Saturday, June 23, 2012

አባ አብርሃም ኢየሱስ አያዋጣም አሉ!!

Click here to read in PDF
በሀረር ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለሦስት ቀናት የቆየ እጅግ ደማቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ተካሂዶ ነበር። በወንጌል ወዳድነቱ የሚታወቀው የሐረር ህዝብ በሶስቱ ቀን ጉባዔ በከፍተኛ ሁኔታ የተገኘ ሲሆን በጉባኤው ሰዓት የክልሉ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አባ አብርሃም አገልጋዮቹን ጠርተው “…ይሔ ኢየሱስ ኢየሱስ የምትሉት የሚያዋጣችሁ  አይመስለኝም። ብትተዉት ይሻላል።” በማለት ተናገሩ።
የአባ አብርሃም የጉድ ሙዳይ በከፈቱት ቁጥር በውስጡ የተደበቀ ነገር እየወጣበት ከማስደነቅ አልፎ ማሳዘን ከማዛዘንም አልፎ ማስደንገጥ ጀምሯል። ይህ ንግግራቸው ሰውየው በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ያላቸው አጀንዳ ምንድን ነው? አሰኝቷል። ህሊናቸውን ተጠቅመው የሚያደርጉት ነገር እንደሌለ እና ማኅበረ ቅዱሳን ከሰጣቸው ተልዕኮ ውጭም ሌላ አጀንዳ እንደማይታያቸው ያሳየው እንዲህ ያለው ንግግራቸው ከወንጌሉ እውነት ውጭ መስማት በማይፈልገው የሐረር ሕዝብ ፊት እንዲፈጸም በማዘዛቸው ትዕዛዛቸው ሳይሳካለት ቀርቷል። ከዛም በኃላ ደግሞ የደብሩን አስተዳዳሪ ጠርተው “…ይሄ ኢየሱስ ኢየሱስ የምትሉትን የማያዋጣ ጉዞ መቸ ነው የምትተዉት?...” ሲሉ ለመውቀስ ሞክረዋል። 

ስለ ጽድቅ ስለ ኃጢአትና ስለ ፍርድ አለምን ይወቅሳል የተባለው የመንፈስ ቅዱስ ወቀሳ እንዳያገኛቸው ከመንፈስ ቅዱስ የሆኑ መልዕክቶችን በመግፋት የሚታወቁት አባ አብርሃም ካፈርኩ አይመልሰኝ በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደማያዋጣቸው ደጋግመው መናገር ይዘዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ካላዋጣ የሚያዋጣው ማን ይሆን? ማኅበረ ቅዱሳን? ወይስ በቆብ ተሸሽገው ቆብ ገልጠው የሚገቡት አባ አብርሃም?
ለነገሩ ክርስቶስ የመጠላቱ ሚስጢር ገብቶናል። ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ “…ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤” ብሎ በጻፈው የእውነት ቃል እንደሚያረጋግጥልን ብርሃን የሆነውን ጌታችንን ስሙን መጥራት ራሱን ለጨለማ ሀሳብ ላስገዛ ሰው ይከብዳል። አባ አብርሃም እውነታቸውን ነው ክርስቶስ ብርሃን ነው። የጨለማን ሥራ ያስወግዳል። በጨለማ ስራ ለመኖር የሚፈልግ ግን የብርሃንን መልዕክት መሰማት አይፈልግም። እሳቸውም ካሉበት ቦታና ድርጊት አንጻር ስለ ብርሃን ጌታ መስማት አይፈልጉም። ነገሩ በአንድ ወቅት አንድ ጸሀፊ “ኃጢአትም ከመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስም ከኃጢአት ይጠብቃል።” እንዳለው ሆኖባቸው ነው።
አባ አብርሃምን በምን እንምንከተላቸው ግራ ገብቶናል። ከሃይማኖት ሃይማኖት የላቸው። ከምግባር ምግባር የላቸው። ከአስተዳደር ችሎታ የአስተዳደር ችሎታ የላቸው። ከእውነት እውነት የላቸው። ከህዝብ ፍቅር ራሳቸውን ካስገዙላቸው የማቅ ሰዎች ውጭ የሚወዳቸው የለ። በገንዘብ ፍቅር በሴት ፍቅር በሥልጣን ፍቅር… የተያዙ ሰው ናቸው። የሞነኮሱ ለት ስርዓተ ግንዘት የተፈጸመላቸው ለዓለም እና ለምኞቱ እንዲሞቱ ሳይሆን ለመንፈሳዊ ነገሮች ሞተው ለአለማዊ ነገሮች ህያውነትን ለማግኘት ሳይሆን አይቀርም። ምን… ችግር እኮ ነው እነ ደብተራ አስቻለው የማይሰሩት የለ!!
ከሁሉ ከሁሉ የከፈፋው ጉድና ጉድለታቸው ግን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እንዲህ አድርገው መጥላታቸው ነው። ይህ ተግባራቸው እጅግ የሚያሳዝንና ሰውየው በመዳናቸው ጉዳይና በመንግስተ ሰማያት ተስፋ ቆረጡ እንዴ? ያሰኘ ነው። አሁን ያሉበትም ሁኔታ እነደ ሥጋዊ ሰው እንኳ በማንነታቸውና በጤንነታቸው የሚያስመካ አይደለም እና  የጌታችን የኢየሱስ ክርቶስም ደም ከኃጢአት ሁሉ ነፃ እንደሚያወጣቸው አውቀውና አምነው ንስሐ በመግባት ፊታቸውን ወደ እርሱ ዘንበል ቢያደርጉ የተሻለ ነው እንላለን።   
ብቸኛ የድኅነት አማራጭ መሆኑን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በሙላት ያረጋገጠውን ክርስቶስ አያዋጣም ማለትን እንኳን እሱን አገለግላለሁ የሚል ጳጳስ ምዕመንም ሊናገረው የማይገባ ክህደት ነው። ለክብሩ የማይደራደረው ጌታን እያመለክን እኛም ብንሆን ለክብራችን መደራደር አይገባንም። ሚሥጢር ገላጩ ጌታ በመንፈሳዊነት ካባ ኃጢአት ሲያደባ ምን እንደሚመስል ተራ በተራ እያሳየን ነው። አባ አብርሃምን የተንጠለጠሉበት ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው የሸንበቆ ዛፍ ከምንም አያስጥሎትም እና ወደ እውነተኛው እና አስተማማኙ የወይን ግንድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲጠጉና ከዘላለም ጥፋት እንዲመለሱ በአደራ ጭምር እናሳስባለን።
      

