Friday, October 26, 2012

የሲኖዶሱ ስብሰባ አምስተኛ ቀን ውሎ

click here to read in PDf: sinodosday five
  • ሲኖዶሱ የትናንትናው ውሳኔውን ሽሮ ተስፋዬ በቦታው በምክትል ስራ አስኪጅነቱ እንዲቀጥል ወስኗል
  • ለአክሱም ሚዚየም 13 ሚሊየን ብር ፈቅዷል
  • የአቡነ ጳውሎስ ንብረት እንዲቆጠር እና ወደ ሙዚየም እንዲገባ ወስኗል
  • ለአብነት ትምህርት ቤቶች በጀት መድቧል
  • የፓትርያርክ ምርጫ ደንብ እስከ ህዳር 30 ድረስ የሚያዘጋጅ ኮሚቴ ተዋቅሯል ከኮሚቴው አባለት አንዱ አዲሱ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ እና በተማሪዎቹ ዘንድ ችኮው ተብሎ የሚጠራው ዶ/ር ሰሙ ይገኝበታል

ሲኖዶሱ በአምስተኛ ቀን ስብሰባው በአቡነ ፊሊጶስ አማካኝነት  በተነሳው የተስፋዬ ይመለስልኝ ጥያቄ ግማሽ ቀኑን አቃጥሏል፡፡ በትናንትናው እለት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተስፋዬ እንዲነሳ ሲወሰን አጨብጭበው ተቀብለው የነበሩት አቡነ ፊሊጶስ ከማኅበረ ቅዱሳን በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በዛሬው እለት ተስፋዬ ይመለስልኝ በማለት በመጠየቃቸው አብዛኛውን ጳጳሳት ያስቆጣ ቢሆንም በተለይም የአቡነ ቄርሎስ የአቡነ እስጢፋኖስ የአቡነ ማርቆስ እና የአቡነ ሳዊሮስ ተቃውሞ ከፍተኛ ነበር፡፡
አቡነ ፊሊጶስ ትናንት ከስልጣኑ ይነሳ ሲባል ተስማምተው ሲያበቁ ዛሬ እንዴት ይመለስ ይላሉ ሲባሉ መልስ ለመስጠት ባይችሉም እንዲሁ በድርቅና ብቻ ያለተስፋዬ ስራ መስራት አልችልም በማለት ጸንተዋል፡፡


