Wednesday, November 7, 2012

ዓይነ መርፌው የጠፋበት ሲኖዶስና ሴራዎቹ

Ayne merfe
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
እስራኤል በርካታ እግዚአብሔር የሚያስከፉ ከጠየቃቸው ጥያቄዎች መካከል ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ንጉሥ ስጠን በማለት ያቀረቡት ጥያቄ ተጠቃሽ ነው። ይህን የእስራኤል አሳብና ጥያቄም እግዚአብሔር ክፉኛ እንዳሳዘነና ለጥያቄአቸውም በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ አህያ ፍለጋ የወጣውን የቢንያማዊው የቂስ ልጅ ሳዖል ንጉሥ አድርጎ እንደሰጣቸው በቅድሳት መጻህፍት በስፋት ታትቶ እናገኘዋለን። ንጉሥ ሳኦል በዋናነት የሚታወቀው ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሾመ ንጉሥ ቢሆንም እግዚአብሔር በመታዘዝ ባለመጽናቱ እግዚአብሔር የናቀው ከዚህ ጊዜ ጀምሮም ክፉ መንፈስ ያደረበትና መናፍስት ጥሪ ወደ ሆነች ሴት የሄደም ፍጻሜው ያላማረለት ታሪኩ ባነበብት ቁጥር ልብ  የሚሰብር ንጉሥ ነው። 
በእርግጥ የሲኖዶስ አመሰራረትና አነሳስ በተመለከተ በመጠኑም ቢሆን ከሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍ ለመረዳት እንደሚቻለው ዓላማውና ግቡ የእግዚአብሔር ክብር ለመግለጥና እውነት የሆነችውን የጽድቅ መንግሥቱም በምድር ሁሉ  ላይ ለማስፋት እንደሆነ/እንደነበር ለመረዳት አያዳግትም። በሌላ መልኩ ያየነው እንደሆነም የአባቶች መሰባሰብና በህብረት መቀመጥ ጥቅሙ የሚያጠያይቅ አይሆንም።
ወደ ነባራዊው የራሳችን ጉዳይ የተመለስን እንደሆነ በአንፃሩ ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ ነው የምናገኘው። ሁላችን እንደምናውቀው ሲኖዶስ ተሰበሰበ በተባለ ቁጥር ለመስማት የምንጓጓው ዛሬስ በተራው ማን ይወገር ይሆን?፣ ማን ማንን ይዘልፍና ይዘነጥል ይሆን? የሚል ነው። እውነትም ስብሰባው በተጠናቀቀበት ቅጽበት ከወደ መገናኛ ብዙሐን በኩል የምንሰማውም "ለ … ያህል ቀናት ስብሰባውን ሲያካሂድ የሰነበተው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ስብሰባውን አጠናቀቀ። ስብሰባው በርካታ ትእይንቶች የታየበት ሲሆን አቡነ እገሌ አቡነ እገሌ … ሲሉ መዝለፋቸውን፣ …  የውስጥ አዋቂ ምንጮችቻችን በደረሱን ዘጋባ ለማወቅ ተችለዋል"  ጨምሮ ሌሎች በርካታ የማይሰማ አሳዛኝ ነገር የለም።

Monday, November 5, 2012

የግብጽ ቤተክርስቲያን አቡነ ቴዎድሮስ ሁለተኛን 118ኛዋ ፓትርያርክ አድርጋ ሾመች


read in PDF:
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ አቡነ ቴዎድሮስ ሁለተኛ በመባል የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አዲሱ ፓትርያርክ ሆነው በትናንትናው ዕለት በመንፈስ ቅዱስ ተመረጡ፡፡ ለምርጫው የመጨረሻ እጩ ከነበሩት ከሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት እና ከአንድ መነኩሴ መሀል የመንፈስቅዱስን ሞገስ ያገኙት አቡነ ቴዎድሮስ ህዳር 9 ቀን በፓትርያርክነት ይቀባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ  በዕጣ ፓትርያርክ መሾም የጀመረችው በ18ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ የእግዚአብሐየር ፈቃድ ሆኖ ከ6 ዓመት ያልበለጠ ልጅ ዓይኑ በጨርቅ ታስሮ ባወጣው ዕጣ የተመረጡት አቡነ ቴዎድሮስ ሁለተኛ የ60 ዓመት አዛውንት ናቸው፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የምርጫው ዕለት የልደታቸው ቀን የሆነው አቡኑ የሁኔታው መገጣጠም ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1997 በጵጵስና የተቀቡት አቡነ ቴዎድሮስ ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በመንፈሳዊ አባትነታቸው የተመሰገኑ እና የቤተክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስም ሙሉ ድጋፍ ያላቸው አባት ናቸው፡፡

