Thursday, June 21, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን አመራር አባላት ማኅበሩን እየለቀቁ ነው፡፡

Click Here to Read in PDF
ከይሔ ነው እውነቱ
ሲመሰረት የነበረውን ውጫዊ አላማ አድንቀው እና ወደው ቤተክርስቲያኒቱን በተደራጀና በተጠና መንገድ ለማገልገል የፈለጉ አንዳንድ የዩኒቨርስቲ ምሩቃንና “በጎ” ዓላማውን የደገፉ ግለሰቦች ማኅበሩን ቀረብ ብለው ሲያዩት እና ውስጣዊ አላማውን ሲረዱ እንደ ድቡልቡል አለት ተገትሮ ለመጨበጥ የማይቻል መሆኑን በመረዳታቸው ተራ በተራ እየለቀቁት መሆኑ ተሰማ። እነዚሁ ከአባልነት እስከ ከፍተኛ አመራር ሰጪነት የደረሱ የስራ አመራር አባላት ለማህበሩ የወገብ ትጥቅ ሆነውለት በከፍተኛ ደረጃ ሌሎች  አባላት የሚመኩባቸው የነበሩ ቢሆንም ለራሳቸው በገባቸው የማህበሩ ከፋፋይ አጀንዳ ዕጣ ለእነርሱም ወጥቶ ሊሰሩ የፈለጉትን ሥራ በአግባቡ ለመስራት ባለመቻላቸው ምክንያት ማኅበሩን ለመልቀቅ ወስነው የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል።
በእግዚአብሔር ሀሳብ ቀዳሚ የሆነውን አህዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እያጠመቃችሁ ደቀ መዛሙርት  አድርጉአቸው የሚለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልዕኮ ቸል ብሎ ወንጭፍ ወርዋሪ አገልግሎት ላይ ራሱን የጠመደው ማኅበረ ቅዱሳን ራሱን ጠልፎ የሚጥል እንቅስቃሴ ከጀመረ ሰንብቷል። ከቤተክርስቲያን የአገልግሎት ራዕይ መቀበል ሲገባቸው ያልሰከነ ስሜታቸውን አጀንዳ በማድረግ ግለሰብ ተኮር እንቅስቃሴ በማድረግ ደግመው እንኳን ሊያጣሩት የማይፈልጉትን ጥርቅምቃሞ ወሬ ማስረጃ ብለው በመያዝ እንደ አበደ ውሻ እየተክለፈለፉ ያሉት የማህበሩ ሰዎች ውድቀታቸውን በሚያፋጥን እንቅስቃሴ መጠመዳቸው እያስተዛዘበ ይገኛል። በዚህ ግለሰብ ተኮር እንቅስቃሴ ከየት እንደሚነፍስ የማይታወቅ ነፋስ አባላቱን ተረጋግተው የተሰበሰቡለትን ዓላማ ተፈጻሚ እንዳያደርጉ አጀንዳ በመስጠት ከቤተክርስቲያኒቱ አባቶችና ከፖለቲካው ጋር እያላተማቸው ነው፡፡ በዚህ ግጭት መካከል የራሳቸውን አጀንዳ የሚያስፈጽሙ ጆቢራዎች ግን በሌላው ቁስል ኑሮቸውን እያስተካከሉ አላማቸውን እያስፈጸሙ ይገኛሉ፡፡

