Sunday, May 6, 2012

እጅግ በጣም ብርቱ ሚስጥር!!!


"ማኅበረ ቅዱሳን" ጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎችን መሣሪያ በማድረግ አቡነ አብርሃምን ወደ ሀዋሳ በማዛወር አቡነ ገብርኤልን የማፈናጠር የድጋፍ ዕምፅ (Petition) እያስፈረመ ነው
                                            ምንጭ፥ http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com

ሀዋሳ እና አካባቢውን እንደ ገዢ መሬት ለመቆጣጠርና ከሕዝብ የተፈጠረበትን ተቃውሞ ለማፈን ሌት ተቀን የሚፍጨረጨረው "ማኅበረ ቅዱሳን" ከጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎች ጋር በማበር አቡነ አብርሃምን ከሐረር ወደ ሀዋሳ ለማዛወርና የሕዝቡን ሰቆቃ እንዲባባስ ለማድረግ እጅግ ሚስጥራዊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ውስጡን የድጋፍ ድምፅ በማሰባሰብ ላይ መሆኑን እዚያ ያሉ የመረጃ ምንጮቻችን አመለከቱ፡፡

ማኅበሩ ከከተማው ነዋሪዎች ድጋፍ ማሰባሰብ ባይችልም፣ አባላቱን በተለይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ልዩ ካምፓስ የግቢ ተማሪዎችን በማሳተፍ የሀዋሳ ምዕመናንን ጥያቄ አስመስሎ ለማቅረብ ማቀዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በቤተክርስቲያን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ራሱን የዘፈቀውና ጭራሽ ሐፍረት የሚባል ነገር ያልተፈጠረበት "ማኅበረ ቅዱሳን" ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ያለግብራቸው ግብር እያሸከመ፣ ያለ ስማቸው ስም እየሰጠ ሀገረ ስብከቱን ለቀው እንዲዛወሩ ግፊት ካደረገባቸው በኋላ፣ አቡነ ገብርኤልን በድርጅታዊ አሠራር ሀዋሳ ላይ አስመድቦ የፈላጭ ቆራጭነትን ሚና በጋራ ሲጫወቱ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የመባረር ጽዋው ወደ አቡነ ገብርኤል ዞሮ "ማኅበረ ቅዱሳን" እንዲነሱለት ውስጥ ውሰጡን ሲደግስላቸው መክረሙ ታውቋል፡፡  

አቡነ ገብርኤል "ማኅበረ ቅዱሳን" ጋሻ ጃግሬ ከሆነው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከይትባረክ ታጠቅ ጋር ሊስማሙ ባለመቻላቸው የማኅበሩ አመራር አካላት በፊርማና ማኅተም ያሻቸውን የሚፈጽምላቸውን ምርጥ ዕቃ ለማቆየት ሲሉ አቡነ ገብርኤልን ለማባረር ሤራ መጎንጎኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በተለይም ይትባረክ ታጠቅ "ሊቀጳጳሱ የምሽረውን እየሾሙ፣ ያባረርኩትን እየመለሱ፣ የገነባሁትን እያፈረሱ ስላስቸገሩኝ ሥራዬን ለቅቄ የትም እደርሳለሁ" ብሎ በቁጭት ሲያለቅስ "ማኅበረ ቅዱሳን" ቡችሎች በበኩላቸው፣ "አቡነ ገብርኤል ይነሷታል እንጂ እርስዎ የትም አይሄዱብንም" ብለው እንደተማጸኗቸው መዘገባችን ጭምር አይዘነጋም፡፡

አቡነ ገብርኤል እየፈጸሙ ካሉት ከሲኖዶስ ያፈነገጠ ድርጊትና በሀዋሳ ሕዝብ ላይ እያሳደሩ ካሉት ግፍና ጫና አንፃር ዞሮ ዞሮ ከአካባቢው እንደሚነሱ ያመነው "ማኅበረ ቅዱሳን" "ማኅበሩ" ንክኪ ነፃ የሆነ ሊቀጳጳስ በቦታው እንዳይመደብ ለማድረግና ምሽጉን ላለመልቀቅ ሲል ቀንደኛውን "ማኅበረ ቅዱሳን" ሊቀጳጳስ አቡነ አብርሃምን ለማዛወር ከመጋረጃ ጀርባ እየተሯሯጠ መሆኑ ታውቋል፡፡

ታዛቢዎች እንደሚሉት፣ ለሀዋሳ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ማንም ሄደ፣ ማንም ተነሳ እዚያ የሚመደበው ሊቀጳጳስ አፍቃሬ "ማኅበረ ቅዱሳን" እስከሆነ ድረስ ሀዋሳ ላይ ሠላም እንደታጣ፣ ግጭቱ እንደቀጠለ መሄዱ አይቀርም፡፡ በተለይም፣ ምንም እንኳን የአቡነ አብርሃም ከሐረር መነሳት ለሐረሮች እፎይታ የሚሰጥ ቢሆንም፣ ሊቀጳጳሱ ካላቸው "ማኅበረ ቅዱሳን" ፍቅርና ለፓትርያርኩ አልታዘዝ ባይነት ባህርያቸው የተነሳ፣ የሀዋሳን ግጭት ቢያባብሱት እንጂ አንዳች የሠላም ውጤት እንደማያስገኙ ይታወቃል፡፡