27 comments:

  1. wey gize ayaseman yele? ewnet kehone yasazenal

    ReplyDelete
  2. በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ባለወርቅማ ብዕር ጸሐፊ የሆነው መምህር ዲ/ን አሸናፊ መኮንን የያዝነው ምዕመን የኢየሱስ ስም ሲጠራ ከአጋንንት እኩል የሚፈራ ነው ብሎ በመጻፉ ምን እንደሚያስወግዝ የማያውቁ ጳጳሳትና ደንባራው በክፉ አጋንንት የሚመራው ማቅ ኡኡ ካልተወገዘ ብለው በክርስትና ታሪክ የሐይማኖት ስህተት ባልሆነ ከንቱ ጥላቻ ተወግዟል። በርግጥ የእነርሱን ውግዘት መንፈስ ቅዱስ ስለማይቀበለው ከሰማይ መንግስት የሚነሳው ነገር ስለሌለ ችግር የለውም። ግን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሳያውቁ ጳጳስ በሆኑ አባቶቻችን ግን አዝነናል። አፍረናል። ይኸው ዲያቆኑ ያለው እውነት ሆኖ የኢየሱስ ስም ሲጠራ ከአጋንንት እኩል የሚደነግጡ ምዕመን ጳጳስ አይተናል። እንዲያው ምንስ ቢጠላ የአዳነን ጌታ ስም ይጠላል? አይ አባቶቻችን ታሳፍራላችሁ

    ReplyDelete
    Replies
    1. ከራጉኤል ቤተክርስቲያንJune 24, 2012 at 7:25 AM

      መቶ በመቶ ትክክል ነው። የማቅ አባላት 1000ሺህ ጊዜ እየተደጋገሙ ቢፈጠሩ ወይም ደግሞ ተጨፍልቀው አንድ ሰው ቢሆኑ አንድ አሸናፊን አያክሉም። የሚጽፋቸው በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ መጽሀፍት የሚያሳዩን ይሔንን ነው። ጌታችን ከተወለደ 2000 አመት እንዳለፈው ያልሰማ ሁላ ተሰብስቦ ባርያውን መናፍቅ ሲል አያፍርም? ያውም ክብራችን ተነካ በመጸሀፍህ ቤተክርስታን መሪ የላትም አልክ አሉ ብሎ። አና እነ ቹቹ ናችው አባቶች?