ይህን ስውር ፖለቲካና ዘረኝነት የተላበሰ አካሄድ ያልተዋጠላቸው የተቀየጠብን እንክርዳድ ይለይ ማህበራችን ውበቱ መንፈሳዊነቱ ነው በማለታቸው ሆዳቸው አምላካቸው የሆነና የአካሄድ ብስለት የሌላቸው ባለሥውር አጀንዳዎቹ አመራሮች የተመቻቸውን ስም በመስጠት መልቀቂያ ያስገቡ አባላትን  ከማህበሩ የማይጠበቅ ጸያፍ ደብዳቤ በመጻፍ እያባረሩ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ ሰዎች ለማኅበሩ ህልውና ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ እና አስከ ቅርብ ጊዜም እየከፈሉ የነበረ ሲሆን በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያየኝን ያስነክሰኝ የሚል “ጸሎት” እያደረሱ ከቤታቸው የሚወጡት አመራሮች በሁሉ አቅጣጫ ከመንግስት እስከ ግለሰብ ድረስ ለማጥቃት በዘረጉት አካሄድ ማኅበሩ ከሁሉ ጋር እየተናከሰ ስላስቸገረ ምን እየሰራን ነው? የተነሳንበት አላማ ይሄ ነው ወይ? ሰው የማኅበረ ቅዱሳን አባል ሳይሆን መኖር አይችልም ወይ? ምንፍቅናና ቅድስና ማኅበረ ቅዱሳንን ከመውደድና ከመጥላት ጋር ለምን ይያያዛል? ለምን እውነተኛ አጀንዳ እውነተኛ ፍረጃ እውነተኛ አካሄድ አይኖረንም? የሚል ጥያቄዎች ከአመራር አባላቱና ከስራ አስፈጻሚ አባላቱ መካከል እየተነሳና ድምጹም ጎልቶ መሰማት በመጀመሩ በተለመደው ስም ማጥፋትና ፊት መንሳት አካሄድ የተከተለው ማኅበርን የለም አያዋጣም ብለው ፊት ለፊት የተጋፈጡት ሰዎች እየተንገዋለሉ እንዲቀሩ ተደርገዋል። ከነዚህም መካካል
1.     ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ የትምህርት ክፍልና የዋና ማዕከል ሥራ አመራር(የማኅበሩ ቁጥር አንድ ሰባኪ ወንጌል የነበረና ከዩንቨርሲቲ ተማሪነቱ ጀምሮ ማታ ማታ ባዶ ክፍል እየፈለገ ተማሪዎችን ሰብስቦ በማስተማር የሚታወቅ። ከማኅበሩ ከወጣም በኃላ ብዙ ጊዜውን ለአገልግሎት ሰጥቶ በቦሌ መድሀኒዓለም ቤተክርስቲያን ከህጻናት እስከ አዋቂ በተለያየ መርሐ ግብር እያስተማረ ያለ። በቅርቡም ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ትምህርቱን ጨርሶ የተመረቀ።)
2.    መንግስቱ ጎበዜ የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር
3.    ዲ/ን በለጠ አምስት ኪሎ ሌክቸረር የአዲስ አበባ ማዕከል ዋና ጸሐፊ
4.    አስራት ከበደ የማህበሩ መጽሔትና ጋዜጣ አዘጋጅ
5.    አሉላ ጥላሁን የማህበሩ መጽሔትና ጋዜጣ አዘጋጅ(አይታክቴ በሚል ስም በወዳጆቹ መካከል የሚታወቀው አሉላ አቋምም ዝግጁነትም አለው የሚባል ሰው ነው። አዲስ ነገር ጋዜጣ በነበረበት ጊዜም ጭምር የጀመረውን ሥራ ሳይፈጽም እንቅልፍ የማይነካካው ሰው እንደሆነ ይነገርለታል። ለስነጽሁፍ ባለው ዝንባሌ ከሐመር መጽሄት ምክትል ዋና አዘጋጅነት እስከ ሕገ ወጦቹ የማኅበሩ ብሎጎች እስከ ሕጋዊዎቹ ብሎጎችና የህትመት ሚዲያ ውጤቶች ድረስ በኃላፊነትና በተቆጣጣሪነት  እና በጹሁፍ አቅራቢነት ሰርቷል።)
6.    ሂሩት የገዳማትና አብነት መምህራትን መርጃ ዳይሬክቶር
7.    መንግስቱ ገ/ዮሐንስ የልማትና ተቋማት ዳይሬክቶር
8.    ዲ/ን ዳንኤል ተስፋዬ ከሙሉጌታ ኃ/ማርያም በፊት ዋና ጸሐፊ የነበረ
9.    ዶ/ር ያየህ የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶር (ከመንግስቱ ጎበዙ በፊት የነበረ)
10.  መድሀኒት ዘዋለ የመለከት መጽሔት ዋና አዘጋጅ
11.    ቅድስት ማሙሻ የኤፍሬም እሼቴ የብዙ ግዜ እጮኛ የነበረች እና የማህበሩ ከፍተኛ አመራር
12.    ዳንኤል ክብረት ለብዙ ዘመናት ዋና ጸሐፊ(በአንድ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ዳንኤል ነው እስኪባል ድረስ ከፍተኛ ተቀባይነትና ዝና የነበረው ሰው ነው። ዳንኤል በሥራው አይለግምም። በተንኮሉም አይለግምም። ሁሌም በማግባባት ሰዎች ወደ ሀሳቡ አንዲመጡ ከማድረግ ወደ ኃላ የማይል ሰው ነው። የተቃወሙትን ሰዎች ደግሞ ጥርሱን እያሳየ ቀስ ብሎ አፍር በማስላት ታዋቂ ነው። ሰዎችን በማግባባት ጎበዝ ስለሆነም አንዱን ሲያጠቃ የሚያጠቃውን ሰው የልብ ወዳጅ ሳያስበው መሳሪያ ያደርገዋል። አርሱ ብቻ በገባው መንገድ የልብ ወዳጆቹ እርስ በራስ ተቀዋሚ ይሆናሉ። ስለዚህ ማንም ሰው ዳንኤል ነው ይህን ያደረገው ብሎ አይጠረጥረውም። ማሕበሩን ከሩቅ ሆኜ መቆጣጠር እችላለሁ ብሎ ያመነው ዳንኤል ከማኅበሩ ራቅ ብሎ የግል ሥራውን እየሰራ ማኅበሩን በራሱ አቅጣጫ ማስኬዱ ተሳክቶለት የነበረ ሲሆን ዋና ጸሐፊነቱን ሙሉጌታ ከያዘው በኃላ ግን በማኅበሩ ውስጥ የነበረው የቀድሞ ግርማው ተገፏል። ባለፈው አመት ከሙሉጌታ ጋር የነበረው ቁርሾ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ታይቷል። እርቅ ከተባለም በኋላ እርቁ ለይምሰል ስለነበር ቁርሾው እንደቀጠለ ሲሆን፣ ሙሉጌታም ዳንኤል ቀርታው የነበረውን ብጣቂ ተቀባይነት ተሟጣ ከማኅበሩ እንድትጠፋ አጥጋቢ ሥራ ሠርቷል። አሁን ከአዲስ አበባው አመራር ጋር ሙሉ በሙሉ ሥራ መሰራት እንደማይችል ተረድቶ ፊቱን ወደ አሜሪካ አዙሯል።)