የሀዋሳ ችግር የሚፈታው ሊቃነጳጳሳትን በመለዋወጥ ብቻ ሳይሆን "ማኅበረ ቅዱሳን" በቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ፍፁም ማስወገድና፣ በሀዋሳ እና በሌሎች የሀገረ ስብከቱ ክፍሎች በሚገኙ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የሰበካ ጉባዔና ልዩ ልዩ አገልግሎት ክፍሎች የተዋቀሩ ኮሚቴዎችን "ማኅበረ ቅዱሳን" ነፃ ማድረግ መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል፡፡

በአሁኑ ጊዜ "ማኅበረ ቅዱሳን" በጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎች ጀርባ ታዝሎ በሀዋሳ የሚገኙ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን መዋቅር ከላይ እስከታች ሰቅዞ መያዙን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚህም የተነሳ አንድ ነጋዴ ከቃለ ዐዋዲው ውጪ በየአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ ሦስትና አራት ሰበካ ጉባዔና ልማት ኮሚቴ ውስጥ እጁን በመንከር አላስወጣ አላስገባ በማለት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

በመንበረ ጵጵስናው የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አንድ ባለአራት ፎቅ የልማት ሕንፃ ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ ለሰባት ዓመታት ያህል ተገትሮ የቆየ ሲሆን አሁን ደግሞ ጭራሹን የግንባታ ዝመት ታይቶበታል ተብሎ የወደፊት ዕጣ ፈንታው በቅጡ ሊታወቅ አልቻለም፡፡ ከዚህም በላይ ጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎች የልማት ሕንፃው ኮሚቴ ነን በሚል ራሳቸው አሠሪ፣ ራሳቸው የጥሬ ዕቃ አቅራቢ በመሆን ያለጨረታ የሕዝብና የቤተክርስቲያንን ሀብት በማንአለብኝነት ሲያባክኑ የኖሩ ከመሆናቸውም በላይ ለሰባት ዓመታት የፋይናንስና የፊዚካል ሥራው ኦዲት እንዳይደረግ በመከላከል እስካሁን መቆየታቸው ታውቋል፡፡

በኪራይ ሰብሳቢዎቹ ነጋዴዎች ላይ ሥራው ኦዲት እንዳይደረግና በሌብነት ስማቸው እንዳይጠፋ አቡነ ገብርኤል ሽፋን ሰጥተዋቸው የነበረ ሲሆን፣ እነዚሁ ጉዶች የተደረገላቸውን ውለታ ረስተው ይዞታቸውን ለማጠናከርና ፍጹም አስተማማኝ ለማድረግ "ጠፍር በሊታው" አቡነ ገብርኤልን "Use and Throw" (ተጠቅሞ መጣል) ፍልስፍና ሊያሰናብቷቸውና ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ጋር ሊጣጣሙና አብረው ሊሄዱ የሚችሉትን "ልጓም በሊታው" አቡነ አብርሃምን ወደ ሀዋሳ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን፣ ሰሞኑን በሚካሄደው የግንቦት 2004 የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ በአፍቃሬ "ማኅበረ ቅዱሳን" ሊቃነጳጳሳት በኩል በአጀንዳነት አስርጎ በማስገባት ለማስመደብ ዕቅድ ተይዟል፡፡ 

የነገር ክፋት እንጂ የአካሄድ ስልት ብልህነት የሌላቸው አቡነ ገብርኤል የተደገሰላቸውን ይወቁትም አይወቁትም መነሳታቸው የማይቀር ይመስላል፡፡ ቀጣዩ "ማኅበረ ቅዱሳን" ድራማም ለአቡነ ገብርኤል ዕንባ የሚያራጭ አሸኛኘት ፕሮግራም በማዘጋጀት ለአቡነ አብርሃም ቅኔ መወድሱን በማዥጎደጎድ ሚስጥራዊ ሥራውን ማከናወን ነው፡፡

ማን ያውቃል አቡነ አብርሃምም ያፈነገጡ ዕለት ተረኛ ሆነው ሌላ ይተካባቸው ይሆናል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደዚህ እጅ መስጠታቸውና እንደባትሪ ድንጋይ "ማኅበረ ቅዱሳን" ፍላጎት መቀያየራቸው፣ የቱን ያህል እንደተዋረዱና የእግዚአብሔርን ክብር ማቃለላቸውን መረዳት ይቻላል፡፡

