Monday, September 24, 2012

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን መሪዎች ሊቃነ ጳጳሳት ህይወት አደጋ ላይ ወድቀዋል


                                            በዲ/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
(ዐውደ ምሕረት፣ ሠኞ፣ መስከረም 14 2004 ዓ.ም. awdemihret.blogspot.com//awdemihret.wordpress.com)(ቀጣዩ ጽኁፍ ኢትዮጵን ሪቪው በተባለ ዌብሳይት ላይ ከወጣ በኃላ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማህበረ ቅዱሳን ኢሳት በመባል ከሚታወቀው ያለ ነውርና ጠማማነት በጎነትና ቅንነት የማይወጣበት የህውከተኛችና የነውጠኞች የፕሮፖጋንዳ ማእከል ለጥፋትና ለመዓት ከማህበሩ ጎን ተሰልፎ የሚሰራቸው ስራዎች በመንቀፉ እንዲወገድ የተደረገ ጽኁፍ ነው፡፡ 
ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በበሬ ወለደ ውሸት ተቃቅፎ እያሸረገደ የሚገኘው ይህ "የቴሌቭዥን ጣቢያ" በሚፈጥረው ተጽእኖ ድህረ ገጹም በበኩሉ ኢሳትን አትንኩብኝ ከእሱ ጋር ያለኝ የአላማ አንድነት ጽኁፎቻችሁን በነፃነት ለማስተናገድ አይፈቅድልኝም ሲል የዲያቆን ሙሉጌታ ወልደገብርኤልን ጽኁፍ ከድረ ገጹ አስወግዷል፡፡”
ስለዲሞክራሲያዊ መብት እታገላለሁ እያለ ባለው ትንሽ እድሉ ዲሞክራሲያዊ መብትን የሚያፍን ስብስብ ከዚህ አስተሳሰባችሁ ጋር ስልጣን ብትይዙ ምን አይነት አምባገነን እንደምትሆኑ ስናስብ ይዘገንነናል፡፡ ኢትዩጵን ሪቪዎች ሕሊናችሁ ስለማያምንበት ዲሞክራሲ ማውራት ብታቆሙ ጥሩ ነው፡፡ ሙሉጌታንም አይዞህ በርታ ለእውነት መታገልህን ቀጥል ልንለው እንወዳለን፡፡ መልካም ንባብ ይሁንላችሁ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ሆነ በነባራዊው ዓለም እንደ እስራኤል ያለ ለሰውም ለፈጣሪም የማይመለስ እልከኛ፣ ፈታኝ፣ አመፀኛና አብግን ዜጋ ሌላ ይኖራል ብዬ አላስብም። እስራኤል ከተፈጠረበት ጊዜ ጀመሮ አሁን እስካለበት ጊዜ ድረስ ያለውን ገጽታና መታወቂያ ከወንጭፍና ሰይፍ ወደ መከናይዝድ ተሸጋገረ እንጅ አንዲትም ዘመን ብትሆን እየጎነተለም ሆነ እየተጎነተለ በሰላም የተኛበት ዕለት የለም። ወደ ጥንተ ነገሩ በመመለስ የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ፣ ባህልና ወግ ምን ይመስል እንደነበረ/እንደሚመስል ለማወቅና ለመመርመር የተፈለገ እንደሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ ታሪክ ሳያዛንፍ ሊተርክልን የሚችል ሌላ መጽሐፍ አይኖርምና መጽሐፉን በሽፍኑ ከመሳለም ባለፈ ገልጠን ማንበቡ የላቀ ጥቅም ሊኖረው እንደሚችል በዚህ አጋጣሚ ለመጠቆም እወዳለሁ።