እነዚህ ከላይ የዘረዘርናቸው የማኅበሩ የቀድሞ አመራር አባላት ማኅበሩን ሲያግዙና መንፈሳዊ አገልግሎትን ሲያጠናክሩ ከቆዩ በኋላ ማህበሩ ሃይማኖታዊ ፋይዳውን እያጣ ፖለቲካዊ አጀንዳው እየጎለበተ በግልጥ ሥራ ሲጀምር ከኑግ የተገኘ ሰሊጥ ከመሆን ብለው ለቀው ወጥተዋል፡፡ እነኚህ የቀድሞ አመራር አባላት አሁን ያሉትን አመራሮች ቢመክሯቸውና ቢያስመክሯቸው ከዓላማቸው ፈቀቅ ማለት አለመፈለጋቸውን ተረድተውና ኦርቶ-ሰለፊያ አራማጆችን ትተው የእግራቸውን ትቢያ አራግፈው ከማኅበሩ ወጥተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአሜሪካው እና በአዲስ አበባው አመራር መካከል ግልጽ ልዩነት እየታየ የመጣ ሲሆን እሱን የሚያክም ጠፍቶ ልዩነቱ ከቀን ወደ ቀን እየሰፋ ይገኛል።
ማኅበሩ ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም እንደሚባለው ያለበትን ስህተት አርሞ የተሰጠውን እድል ተጠቅሞ አቅጣጫውን አስተካክሎ ለመጓዝ ፈቃደኛ አለመሆኑ ብዙዎቹን አስገርሟል፡፡ የፖለቲካውን ካባውን አውልቆ በእግዚአብሔር የተመሰረተችን ሐዋርያዊትና ጥንታዊት ቤተክርስቲያንን በቅንነት አባቶች ባስቀመጡለት መመሪያ መሠረት መመራት ሲገባው ፈቃደኛ አለመሆኑ ከአፈርኩኝ አይመልሰኝ አካሄድ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ሁሉን በእነርሱ ቅኝት መቃኘትና የአባልነት መታወቂያ የሌለውን ኢ-ኦርቶዶክሳዊ እያሉ የራስን ጡንቻ ማፈርጠም ውሎ ሲያድር እንደጎልያድ የሀፍረት ሸማ ለመከናነብ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡ አሁን አሁን አባላቱ “የማኅበረ ቅዱሳን አባል ያልሆነ ሰው ሁሉ ተሃድሶ ነው ጸረ ቤተክርስቲያን ነው።” በማለት በድፍረት መናገር በመጀመራቸው አላማቸው ምን እንደሆነ በግልጽ እያሳየ መጥቷል። የማኅበሩ አካሄድም በውሃ አልረሰርስ ብሎ የደነደነ ልብ በመዶሻ መድቀቁ አይቀሬ መሆኑን ያመላከተ ነው።
የለቀቁት አመራር አባላት ችግሩን በውስጥ ሆነው ለማስተካከል ቢሞክሩም በአንዳንድ ከእኛ በላይ ለአሳር ባይ ነውጠኛ አመራር አካላት ከፍተኛ ጫና ስለደረሰባቸው ውጥናቸውን ተፈጻሚ መሆን አልቻለም፡፡ ይሁን እንጂ በውስጥ ካሉ የማህበሩን አካሄድ ከሚቃወሙ የሀሳብ ተጋሪዎቻቸው ጋር በመሆን ማኅበሩ ስውር ካባውን እንዲያወልቅ በቅንጅት በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በጭፍን ማኅበሩን እየደገፍን ያለን አባላትና ግለሰቦች  እየተቃወምነው ያለነው በሐዋርያትና በነቢያት ደም የተመሠረተውን እውነታ መሆኑን አጢነን ፍጻሜው እንዳይጠፋብን ዛሬ ተብሎ በተጠራበት እለት ነቅተን የአንዲት ቤተክርስቲያን ማኅበር አባላትን እንድንሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ ሐዋርያት ያቆዩሉን አንዲት ማኅበር ይህቺውም ሁላችንም በውስጧ ልንጠለልባት የሚገባ ሁሉን አቀፍ የሆነች የግለሰብን አላማ ሳይሆን የመሰረታትን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አላማ የምታራምድ በሁሉ ስለሁሉ የሆነች የሐዋርያት ማኅበር ነች፡፡  
ማኅበሩ በገጠር ያሉ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን አስከፈረታለሁ፣ የአብነት ት/ቤቶችን እረዳለሁ፣ ገዳማትን እደጉማለሁ ቢልም የባለፉት ሀያ አመታት ነባራዊ ውጤት ግን የምዕመናን ቁጥር መቀነስ፣ የመቻቻል መንፈስ መበረዝ፣ ጎጠኝነት እና ዘረኝነት መንሰራፋት፣ እድሜ ጠገብ ቅርሶች መዘረፍ፣ የአብነት ተማሪዎች መበተን እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ ነው፡፡
መቼም በተጠና ሁኔታ የቤተክርስቲያኑቱን ችግር እቀርፋለሁ ብሎ ፕሮጀክት ቀርጾ ገንዘብ በመሰብሰብ ወደር ያልተገኘለት ማኅበር የሰበሰበው ገንዘብ ለታቀደለት አላማ አለማዋሉን የሚያረጋግጥልን እውነታም የማኅበሩ አካሔድ ችግር ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ አንዳንድ የማኅበሩ አመራር አባላት ምንም እለታዊ ሆነ ወርሀዊ የገንዘብ ምንጭ ሳይኖራቸው በአዲስ አበባ ከፍተኛ ቦታዎች ባለሁለት ፎቅ መኖሪያ ቤት ማሰራታቸው የገንዘብ መና ከሰማይ ወርዶላቸውም አይመስለንም፡፡
ስለሆነም ምዕመናን በጎነቱ ብቻ እየታያችሁ የምትለግሱት ገንዘብ ለታቀደለት ዓላማ አለመዋሉን እንድታጤኑ እያሳሰብን በሃይማኖት ስም የሚፈጸመውን የተደራጀ ዘረፋ ሁላችንም ባለንበት አጥቢያ ልንቃወመው ልናስቆመው ስለሚገባ ይህንኑ ተግባራዊ እንድናደርግ በቤተክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
  