      Delete
    2. በዲያቆን አሸናፊ ላይ የሰነዘሩት ውግዘት አሳዛኝና ለቤተ ክርስቲያን ውድቀት ትልቅ ማሳያ ነው። በመሠረቱ መጻሕፍቶቹ ከክርስቲያን ተቀዋም አልፈው በእስልምና ውስጥም እንደ አንድ ማስተማሪያ ሆነዋል። ያላነበቡት ሳይሆን ያነበቡት ቢገመግሙና ቢናገሩ ያምር ነበር። የማይጽፉ ሰዎች ጽሑፍን እንኳን ማውገዝ መተቸት አቅም ያላቸው አይመስለኝም። ከውግዘቱ በኋላ አንዳንድ ጳጳሳትን አነጋግሬ ስሙንም ያለ ዛሬ አልሰማንም ለመሆኑ ማን ነው? ሽማግሌውን/ አቡነ ጳውሎስን ማለታቸው ነው/ እንደሚቀርብ ሰምተናል ዋናው ከእርሳቸው መለየት ነው ሲሉኝ ስሰማ ወዴት እየሄድን ነው አሰኝቶኛል። አንዳንድ አባቶችም ካላወገዝን አያኖሩንም ከጀርባችን ያለብንን ተጽእኖ ብታውቁት እንዲህ አትፈርዱብንም ሲሉኝ ምንድነው? ብዬ ተጨንቄአለሁ። በዚህ ክፍል ላይ ጉዳዩ ስለተነሣ ደስ ብሎኛል በሰፊው ቢታተት መልካም ይመስለኛል። እርሱም አነጋግሩኝ ብሎ በደብዳቤና በአካል እንደጠየቀ ከአባቶች ሰምቻለሁ ማነጋገር እንዳልፈለጉ ነግረውኛል። ታዲያ ሰው በሌለበት ባልተጠየቀበት አውግዘናል ማለት እነርሱን መልሶ የሚያስር ውግዘት ነው። ግፋችን ማባሪያ ያገኝ ይሆን? Tedla Eysus Amare

      Delete
  3. አባ አብርሃም ራጉኤል ሳሉ በከፍተኛ ደረጃ የተጠሉ አስተዳዳሪ ነበሩ እሳቸው አባ ቃለ ጽድቅ ሳሉ በቤተክራስቲያኑ አስተዳዳሪ በነበሩ ጊዜ ከሰው የማይጠበቅ ጭካኔና ግፍ አይተንባቸዋል። አሁን አሁን እንኳ ስማቸውን ስሰማ ያንገሸግሸኛል። ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና የጌታችን ስሙ አይጠራ በማለታቸው አልገረመኝም። እሱን ቢያውቁት መቸ እንደዚህ ጨካኝ ይሆኑ ነበር?

    ReplyDelete
  4. Yeherer hizbe egin seweye betam eyetelachew. new endet yale neger new abo eyesusen yemiyastela eref beluwache yemisalew yehe new. ayabesachun alebeleziya yeabune yosef eta new yemigetemachew.

    ReplyDelete
  5. ለአሕዛብ ሁሉ መስክር እንድሆን ይህ የመንግስት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል በዚያ ግዜ መጨረሻው ይመጣል። ማቴ 24 13። በዘመናችን የይሁዳ መጥፎ ምግባር ያላቸው አባቶችን ከዚህ ክፉ መንፈስ ተመልሰው በእውነት መንግድ እንድሄዱ እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው። በውኑ አባ አብርሐም የንስአ አባታቸውን ተቃውመው እርሳቸው ልከበሩ ይፈልጉ ይሆን ? በመጀመሪያ ሄደው ኣባ ጳውሎስ ይቅርታ ልጠይቁ ይገባቸዋል እንደ ጌታ አምላካች ቅዱስ ቃል። የሚውደኝ ብኖር ቃሌን ይጠብቅ ዮሐ 14፤13።

    ReplyDelete
  6. lambalwalebet kubet lekema yilual yihichi nat!!!!!! Ersachewin atinkubin.Ke Harar

    ReplyDelete
  7. ጳጳሱ ለአገልጋዮች ከሚናገሩ ለሕዝቡ ቢናገሩ ኖሮ ልክ ይገቡ ነበር። ጉባኤው ላይ የነበሩት እራሱ አንድ ቀን ብቻ ነው።ቀጣይ ቀኖችን አልነበሩም። እስኪ ፊት ለፊት እንዲህ ያለውን ነገር ለህዝቡ ይናገሩማ በጓዳ አገልጎችን ከማናገር ፊት ለፊት ይነገሩን ሀረር እንዴት ያለች ከተማ መሆንዋን በቅጡ ያውቁ ነበር

    ReplyDelete
  8. yechi le dejeselam counter-attack mehonewa new? Endet ehadigna gebreaberochun ye Ethiopia heseb endetelachehu betaku yehenen lemakefet balmokerachehu. By the way, dejeselam eko eweneten bemawetat lebetakerestiyan andinet yamisera new yehe dagmo letekaraniw. Don't waste your time gin ketornet lela minim selemateserubet gize masalefiya yehonachehuale. Shut your big trash mouthhhhhhhh!!!

    ReplyDelete
  9. በሰውየው ፎቶ ላይ ጸጋ የራቀውና የጵጵስና ግርማ ያልጎበኘው፤ የሆነ እንትን ይመስላል። በቃ አለ አይደል! የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የተለየው ነገር ይመስላል። እስኪ የአቡነ ሰላማ«የአክሱም» ሊቀጳጳስንና ይህንን የሐረሩን ሰውዬ አስተያየዩት። አቡነ ሰላማ የሚከብድና የሚያስፈራ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዳላቸው ይሳያል። ያለምንም ማጋነን ይህ ሐረሩ ሰውዬ ጸጋ የተለየውና የቀረበውን ገጹን አይቶ መገመት ይቻላል።
    ኢየሱስ የሚያስጠላው ሰው ሆኖ የቀረው ለዚህ ይመስለኛል።

    ReplyDelete
    Replies
    1. manehe ante endihe lemalete yedefereke?mejemeriya seyetane silehonek ye egiziabehere berekete mayete atechelem!!!!

      Delete
  10. My grand father Ato Redi Geberwolde was the one who built the Dire Dawa Saint Micheal Church, my mother told me that how it was difficult to build this church at that time while the Catholic church was strong in Finance during that time. I was thinking about this church and the people of the people Harere and Dire Dawa. I am proud that the Harere orthodox christian sticking with the Bible, the word of gospel will be preach widely in Ethiopia. I hope Aba Paulos put aside this player bishop from our church.

    ReplyDelete
  11. ስሞኑን ደግሞ ደጀ ስላሙ ባላባቶቹ በደጀ ሰላማውያን ተተቹ [ወይ እናባ]

    ReplyDelete
  12. ቅዱስ ፓትርያሪኩ ከሆኑ ሰው አይወጣላቸውም ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባውን ሲጀምር በ አድማና በብጥብጥ የተካኑትን አባ ሳሙኤልንና አባ አብርሃምን ብዙ የጉድ ሙዳይ እንዳለባቸው እየታወቀ ቅዱስነታቸው ልሹማቸው ፍቀዱልኝ ብለው ስለተየኩ የፓትርያሪኩን ጥያቄ በምሁራኑ አበው ጳጳሳት ዘንድ ተቀብለው ብዙ እያወቁ ካለእድሜያቸው የአበውን ጵጵስና ተሸክመው ይንገዳገዳሉ አሁንም ቆይ ጵጵስናውን ላግኝ እያሉ የሚዝቱትና የሚፎክሩት አፈ ቀላጤው ገብረ ስላሴ ጉበና ብዙ የጉድ ሙዳይ ያለበት አሁንም ሹሙኝ በማለት ካውስትራልያ ኢትዮ በመመላለስ ላይ ይገኛል ነገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ለመበዝበዝ ለማወክ ካልሆነ ምን ይሆን ጥቅሙ እነዚህ የጉድ ሙዳዮች እንደ ቀደሙት አባቶች ለሀገር ለወገን ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ይጸልዩ ይሆን አለመጸለያቸውን ለማወቅ ግን ቀላል ነው በራሳቸው ሰላም ማጣት ይታወቃልና፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

