Tuesday, September 18, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ጀሌ በመሆን ጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከትን እየበጠበጠ ያለው ሲያምር የሀገረስብከቱን የህግ ክፍል ለመደብደብ ተጋበዘ፡፡


ሕገ ወጦቹና ወንጀኞቹ ሲያምር ተከለማርም እና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ሆኖ የጉጂ ቦረና ሀገረ ስብከትን ህዝብ ሲያውክ የነበረው ዲያቆን ሰይፉ እሸቱ በፈጸሙት ወንጀል ፍርድ ቤት ከሰው  ያስፈረዱባቸውን የሀገረ ስብከቱን የህግ ክፍል ሃላፊ ሊቀ ትጉሀን ዘነበ አለማየሁን ሊደበድቡ ሲል የጠቅላይ ቤተክህነት ጠባቂዎች አስጥለዋል፡፡ ነገሩ ግርምት የፈጠረባቸው የጠቅላይ ቤተክህነት ሰራጠኖች በግቢው ውስጥ የተፈጠፀመውን ነገር ሰምተው ከየቢሮዋቸው እየተጠራሩ መጥተው ሁኔታውን ለመታዘብ ችለዋል፡፡
ቅዱስነታቸው ካረፉ በኃላ ሚናንውን አስተካከልሎ ሙሉ  በሙሉ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር የተሰለፈው የጠቅላ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጁ ተስፋዬ ለሲያምር ደብዳቤ የጻፈለት ቢሆንም ከጉጂ ቦረና አካባቢ በተቀሰቀሰው ከፍተኛ ተቃውሞ እና ወደ መንግስት ቢሮዎች በከፍተኛ ደረጃ እየጎረፉ ያሉት አቤቱታዎች ያስነሱበትን ተቃውሞ ለማስተባበል ሲል እና ከመንግስት የቀረበለትን ማጣራትህን ሳትጨርስ ለምን የሚለውን ጥያቄ ላማለዘብ “ደብዳቤ የጻፍንለት ሥራ ያለው እንዲመስለው እንጂ በቦታው ላይ ተቀምጦ ሥራ እንዲሰራ አይደለም” ሲል የጅል መልስ ሰጥቷል፡፡
የተቃውሞው ማየል ግራ ያጋባቸው እነ ሲያምር በሌላ ጉዳይ ወደ ቤተክህነት የመጡትን የሀገረ ስብከቱን የህግ ክፍል ሲያዩ አንቀን ካልገደልን ማለታቸው ድሮም የደርግ ወታደር ያሰለጠነው ምን ከጸብ ውጭ ምን አይነት መፍትሔ ሊያስብ ይችላል አስብሏል፡፡
ሊቀ ትጉሀን ዘነበ አለማየሁ የድብደባ ሙከራ እንደተፈጸመባቸው ጠቅላይ ቤተክህነት አካባቢ ባለው ፖሊስ ጣቢያ እነ ሲያምርን መክሰሳቸው ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment