Thursday, September 13, 2012

"ማኅበረ ቅዱሳን" ፓትርያርክ መርቆሪዮስን እንደማይቀበል አቋሙን በይፋ አሳወቀ:: ፓትርያርክ ቴዎፍሎስንም ኮነነ፡፡


በዲ/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
"ያለውን" በመቅበር የሌለውን በመጥራት የሚታወቀው የጥቁር ራስ ስብስብ የሆነውን ማህበረ ቅዱሳንበጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲሁም በቤተ መንግሥት አከባቢ የታየውን ድንገተኛ ክስተት አጥፍቼም ብሆን እጠፋለሁ እንጂ ይህን ወለል ብሎ የተከፈተ በርስ ሳልጠቀመት አያልፈኝም! የሚል መፈክር አንግቶ በሀገሪትዋ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንደቀዳዳ በማየትና ቀዳውን በማስፋት በዚህ ማኸልም ሾልኮ በመውጣት ያልተጠራበት ዙፋን ለመጠቅለል በስውርም በይፋም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቀን ከሌሊት ሴራውን እየሸረበና እየዶለተ እንደሚገኝ ምንም አያጠያይቅም።
ባሳለፍነው ሳምንት ሽብርና ህውከት በሚነዛባቸው መካነ ድሮቹ አመካኝነት " ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የት ነዎት ? " ሲል ሳይጠራ አቤት ሳይላክ ወዴት አንደማለት ያልተጠየቀውን ሲያመናታ ሲሳለቅ በሌላውኛው እጁ (በህጋዊው ድረ ገጾቹ) በኩል ደግሞ "ቤተ ክርስቲያንና የፓትርያርክ ምርጫበሚል ርእስ ቀደም ሲል ማኅበሩ አሁን በሚጠራበት "ማኅበረ ቅዱሳን" የሚለው ስያሜ ከመያዙ በፊት አጠቃላይ ጉባኤ ተብሎ ይታወቅበት በነበረበት ዘመን ገድሎ የቀበራቸው ፓትሪያሪክ ቴዎፍሎስ እንዲሁም ያለ አንዳች ተጨባጭ ማስረጃ ርዕሰ መናፍቃን በማለት የሚወቅሳቸውን ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ አሁን ደግሞ ሆን ብሎ "ቀድሞም በእግዚአብሔር ፈቃድ ያልተሾሙ ናቸው" ሲል በመዋቹ ቅዱስ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ምትክ መንበሩ የሚገባው ለፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ ነው! የሚል ከየአቅጣጫው እየገፋ እየመጣ ያለውን የአብያተ ክርስቲያናት ድምጽና ለቤተ ክርስቲኒቱ ሰላም: ለተከታዮችዋ ምእመናን ደግሞ አንድነትንና ፍቅር በብርቱ የሚሹ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ምልከታ ለማሳጣት ብሎም ዕርቀ ሰላሙንም ለማደናቀፍ ይህን አደረገ።


ከእኛ ፓትርያርኮች ሁለቱ ከምንኩስና አንዱ ከአጠቃላይ ጳጳስ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ሀገረ ስብከታቸውን ትተው የተሾሙ ናቸው። እነዚህም አቡነ ቴዎፍሎስና አቡነ መርቆሬዎስ ሲሆኑ በጣም የሚያስገርመው በእነዚህ በሁለቱም ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ፈተናዎች ከማስተናገዷም በላይ የሁለቱም ዘመነ ፕትርክናቸው አጭር ነበረ። ለራሳቸውም ሆነ ለቤተክርስቲያኒቱ ጥቁር ነጥቦች የተቀመጡትም በእነርሱ ዘመን ስለሆነ ከትውፊት መውጣታችን ባናስተውለውም እግዚአብሔር አምላካችን አልፈቅድላችሁም ያለን ይመስላል።[1] ልብ ይበሉ! ይህ የማህበሩ (“የማህበረ ቅዱሳን”) የአቋም ማሳያ ጽሑፍ ፓትርያርክ መርቆሪዮስ ወደ ቀድሞ መንበራቸው እንዳይመለሱ አመጽን የሚቀሰቅስ: በሀገር ቤት ያለውን ጉባኤም በመዋቹ ቅዱስ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ከመካከሉ መርጦ ሌላ እንዲሾም የሚገፋፋና ብሎም በቤተ ክርስቲያኒቱ መካከል የማይበርድ ጸብና ክርክር ለማንገስ ጨርሶ ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ የሚባል የለም! በማለት ሲመታቸውን በመግፈፍ የፕትርክና ማእረጋቸውንም እንደማይቀበል ቁልጭ ባለ አገላለጽ እምነቱን መግልጽ ነው። አሁን ማህበሩ ለማስተላለፍ የፈለገው የአመጽ መልዕክቱን አንድ በአንድ እንመልከታለን።
በጣም የሚያስገርመው በእነዚህ በሁለቱም ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ፈተናዎች ከማስተናገዷም በላይ የሁለቱም ዘመነ ፕትርክናቸው አጭር ነበረእንዲል ከዚህ ቀደም በሰነድ የተደገፈውን ሐተታዬ ላይ በስፋት እንዳስነበብኩት ይህ መሰሪ ማህበር የኢህዴግን መንግስት ለማስመታትና ለማስጠቆር ሲፈልግ: ወደ ምዕራቡ ዓለም የከተሙ ወደ ተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉ ኢትዮጵያውያን መሃከልም የተገኘ እንደሆነ በመንታ ምላሱ ፓትርያርክ መርቆሪዮስ በሃይል ተገፍተው ከመንበራቸው እንደተነሱ ምስክርነቱ ሲሰጥና ሲያምታታ አሁን የራሱ አጀንዳ ላይ ሲደርስ ደግሞ ይሄው በማያሻማ ቋንቋ ይቅር እውነትም የተገፉና የተሰደዱ አባት ናቸው በማለት ሊያዝንላቸው ከዛሬ ነገ ወደ ቀድሞ መንበራቸው ይመለሳሉ በሚል መረን የለቀቀ ፍራቻ ተውጦ የሚይዘው የሚጨብጠው አጥቶ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ ጨምሮ ፓትርያርክ መርቆሪዮስን የቤተ ክርስቲያን ነቀርሳ ነበሩ ሲል ሲገልጻቸውና በጠራራ ጸሐይ ዘመቻ ሲከፍትባቸው እየተመለከትን ነው።
ማህበሩ በዚህ አልተመለሰም የሁለቱም ዘመነ ፕትርክናቸው አጭር ነበረእንዲል ይህ ሊሆን የቻለበት ምክንያትም ይላል ማህበረ ቅዱሳንየፓትርያርክ ቴዎፍሎስ በግፍ መገደልና የፓትርያርክ መርቆርዮስ ከመንበራቸው መወገድ ማለት ነው የስልጣን ዘመናቸው አጭር የመሆኑ ምስጢር ባይገባን ነው እንጅ ማእረገ ጵጵስናቸውም ሆነ የፕትርክና ሲመታቸው ቀድሞውኑ ትክክለኛና መንፈሳዊ አለመሆኑ ነው እያለ ሰምተነውም ሆነ አንብበነው የማናውቀው ለእኛ ለቤተ ክርስቲያን ልጆችም ሆነ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንግዳ የሆነ ታሪክ ፈብርኮ እየተረከ ነው:: እንዲህ ያለ ከስህተት ትምህርት ይልቅ የከፋ ታሪክን የመበረዝና የማዛባት እኩይ ምግባር ደግሞ እንዲሁ በዋዛ ፈዛዛ የሚታለፍ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን አጽንዖት
ሰጥታ ተገቢ የሆነ እርምጃ ትወስድ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ለሚመልከታቸው አካላት ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
ሌላው እውነት ለመናገር ያክል ከዚህ ስመ መንፈሳዊ የሰይጣን ማህበር "ከማህበረ ቅዱሳን" በቀር ፓትርያርክ ቴዎፍሎስን በክፉ የሚያነሳ ገጥሞኝም አያውቅ። ገድሎ ቀብሮአቸው ሲያበቃ ዛሬም በአጥንታቸው ላይ ቆሞ ከመራገም የአለመቦዘኑ ምስጢር እንደሆነ ማህበሩ ምን ያክል በእኝህ አባት ታሪክ የማይረሳው ትውልድ የሚሻገር የጽድቅ ስራ ማለትም ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ የኢ////ያን ስርዓትንና ሕግ በመቅረጽ: የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ መዋቅር መልክና ወጥነት ያለው አሰራር በማስተዋወቅ ከዚህም አልፎ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተመጽዋችነት ተላቃ ራስዋን በመቻል ካህናትዎችዋን የምትመግብበትን የልማት ተቋማትን በመገንባት ያደረጉትን ትውልድ የማይረሳው መልካም ስራና ያበረከቱትን አስተዋጽዖ