    ReplyDelete
  13. አባቶችን የመሳደብ ቋንቋ የማዋረድ ቃላት አንጠቀም እያሉ መዘርጠጥ ይቅር እውነቱን በፍቅር መናገር ምን እንደሆን እንማር ምን ይሁኑ ምን ጳጳስ ተብለው ተሹመዋል ሥልጣን ከእግዚአብሔር ነውና በአክብሮት መናገር ልክ አይደሉም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ማለት ነው እንጂ እንዲህ ካደረግን እኮ የባሰውን ዕድሜያቸውን እያራዘምን እንሄዳለን::እግዚአብሔር የልቡን ፈቃድ የሚፈጽም እንደሳሙኤል ያለ ሰው ተወልዶ እስከሚያድግ ተወልዶም ከሆነ እስከሚያድግ ድረስ ነውና አትጨነቁ <የሚያከብሩኝን አከብራለሁ ይህ አይሆንልኝም ያለው የሳሙኤል ነብዩ አምላክ እግዚአብሔር አሁንም አለና አይዞአችሁ የሐረር መድሃኔዓለም ምእመንን እንኳን ይህችን ሌላም ያውቃል ከአባቶች መጥቆ ከሄደ ቆይቷልና አታስቡ እናንተም ዐውድ ምህረቶች ስድብ አታስተናግዱ እባካችሁ!በርቱ የኢንፎርሜሽናችሁ መዋቅር በደንብ ተዘርግቷል::
    ኒቆዲሞስ

    ReplyDelete
  14. Niqodimos - belexet mehonu new? Teneqtual abatochen be agul ye shengela qalat masasatu yebeqa ! E/R AMELAK yewededewn yadreg. Eski zem enebel.

    ReplyDelete
  15. አባቶችን አለመሳደብ ጥሩ ነው ነገር ግን አባቶችም በአባቶች ቦታ ተገኝተው የቤተ ክርስቲያናን ሰላም ሊያስተብቁ ይገባል አለያ ግን የታሪክ ቦታ የሆነችዋን ብቅዱሳን ስም ማህበር መስርተው የሚንቀሳቀሱት ማቆች በእየ አጥቢያ ተሰግስገው ማህበሩን በማይደግፉ ከዲ እስከ ፓት ድረስ ክርስቶስ ቀርቶ እኛን አልሰበኩም በሚል መናፍቅ እያሉ እንደ ሚቀጥሉ አይጠራጠሩ፧ ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘብ ይቁሙ ማቅ ማቅ ማለቱን ይተው

    ReplyDelete
  16. ከሀረር ሚካኤል
    በመጀመሪያ የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን በቤተ ክርስቲያን ውሰጥ እሰከ አሁን በማን እንደዳኑ የማያውቁ በመጽሀፍ ቅዱስ የማያምኑ ባህልና ወግ ከሀይማኖት ጋር የሚያደባልቁ ክርስትና ያልገባቸው ሰዎች አሉ ከእነዚ ሰዎች አባ አብርሃም አንዱ ናቸው የተፈታውን ህዝብ ወደባርነት ለመክተት የጌታ ስም የያዘ መዝሙር እንዳይዘመር በወንጌል አገልግሎት የኢየሱስ ስም እንዳይጠራ በማለት ከማይገፉት ጌታ ጋር በመጣላት ለላየይ የመሚገኙ አባት ናቸው ለእሳቸው ከስህተታቸው እንዲመለሱ እንጸልይላቸው ክፉውን መንፈስ ግን እስከ ሞት ልንዋጋው ያስፈልጋል ክርስቶስ ሀረር ላይ ነግሶ ይኖራል የመውጊያውን ብረት ብትቃወም በአንተ ይብስብሀል ከመንገድህ ተመለስ ህዝቤን ልቀቅ ይላል እግዚአብሔር.

    ReplyDelete
  17. ከሀረር ሚካኤል
    በመጀመሪያ የክርስቶስ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን በቤተ ክርስቲያን ውሰጥ እሰከ አሁን በማን እንደዳኑ የማያውቁ በመጽሀፍ ቅዱስ የማያምኑ ባህልና ወግ ከሀይማኖት ጋር የሚያደባልቁ ክርስትና ያልገባቸው ሰዎች አሉ ከእነዚ ሰዎች አባ አብርሃም አንዱ ናቸው የተፈታውን ህዝብ ወደባርነት ለመክተት የጌታ ስም የያዘ መዝሙር እንዳይዘመር በወንጌል አገልግሎት የኢየሱስ ስም እንዳይጠራ በማለት ከማይገፉት ጌታ ጋር በመጣላት ለላየይ የመሚገኙ አባት ናቸው ለእሳቸው ከስህተታቸው እንዲመለሱ እንጸልይላቸው ክፉውን መንፈስ ግን እስከ ሞት ልንዋጋው ያስፈልጋል ክርስቶስ ሀረር ላይ ነግሶ ይኖራል የመውጊያውን ብረት ብትቃወም በአንተ ይብስብሀል ከመንገድህ ተመለስ ህዝቤን ልቀቅ ይላል እግዚአብሔር.