እንግዲህ መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ መጻህፍትም ሆነ በሌሎች የመጽሐፉ ክፍሎች ውስጥ ተጽፎ እንደምናገኘው የእስራኤል መልክ ቀደም ብዬ በግርድፉም እንደገለጽኩት ከሞላ ጎደል እስራኤል እልከኛ፣ አስቸጋሪና ነገሮችን በራሱ ዕይታ ብቻ የሚያይ፣ የሚመዝን፣ ቅድመ ማስጠንቀቅያ ብሎ ነገር የማይቀበል ይህ ማለት በመንፈሳዊ አነጋገር ለነቢያት ቃል ጆሮ የሌለው፣ ለክፉም ለደጉም ፈጽሞ ነቅሎ የተነሳ እንደሆነ የማይመለስ፣ መስሎ በታየው አቅጣጫ ብቻ በመሄድ መንገዱን በራሱ የሚወስንኃይለኛሕዝብ ሆኖ ነው የምናገኘው።

ይህ ብቻም አይደለም ምርጫዎች ከሚያስከፍሉት ዋጋና ከሚያስከትሉትም መዘዝ የተነሳ እንደ እስራኤል ያለ ተደጋጋሚና ለዘመናት የዘለቀ ዘግናኝ ዋጋ የከፈለ፣ የተገፋ፣ የተረገጠ፣ የተጨፈጨፈና የተሰደደ፣ ለሰሚም ጆሮ የሚሰቀጥጥ ታሪክ ያለው እስራኤልን የሚስተካከል ሀገርም ሆነ ሕዝብ ሌላ ማንም ሊኖር አይችልም ብል ማጋነን አይሆንብኝም። እስራኤል እንደ ሀገር/ሕዝብ የተበተነ፣ የተገፋ፣ አጥንተ ሥጋውንም እንደ እህል ተፈጭቶ ለሳሙና ማሰሪያ የዋለ ሕዝብ ነው። ስለ ግርፋት፣ ስለ ውርደት፣ ስለ ባርነትና ስደት በእስራኤል ፊት አፉን ሞልቶ ታሪክ አለኝ በማለት ሊተርክ የሚዳዳው/የሚቻለው አንድም የዓለማችን ክፍል የለም። በእነዚህና ሌሎች ክቡር ለሆነው ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ፈጽመው የማይደሉ፣ የማይመቹና የማይጥሙ መጥረቢያዎች የቆሳሰለና ምልክት ያለበት ሕዝብ ይጠራ ቢባል እስራኤል ቀዳሚ ነው። ታድያ ይህችን ጦማር በሚያነቡበት ሰዓት እንኳን ይህ ሕዝብ ከሌላው ዓለም ተለይቶ ይህን ሁሉ ግፍ በላቀ መልኩ እንዴት ሊያስተናግድ ቻለ? በማለት ሳይጠይቁ አይቀሩም።

ጥያቄው ተገቢና መነሳት ያለበትም ነው አንድም የጥያቄው መልስ የሚያመራው የመመካከሩ ጊዜ ገደብ አልፎ በሩ በብረት ናስ ሳይቀረቀር እንነጋገርበትና እንወያይበት ዘንድ በዛሬው ዕለት ወደ ተነሳው ርዕስ ያመራናልና። ከቅድመ ውድቀት አንስቶ ይህ ማለት እግዚአብሔር አዳምንከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህናሲል ከሰጠው ትዕዛዝ ጀምሮ በእግዚአብሔር በኩል እንደሆነ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ አስቀድሞ ሳያሳውቅና ሳይናገር በሰው ልጅ የሆነ አንዳች ነገር የለም። በአንፃሩ የሰው ልጅ በራሱ ተነሳሽነት ይበጀኛል ሲል በሚወስደው ማንኛውንም ዓይነት የግል ውሳኔዎችና እርምጃዎች ደግሞ እርምጃዎቹ ያልተገቡ እንደሆነ ለዘራው ዘር የዘራውን ማጨዱ የማይቀር ሆኖ ፍዳውን ሲያይ እንንመለከታለን።