በአጠቃላይ በዘመነ ፕትርክናቸው ለኢ////ያን የዋሉት ውለታ ዛሬም ድረስ ምን ያህል ማህበሩን እያቃጠለው እንዳለና እንደሚኖር የሚያመላክት ነው።
በመቀጠልም "ለራሳቸውም ሆነ ለቤተክርስቲያኒቱ ጥቁር ነጥቦች የተቀመጡትም በእነርሱ ዘመን ስለሆነ ከትውፊት መውጣታችን ባናስተውለውም እግዚአብሔር አምላካችን አልፈቅድላችሁም ያለን ይመስላልእንዲል። እዚህ ላይ እንግዲህ ከወደ መግቢያዬ አከባቢ ጠቅለል ባለ መልኩ እንደገለጽኩት "ማህበረ ቅዱሳን" እንዲህ ባለ ሰዓት ላይ እንዲህ ያለ ታሪክ ይዞ ለመምጣት የተገደደበት ዋና ምክንያትና በሚያሰራጨውም ወሬ አተርፋለሁ ብሎ ያሰላውን ትርፍ ቀደም ሲል እንደተገለጸ የሃይማኖት መሪዎቹ ከነ ቅራኔአቸው ማዶ ለማዶ እየተያዩ እንዲኖሩና በዚህም ሂደት ውስጥ በሚያካሂዱት የእርስ በርስ መጎሻሸም እድሜዬን አራዝማለሁ ብሎ ስለሚያምን ነው።
ከዚህም የተነሳ "ከትውፊት መውጣታችን ባናስተውለውም እግዚአብሔር አምላካችን አልፈቅድላችሁም ያለን ይመስላል" ሲል በድፍረት የታጠረ ነውራም አነጋገሩ ፓትሪያሪክ ቴዎፍሎስም ሆኑ ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ ድሮም የተሾሙት "ትውፊት ተጥሶ ነበር" (እዚህ ላይ ስለየትኛው ኢትዮጵያዊ ትውፊት እያወራ እንዳለ ለራሱ እጹብ የሚያሰኝ ነው) በህገ ወጥ ወደ መንበሩ የወጡና የተሾሙ ናቸው በማለት በሃይማኖት መሪዎቹ መካከል ለረጅም ጊዜያት የዘለቀውን አለመግባባትና መለያየት መቋጠሪያ ለማበጀት በሚደረገው አስታራቂ ነጥብ ማካከል ጣልቃ በመግባት የቀድሞ ፓትርያርክ መርቆሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ የሚለውን ወሳኝ አስታራቂና መግባቢያ ሃሳብ ተግባራዊ እንዳይሆን "ማህበረ ቅዱሳን" በዚህ ለንባብ ባሰራጨው የአቋም ጽሑፉ ፓትሪያሪክ መርቆሪዮስ ተመስልሰው በመንበረ ፕትርክናው የሚቀመጡበት ምንም ዓይነት መንገድም ሆነ ምክንያት የለም በማለት በማያገባውና በማይመለከተው የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊ ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት መሞገቱ ማህበረ ምን ያህል አደገኛና የቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ የተከታዮችዋ ሰላም የማይፈልግ ጸረ ሰላም ሃይል ለመሆኑ በተጨባጭ የሚያረጋግጥ ነው።
ስለሆነም በአርባና በሰማንያ ቀንህ ስመ ቅዱሳንና ስመ ፃድቃን እየሰጠች በጥምቀት የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን ያገኘህ ወንዶችም ሴቶችም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ በሙሉ: ይህ ራሱ የቅዱሳን ማህበር በማለት የሚጠራ ነፈሰ ገዳይ ስመ መንፈሳዊ ድርጅት ከዕለት ወደ ዕለት እየገፋበት እየሄደ ያለውን ቤተ ክርስቲያኒቱ የማፈራረስና የማውደም ዓላማውን እንዲሁም የጸረ ሰላምና አንድነት የሆነውን እኩይ እንቅስቃሴው በመቃወም ከእውነት ጋር እንቆምና እንሰለፍ ዘንድ በድጋሜ በእግዚአብሔር ስም ጥርዬን አቀርባለሁ።
/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
E-mail yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America



[1] http://www.eotcmk.org/site/images/stories/pdfs/patriaric%20election.pdf

2 comments:

  1. Seweyew menesha yaderkew yehe hasab kehone atilfa ante kalkew gar ayihedim....
    ኢትዮጵያውያን ፓትርያርኮች
    በቄርሎስ ስድስተኛ ዘመን ሙሉ በሙሉ ራሷን የቻለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዚህ በጣም
    አጭር ጊዜ ውስጥ ፭ ፓትርያርኮችን አሳልፋ ስድስተኛውን ለመቀበል በመሰናዳት ላይ ትገኛለች። የአምስቱንም አመራረጥ
    ከቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ከትውፊተ አበው አንጻር ሰፊ ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም እስካሁን በቀደሙ ግብጻውያን አባቶቻችን
    ሥርዓተ ሲመት አንጻር በአጭሩ መቃኘት ይቻላል። በእነዚህ አጭር ጊዜያት የተሾሙት አምስቱም ሁሉ በሚሾሙበት ጊዜ
    የነበሩት መንግሥታት እጃቸው ከፍተኛ እንደነበርና የእነርሱ የተጽእኖ ውጤትም እንደሆኑ በየጊዜው ተሳታፊ የነበሩ ሰዎች
    ርግጠኞች ሆነው የሚናገሩት ነገር ነው። እንደተባለው የሁሉም በዚሁ መልክ ተፈጽሞ ከሆነ ገና ከመጀመሪያው ራሷን
    መቻሏን ፈተና ውስጥ ከትተነው ቆይተናል ማለት ነው። ለዚህ ያጋለጠው ዋናው ምክንያት ደግሞ ጠንካራ የሆነ የምርጫ
    ሥርዓት ሳይዘረጋ ለቁጥጥርና ለክትትልም ምቹ ሁኔታ በአግባቡ ሳይፈጠር መፈጸሙ ይመስለኛል። ከዚህም ጋር ደግሞ
    ዐመት በላይ በዘለቀው ግንኙነታችንና ደጂ ጥናታችን ከግብጽ ያመጠናው የሲመት ክትትሉን ብቻ ነው እንጂ ሥርዓተ
    ሲመቱን አይደለም። የሚያሳዝነው ያ በግብጽ ውስጥ የነበረ ሲኖዶስ የእኛም ሲኖዶስ ስለነበረ በግልጽ አዲስ የምርጫ ሕግ
    እንደ አስፈላጊነቱ እስከሚወጣ ድረስ ያንኑ ትንሽ አሻሽሎ መጠቀም ቢጀመር ኖሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ አወንታዊ
    ለውጦችን ልናይ እንችል ነበር።
    ከእኛ ፓትርያርኮች ሁለቱ ከምንኩስና አንዱ ከአጠቃላይ ጳጳስ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ሀገረ ስብከታቸውን ትተው የተሾሙ
    ናቸው። እነዚህም አቡነ ቴዎፍሎስና አቡነ መርቆሬዎስ ሲሆኑ በጣም የሚያስገርመው በእነዚህ በሁለቱም ቤተ ክርስቲያን
    ከፍተኛ ፈተናዎች ከማስተናገዷም በላይ የሁለቱም ዘመነ ፕትርክናቸው አጭር ነበረ። ለራሳቸውም ሆነ ለቤተክርስቲያኒቱ
    ጥቁር ነጥቦች የተቀመጡትም በእነርሱ ዘመን ስለሆነ ከትውፊት መውጣታችን ባናስተውለውም እግዚአብሔር አምላካችን
    አልፈቅድላችሁም ያለን ይመስላል።
    ካለፉት ሂደቶች የተማርናቸው ምን ምን ናቸው?