ከትናንትና ማታ ጀምሮ ተስፋዬ እንዴት እንዲሁ እጣላሁ እያለ በጳጳሳቱ ቤት እየዞረ ቢማጸንም ሰሚ አላገኘም ነበር፡፡ አቡነ አብርሃም ብቻ አቡነ ፊሊጶስን ዛሬ በጠዋት ደውለው በተስፋዬ ጉዳይ አነጋግረዋቸው የነበረ መሆኑ ታውቋል፡፡ ማኅበርዋ ግን ካላት ባኅሪ የተነሳ ለእስዋ ጥሩ እየተጋደለላት ያለውን ተስፋዬን ማጣት ስላልፈለገች ለአቡነ ፊሊጶስ ተስፋዬ መነሳት ስለሌለበት ድርቅ ብለው ይከራከሩ ብላ ማዘዟም ታውቋል፡፡
አቡነ ፊሊጶስ እና ተስፋዬ በእጅግ መቀራረብ የጀመሩት ተስፋዬ የትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት ምክትል ስራ አስኪጅ እያለ ሲሆን በወቅቱ አቡነ ፊሊጶስ የትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት የበላይ ጠባቂ ሆነው በተሾሙ ጊዜ ነበር፡፡ ያን ጊዜ ተስፋዬ ከማተሚያ ቤቱ 18000 ብር ወጪ አድርጎ ሃይከን መስቀል በእንኳን ደህና መጡ ስነ ስርዓት ላይ ሸልሟቸዋል፡፡ በወቅቱ አቡነ ፊሊጶስ ሰው ሲሰናበት ሽልማት ይደረግለታል እናንተ ልጆቼ ግን ገና ስመጣ ሸለማችሁኝ! እንዴት ብትወዱኝ ነው!!  በማለት ተናግረው እነደነበር ይታወሳል፡፡ አሁን የኖረ ውለታ ቀስቅሷቸው በቦታው እንዲቆይ ታግለውለታል፡፡
አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ ሁነው ከተሾሙ በኋላ ተስፋዬ በምክትል ስራ አስኪያጅነት አንዲሾምላቸው አቡነ ጳውሎስ ጋር አቅርበውት እንዲሾም አድርገውታል፡፡ በወቅቱ ተስፋዬን ለማሾም የሰሩት ድራማም የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ አባ ሰረቀ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በገቡት እሰጥ አገባ ማኅበሩ በደጋፊ ጳጳሳቱ አማካኝነት የአባ ሰረቀ ይነሱ የሚል ዘመቻውን ሲያካሂድ ምክንያቱ በቂ ባለመሆኑ ቅዱስነታቸው ኤነሳም በማለታቸው ቅዱስነታቸውን አግባብተው አባ ሰረቀ ልጄ ነው ይነሳ እና እኔ ጋር ይምጣ በምክትል ስራ አስኪጅነት ይሾምልኝ በማለታቸው ከሰንበት ማደራጃ ተነስተው በጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅነት ሲሾሙ ወትሮውንም የአቡነ ፊሊጶስ ፍላጎት ለማኅበረ ቅዱሳን ብለው አባ ሰረቀ ብርሃንን ማስነሳት ነበረ እና አባ ሰረቀ ከሰንበት ማደራጃ መነሳታቸውን እንዳረጋገፁ ከእሳቸው ጋር አልሰራም በማለት አገነገኑ፡፡ በለመዱት አፋቸው አዣኝቷን ወላዲተ አምላክን እኔ እቀበለዋለሁ እኔ ጋር ይሾም ካሉ በኃላ ወላዲተ አምላክን አልፈልገውም አሉ፡፡ ከዛም ተስፋዬን አምጥተው ይሾምልኝ በማለት አሹመውታል፡፡
በትናንትናው እለት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ተስፋዬ ይውረድ ጠቅላ      ይ ቤተክህነቱ በአቶ መመራት የለበትም ሲባል ልክ ነው ያሉት አቡነ ፊሊጶስ ዛሬ ደግሞ በተለመደው ተገላባጭ ባኅሪያቸው አይነሳብኝ ብለው ግድ በማለታቸው ሲኖዶሱም በጠዋቱ ስብሰባ የነበረውን ተቃውሞ አለዝቦ በከሰዓቱ ስብሰባ በቦታው ይቆይ ሲል ወስኗል፡፡
በቅዱስነታቸው አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርዓት ላይ አስከሬኑ በመስቀል አዳባባይ ስነስርዓት ተደርጎ ስላሴ ይቀበር  ሲባሉ “የሚነሳው ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ነው፡፡ አንዴ ወስነናል የህጻን ስራ አንሰራም ቃላችንን መለወጥ አንችልም፡፡ የሲኖዶስ ውሳኔ አይገለበጥም፡፡” ያለው ሲኖዶስ አሁን በትናንትናው እለት ከቦታው ያነሳውን ተስፋዬን በቦታው እንዲመለስ በማድረግ “የህጻን ስራ” ሰርቷል፡፡
በዛሬው እለት የተነሱት ጉዳዮች አንዱ የአክሱም ሙዚየም ስራ ጉዳይ ሲሆን ኮሚቴው ሊቀመንበር የአቡነ ገሪማን ሪፖርት አዳምጧል፡፡ ከአክሱም የመጡትም የኮሚቴው አባላት ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለሙዚየሙ ስራ ተጨማሪ 13 ሚሊየን ብር እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ሲኖዶሱም የተጠየቀውን ገንዘብ እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ አጠቃላይ የሂሳቡ እንቅስቃሴ ግን ኦዲት እንዲደረግ አዟል፡፡
የታሸገው የቅዱስ ፓትርያርኩ ቤት እንዲከፈት እና ያለው እቃ ሁሉ እንዲቆጠር የታዘዘ ሲሆን ተቆጥሮም ወደ ሚዚየም እንዲገባ ይደረግ ተብሏል፡፡ ቤቱ ከዚህ በፊት በአቡነ ፊሊጶስ አማካኝነት ተከፍቶ የነበረ መሆኑ ሲታወቅ እሳቸውም ቤቱን ከፍተው ገብተው ምን እንደሰሩ ግን ሊታወቅ አልቻልም፡፡
ለአብነት ት/ቤቶች በጀት እንዲመደብም ታዟል፡፡ ይህ ውሳኔ ተገቢም አስደሳችም ነው፡፡ የጥንቱን ትምህርት ጠብቆ ለመቆየት አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
የፓትርያርክ ምርጫ ህገ ደንብ እስከ ህዳር 30 ድረስ እንዲረቅ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን ከኮሚቴዎቹ ውስጥ አንዱ የማቅ አዲስ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰሙ ነው፡፡ ዶ/ር ሰሙ እጅግ ድርቅ ያለ ህጎችን በማውጣት እና በማንኛውም አሳማኝ ምክንያቶች ቢሆን የተማሪዎቹን ጥያቄ የማያስተናግድ በመሆኑ በተማሪዎቹ ዘንድ ችኮ የሚል ስም የተሰጠው ግለሰብ ነው፡፡


No comments:

Post a Comment