የእስራኤል ውድቀት፣ ስብራት፣ ድቀት፣ ውድመት፣ ዋይታና የለቅሶዋም መንስኤ ከመስመር ሲወጣና የጠራውንም አምላክ በማይከብርበት ስፍራ/መዋያ ሲገኝ የእጁን ከማግኘቱ በፊት አካሄዱን ይመረምር ዘንድ ወደ ስፍራውም ይመለስ ዘንድ እግዚአብሔር በነቢያቶቹ አድሮ ይነግረው፣ ያስተምረውና ይገስጸውም እንደነበር መጽሐፉን ላነበብ ሰው አሌ የማይበል ሐቅ ነው። እንቢ፣ አሻፈረኝ በማለትም በአመጽ ክፉ ምግባሩን የገፋበት እንደሆነም ልኩን ያውቅ ዘንድ አጸፌታውን ሊያገኘው እንደሚችልም በላዩ ላይ ያጠላውን የጥፋት ደመና ለነቢያቶቹ ገልጦ በማሳየት ይመለሱ ዘንድም ያደርግ ነበር። ይህም ሁሉ ሆኖም ከቀድሞ ጥፋቱና ስህተቱ የማይማር እስራኤል ያላየው የመከራ ዓይነት የለም። ከእንቢተኝነቱ የተነሳወርቅ ባበደረ ጠጠርእንዲል ያገሬ ሰው መልካምን በተናገሩ ነቢያት ላይ እጁን እያነሳ የንፁሐንን ደም ያፈስ ነበር።
እስራኤል: እግዚአብሔር እንደነኤርምያስ ያሉትን የአፋቸው ቃል መሬት ጠብ የማትል ነቢያት ልኮ ለሃያ ዓመታት ያክል በቀንም በሌሊትም ቢጮኹም ፊቱ አዙሮ የስላቅ ዳንኬራውን እየመታ፣ አለሁ አለሁ እያለም ሳይታወቀው ራሱን በባዕድ ምድር በምርኮ መንደር ያገኘ ሕዝብም ነው። እንግዲህ መጽሐፍከራሱ የሚናገር የራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላከውን ክብር የሚፈልግ ግን እርሱ እውነተኛ ነው በእርሱም ዓመፃ የለበትም።እንዲል የሰይጣን ማኅበርማኅበረ ቅዱሳንበማስመለከት ከዚህ ቀደምም ሆነ በአሁን ሰዓት ለቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የሰሚ ጆሮ ያለህ! በማለት ድምፃችውን ያሰሙ የቅድስት ቤተ- ክርስቲያን ልጆች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው፣ ከስራ ቦታቸው ተሰናብተው፣ አሰረ ክህነታቸውንም ጥለው እንዲኮበልሉ፣ እንዲሰደዱና ቤት ንብረታቸውንም አውላላ ሜዳ ጥለው በእንግድነት ከተማ በግዞት እንዲኖሩም ተገደዋል።
በዚህ ሁሉ ግን የእነዚህ ኅሩያነ እግዚአብሔር የሰሚ ጆሮ ያለህ! የሚለውን ድምጽ የማስተጋባታቸውና ቃል የመናገራቸው ምስጢሩ ጥቅም ፍለጋ ነው፤ በተጨማሪም ያልሆነውን ሆነ፣ ያልተደረገውን ተደረገ በማለት የሐሰት ቃል በመናገር ትርፍ ለማግኘት ነው የሚል ያለ ሰው እንደሆነ ባልተገባ ምክንያት ራሱን እንዳያታልል ይጠንቀቅ። እንቅጩ ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለማኅበረ ቅዱሳንያልሆነውን ለመናገር የሚተጋ ሰው አለ ብለውም እንዳያስቡ። የሚነገረው ቃልም እንደሆነ ከምንም በላይ ለተናጋሪው ጥቅም ሳይሆን ለመልዕክቱ ተቀባይ/ለሰሚው እንደሆነም ሌላው ሊዘነጉት የማይገባ ወሳኝ ነጥብ ነው።
ይህ ስሙ እንክን የማይወጣለት ዳሩ ግን በምግባሩ መራሄ ሲኦል የሆነው ራሱንማኅበረ ቅዱሳንበማለት የሚጠራ ስብስብ የኃይማኖት መሪዎችም ሆኑ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የማህበሩ ስውር ትውልድ ገዳይና አገር አጥፊ አካሄዱን በማስመልከት ከዚህ ቀደም የተነገሩና አሁንም እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ መነገሩ የሚዘለቀውን ቃል ያልሰሙና ምላሽ ያልሰጡ እንደሆነ ጦሱ ከቤተ-ክርስቲያን አልፎ ለሀገር የሚተርፍበት ጊዜው እሩቅ አይሆንም።
