቢሰጣት እንደማይጎድለበት አስባ ልቧ በኩራት ተሞላ፡፡ ለሁልጊዜውም ቢሆን የእሷ ችግር ከሱ አቅም በታች እንደሆነ አውቃ ተማመነችበት፡፡
ወገኖች ልክ እንዲሁ የአንዳንዶቻችን ችግር በእግዚአብሔር ፊት እንደ ትንሿ ጥንቸል ውሃ ጥም ነው፡፡ የእሷ ቃጠሎ  . . የእሷ በረሃ  . . በትልቁ ወንዝ ፊት ኢምንት እንደሆነ ሁሉ የእኛም ጥያቄና ችግር በእግዚአብሔር በአምላካችን ፊት ኢምንት ነው፡፡