Thursday, September 6, 2012

ሲኖዶሱ ለ15 ቀን የሚቆይ የምህላ አዋጅ አወጀ



ሲኖዶሱ ለ15 ቀን የሚቆይ የምህላ አዋጅ አወጀ
በትናነትነው ዕለት ለጋዜጠኞች በተሰጠ የጽሁፍ መግለጫ ሲኖዶሱ ከጳጉሜ 1 አስከ መስከረም 10 የሚቆይ የምህላ አዋጅ አውጇል፡፡ በብጹዕ አቡነ ሐዝቅኤል ፊርማ በተለቀቀቅ የጽኹፍ መግለጫ እንደሚያመለክተው ምኅላው ጾመን አያካትትም፡፡ ዋነኛ አላማውም የተሻለ አባት ለቤተክርስቲያን እንዲያስነሳ ነው፡፡ የሰላም አምላክ አግዚዘብሔር ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን ያምጣልን፡፡
የሱባኤው ዓላማ ተገቢ እና አስፈላጊ ቢሆንም ቀጥታ ፓትርያርክ ምርጫ ጋር ከማተኮር ሁለቱ ሲኖዶሶች የሚዋሀዱበትን ሁኔታዎችን እና እርቁ የሚቀላጠፍበትን ሁኔታ የሚያመቻች ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት እርቅ እንዳይፈጸም እንቅፋት የሆኑት አቡነ ጳውሎስ ናቸው እየተባልን ኖረናል፡፡ አሁንስ ታድያ ምን እየተደረገ ነው? ምህላ አዲስ ፓትርያርክ ለመምረጥ ከሆነ እርቁ ለምን ያስፈልጋል? ከአሜሪካ መጥተው የሀዘኑ ጊዜ እስኪያልፍ ጠብቁ የተባሉት ሰዎችስ ምን ሊባሉ ነው? እውን አሁን ያሉት አባቶቻችን እርቁን ይፈልጉታል? ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አባቶቻችን አንድ ብትሉን መልካም ነው፡፡ 


3 comments:

  1. በጣም ያሳዝናል። ጸሎተ ምህላው ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ሳይሆን ስላ ሥልጣን ሽምያ ነው። ደስ የማይል አካሄድ ነው። ቀድሞ ብጸዕ አቡነ ጳውሎስ ናችው ለዚህ ልዩነት መንስኤው ይባል ነበር።አሁን ግን አንደምናየው አይደለም።ጸሎትና ጾም አብረው ነው ሰቡኤ የሚደረጉት አንዴት ነው ነገሩ።ለዚህች ቤተ ክርስትያን የሚያዝንላት አባት እንዴት ይጥፋ?

    ReplyDelete
  2. It is not good for our church unity. Nobody caring regarding the church be come unities . That too bad ideas . How our pray going to reach Lord God? Look like somebody paying the game behind the bar.

    ReplyDelete
  3. Be patient for every thing what will happen in the future in this senodios members. God have a plan for all things ...but no body no his plans.

    ReplyDelete