Friday, November 2, 2012

‹‹በጎውን ማን ያሳየናል የሚሉ ብዙ ናቸው››(መዝ. 4፥6)፡፡


Click here to read in PDF:Begowen
ስለ ዘመናችን ድንቅነት ብዙ ተነግሯል፡፡ የንግግሩ ምራቅ ሳይደርቅ ግን አሳዛኝነቱ ይተረካል፡፡ ዘመናችን ከተደነቀባቸው ነገሮች አንዱ የመረጃ ዘመን መሆኑ ነው፡፡ ሰዎች ስለ ራሳቸው ሳይሆን ስለ ሌሎች፣ ስለ ጎረቤታቸው ሳይሆን ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ብዙ መረጃዎችን የሚሰሙበት ዘመን ነው፡፡ የመስማት አንዱ ዓላማ ለመመካከር፣ መራራው ወደ ጣፋጭ እንዲለወጥ ለመጸለይ ነው፡፡ የመረጃው ዘመን ግን ሰምቶ ማዳነቅ ብቻ ነው፡፡ ችግሮች ብዙ ናቸው፣ የመፍትሔ ድምፆች ግን አይሰሙም፡፡ ብዙ የመረጃ መረቦች የጭንቅ ወሬ ካጡ ይጨነቃሉ፡፡ የጦርነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የእርስ በርስ መተላለቅ ትልቅ ርእሳቸው ነው፡፡ 
በአገራችን በኢትዮጵያ በ1998 ዓ.ም መጀመሪያው ወር ላይ ከ1997 ጀምሮ በነበረው ግርግር አንድ የጋዜጣ አዘጋጅ ለጓደኛው ሲናገር፡- ‹‹ይህ ግርግር ሳይበርድ ለሦስት ወር ከቀጠለ የጀመርኩትን ቤት እጨርሳለሁ፡፡ አንድ ዓመት ቢቀጥል ምን የመሰለ መኪና ይኖረኛል፡፡›› እንዳለ፣ ጭንቅ ባላለቀ እያሉ የሚሳሉ፣ እንደ ዕድር ጡሩንባ ነፊ ሞተ እንጂ ተነሣ የማይሉ፣ እንደ ጠመንጃ አፈ - ሙዝ ከአፋቸው ደህና የማይወጣ፣ ያልተባረኩ አንደበቶች በዝተዋል፡፡ ብዙ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን እንለዋውጣለን፡፡ ሁሉም የሚያመነዥጉት ያንን ክፉ ነው፡፡ አዋቂዎቹ የሚሰጡት ትንታኔ የሚመጣውን ቀውስ ጠቋሚ ነው፡፡ ስለዚህ የግለሰቦች ቀውስ እያለፈ ዓለም ራሷ እየቀወሰች መሆኗን እንረዳለን፡፡ ግለሰቦች ሲቃወሱ ምድር ችላቸው ብዙ ዘመን ኖረናል፡፡ ምድር ከቀወሰች ግን ማን ይችላታል@

Wednesday, October 31, 2012

የሲኖዶሱ የስምንተኛ ቀን ውሎ

READ PDF: sinodos 8
  • ·        ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ በቦታው ይቆያል
  • ·        አዲስ አበባ ለአቡነ ህዝቅኤል እና ለአቡነ ዳንኤል ተሰጥቷል
  • ·        የአክሱሙ ንቡረዕድ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተወስኗል

የእነ አባ መሸ በከንቱ ስብስብ የሆነው የጉድ ሙዳዮቹ ሸንጎ የሚተዳደሩበትን ሕግ እና ያላቸውን የስልጣን ደረጃ በማያውቁ እና ወይ ከእውቀት ወይ ከምግባር በሌሉበት ጨዋዎች በመወረሩ የማይመለከተውን ነገር እያየ በጊዜው ሲቀልድ ውሏል፡፡
ደንብ የማያነቡ ሕግ የማይገዛቸው ጮሆ ማውገዝ ጮሆ መወሰን እንጂ በምክንያት እና በእውነት ተገዝቶ ለመኖር በማይፈልጉ እና በማይችሉበትም ጳጳሳት ስለተሞላ የአንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ምርጫ  የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስን ብቻ የሚመለከት መሆኑን እየዘነጉ ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስን ከስራ አስኪያጅነት ለማውረድ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡

Tuesday, October 30, 2012

ሲኖዶሱ በሰባተኛ ቀን ውሎው ቃለ ጉባኤ ላይ ሲጨቃጨቅ ዋለ

Click here to read in PDF:sinodos 7
ሲኖዶሱ በትናንትናው ዕለት በነበረው ስብሰባ ቃለጉባኤ ሲያስነብብ እና ሲጨቃጨቅበት ውሏል፡፡ አቃቤ መንበሩ አቡነ ናትናኤል የባንዲራ ቀን ለማክበር ሄደው ስለነበር ስብሰባው የተካሄደው እሳቸው በሌሉበት ነበር፡፡ ቃለጉባኤው ሲነበብ ካነጋገሩት ነገሮች መካከል ዋነኛው የአሜሪካው ጉዳይ ነበር፡፡ ያጸደቁትን እና የሚተዳደሩበትን ህግ የማያውቁ የሲኖዶሱ አባላት የአርባ ምንጩ አቡነ ኤልያስ መሪነት እኛ የወሰንነው ሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ ይነሳ ብለን ነው ለምንድን ነው የማይነሳው? ብለው ህገ ደንቡ በማይፈቅድላቸው ጉዳይ ሙግት ጀመሩ፡፡
ነገሩ ወደ ጭቅጭቅ በማምራቱም አቡነ ናትናኤል ባሉበት በዛሬው ዕለት እንደገና እንዲታይ ተወስኗል፡፡ እንደገና ይታይ ሲባልም በክብረ መንገስት ሕዝብ ተዋርደው እና አንገታቸውን ደፍተው የወጡት አቡነ ዮሴፍ ጉዳዩን ደግመን የምናየው ከሆነ የምናየው አቡነ ፋኑኤል በሌሉበት መሆን ነው ያለበት ቢሉም አቡነ ፋኑኤል ግን እስከ አሁን ድረስ የማንም ሀገረ ስብከት ጉዳይ በሲኖዶስ ሲታይ ሊቀ ጳጳሱ ባለበት ነው የኔ ጊዜ ለምንድን ነው የምወጣው? የአቡነ ገብርኤል ጉዳይ የታየው እሳቸው ባሉበት ነው ስለዚህ እኔ ባለሁት ነው የሚታየው በማለት መልሰዋል፡፡

Sunday, October 28, 2012

ለቅዱስ ፓትሪያሪክ መርቆሪዎስ


በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
በለሱንየጠበቀፍሬዋንይበላል፥ጌታውንምየሚጠብቅይከብራል!
ቅድመ ሐተታ
በይድረስ የተጻፈውን ደብዳቤ ከመልዕክቱ ተቀባይ ከቅዱስ ፓትሪያሪኩ አልፎ ለአንባቢያን በግላጭ ማቅረብ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ቅዱስነታቸው ፊት ለፊት አፍጥጦ የሚጠብቃቸው በሁለቱም የሃይማኖት መሪዎች መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ቅራኔ ከዚህም አልፎ የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን  "ልክ ለሌለው" የመከፋፈልና የመለያየት፤ ማንም እንዳሻው እየተነሳ በራሱ አለቃ የሚሆንበት ሥርዓት አልበኝነት/ጋጠወጥነት ያነገሰ አሳፋሪ ገጽታ ለማስቆምም ሆነ አሁን ካለበት ሁኔታ ተባብሶ እንዲቀጥል ለማድረግ ሁለቱም አካላት የሚያሳዩት/የሚያንጸባርቁት አቋም በሌላ አገላለጽ በሚያስተላልፉት ውሳኔና በሚወስዱት እርምጃ በቀጥታ ቀዳሚ ተጠቃሚም ሆነ ተጎጂ የሆነውን የቤተ እምነቱ ተከታይ (ምእመናን) በመሆናቸው በዚህ ጉዳይ ማለትም እርቀ ሰላሙን በማውረድ ረገድ ማን ምን እያደረገ እንዳለ መጠነኛ ግንዛቤ ይኖረውና ያውቅም ዘንድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው።

ሲኖዶሱ በስድስተኛ ቀኑ ውሎው

Click here to read in PDF:Sinodos Day 6
  • የአሜሪካው አህጉረ ስብከት ጉዳይ አነጋግሯል
  • የካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር ብጹአን እነ ማን ናቸው? የሚለው መጽሐፍ ሰበር አጀንዳ መሆኑ አስገርሟል፡፡
  • ሊቀ ኤጲስ ቆጶስ ወይስ ሊቀ ጳጳስ?