28 comments:

  1. እግዚአብሔር ይባረካችሁ ዐውደ ምህረቶች የወቅቱን የማቅ እንቅስቃሴ ወደ በዶነት እየተሻጋገረ መሆኑን በግልጽ ይፋ እያደረገ ያለውን ሁኔታ የሚያሳየውን መረጃ በማቅረባችሁ እግዚአብሄር ይሰጣችሁ።ድሮ የአንድ ወግን የጨለማ ወሬ ነበር የሚነሰማው አሁን ግን እግዚአብሔር የራሱ የሆኑትን በወቅቱ ያስነሳቸዋል። እዉነት መናገር በጠፋበት በዚህ በእኛ ዘመን እንድህ የተደበቀውን እውነት በአደባባይ በማውጣራችሁና እያንዳንዱ የማቅ የጥፋት ድብቅ ዓላማ በማጋለጣችሁ ከልብ እንኮራባችሁዋልን። በርቱ የእውነት አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንና ህዝቧን ይጠብቅልን።
    አንድነት ከአሜሪካ

    ReplyDelete
  2. Wushet Hatiyat mehonun satawuku sile kiristina mawuratachihu betam yigermal !! MK wede 100,000 yemitega hulemenachewun lebetekiristianuwa yesetu ewunetegna yetewahido lijoch abalat yalew new. 10-20 sew eyeterachihu gizeyachihun atatifu.Degmom enezih sewoch tamagn yetewahido lijoch nachew ! yetim bihonu yebetekiristian guday yasasibachewal.Ende enante hodachewun ayaskedimum.Ye genzeb zerefa lalkew gin abune paulos ena tehadisowochin bititeyikachew bedenbi yinegruhal.Man yebetekiristianuwa ewunetegna lijoch endehonu alem bemulu yawukewal !! Hulum eskiley dires EGZIHABIHERIN metebek new.TEWAHIDO enkuan yihichin Ahamed Gragn ena Yodit Guditim alfalech !!

    ReplyDelete
    Replies
    1. የማህበሩ ዋና ጸሀፊ አባላቶቼ 20000 ናቸው ብሎ ለዕንቁ መጽሔት መግለጫ ሰጥቷል። አንተ ወጥ ቤቴ ምን ቤት ነኝ ብለህ ነው መቶ ሺህ ነን የምትለው? ህልምህን ዝም ብለህ አታውራ

      Delete
    2. yes with 100,000 evil idea MK member

      Delete
    3. yes with 100,000 evil's

      Delete
  3. keep on dreaming, we know what MK is doing. members, if they want, they can leave the association, we can deploy others, there are 80,000 members, still the number is increasing. any body who feel discomfort can go out ( 'medawum yaw fresum yaw' ). thanks for their long service, BUT NEW BLOODS WILL JOIN MK ,DONT'T BOTHER!!!!

    ReplyDelete
  4. በጣም ያሳዝናል፡፡ የተጠቀሰው ከእውነታው ውጭ ነው፡፡ ሁሉም የአገልግሎት ክፍሎች በአንድ ሰው ሁሌ መመራት አለበት ብላችሁ ማመናችሁ ስህተት ነው፡፡ ከዚህ በፊት አዳዲስ አካላት የሉም ዛሬ ደግሞ አዲስ ሰው ለምን ብሎ መጠየቅ ራሱ ለምን ብሎ ሌላ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ እንደሚታወቀው አብዛኛው አገልጋይ ቋሚ ሠራተኛ ሳይሆን ካለው ሥራ ጨምሮ በትርፍ ሰዓት የሚያገለግል ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም በተሰጠው ጊዜ ያገለግላል፣ አዲስ ትውልድ ሲመጣ አዲሱ ይተካል፣ … ይቀጥላል፡፡ ለምን አዲስ ሰው ተመረጠ ማለት ስህተት ነው፡፡ ምነው ሰንበት ት/ቤት ተምራችሁ አላለፋችሁም? የሰበካ ጉባኤ አባል አይደላችሁም? ለምንድነው በየዓመቱ የሚመረጠው? እናንተም ሁሌ እኛ/እነከሌ ካልሰራነው/ካልሰሩት ወጡ አይጣፍጥም ዓይነት አስተያየት ትሰጣላችሁ… ይሔ ነው እውነቱ! ኪኪኪኪኪ