አሁን አሁን ቤተ-ክርስትያኒቱ በምታዘጋጃቸው መድረኮችም ሆነየቤተ ክርስቲያኒቱመሪዎች በተገኙበት ስፍራ ሁሉ ሊቃነ ጳጳሳቱም ሆነ ሌሎች ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት ቤተ ክርስቲያንን በመወከል በሚያደርጓቸው ንግግሮች ሁሉ ቀዳዳ ፈልገው፣ እሬት እሬት እያላቸውም እንደሆነ ፊታቸው አዙረውም ቢሆንማኅበረ ቅዱሳንንሳያወድሱ፣ ሳያሞካሹ፣ ማኅበሩን አቆላምጠው ሳይጠሩና የማህበሩ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት በማለት ለሚታወቁ ግለሰቦች እጅ ሳይነሱ መውረድ የማይታሰብ እየሆነ መጥተዋል። ቅዳሴን የማስታጎል ያክልም በፍርሃት ውስጥ ተውጦውና ተንጠው ስለማኅበረ ቅዱሳንእንዲናገሩ የተደረጉባቸውን ዓረፍተ ነገሮችም እየተመዘዙ በተለይ ወፍ ዘራች ፖለቲካ አራማጅ ኃይሎች የፕሮፖጋንዳ መድረክ በሆኑት ትልቅ ሽፋን እየተሰጠው ለዘመናት የዘለቀችውን ቤተ- ክርስቲያን ወደ ጎን እየተገፈተረች ስለ ማኅበሩ ምጸታዊየጽድቅዜናዎች መስማት እየተለመደ መጥተዋል።
በአሁን ሰዓት ሊቃነ ጳጳሳቱ የማህበሩ ዓላማ ደገፉም አልደገፉም ወደዱም ጠሉም የታዘዙትን ከማድረግ፣ ተጽፎ የተሰጣቸውን/የቀረበላቸውን አሜን ብለው ከመቀበልና ከማጽደቅ ውጭ ምንም አማራጭ በሌለው ሁኔታ ላይ ወድቀዋል። ቤተ ክርስቲያን በሲኖዶስ መመራትዋ እየቀረም በማኅበሩ (ግልጽና የስውር አመራር አባላት) ወደ መመራት እየገሰገሰች ነው። ይህም ሊሆን የቻለበት ምክንያትም ሌላ ምንም ሳይሆን ማህበሩ የካህናትንና ዲቆናትን ስም ከማጥፋት ከማሳደድና ከመደብደብ አልፎ ለሊቃነ ጳጳሳቱ ለህይወታቸው ራሱ አስጊ እየሆነ ከመምጣቱ የተነሳ ነው።
ለምሳሌ ያክል አሁን በቅርብ ጊዜ የሆነው የተመለከትን እንደሆነ በሞቱት ቅዱስ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ፈንታ ሲመተ ፕትርክና እስኪ ፈጸም ድረስ በጊዜያውነት በአቃቤ መንበርነት የተሾሙትን ብጹእ አቡነ ናትናኤል የዘመን መለወጫ በዓል በማስመልከት ያደረጉት ንግግር እኛ እርስ በርሳችን ባለ መስማማታችን ይሄው ሀገር እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያ በፕሮቴስታን እምነት ተከታይ ግለሰብ ልትምራ ነው። በማለት ሌላው ይቅር ከአንድ የዕድሜ ባለጸጋ አባት የማይጠበቅ ንግግር ለማድረግ ተገደዋል። ይህን ንግግራቸው ብዙሐኑ ታዳሚዎች ሲያስደምምና ሲያስቆጣ ጥቂቱ በመድረኩ ውር ውር ሲሉ ይስተዋሉ የነበሩየማህበረ ቅዱሳንከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት ደግሞ በአንጻሩ ያቀዱትን ተግባራዊ ሆኖ በማየታቸው የደስታ ፊት እንደታየባቸው ለማወቅ ተችለዋል። ከዚህ ንግግር በኋላም እንደሆነ ግን የቤቱ ሰላም ተወስዶ ሁሉም ከታቀደው የጊዜ ሰሌዳ ቀድሞ ጥሎ በመሄድ አዳራሹ ባዶ መቅረቱንም በተጨማሪ ለማወቅ ተችለዋል። እስከ ዛሬ ዕለት ድረስም በቤተ ክህነት ሰራተኞች ዘንድ የአረጋዊው አባ ናትናኤል ሚዛኑን የሳተ አነጋገር ከፍተኛ አነጋጋሪ መሆኑ እንደቀጠለ ነው።