አቡነ ገብርኤል ተቃውሞ የገጠማቸው "ማኅበረ ቅዱሳን" ከኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎች ብቻ ሳይሆን ከጎንደሬዎቹ ካህናት ጭምር ነው፡፡ የጎንደሬዎቹን ተቃዉሞ የሚያስተባብረው ሄኖክ የተባለ የአብነት /ቤት ምሩቅ ሲሆን የገዳሙ አስተዳዳሪም አባ ፍቅረ ማርያምም ውስጥ ውስጡን ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት /ቤት በመሄድ አቡነ ገብርኤል ስለሚነሱበት ሁኔታ እና በምትካቸው ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ስለሚመደቡበት ሁኔታ ሲያደራጅ መክረሙን ውስጥ ዐዋቂ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ሄኖክ አቡነ ገብርኤልን የጠመደበት ምክንያትም በሀዋሳ የጎንደር ተወላጆች ስም መንፈሳዊ ጉባዔ እናዘጋጅ ብሎ ሲጠይቅ አቡነ ገብርኤል "በዘር ተደራጅቶ መንፈሳዊ ጉባዔ መጥራት ለምን አስፈለገ? ይህ ትክክል አይደለም" ብለው ስለመለሱት እና ከወንጌል ፈጽሞ በራቀ የተረታ ተረት የስብከት ዝንባሌው አለመደሰታቸውን በማወቁ እንደሆነ በቅርብ የሚያውቁት ይመሰክራሉ፡፡

"ማኅበረ ቅዱሳን" ልምድ እንደሚያሳየው፣ ይህች የዘር ነገር አቡነ ገብርኤልን(ወሎዬ ናቸው) ለማጥቂያ ስልት ይጠቀሙባት እንጂ፣ ነገ ደግሞ ሌላ ምክንያት ፈልገው ከመወንጀል እንደማይመለሱ ነው፡፡ ሄኖክ ዛሬ "ማኅበረ ቅዱሳን" መሣሪያ ሆኖ  ጳጳሱን ለመቃወም ቀዳሚውን ሥፍራ ቢይዝም፣ አቡነ ገብርኤል በኪራይ ሰብሳቢ ነጋዴዎችና "ማኅበረ ቅዱሳን" ጀርባ ታዝለው ወደ ሀዋሳ ሲሄዱም ቀዳሚውን ሥፍራ ወስዶ "ለገብርኤል ገብርኤል መጣለት፤ ያውም ዶክቶር" በማለት በግዕዝና በአማርኛ ቅኔ መወድስ በማቅረብ የቀደመው አልነበረም፡፡

በሌላ በኩል አቡነ ገብርኤል የካህናቱ አካሄድ ስላልጣማቸው "ይህችን ግንቦት ልለፍ እንጂ ሁሉንም ልክ አስገባለሁ" ማለታቸውን የሰሙ የቅርብ ሰዎች እንደሚሉት፣ የአቡነ ገብርኤል እንደዚህ በጥላቻ መከበብ ሚስጥሩ በጥቅምና ሥልጣን ክፍፍል ዙሪያ አለመግባባትና የቤተክርስቲያንን ሥርዓት የመጣስ ልምምድና ማኅበረ ቅዱሳን-ሠራሽ አዲስ ባህል ያመጣው ጦስ ነው፡፡

አቤቱ ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ!!!
ምሕረትህ፣ ቸርነትህና ጥበቃህ ከእኛ አይለይ!!!
አሜን!!!

8 comments:

  1. አረ መቅ ተወን ይህ የታሊባን መንፈስ እኮ አስቸገረን

    ReplyDelete
  2. mk ksera weche yemetehonewe meche new? are neseha gebuna temelesu

    ReplyDelete
  3. ማህበረ ቅዱሳን 20ኛ አመቱን ሊያከብር ነው! ይገርማል!
    1 ሰውን በመክሰስ
    2 መነኮሳትን በማሳደድ
    3 ቤተክርስቲያንን በመዝረፍ
    4 ኢየሱሳውያንን በመግደል
    5 ወንጌልን በማጣመም
    6 አገርን በመካድ
    ስንቱ ተነግሮ! አመተ ምህረት የሌላቸው አመተ አለምን የሚቆጥሩ የተዋህዶ ጀግኖች!ኢየሱስን የሚያውቁ ነገርግን ኢየሱስ የሌላቸው! የሚያከብሩት የ እድሜ ዘመን ከላይ ወደታች እንዲዎርድላቸው አደራ እላለሁ! ከአሁን በኋላ የማቅ አባልነቴን በገዛ ፈቃዴ ልቅቂያሉ! ግልባጭ ለአውደ ምህረት

    ReplyDelete
    Replies
    1. http://www.facebook.com/birhan.bihil/posts/309317349143150?notif_t=close_friend_activity

      Delete
    2. ANTE YE MK ABAL STIHO YEDABILKOS ENA YEHADISO KITREGNA NEH. YEMATAWKNE ATIKABATIR.

      Delete
  4. let devil talks & dreams much and MK works with the help of god

    ReplyDelete
  5. YEBETKIRISTIYAN ENA YEKIRISTOS TELATOCH SILIHONACHU MELKAM ATASIBUM ATAWERUM KENANT BELAY MIN KESSASH AFERRASH LEHAGER SAYEKER TELATOCHE AYEDELACJHUM ENDA?

    ReplyDelete
    Replies
    1. enante bianse enkuane ende menfesawi asebu enji yehulume alama mengistuene meures new!!!!!!!!!!! enante gin lemin teragemalachehu yehe hatiat new nesha gebu amlak yerdachehu amen!!!!!!!!!!!

      Delete