በሲኖዶሱ የስድስተኛ ቀን ውሎ የአሜሪካው አኅጉረ ስብከት ጉዳይ ተነስቶ ያነጋገረ ሲሆን የአህጉረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ የሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ መልዕክት በንባብ ተሰምቷል፡፡ አንዲሁም የክህነት እገዳው ጉዳይ ይታይልኝ ያለው የማኅበረ ቅዱሳኑ ኦሪታዊው “ካህን” አቶ መስፍን ደብዳቤም በንባብ ተሰምቷል፡፡ አቡነ ፋኑኤል አለ የተባለውን ነገር ሁሉ በጥሩ ሁኔታ አብራርተዋል፡፡ ከአሜሪካ መነሳታቸው ሁሌም የሚያንገበግባቸው የጉድ ሙዳዩ አቡነ አብርሐም በሰሞኑ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የነበራቸው ዝምታ ተሰብሮ ካልመለሳችሁኝ የሚል አይነት ጩኸት ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ አቡነ ማቲያስም እኔም እኮ በአሜሪካ ስንት ስራ ሰርቻለሁ አትርሱት እንጂ እዛ የነበርኩ መሆኔን አይነት መልዕክት ሲስተላልፉ አቡነ ማርቆስ ደግሞ አቡነ ማቲያስን ለመገሰጽ ሞክረዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤልም አቡነ አብርሃምን ደግፈው ለመናገር ሞክረዋል፡፡ ምነው ቢሉ የሁለቱም ማዘዣ ጣቢያ አንድ ነዋ የሚል ምላሽ ያገኛሉ፡፡

Friday, October 26, 2012

የሲኖዶሱ ስብሰባ አምስተኛ ቀን ውሎ

click here to read in PDf: sinodosday five
  • ሲኖዶሱ የትናንትናው ውሳኔውን ሽሮ ተስፋዬ በቦታው በምክትል ስራ አስኪጅነቱ እንዲቀጥል ወስኗል
  • ለአክሱም ሚዚየም 13 ሚሊየን ብር ፈቅዷል
  • የአቡነ ጳውሎስ ንብረት እንዲቆጠር እና ወደ ሙዚየም እንዲገባ ወስኗል
  • ለአብነት ትምህርት ቤቶች በጀት መድቧል
  • የፓትርያርክ ምርጫ ደንብ እስከ ህዳር 30 ድረስ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተዋቅሯል ከኮሚቴው አባለት አንዱ አዲሱ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ እና በተማሪዎቹ ዘንድ ችኮው ተብሎ የሚጠራው ዶ/ር ሰሙ ይገኝበታል

ሲኖዶሱ በአምስተኛ ቀን ስብሰባው በአቡነ ፊሊጶስ አማካኝነት  በተነሳው የተስፋዬ ይመለስልኝ ጥያቄ ግማሽ ቀኑን አቃጥሏል፡፡ በትናንትናው እለት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተስፋዬ እንዲነሳ ሲወሰን አጨብጭበው ተቀብለው የነበሩት አቡነ ፊሊጶስ ከማኅበረ ቅዱሳን በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በዛሬው እለት ተስፋዬ ይመለስልኝ በማለት በመጠየቃቸው አብዛኛውን ጳጳሳት ያስቆጣ ቢሆንም በተለይም የአቡነ ቄርሎስ የአቡነ እስጢፋኖስ የአቡነ ማርቆስ እና የአቡነ ሳዊሮስ ተቃውሞ ከፍተኛ ነበር፡፡
አቡነ ፊሊጶስ ትናንት ከስልጣኑ ይነሳ ሲባል ተስማምተው ሲያበቁ ዛሬ እንዴት ይመለስ ይላሉ ሲባሉ መልስ ለመስጠት ባይችሉም እንዲሁ በድርቅና ብቻ ያለተስፋዬ ስራ መስራት አልችልም በማለት ጸንተዋል፡፡