Wednesday, September 26, 2012

‹‹አንድ አድርገን›› እውነት ተናገረ


በዲያቆን ፈታሂ በጽድቅ
በኦገስት 23, 2012 በአንድ አድርገን ብሎግ ላይ ፖስት የተደረገውን ‹‹የአቡነ ጳውሎስ ሽኝት በፎቶ›› የሚለውን የፎቶግራፍ ስብስብ አይተው ሲጨርሱመጨረሻቸው መጨረሻችን የሚል ቃል በትምህርተ ጥቅስ ተቀምጦ ያነባሉ፡፡ ይህን ቃል ሳነብ ነው ‹‹አንድ አድርገን›› እውነት ተናገረች የሚለውን ለማስፈር የተነሳሳሁት፤ ምክንያቴንም እነሆ፡-
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ በክብር የትንሳኤው ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከአዳም የወረሱት ነውና ስጋዊውን ሞት ሊያስተናግዱ ግድ ነው፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ በማመናቸው ሁለተኛው ሞት እነርሱ ላይ ስለማይሰለጥን በትንሳኤ ሞት ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ ሲሉ ይሳለቁበታል፡፡ ትንሳኤው ለማግኘት ግን በክርስቶስ ብቻ ማመን የመጀመሪያውም የመጨረሻውም መንገድ ነው፡፡
‹‹አንድ አድርገን›› ላይ አመጽንና ጸረ ወንጌልነትን የሚሰብኩን ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ የማያምኑ ሰዎች መሆናቸውን ጽሑፎቻቸው የሚናገረ በመሆኑ ለትንሳኤ መብቃታቸውን ብጠራጠር ለምን ብሎ የሚሞግተኝ ሰው ይኖራል ብዬ አልጠብቀም፡፡ ይህን ጥርጣራዬን ደግሞ ራሳቸው ቀደም ሲል ባሰፈርኩት ቃል አረጋግጠውልኛል፡፡
መጨረሻቸው መጨረሻችን” የሚለውን ያሰፈሩት የአቡነ ጳውሎስ በድን ያረፈበትን ባዶ ጉድጓድ ካሳዩ በኋላ ሲሆን የአቡነ ጳውሎስ መጨረሻ የሆነው ይህ ጉድጓድ የእኛም መጨረሻ ነው ማለታቸው እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ የአቡን ጳውሎስ መጨረሻ ያቺ አርባ ክንድ ጉድጓድ እንዳልሆነች እርግጠኛ ብሆንም  የእነርሱን መጨረሻ ግን ራሳቸው መጨረሻችን” ብለው ያሰፈሩትን እንድቀበል እገደዳለሁ ‹‹ከባለቤቱ ያወቀ…›› ይባል የለ?

No comments:

Post a Comment