    ReplyDelete
  5. በእርተግጥ ማህበረ ቅዱሳን ችግር የለበትም አይባል ዘር ብዙ ችግሮች አሉበት ሆኖም እንዚህ ችግሮች ከተቀረፉ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ መኖሩ ይጠቅማል የማህሩ አባላት መልቀቅ ከጀመሩ ቆይተዋል እነዚህ ስማቸው የተጠቀሱት ሰዎች በራሳቸው ገፍተው የገቡባቸው ታላላቅና ማስተዋል ያለባቸው ልጆች ብዙ ናቸው የቀደሙት አባላት ሲሰባሰቡ በሰበካ ጉባኤው ውስጥ ተደራጅተው በየሰንት ትምህርት ቤት ውስጥ ገብተው ሊያገለግሉ ቃል ገብተው ነው የጀመሩት ለዚህም የሞሪቾ ሚካኤል/ብላቴ/ ምስክር ነው የቀደሙት የራሳቸውን ሥራ እየሰሩ የሚራዱ የነበሩ ሲሆን ያሁኖቹ እንጀራቸውንም እዚያው ያደረጉ ናቸው ጠቀም ያለ ደሞዝም ይከፈላቸዋል ስለዚህም የሚሟገቱት ስለ ቤተ ክርስቲያን ፍቅርና ስለ ማህበሩ አላማ ሳይሆን ስለ ደሞዛቸውም ጭምር ነው ይሄ መስተካከል ያለበት ይመስለኛል ጥሎ መሄድም ተገቢ አይደለም የሚያውቁትን ነግሮ አሳምኖ የመፍትሄ ሃሳብ ለሚያፈላልግ አካል ጠቁሞ እንጂ ዝም ብሎ መልቀቅ ሀይማተኛ ነኝ ወይም ሀቀኛ ነኝ አያሰኝም ይልቁንም የለቀቁበት ሀሳብ ጸሐፊው ከላይ እንደገለጠው እውነት ከሆነ ቤተ ክርስቲያንን ለከፋ አደጋ በመጣል ተጠያቂዎቹ ያሉት ሳይሆኑ የለቀቁት ናቸው ባይ ነኝ

    ReplyDelete
  6. "yeMaygelet yetekedene yeMaytawok yetesewore yelem"

    gena bizu enayalen, YeEwunet amilak leHulum gize alew+++

    ReplyDelete
  7. ማ/ቅ እየተፈረካከሰ እዚህ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ ከክፉ ጠባቂዎቹ ከተባሉለት ጠንቋዮች እነ መርጌታ ደጉ ዓለም የት ሄደው ነው፡፡ ለማ/ቅ ብለው መንፈሳዊ ኮሌጅ ውስጥ ራቁታቸውን ሲዞሩ ማደራቸውን ተውት እንዴ?

    ReplyDelete
    Replies
    1. ante balege neh pls be the truth disciple.

      Delete
  8. zeme belachehu lefelefu mahiber kidusan mecham behone kalebete bota nekeneke yemale lebetekeresetiyanachen yemiyasefelege enkuachen new rejime edema yestelene enanete wergnoch megebiya setatu taweralachehu. maneme yemisemachehu yeleme mekeneyatum wushetam selehonachehu.

    ReplyDelete
  9. እነሱ ለቀቁ አለቀቁ ምን ያመጣል ብለህ ነው?ዋናው መልቀቅ ያለበት መንፈሱ ነው!!የትኛው መንፈስ ብቻ እንዳትለኝ እንጂ የክፉው መንፈስ ነዋ!ይህን መንፈስ እጃቸውን እየጫኑ እያስተላለፉ ነው እኮ!ለነገሩ መሰነጣጠቅ ከጀመረ ቆይቷል እኮ ታስታውሳላችሁ እነዚያ የሎስአንጀለስ አሜሪካ ያሉት ጀግኖች ዳንኤልን ክብረት ቀልቡን ገፍው ካባረሩት በኋላ እኮ ነው የመጀመሪያው ምት ያረፈበት ይመስለኛል!ከዚያ በኋላማ ምኑን ልግለጽልህ የብዙ የማቅ አባላት ዓይን ተከፈተ!!አሁን ቢቸግራቸው ወደ መንግሥት አካላትም ዘመቱና ለሥራችን ይጠቅሙናል የሚሉትን ወደ ወጥመድ አስገቧቸው ግን የማያዋጣ ነገር ሆነ!ሰለፊያ ሆነው ተገኙ የክርስቲያኑ ሰለፊያ እንዳንላቸው ክርስቲያኖች አይደሉም ታዲያ ምንድናቸ ኧረ እባካችሁ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ በሏቸው ይሰሟችሁ እንደሆነ ሀገሪቱ እንኳን ለክርስቲያኑ ለሌሎችም እምነት ነዋሪዎች የተፈቀደች ናት የሚሻላችሁ በሰላም መደራደር ነው እምቢ ብትሉ እንኳን ለሀገራችን ህዝብ ለዓለም መሳቂያ እንዳትሆኑ!የሚያዋጣው ንስሐ ብቻ ነው!ሰዎችን በመለወጥ በመተካት አታመካኙ ይህችን እንኳን ተወት አድርጓት ሰዎች የሃይማኖት የሰላም እውነትም መቋቋም መስሏቸው ነበር ለካ የፖለቲካ ድርጅትና ሀገርና ሕዝብን የሚያራብሽ ነው በማለት ሸርተት እያሉ ነውና አትታለሉ እኛ እንኳን ነቅተናል ሰው አንዴ ሁለቴ ሊታተል ይችላል ዘመኑን ሁሉ ግን ሊታለል አይችልም!ለማንናኛውም ዐውደ ምህረቶች በርቱ እንደው ጉደኞች ናችሁ ለመሆኑ ዜናውን ከየት ነው የምታገኙት ፈጣኖች ናችሁ ደግሞ ከተመሳሳዮቻችሁ ጋር ስትቀባበሉ ጉድ ነው!ነው ወይስ ስማችሁ የተለያየ ስራች ዓላማችሁ አንድ ነው!በርቱ ለማንኛውም!
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete
  10. at least, we are proud of them that they can not be menafikan, b/c they were committed to their church while they were in MK. morever, if it is true that they leave, then it can be considered as their retirement. but as far as support to MK is concerned, look back the clourfull celebration (more than 10,000 attendants) , a week ago at 'bete khnet' hall. as far as management members is also concerned, would you think that MK faces problem?????? hahhhahhahhhahhahha. any way this blog is a lier blog. we read 2 weeks ago that yaregal abegaz stop serving MK, BUT HE PREACHED WONGEL AT THE 20 TH YEAR MK CELEBRATION LAST WEEK.SO, 80%OF YOUR TALK IS FALSE.