    ReplyDelete
  18. hahahaha we all know that menafikanoch betam yeras mitat yehebachihu MK ena Ende abune abreham yalu yetewahido ewunetegna abbatoch nachew !! yihi degmo yiketilal atiterateruuu !! We all 45 million Orthodox are just behind them !! Enante gin askedimom yetesadabiw ye dabilos lijoch silehonachihu sirachihu hulu sidibina sim matifat,mewashet new ...!! Geta mastewalin yistachihu.

    ReplyDelete
  19. ይሥሐቅ ነኝ ሐረር አደሬ ጢቆ ሰፈር
    ይድረስ ለተከበሩት አባቴ ለአቡነ አብረሃም፡-
    እስከሚገባኝ ድረስ መፅሐፍ ቅዱሳችንም በግልፅ እንዳስቀመጠዉ እርስዎ የተሾሙት የእግዚአብሔርን መንጋ ይጠብቁ ዘንድ ነው፡፡ይህን ኃላፊነትዎን መወጣት ይችሉ ዘንድ የሾመዎትን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ይፈፅሙ እንደሆነ በዚህ ይትጉ፡፡ያለበለዚያ ግን በሞተልን ጌታ በኢየሱስ እና በምናቀረብለት ዝማሬ ቀለድ የለምና ይረፉ፡፡

    ReplyDelete
  20. ማቅና አባ አብርሃ እውነተኛ የኦርቶዶክስ አገልጋዮች መሆናቸውን ሁላችንም በደንብ ጠንቅቀን እናውቃለን! በተመሳሳይ ደግሞ እውነተኛ የክርስቶስ ቀንደኛ መሆናቸውን ደግሞ አንዘነጋውም! ስለዚህ ማቅ ማለት
    1.ድርጅቱን እየወደደ ሃይማኖቱን የሚጠላ
    2.ምድራዊዉን እየሰበከ ሰማያዊዉን የሚረሳ
    3.የገድልን ነገር እያፈቀረ የወንጌልን ነገር የማይናገር
    4.ጻንቃንን የሚማጸን አጽዳቂውን የሚከለክል
    5.ጻድቃን ሰማእታት ያዋጣሉ ኢየሱስ አያዋጣም የሚሉ
    6.በአንድ ወር (በ30 ቀን)ውስጥ 27ቱን ቀን ለጻድቃን ለመላእክት የሚዘምሩ 3ቱን ቀን( 7ስላሴን 27 መድሃኔአለምን 29 ባለግዚአብሄርን) ከቻሉ ለማስታወስ የሚሞክሩ
    7.ጻድቃን ብለው የሚጠሯቸው በገነት ይሁኑ በሲኦል ሞናቸውን ሳያውቁ ነብሴን አደራ ብለው የሚዘምሩ
    አንድ ቀን የጌታ ፍቅር እንዲገለጽላቸው የዘወትር ጸሎቴ ነው እንናነተም የጌታ ነገር የገባችሁ ድካማቸውን ሳታዩ ስህተታቸውን እያረማችሁ ገስጹልንሁላችንም በነጻ ያገኘነው ነገር ስለሆነ በማናቸውም ደካማ ሰዎች ሳንፈርድ አንድ እምነት በጌታ እንዲኖረን አደራ? የተፈረደብን ሳንሆን የተፈረደልን በመሆናችን ደስ ይበለን! ለዘለአለም ሞተን ልንቀር የነበርነውን ለዘለአለም በህይወት እንድንኖር የጌታ ፈቃድ ሆነልን!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. hulachihum bedenb awuru endikelachihu

      Delete
    2. you know you are simple man you know nothing about bible but are talking a lot on it but it is better for you to learn by sitting at the leg of literates to know more, because to know who saints are you have to have the gift of good otherwise you will be wondering in the ideal point with out getting God. but Jesus Christ is the one who saved us from death so i believe on that.

      Delete
  21. ahiiiiiiiiiiiiiii labochi nachihu

    ReplyDelete