የዛሬ አያድርገውና መስቀል ተሸክሞ አላህ ወአክበር! እያለ በዬ አደባባዩ እንደ ብቅል ሊሰጣ ቀደም ሲል በነደፈው እቅድ መሰረት የኢ////ያን እምነት ተከታዮች ከእስልምና የእምነት ተከታዮች ጋር በማጋጨት በሚፈጥረው ትርምስ መንገዴን እጠርጋለሁ በማለት ለህውከትና ለሽብር ድርጊት የሚያነሳሱ መካነ ድሮቹ በኩል የነደፈው ስልቱ ወቅቱ ባመጣው ነፋስ ለጊዜው አጀንዳውን እንዲጥል በመገደዱ አሁን ደግሞ መልኩን ለውጦ የሃይማኖት መሪዎችን በመጠቀም መንግሥትን የመተናኮስና ቤተ ክርስቲያን ከመንግስት የማጋጨት ስራ አንድ ብሎ ተያይዞታል።
ይህ በሽብርና በህውከትም አቅሙን ካላጎለበተ በቀር ሌላ አማራጭ የሌለው ያለ እውቀት የሚጋልብ ጽንፈኛ ማህበር የሃይማኖት መሪዎች በማስገደድ መንግሥት ሊያስቆጣ የሚችል ሃይለ ቃል እንዲናገሩ፣ የአመጻ መንገድም ተከትለው እንቢተኝነታቸውን እንዲያሳዩ በማድረግ መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ላይ ጥርሱን እንዲነክስና ምእመናንም በመንግሥት ላይ እንዲነሱ በማድረግ ህውከትንና ትርምስን ለመፍጠር አረጋዊው አቃቤ መንበር አባ ናትናኤል አፍ ተቀምጦ ይህ አደረገ። እንግዲህ እንዲህ ያለ አካሄድ ደግሞ አገሪትዋ ወዴት አቅጣጫ ሊያመራት እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው።
እዚህ ላይ "የማኅበረ ቅዱሳንን" ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል በሃይማኖት መሪዎችና በመንግሥት መካከል በሚፈጠረው አለመግባባት ሕዝብና ሀገር በቀላሉ ሊወጡት ወደማይችሉ አዘቅት መስመጣቸውና መናጣቸው እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም እንደሆነ ግን ማኅበሩ በዚህ ሁሉ ብቸኛ ተጠቃሚ ነው። ታድያ ምን እናድርግ? ሀገር የሚያወድም ትውልድንም የሚገደል ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ ዓይኑ አፍጥጦ ጥርሱ አግጥጦ ሲመጣ ሀገርዎንና ትውልድዎን ከአገር በቀል አሸባሪ ድርጅት ለመታደግ ምን አስበዋል? እንዴትስ ባለ ዘዴ ለመመከት ተዘጋጅተዋል? ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፈሶን ሰዎች በጻፈው መልእክት ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ እንዲል ሀገርንና ትውልድ ለማዳን ሲባል የማህበሩ ስውር ፓለቲካዊ አጃንዳ በመገለጥ የሚደረገውን ተጋድሎ በመቀላቀል/መሳተፍ የድርሻዎትን ይወጡ ዘንድ ብቻ ይጠየቃሉ።
/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E- mail yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America

No comments:

Post a Comment