    ReplyDelete
  11. ማኅበሩ በገጠር ያሉ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን አስከፈረታለሁ፣ የአብነት ት/ቤቶችን እረዳለሁ፣ ገዳማትን እደጉማለሁ ቢልም የባለፉት ሀያ አመታት ነባራዊ ውጤት ግን የምዕመናን ቁጥር መቀነስ፣ የመቻቻል መንፈስ መበረዝ፣ ጎጠኝነት እና ዘረኝነት መንሰራፋት፣ እድሜ ጠገብ ቅርሶች መዘረፍ፣ የአብነት ተማሪዎች መበተን እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ -----IT IS B/C OF THE RACIST AND MAFIA PATRIARICH AND WOYANE THAT MAKES THIS, NOT MK.

    ReplyDelete
    Replies
    1. recistu ena mafiyaw mk new eng abune pawlos aydelum. maferiyawoche

      Delete
  12. weshete bibeza ewente ayhonme ebaqachu wera atedoletu

    ReplyDelete
  13. በአንድ ቤተ ክርስትያን ውስጥ የተወሰኑ ሰዎች ቡድን ሰርተው እራሳቸውን ማህበረ ቅዱሳን ብለው ከጠሩ ሌሎች የቤተክርስቲያን ልጆች ማን ተብለው ይጠሩ? ማህበረ ቅዱሳን ስያሜው በራሱ ትክክል አይደለም፡፡ ክርስቲያኖች በሙሉ በአንዲት ማህበር በአንዲት ቤተክርስቲያን ተጠልለው ይኖራሉ እንጂ እንዴት በተለያየ ማህበር ይከፋፈላሉ? ቤተክርስቲያን ልጆቿ በማህበር ተከፋፍለው ሲጣሉ እያየች ዝም ማለቷ ተገቢ አይደለም፡፡ ማህበራቱ ለቤተክርስቲያን አደጋ ከሆኑ ይበተኑ፡፡፡፡፡፡፡

    ReplyDelete
  14. ቅዱሳን ስድብን ታግሠዋል

    ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ሲሰድቡን እንመርቃለን ሲያሳድዱን እንታገሣለን ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጕድፍ ሆነናል›› ብሎ እንደተናገረ ስድብን በጸጋ መቀበል የክርስቲያኖች መታወቂያ ነው፡፡ (1ቆሮ. 4÷12) በብዙ ቅዱሳን ሕይወት ውስጥ ያለአግባብ መሰደብ የተለመደና በደስታ የሚቀበሉት ተግሣጽ ነበር፡፡ ቅዱሳኑ ስድብን በደስታ ይቀበሉ የነበረው ለስድብ የሚያበቃ ጥፋት ስለ ሠሩ አልነበረም፡፡ ያለ ስሙ ስም፣ ያለ ግብሩ ግብር ተሰጥቶት በዕለተ ዓርብ በአደባባይ የተሰደበውና የተተፋበትን አምላካቸውን መድኃኔዓለምን በእምነት እያዩ ‹ከእኔ ትለፍ› ያላትን የመከራ ጽዋዕ በመቅመሳቸው ደስ እየተሰኙ ነበር፡፡ ከሸንጎ ፊት ሲወጡም ጮማ እንደቆረጡ፤ ጠጅ እንደጠጡ ሁሉ ፊታቸው በደስታ በርቶ የወጡት ‹‹ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለተቆጠሩ›› ነበር፡፡ (ሐዋ 6÷41)



    በአበው መነኮሳት ታሪክ ስድብና እርግማንን ሳያስተባብሉ በአኮቴት መቀበልን የመረጡ ብዙ ቅዱሳንን እናገኛለን፡፡ በንጽሕናቸው መላእክትን መስለው ይኖሩ የነበሩት ቅዱሳን ከዝሙት ርቀው ሳለ ዘማውያን ሲሏቸው ታግሠዋል፡፡ አባ መቃርዮስ የተባለ አባት ከአንድ ጎልማሳ የጸነሰች ወጣት ከእርሱ ነው የጸነስኩት ብላ በከሰሰችው ጊዜ እኔ አይደለሁም ሳይል ‹‹እየሠራሁ ልርዳ›› ብሎ ተቀብሏል፡፡ እስክትወልድ ድረስ ሰሌን እየሸጠ ሲረዳት ከቆየ በኋላ በምጥዋ ጊዜ ጭንቋ ሲበዛ እውነቱን ተናግራለች፡፡ ቤተሰቦቿ ይቅር በለን ሊሉት በሔዱ ጊዜ በአቱን ለቅቆ ሔዷል፡፡ (ስንክሳር ዘወርኀ መጋቢት 27)



    እንደ አባ መቃርዮስ ያለ ስድብን የታገሠው አባ በጥል እና በጾታ ሴት ሆና ሳለ ሴት መሆኗን ሳያውቁ በሐሰት ድንግል ሴትን አስረግዘሻል ብለው ዕድሜዋን ሙሉ የነቀፏት ቅድስት ዕንባ መሪናም ባልሠሩት መነቀፍን መታገሥ እንደሚገባን የሚያስረዱ እንደ ደመና የከበቡን ምስክሮቻችን ናቸው፡፡ እውነተኛ ትሑትም ሲሰድቡት የሚታገስ ነው እንጂ ስድብን የሚያስተባብል አይደለም (ማር ይስሐቅ 6)፡፡


    ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ !

    ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፥ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።›› በማለት እንደተናገረ ሲሰድቡት መልሶ መሳደብ የክርስቲያን ተግባር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ክርስቲያን ያሰኘን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤›› እንጂ (1ጴጥ.2÷23 ፣3÷9)፡፡



    በእውነቱ ክርስቲያኖች እንሰኝ እንጂ ተሰድቦ መታገስ ግን ለብዙዎቻችን የሚዋጥ አይደለም፡፡ ተሰድቦ ዝም ማለት በብዙዎቻችን ትርጓሜ ራስን ማስናቅ፣ ፊት መስጠት፣ ፈሪነት እንጂ ትዕግሥት ተብሎ አይጠራም፡፡ አንዳንድ ዝም ያልንባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም እንኳን በትሕትና ታግሠን አለመሆኑና የዝምታችን ምክንያት ሌላ መሆኑ የመታገሣችንን ደረጃ ዝቅ ያደርገዋል፡፡ ተሰድበን ዝም የምንልባቸው ብዙ ምክንያቶችም አሉ፡-

    • ለተሳዳቢው ቦታ ካለመስጠት ንግግሩን ‹‹እንደ ዘፈን ቆጥሮ›› ‹ያሻውን ይለፍልፍ፣ ምን ያመጣል?› ከሚል ንቀት፤

    • ተሳዳቢው አካል በቀላሉ ልንጋፋው የማንችለው የበላያችን ሆኖ መልስ ብንሰጥ የሚመጣብንን በመፍራት፣

    • በአንደበት መልስ ከመስጠት ይልቅ ሌላ መበቀያ ምቹ መንገድ ለመፈለግ፣

    • በቃል በሚደረግ እሰጥ አገባ የተነሣ በሌሎች ሰዎች ዐይን ትዝብት ውስጥ ላለመውደቅ

    በመሳሰሉ ተርታ ምክንያቶች ተሰድበን ልንታገስ እንችላለን፡፡ ይህ ግን ትዕግሥት ሆኖ ዋጋን የሚያሰጥ አይደለም፡፡

    አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ብዙ ጊዜ ታግሠን ከቆየን በኋላ በአንድ አጋጣሚ ስንጋጭ ታግሠን ያሳለፍናቸውን ስድቦች ሁሉ ካጠራቀምንበት ልባችን አውጥተን ‹‹ታግሼ ነው እንጂ፤ ለእግዚአብሔር ሰጥቼ ነው እንጂ እንዲህ እንዲህ ብለኸኝ/ ብለሽኝ ነበር›› ብለን እናስታውሳቸዋለን፡፡ ቅዱስ ዳዊት ግን በተግባር ያስተማረን ስድብን መታገስ ብቻ ሳይሆን ይገባኛል ብሎ ማመንንና ከእግዚአብሔር እንደተላከ ተግሣጽ መቀበልን ነው፡፡



    ውድ ክርስቲያኖች! የጌራ ልጅ ሳሚ ቅዱስ ዳዊትን የሰደበው ስድብ ተገቢ አልነበረም፡፡ እኛን ግን ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚሰድቡንና የማንታገሠው ስድብ አንዳች እውነታንም ያዘለ ነው፡፡ ያለ አንዳች ምክንያትም የሚሰድበን የለም፡፡ ይሁንና ሌላው ቀርቶ ስማችንን የመጥራት ያህል ለእኛ በሚመጥን (በሚገባን) ክፉ ስም ሰዎች ሲጠሩን እንኳን ይበሉኝ ብለን ከመታገስ ይልቅ ለጠብ እንቸኩላለን፡፡ ልሳነ ወርቅ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹አንድ ሰው "አንተ አመንዝራ" ብሎ ሲሰድብህ ለምን ትቆጣለህ? በሐሳብህም እንኳን ቢሆን አመንዝረህ አታውቅም? ወይም ደግሞ በክፉ የጎልማስነት ምኞት ዝለህ አታውቅም? ስለዚህ ይህንንም ስድብ ለክፉ ሐሳቦችህ እንደ ቅጣት አድርገህ ልትቆጥረው ይገባሃል፡፡››