    ፩ኛ) ከግብጽ ፓትርያርኮች ውስጥ ከአጠቃላይ ጳጳሳት ሦስት፤ ሀገረ ስብከት ካላቸው ውስጥም ሦስት ከተመረጡት
    በቀር ሌሎቹ በሙሉ ከመነኮሳት፣ ከቀሳውሰት፣ ከዲያቆናትና ከምእመናን የተመረጡ ናቸው።።
    ፪ኛ) ሀገረ ስብከት ካላቸው መምረጥ የተከለከለ ነው፤ በተመረጡም ጊዜ ጉዳቱ እጂግ ከፍተኛ ነበር።።
    ፫ኛ) በመንግሥት ባለ ሥልጣናት ርዳታ የሚገኝ ማንኛውም ክህነት የተወገዘ ነው።
    ፬ኛ) በልምዳቸው በዕውቀታቸውና በማንኛው ሁኔታቸው ምክንያት ሰዎችን መምረጥ እግዚአብሔርን እንደሚያሳዝነውና
    በአንዳቸውም ከመከራና ከፈተና በቀር ቤተ ክርስቲያን ተጠቅማ የማታውቅ መሆኗ በታሪክ ታይቷል፡፡
    ነሐሴ 24/2004 ዓ.ም
    16
    መካነ ድራችንን በ www.eotcmk.org ይጎብኙ፡፡ በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
    ፭ኛ) ሕጋቸውን እስከመተላለፍ ደርሰው በደጋፊ ውለታ የሚመረጡ ፓትርያርኮች ሁሉ አጥፊነታቸው ከባድ መሆኑ በታሪክ
    ተረጋግጧል፡፡
    ፮ኛ)ሦስት የምርጫ ሥርዓት ነበሩ። በተለይ በዕጣ ምርጫ ወቅት በታሪካቸው አራተኛ ዕጣ የጌታ ስምም ይገባ እንደነበር
    ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ይህም ሦስቱንም ጌታ ካልፈለጋቸው የእርሱ ስም እንዲወጣ ያደርጋል በሚል ጽኑ እምነት ነው፡፡
    ምንተ ንግበር?
    በቤተ ክርስቲያናችን በሕገ ቤተ ክርስቲያን በ1991 ዓ.ም. ከተቀመቱት ትንሽ ጥቁምታዎች ውጭ ከአንድ ጊዜ በላይ
    ሊያገለግልና ያለቀለት ሊባል የሚችል አጠቃላይ የምርጫ ሕግ አለን ለማለት አንችልም፡፡ ሆኖም ከሁኔታዎቹ በመማርና
    ነገሮቹን ከማስተዋል ግን የተሻለ ሒደት ይኖራል የሚለው ተስፋ ከፍተኛ ነው። በዚህም መሠረት የአሁኑ ሲኖዶስ ቛሚ የሆነ
    የፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ከማውጣት እንደሚጀምረው ይጠበቃል። የማንኛችንም አስተዋጽኦም ከዚህ በላይ መሆን ያለበት
    አይመስልም፡፡ ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱም ሊያገለግል የሚችል ጠንካራ፤ ግልጽና የማንንም ውጫዊ አካል ተጽእኖ
    የሚቋቋም ሕግ ከወጣ በዚያ መሠረት ከአስመራጭ ኮሚቴው አንሥቶ የተጠቋሚዎች የመራጮችና የሌሎችም አፈጻጸም
    በዝርዝር ከተቀመጠ ከእግዚአብሔር ጋር ለልዩነቶቻችን ለመተማማታችንና ለመወዛገባችን ብሎም ለመወጋገዛችን ሁሉ
    ፍጻሜ አስተዋጽኦ ሊያደርግ አንድነታችንም ሊያመጣ ይችላል፡፡ ከላይ ከተጠቆሙትና ካለፈው ታሪካችን አንጻር ትልቁ
    የምእመናን ድርሻ ቤተ ክርስቲያን በጸጥታ ወደብ የምትመራበት ሕግ እንዲወጣ ድጋፍ ማድርግ ሊኖር ቢችልም ዋናው ግን
    የቤተ ክርስቲያን ራስ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ቸር እረኛ እንዲሰጠን መለመንና በሚወጣው ሕግ ብቻ እንዲከናወን መጣር
    ነው፡፡ ስለ አንድነታችንና ከእርሱ የሆነውን ቀኖናዊውን እንድናገኝ ስለመንጋው አንድነት በመዋዕለ ሥጋዌው ጌታ ስለሁላችን
    ያቀረበውን ጸሎት እንጸልየው፡፡
    ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤
    አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ
    አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ
    ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ
    በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል። አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ
    የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ። ጻድቅ
    አባት ሆይ፥ ዓለም አላወቀህም፥ እኔ ግን አወቅሁህ፤ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አወቁ፤ እኔንም የወደድህባት
    ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ/ ዮሐ 17፤ 20-26/፡፡
    አቤቱ አንድ ለመሆን እርዳን፤ አሜን፡

    ReplyDelete
  2. Thank you so much brother. መንግስት አሸባር ያለውን ማህበረ ቅዱሳንን ለሀገርና ለህዝብ ጠንቅ የሆነው ቡድን ያለ አንተ መኖር አንችልም አሉ የማቅ ሊቃነ ጳጳሰት።ጉድ ጉድ ነው።አሁን ገና ማልቀስ ያለብን።ለመሆኑ ማቅ ለቅዶስ ስኖዶሰ ጠባቅ ነው አሉ ይገርማል ይደንቃል።ዘመኑ ምን ያህል የስኖዶስ አባላት እንዳበላሸ እያየን ነው።ለነዋይ ለነዋይ ተብሎ ኤረ ኤረ ጉድ ፈላ ዘንድሮ።የጥንት አባቶቻችን እዉነት ተናግሮ በመሸበት ማደር ነው ይሉ ነበር ይባላል። ከመንፈሳዊን ነን ከምሉት አባቶች እውነት መናገር ቀረ።መጽሐፍ ቅዱስ እንድህ የለናል፦ ሐዋ ሥራ 20፤29 በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ። 1.አንዳንድ የስኖዶስ አባል ሊቃነ ጳጳሳት ማቅን ለምን በስኖዶስ ውስጥ አንድገባ ፈለጉ?
    2. የማቅ አባል የሰኖዶሱ ጠባቅ መሆን ይችላሉ ወይንስ ሥርዓቱ መለወጥ ጀምሮዋል አንዴት ነው ጉዳዩ ?
    3.ስኖዱስ የመንፈስ ቅዱስ ጉባኤ ያለበት ነው ይባል ነበር። አሁን ግን የማህበረ ቅዱሳን ጥበቃ ብቻ ይበቃናል አሉ ተባለ በደጀ ሰላም ድህረ ገጹ በኩል። ኤረ ምን እየሰማን ነው የተዋህዶ ልጆች ? በምን መልኩ ነው አንድነት ለሃይማኖታችን ይመጣል? በዚህ አይነቱ ጉዞ፧ ብላችሁ ተስፋ ታደርጋለችሁ ?
    4.ይህን አይነት በስኖዶሱ ጥሪ ተደረገ ተብሎ በማቅ ድህረ ገጽ የወጣዉ ጉዳይ ስኖዶሱ አባለት ለጥንታዊት ተዋህዶ ህዝበ ክርስቲያን መልስ ልሰጡበት ይባል እንላልን።በጣም ቅር አሰኝቶናል አካሀሄዱ ለእምነቱ አይበጅም።አቡነ መልከ ፀዴቅ እንዳሉት" የባሰው እንዳመጣ" ብለው ነበር ለአዲስ አመት ቃለ ቡረከያቸው ላይ። የስኖዶሱ አካሄድ አነጋገር የሚበጅ አየለም። የመንፈስ ቅዱሰ ጥበቃን እንጅ የማቅ ጥበቃ ለእነርሱ አንመኝም።

    September 13, 2012 5:24 PM

    ReplyDelete