    ReplyDelete
  15. ‹ብልህ ሰው ከስድብ ይማራል› የሚሉት ብሂልም በእርግጥ እዚህ ላይ ሊነገር ይችላል፡፡ ‹ወንበዴ ቀማኛ› ከሚለው ስድብ ጀርባ ‹አትስረቅ› የሚል ምክር አለ፣ ‹ዘማዊ አመንዝራ› ከሚለው ነቀፋ ጀርባ ‹አታመንዝር› የሚለው ተግሣጽ አለና በምን ነቀፈው ነቀፋ መነፅርነት ራሳችንን መመልከት ይገባናል፡፡ ከስድብ ጀርባ ምክርና ተግሣጽ አለ ሲባል ግን ስድቡን ከሚሰማው ሰው አንጻር ነው እንጂ ምክርን ያዘለ ነው እያሉ ሰውን መሳደብ ይገባል ማለት እንዳልሆነ ግልጥ ነው፡፡ ላሳዝነው ብሎ ሥር ገብቶ ቤት መርምሮ ዘር ቆጥሮ መሳደብ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስፈርድ ነው፡፡ ‹‹ወዘይፀርፍሂ ላዕለ እኁሁ ፀረፈኬ ላዕለ እግዚአብሔር ልዑል፤ ወንድሙን የሚሰድብ ልዑል እግዚአብሔርን ተሳደበ›› ተብሎ እንደተነገረ ሕንፃን መንቀፍ ሐናፂውን መንቀፍ፣ ሥዕልን መንቀፍ ሠዓሊውን መንቀፍ እንደሆነ ሁሉ፤ ፍጡርን መንቀፍም ፈጣሪን መንቀፍ ነው፡፡ ፈጣሪን መንቀፍ ነው የተባለውም ሰውን የሠራ እግዚአብሔር ስለሆነ አንድም ደግሞ ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ስለተፈጠረ ነው (ተግሣጽ ቀዳማዊ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)፡፡



    ቅዱስ ዳዊት ‹እግዚአብሔር አዝዞታልና ይርገመኝ!› እንዳለ ሰዎች በክፉ ቃል በተናገሩን ጊዜ ቀንቶብኝ ነው፣ ተመቅኝቶኝ ነው እያሉ ራስን ከመካብ ይልቅ ‹አምላክ በዚህ ሰው አንደበት አድሮ ኃጢአቴን ሊያመለክተኝ ነው› ብሎ በትሕትና ማሰብ ይገባል፡፡ ትሕትና ማለትም ‹‹ራስን መሳደብ ሳይሆን ሌሎች ሲሰድቡን መታገሥ ነው›› ብሏል ቅዱስ ዮሐንስ በተግሣጹ፡፡



    ተሳዳቢው ሰው የቱንም ያህል ክፉ ቢሆን፣ የምንሰደበው እኛም የቱንም ያህል ንጹሐን ብንሆን መልሶ መሳደብ አይገባም፡፡ ንጉሥ ዳዊት ስለ በደለው በደል ንስሓ የገባ ጻድቅ ቢሆንም፤ የጌራ ልጅ ሳሚም መናገር የማይገባውን የተናገረው ቢሆንም ታግሦታል፡፡ እኛም የሚሰድቡን ሰዎች ምንም ቢከፉ እኛም የቱን ያህል ብንቀደስ ለስድብ አጸፋ መመለስ አይገባንም፡፡ ከላይ ከተነሣንበት ታሪክ አንጻር ሙሉ በሙሉ ሊተረጎም አይገባም እንጂ አሁን ላነሣነው ሐሳብ የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ታሪክ ምሳሌ ልናደርገው እንችላለን፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ዲያቢሎስ የድፍረት ቃልን በተናገረው ጊዜ ‹‹እግዚአብሔር ይጣልህ!›› አለው እንጂ የስድብን ቃል ሊናገረው አልደፈረም፡፡ (ዘካ 3÷2፤ ይሁ 1÷9) ከመላእክት ወገን ከቅዱስ ሚካኤል በላይ የከበረ ከዲያብሎስም በላይ የተዋረደ የለም፤ ከነሠራዊቱ ተዋግቶ የጣለውን ውዱቅ መልአክ እንደ ሰው ቢሆን የጥንቱን አንሥቶ ሊያዋርደው ይቻለው ነበር፤ ይሁንና የከበረው ሚካኤል ለተዋረደው ዲያብሎስ እንኳን ክፉ ሊመልስለት አልወደደም፡፡



    እኛም ምንም ብንከብር የቅዱስ ሚካኤልን ያህል አንከብርም፤ የሚሰድቡን ሰዎችም ምንም ቢከፉ የዲያብሎስን ያህል አይከፉምና ለመሳደብ በመቸኮል ለአንደበታችን አርነት አንስጥ! የሚገባንን ስድብ ስንሰደብ ራሳችንን በስድቡ ውስጥ እንገሥጽ፣ ያለ ጥፋታችን ስንሰደብ ደግሞ ያለ ጥፋቱ የተሰደበ አምላክ ባሪያዎች መሆናችንን እያሰብን ከቅዱስ ዳዊት ጋር ‹‹ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ›› ‹‹የሚሰድቡህ ስድብ በላዬ ወደቀ›› ብለን እናመስግን! (መዝ 88÷9)፡፡

    ወስብሐት ለእግዚአብሔር
    ምንጭ፡ሐመር ኅዳር 2003 ዓ.ም

    ReplyDelete
  16. Eset agebaw kerto lehulachin'm libona endiseten fitachin'n wede Egziaybher enimels ena enitsel'y...yihe yimeslegnal meft'hew. Libona yisten!!!

    ReplyDelete
  17. I am stil MK!!!!!! will remain MK,,,,u just talk ,,,,,,

    ReplyDelete
  18. mk is a dead organization. it has to be buried.

    ReplyDelete
  19. Yemogn Lekso Melso Melalso

    ReplyDelete
  20. Yemogn Lekso Melso Melalso

    ReplyDelete
  21. <>Kentu ena bado mignot

    ReplyDelete